እውን መከላከያ የኢትዮጵያና ኢትዮጵያ ሕዝብ ነው?v – ሰርፀ ደስታ

defenseእውን መከላከያ የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው? ታዲያ የአገር ድንበር ሲደፈር ዜጎች በአረመኔዎች ሲተረዱ ዳር ሆኖ ማመልከትን ለምን መረጠ? መቼም በዚህ ሰዓት እንዲህ ያለ ጥያቄ ማንሳት አስቸጋሪ ነው፡፡ ሆኖም ይህን እውነት ልንጋፈጠው ግድ የሚለን ይመስለኛል፡፡ በመከላከያ ሠራዊታችን ላይ ጥርጣሬ እንዲኖር እያደረገ ነው ብላችሁ እንዳታስቡ፡፡ ጉዳዮችን ከምናያቸው እውነታ ጋር እንጂ በቲፎዞና በሆያሆዬ ልመለከት አልወድም፡፡ ኢትዮጵያ ያ የደርግ ተብሎ ከፈረሰው ሠራዊት በኋላ የኢትዮጵያ የሚባል መከላከያ እንዳላት እኔን አይገባኝም፡፡ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ሠራዊቱ የሚታወቅበት የኢሕዴግ እንጂ የኢትዮጵያ እንዳልሆነም መቼም ለብዙዎች ግልጽ ነው፡፡ እስከዛሬም ይሄ ሠራዊት ለተለያዩ ወያኔ ለፈጠረቻቸው ቁማሮች ሲያገለግል ኖረ እንጂ አንድም አገራዊ ተልዕኮ ኖሮት አያቅም፡፡  በሱማሌ ብትሉት ዳትፉር ወይም ሩዋንዳ የወያኔ የንግድ ካምፓኒ ሆኖ ሠራ እንጂ የኢትዮጵያ ሆኖ እንደሰራ ለመረዳት እቸገራለሁ፡፡ የእነዚህ ተልኮዎች ዋና ሚናቸውም የወያኔን ድርጅቶችና ባለስልጣናት ሐብታም ማድረግ እንጂ አገርን የወከለ አልነበረምና፡፡ እንደ ሱማሌ ያሉ ቦታዎች ደግሞ ከእነ ጭርሱ አልሸባብንም ከወዲያ በኩል ስትደግፍ የነበረቸው ወያኔ እንደነበረች ትልቅ ንግድም እንደነበር ይነገራል፡፡ የሆነ ሆኖ እነዚያ ተልኮዎች የምንም ይሁኑ የማ የአንድ አገር መከላከያ የአገር አሌኝታነቱና ሕዝባዊነቱ የሚረጋገጠው የገዛ አገሩን ዳር ድንበርና የዜጎችን ደህንነት በመጠበቁ እንጂ በሌላ አገር በሚኖረው ተልዕኮ አደለም፡፡

ሰሞኑን ወያኔ በከፈተቸው ጦርነት መከላከያው ከሕዝብ ጋር የተቀላቀለ መስሎኝ ነበር፡፡ እንደተባልነውም መከላከያው የኢትዮጵያ ነው የሕዝብ ነው የሚለውን መሠረታዊ እሳቤ በሕዝቡም ልቦና እንዲገባ የተደረገ ይመስለኛል፡፡ ይሄ የኢትዮጵያ ነኝ የሕዝብ ነኝ ያለ መከላከያ መለኪያው ወያኔን በመደምሰስ ላይ ከሆነ ስህተት ነው፡፡ ሲጀምር ከመሠረቱ ወያኔ ይሄን ያህል አቅም ገንብታ መከላከያውን በሰማንው ደረጃ ያጠቃችበት ሂደት እጅግ አደገኛና አንድ መከላከያ ተብሎ የተጠራ ተቋም ሊገጥመው የሚገባ ክስተት አልነበረም፡፡ ወያኔን ያዋረዳት ከላይህ የሕዝብን በደል ብቻውን የሚለካ ቅዱስ እግዚአብሔር እንጂ እንደተፈጠረው ንዝላልነት እጅግ አደገኛ ይሆን እንደነበር ግልጽ ነበር፡፡ የሆነ ሆኖ አሁንም መከላከያው ራሱ ስለተነካና ምን ዓልባትም የዓብይ መንግስት አደጋ ስለተጋረጠበት ተንቀሳቀሰ እንጂ ለኢትዮጵያ ሲል የሚለውን እንዳያደበዝዝበት ትልቅ ስጋቴ ነው፡፡ መከላከያው አሁን ሕዝባዊነቱን የሚያሳይበት ብዙ እድሎችም ሥራዎችም አሉትና፡፡

