እርኩስ ወይም ቅዱስ አስተሳሰብ ችግር

Abiy and Debreየግለሰብ አመራርን ወይም የስራአትን ምዘና ሲደረግ ችግርና ቀና ነገር እንዳለው ያልተገነዘበ ማህረሰብ እየፈጥርን መጥታናል፡፡ ይህን ስል ምን ማለቴ ነው በግዜያዊ ድል ወይንም ሽንፈት በተጨማሪም የኔ ወገን ነው ወይስ አይደለም በማለት፣ አንድን አካል ቅዱስ ወይም እርኩስ ብሎ መፈረጅ ተላምደን ሚዛናዊ እይታ ያጣን ይመስለኛል፡፡ ይህን እንዲያሳይ ብዙ ምሳሌዎችን መጥቀስ እንችላለን፣ ለዚህ ጽሁፍ ይሆን ዘንድ ግን የዶ/ር አብይ አሕመድ አመራርን እንደ ምሳሌ እንውሰድ።

መጀምሪያ ወደ መንበር እንደመጡ ሰውነታቸው ተዘንግቶ በአንድ ንግግር ከሰማይ የመጡ መልእክተኛ ቅዱስ ተባሉ፣ ይህ አባባል ቀድሞ ከነበረው ስርዓት ጥላቻ የተነሳ እና ለውጥን ፍለጋ የመጣ ስሚታዊነት ነበር፣ ነገር ግን ከዚህ ተስፋ ጋር አብሮ የመጣ የለውጥ ፍላጎት ሱሪ በአንገት በመሆኑ ማህበረሰቡ እኛ የምንፈልገው ሳይሆን የእኔ ጎራ የሚፈልገው ለውጥ በፍጥነት አልመጣም ብሎ መተቸት ብቻ ሳይሆን እርኩስ በማለት መፈረጅ ቀጠለ፡፡ በማስከተልም ቀድሞ የነበረው ስርአት ለዓመታት ያጠመዳቸው ፈንጂዎች በየጎራው ሲፈነዱ /ግጭቶች ሲፈጠሩ/ የዶ/ር አብይ “እርኩስነታቸው” በደንብ እየጎላ ተነገረ፤ ታሪክ ተቀይሮ የቀድሞ ስርዓት ቀራጮች በሰሞኑ ያላቸውን ሃይል አጥተው ከፊታችን ሲጠፉ ደግሞ “ቅዱስ” ሁነዋል፣ ይህ አስተሳሰብ ሊታረም ይገባዋል።

በአመራር ሁሉንም ማስደሰት አይቻልም ከ200 ዓመት በላይ ያስቆጠረችው “የዲሞክራሲ ቁንጮ” ተብላ የሚመሰከርላት ሐገር አሜሪካም ሁሉንም አስደስታ አታውቅም፣ ልታስደስትም አትችልም። ይህ ከሰው ልጅ ፍላጎት ልዩነት በተፈጥሮ የሚመጣ ችግር ነው፣ ማድረግ የሚቻለው ልዩነትን በማጥበብ ተስማምቶ የሚኖርበት ደረጃ መድረስ ብቻ ነው። ስለዚህ ለችግሮቻችን ሁሉ መፍትሄ በአንድ ግዜ ይመጣል የሚለው አስተሳሰብ ከአእምሮአችን ማውጣት ይገባል፣ አሁን ካለንበት የተሻለ ማህበረሰብና ኑሮን መጠበቅ ግን ምክኛታዊ እና ተግቢ ከመንግስትም የሚጠበቅ ነው።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የጎጃም አለምዓቀፉ ትብብር ጊዚያዊ ሊቀመንበር የነበሩት ዶ/ር ደመቀ ገሠሠ ይናገራሉ | ንግግሩን ላላያችሁት ብቻ | Video

ከላይ የጠቀስኳቸው ነገሮች አሁንም በጎውን በርታ ስህተቱን ታረም ማለት የተማርን አይመስለኝም፡፡ ዶ/ር አብይ ድሮም እርኩስ አልነበሩም አሁንም ለቅድስና ይቀራቸዋል፡፡

