በባህርዳር ከተማ ሰማዕታት ሀውልት ተብሎ በሚጠራው ግቢ ውስጥ ተደጋጋሚ ቅሬታ ሲነሳበት የነበረው ሀውልት ተነሳ

አማራ ሚዲያ ማዕከል/አማሚ
ታህሳስ 10 ቀን 2013 ዓ.ም
አዲስ አበባ ሸዋ
131917860 4751068591634390 6916834034903695095 n
131987934 4751069174967665 2717488595550951248 nበአማራ ክልል በባህርዳር ከተማ ሰማዕታት ሀውልት ተብሎ በሚጠራው ግቢ ውስጥ የክልሉን ህዝብ የማይወክልና የማይገልፅ ነው ተብሎ የታመነበትን ሀውልት በአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች እንዲወገድ ተወስኖ ተግባራዊ እንቅስቃሴ መጀመሩን የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ አስታውቋል።
ፓርቲው በለውጡ ለህዝብ ከገባቸው ቃሎች መካከል የተሳሳቱ ታሪኮችንና ትርክቶችን የማረም ተግባር በከፍተኛ ቁርጠኝነት እያከናወነ መሆኑን የገለጸ ሲሆን አጠቃላይ ተቋሙን የሚመለከቱ የሪፎርም ስራወችንም በዝርዝር እንደሚያሳውቅ ነው የአብመድ ዘገባ ያመለከተው።
ሀውልቱ መፍረስ አለበት በሚል ተደጋጋሚ ቅሬታዎች ከተለያዩ አቅጣጫዎች ሲነሳበት እንደነበር ይታወቃል።
131920589 4751068771634372 4412288003403404719 n

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.