  1. የሱዳን ጦር የኢትዮጵያን ድንበር አልፎ ጥቃት መፈጸም፡- ይሄ እንግዲህ ከምንምና ከማንም በላይ በቀጥታ ኃላፊነቱ የመከላከያ ነው፡፡ አሁን የምንሰማው ግን የሚገርም አይነት እውነት ነው፡፡ በአማራ ክልል አዋሳኝ የሱዳን ጦር ወደ ኢትዮጵያ ገብቶ ጥቃት ሲፈጽም ወራሪዎችን እየመከተ ያለው ነዋሪው ሕዝብና የአማራ ክልል ልዩ ኃይል እንጂ መከላከያው አለመሆኑ መከላከያው ላይ ትልቁን ማንሳት ያስገድዳል፡፡
  2. በአገሪቱ የተለያየ ቦታ የዜችን ደህንነት አደጋ፡- ቀደም ብሎ በወያኔ ሲሳበብ የነበረው በተለይም ደግሞ በአማራ ላይ ያነጣጠረ ጥቃት በብዙ ቦታዎች እየተፈጸመ መከላከያ የተባለው የለም፡፡ በተለይም በወለጋና ቤኒሻንጉል ጉምዝ ውስጥ ተደራጅተው ሕዝብን እየጨረሱ ያሉትን አረመኔዎች ለመንካት መከላከያ የተባለው ፍቃደኛ የሆን አይመስልም፡፡ እንግዲህ መከላያውን ማን ያዝዋል ከሚለው ጀምሮ ዓላማውና ተግባሩ ምንድነው የሚለውን በደንብ ማጤን ይገባል፡፡ የኦሮሞ አረመኔ ገዳዮች ስለሆኑ ኦሮሞ የሚያዘው መከላከያ ለአማሮች ደህንነት ምን አገረባው ማለት ብቻም ሳይሆን ከዚህ በከፋ በመንግስት መዋቅር ሳይቀር የአማራ ተወላጆች ላይ ጥቃት እንዲሰነዘር እየተሰራም እንደሆነ እየታዘብን እየሰማንም ነው፡፡ ይሄ አረመኔያዊ ግፍ በሌላ ክልል እንደመፈጸሙ መጠን በቀጥታ የሚመለከተው የፌደራሉ መንግስትና መከላከያው ሆኖ ሳለ አሁን ለጉዳዩ ዋና ባለቤት የሆነው የአማራ ክልል ነው፡፡ እንዲህ ያለ ቁማር ነው ያለንበት፡፡ አሁን እንደምንሰማው የአማራ ክልል ልዩ ኃይል እርምጃ ሊወስድ እየተዘጋጀ ነው ነው፡፡ እንግድህ የፌደራል ነኝ የሚለው መንግስትና የሕዝብ ነኝ የሚለው መከላከያ ፍቃደኛ ባለመሆናቸው ብቻም ሳይሆን ከዚህ ግፍ በስተጀርባም ተሳታፊ ሊሆኑ እንደሚችሉ አለመገመት ቁማሩን አለመረዳት ነው፡፡ እንደተባለውም የአማራ ክልል ልዩ ኃይል በእነዚህ ቦታዎች ሠላም ለማስከበር በሚል ቢገባ መከለከያ የተባለው እንደሚዘምትበት አትጠራጠሩ፡፡ በፊት ለፊት ባይሆንም በጎን ለገዳዮች ድጋፍ በማድረግ፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ ይሄው መከላከያ ባለፈው በሻሸመኔና ሌሎች ቦታዎች አረመኔያዊ ግፍ ሲፈጸም አልታዘዝኩም ያለ ሲሆን በወላይታ ግን ስንጥር ያለነሳን ሕዝብ ለመጨፍጨፍ ታዞ እንደነበር አስታውሱ፡፡  ጥያቄውን እስከ ጥግ ድረስ እናነሳለን፡፡ ጉዳዩብ ብናባብለው ብናባብለው ከቀን ወደ ቀን እየከፋ እንጂ እየተሻለ ስላልሆነ፡፡
  3. ከወያኔ ጠባቂነት ወደ ኦሮሞ አብይ ጠባቂነት፡-ከላይ እንደጠቀስኩት ይህ በወያኔ የተመሰረተው የኢሕዴግ ጦር ሲባል የነበረው በኋላ ቆይቶ ራሱን መከላከያ ያለው ተቋም ከሕዝብና አገር ጋር የተገናኙ ግዳጆችን ተወጥቶ ያልታየ ነው፡፡ ምን ዓልባት በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ተሳትፏል ከተባለ ያ ጦርነት እስከዛሬም ምክነያቱን የማናውቀው ምን ከፍ ቢል የወያኔና የሻቢያ ከዛም ቢያልፍ የመለስና የኢሳያስ እንጂ የአገር ማስከበር ተብሎ ሊታሰብ የሚችል አደለም፡፡ አሁንም አብይ አህመድ ምን ያለበት ምን አይችልም እንደተባለው መከላከያ የአብይ አደለም እንዳለው ሳይሆን በግልጽ የምናያው እውነት የአብይ ሥልጣን አደጋ እስካልገጠመው ድረስ የዜጎች ደህንነት አያገባኝም አይነት ምልከታ እነዳለው ነው፡፡ በየቀኑ ዜና የሆነው የዜጎች በግፍ መታረድ ጉዳዩ ሆኖ አይተንው አናውቅም፡፡ ይልቁንም አልታዘዝኩም በሚል ዜጎች ሲታረዱ ሊደርስላቸው እንዳልፈለገ አይተናል እንጂ፡፡ የአሁኑ በወለጋና ቤኒሻንጉል ሌሎችም አካባቢዎች እየሆነ ያለውን አረመኔያዊ ድርጊት ለማስቆምም ፍቃደኛ ሆኖ አላየንውም፡፡ ለዛም ይመስላል የአማራ ክልል ልዩ ኃይል ዜጎችን ለመታደግ የፌደራል መንግስቱ ፍቃደኛ ካልሆነ እኔ እገባለሁ ያለው፡፡ ዛሬ በወያኔ ማመካኘት አይቻልም፡፡ አቅምንም ማሳበብ አይቻልም፡፡ ከወያኔ በላይ የታጠቀ ኃይል እንደሌለ አይተናልና፡፡
  4. የአማራጠል ፖለቲካ አስቀጣይ መሆን፡- ዛሬ የብሔር ፖለቲካ አራማጅ ፖለቲከኛ የሆነው በአማራ ጠል ፖለቲከኛ አራማጅነቱ እንጂ አመክንዮዋዊ አስተሳሰብን በማሳመን እንዳልሆነ ግልጽ እየሆነ መጥቷል፡፡ በተለይም ደግሞ የኦሮሞ ፖለቲከኞች አማራ ጠል ፖለቲካ ማራመድ ብቻ ሳይሆንም ከአማራ ጋር ይወግናን የሚሉትን ሁሉ ኢላማ ማድረግ ዋና ግባቸው ነው፡፡ ዛሬ ላይ የኦሮሞ ፖለቲከኛ ሆኖ ኢትዮጵያዊ የሆነ ስሜት ያለው ካለ እሱ በተዓምር ከ50ዓመቱ የኦሮሞ የጥላቻና ዘረኝነት ፖለቲካ የተረፈ ነው፡፡ አብይ አህመድ አማራ ሲባል እንዴት እንደሚቀፈው በተደጋጋሚ አይተናል፡፡ ሌላ ቀርቶ ወያኔ ተደራጅታ ጥቃት የፈጸመችበት መከላከያ በመቀላቀል ወያኔን በተለያዩ ግንባሮች የተፋለመውን የአማራ ልዩ ኃይልና ሚኒሻ በዚህ በወያኔ ላይ በሆነው ድል ሥሙ እንዳይጠቀስ እንዴት እንሚጠነቀቅ አይተናል፡፡ ይሄ ልዩ ኃይል እንደኦሮሚያው ሕዝብን ለማጥቃት የተዘጋጅ እንዳልሆነ ቢታይም ከዛም አልፎ መከላከያውን ሳይቀር የታደገ እንደሆነ ቢታወቅም ይሄን እውነት ሕዝብ እንዲያውቅ ማድረግ አልተፈለገም፡፡ ምን ዓልባትም በቀጣይ ይሄን ልዩ ኃይል ላይ ማሴርን እየሰራ ይሆናል፡፡ በየቦታው የሚታረደው አማራ ወይም ከአማራ ጋር ወዳጅነት አለው የሚባል በመሆኑ ወሳኝ የሆኑ ስልጣኖች የተያዘው ደግሞ በአማራ ጠል በሆኑ የኦሮሞ ባለስልጣን በመሆኑ ይሄንኑ ስርዓት ማስቀጠል ላይ እንጂ መከላከያው ከማንም በላይ እደግመዋለሁ ከማንም በላይ እውነተኛ ኢትዮጵያዊ ሆኖ ያለውን የአማራን ሕዝብ እንደሕዝብ እያየ አደለም፡፡ ይልቁንም ጸር ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት የሆነውን በተለይም የአማራን ሕዝብ የማይወክለውን የወያኔና ኦነግ ሕገ መንግስትን መጠበቅ ዓላማዬ ነው ይለናል፡፡ ፍትህና የኢትዮጵያ መንግስታዊ ሥርዓት ሳይሆን ይሄ ጠንቀኛ የወያኔና ኦነግ ጸረ ኢትዮጵያ ሴራን መጠበቅ ነው ሥራው፡፡ ለሲዳማ ሲሆን ያልተጠበቀው ይሄው የወያኔና ኦነግ ድርሰት በማይመለከተው በአማራ ሕዝብና በማይመለከታቸው ከአማራ በኃይል የተነጠቁ ቦታዎች ላይ ተንጠራርቶ እንዲሰራ ይሞከራል፡፡ ይሄን የጸረ-ኢትዮጵያ የሆነን ሰነድ ዛሬ አይነካብን የሚሉ ደግሞ የኦሮሞ ፖለቲከኞችና ወዳጆቻቸው እንደነ ሲዳማ ያሉ እንጂ አንድም ሌላ የለም፡፡ ለ50ዓመት በጥላቻ የመረቀዘ ሕሊናቸውን ዛሬም ሊያስቀጥሉት ለሚሞክሩ መከላከያው ዘባቸው እንደሆነ እየተመለከትን ነው፡፡ አብይ ምን ያለበት ምን አይችልም እንደተባለው ከድል በኋላ መከፋፈል እንዳይኖር ይለናል፡፡ ቀልደኛ በወያኔና ኦነግ ሥርዓት አገርን እያፈረሱ ሌላ እድል ጊዜ ማግኘት አለብን አይነት ነው፡፡ አዝናለሁ፡፡