መመዘኛችን ሊሆን የሚገባው በሚከተሉት ሁለት ተግባራት ነው ፡

አንደኛ ነገ ለትውልድ የሚተላለፍ ተቋማት እየተገነቡ ነው ወይ? ዶ/ር አብይም ሆኑ ማናችንም አላፊዎች ነን ነገርግን ባሉበት ጊዜ ቋሚና ለትውልድ የሚተላለፍ ስራ መስራት ይገባል፤ ከነዚህ ውስጥ ዋናው በህና በመርህ የሚመራ በቀላሉ የማይፈርስና ለወደፊቱ ፈር የሚቀድ ተቋም መገንባት ነው። እስካሁን ባየሁት ትዝብት ሁለት መስሪያ ቤቶች ላይ የተሰራው ስራ በርቱ የሚያስብል ነው እነዚህም የምርጫ ቦርድና የሰዓዊ መብት ኮሚሽን ገለልተኛ ሆነው እንዲሰሩ መፈቀዱ ነው፣ ሌሎች መስሪያ ቤቶች እንደ መከላከያና ፍትህ ላይ እየተረጉ ያሉትም እንቅስቃሴዎች ተስፋ የሚሰጡ ሆነው አግኝይቻቸዋለሁ የሚቀረውን ማስተካከያ ለወደፊቱ በዚሁ ቀጥለው ነጻና ከፖለቲካ የጸዱ እንዲሆኑ በዚሁ ምኞቴን እገልጻለሁ።

ሁለተኛ እና ከሁሉም በላይ አድርገን ማየት ያለብን ደግሞ ቀጣዩን ምርጫ ነው፡፡ ይህን ስል ያለምክንያት አይደለም፣ ህዝባችን እስከምናውቀው ድረስ ተወስኖበት እንጂ ወስኖ አያውቅም፣ ሃሳባችንን መግለጫ እርስ በርስ ከማማትና አሁን በፌስ ቡክ እንደምናደርገው ከማማረር ወይም ከመደሰት በስተቀር የእኛ ህዝብ ድምጽ ዋጋ ኖሮት አያውቅም፣ ጉልበትኞች በመጡ ቁጥር ህዝቡ የሚፈልገውን ችላ በማለት ያሻቸውን ሲያደርጉ ነው የኖሩት። አሁንም ቢሆን ትግላችን ሊሆን የሚገባው ብሶቴን ይሰማኛል ፍላጎቴን ለወድፊቱ ያሳካልኛል እምንለውን ወኪል መምረጥ ስንችል፣ ድምጻችን ዋጋ ስለሚኖረው፣ ይህን ለማሳካት የሚቀጥለው ምርጫ ፍትሃዊና ግልጽ እንዲሆን ለማድረግ ነው። ይህ ከተረጋገጠ ችግሮቻችንን የሚያቃልሉ፣ የሚወክሉን ሰዎች ስለሚኖሩን ወስነን እንጂ ተወስኖብን እንደማንኖር እናረጋግጣለን

ተጨማሪ ያንብቡ:  በኦሮምያ ክልል የተጀመረው ሕዝባዊ ንቅናቄና የሃገራችን መጻሒ ሁኔታ! | ከኃይለገብርኤ አያሌው

በበኩሌ ዶ/ር አብይን በርታ በማለት፣ ቅዱስ ለማለት ግን ምርጫውን ለመጠበቅ ወስኛለሁ።

በመጨረሻም ቅዱስ እና እርኩስ ከማለታችን በፊት ከስሜት ወጥተን ነገሮችን በማጤን እኔ እዛ ቦታ ብሆን የኔን ወገን ብቻ ሳይሆን ለብዙሃኑ ልሰራ የምችለው ምንድን ነው? አሁን ባለሁበትስ ሁኔታ የማህበረሰቡን ህይወት ለማሻሻል ትንሽም ምን አድርጌያለሁ ወይም ቢያንስ ህዝቡን ችግር ላይ ላለመጨመር ምን እያደርግኩ ነው ብሎ እራስን መጠየቅ ይገባል።

AAnonymous

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.