በመጨረሻ ዛሬ አለሙ ሥሜ ወጣቶችን ሰብስቦ የተናገረውን ንግግር ሰምቻለሁ፡፡ እንደእውነቱ ከጅምሩም ይሄን ሰው በብዙ ነገር አደንቀው ነበር፡፡ ኦሮሞ ሆኖ ኢትዮጵያዊ አመለካከት ስላለው ከፍተኛ የሆነ ዘመቻ በጸረ-ኢትዮጵያውያን ኦነጋውያንና ጀዋራውያን ተከፍቶበት ነበር፡፡ የዛሬው ንግግሩ ከፍተኛ ጥንቃቄ ያለበት ቢሆንም ከውስጥ የሚናገራቸውን እውነቶች ግን ለማድመጥ አልከለከሉትም፡፡ ከኦሮሞ ፖለቲከኞች ምን ዓልባትም በተዓምር የተረፈ ሊሆን ይችላል፡፡ ምን አልባት አለሙ ሥሜን ለዚህ ያበቃው አስተዳደጉም ሊሆን ይችላል፡፡ ለማንኛውም ያስተላለፈውን መልዕክትና ሲናገርም የነበረውን በራስ መተማመን መንፈስ አድንቄለታለሁ፡፡ ይሄ ንግግሩ ግን በተግባር ሲቀየር ማየት እፈልጋለሁ፡፡

ሌላው ብልጽግና የተባለው ቡድን አሁንም በጸረ-ሐይማኖት ማኒፌስቶው ሊጠየቅ ይገባል ባይ ነኝ፡፡ ይቺ ባቄላ ካደረች አትቆረጠምም እንደተባለው ነው፡፡ ግልጽ የሆነ የጴንጤ ሀማኖት ማራመጃ መዋቅር እንጂ የፖለቲካ ፓረቲ አደለም፡፡ በብልትግና አገራዊ አንድነት ያለው ፓርቲ ተመሰረተ ሲሉን የነበሩት ደግሞ ከወያኔው ኢሕዴግ ለይተው የሚያሳዩን እንኳን ምልክት በሌለበት ነው፡፡ ይልቁንም የጸረ-ኦርቶዶክስና ሙስሊም ማኒፌስቶ ጽፎ መምጣቱ በጸረ አማራነትና ኦርቶዶክስነት ከመጣቸው ወያኔ ጋር ያመሳስለዋል፡፡ ከዚህ በተረፈ የማዕከላዊው መንግስት ሥልጣንም በኦሮሞ ኦነጋውያን ተወረረ እንጂ አጋር ሲባሉ የነበሩትን ወደስልጣን ሲጋብዝ አላየንውም፡፡ መጀመሪያ ከአፋር የመከላከያውን ሚኒሰቴርነት ቢሰጠም ወዲያው ነበር በኦሮሞ የተተካው፡፡ እንደውም ድሮ አጋር በሚባሉ ጊዜ የተሻለ የማዕከላዊ መንግስት ውክልና የነበረቻው ነበሩ፤፡ አሁን ለይቶለታል፡፡ አወቃቀሩም በየብሔረሰቡ የአማራ የኦሮሞ የሚል እንጂ የኢትዮጵያ የሚል ስያሜ የለውም፡፡

የአማራ ክልል የወያን ምልክቶችን እያጸዳሁ ነው እያለን ነው፡፡ እንደ እውነቱ የዚህ ክልል ባለስልጣናት የሚገርም አዚም የተደረገባቸው ነው የሚመስለው፡፡ ሲጀምር ግንቦት 20 የሚል ሥያሜን ሊያውም የባሕርዳርን ኤርፖርት ለሚያህል መሠጠቱ አስገራሚ ነው፡፡ ሲቀጥል በወያኔ ጊዜ እሽ ተገደን ነው ከተባለ ላለፉት ሁለትና ከዛ በላይ ዓመት ይሄው የጸረ-አማራ ብቻም ሳይሆን የጸረ ኢትዮጵያ የሆነው ሥያሜ ሳይነሳ መቆየቱ የሚገርም ነው፡፡ ወያኔ የሰጠቸውን በአዴን የሚለውን ሥም ቢቀይርም የሰጠችውን ባንዲራ እስካሁንም ታቅፎት እናያለን፡፡ በሕግ የወያኔ የሆኑ ምልክቶችን የያዘ መጠየቅ ሲኖርበት ማለት ነው፡፡ አሁን ኀውልት እያፈረሰ ነው፡፡ ሐውልቱ ምን መልዕክት እንዳለው አላውቅም፡፡ ከነጭርሱም የኢትዮጵያ መልክ ያለውም አይመስልም ምን ዓልባትም ከግሪክ ፈላስፎች ይመስላል፡፡ ወይም ከቀደሙ ሐዋሪያት፡፡ ይሄን ትርጉሙን የሚያውቁት ያውቁታል፡፡ ለመሆኑ የታቀፋትን የወያኔ የጥንቆላ ባንዲራ የሚጥላት መቼ ነው?

ቅዱስ እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ! አሜን!

ሰርፀ ደስታ

1 Comment

  1. “በመከላከያ ሠራዊታችን ላይ ጥርጣሬ እንዲኖር እያደረገ ነው ብላችሁ እንዳታስቡ፡፡” አልክ?
    አይ ቅቤ እየቀባኅው ነው እንጂ፤፤ “አልገልህምን ምን አመጣው አለች ጦጣ” ኪኪኪኪ …..You are literally calling for coup d’état. ይቅር ይበልህ! ጁንታውም እኮ ሳሞራን ኩዴታ እንዲያደርግ ጠይቆት ነበር፡፡

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.