ዘረኝነትን የማውደሚያ ጊዜ አሁን ና ዛሬ ነው – መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ

” ዘረኝነት በሽታ ነው።የዘር ግጭት በተነሳባቸው ቦታዎች በሙሉ በሽታ መሆኑንን አይተናል።ዘረኛ ነእሱ ያልሆነንየሌላ ዘር ሰውየሰው ዘር አድርጎ አያይም።ለህጻንነትለሽምግልና ለሴትነት ለአቅመ ደካማነት ርህራሄን የሚያሳይ ልብዘረኞች የላቸውም።የስድስት ወር ሀፃንን ሁለት እግሩን ይዘው ጭንቅላቱን ከግርግዳ ጋር አጋጭተው እንደዱባ ሲፈራርስ ማየት ያስደስታቸዋል።አፍሪካ ውሥጥ አይተነዋል።ሩዋንዳ ውስጥ ይህ ሆኗል።በሀገራችን አይተነዋል።እርጉዝ ሆዶ ተተርትሮ ያልተወለደ ልጇ ሜዳ ላይ ተጥሎ ኢትዮጵያ ውስጥ አይተናል። ሰው እንደ ከብት ታርዶ ኢትዮጵያ ውሥጥ አይተናል።

unnamed 10በሃገራችንየዘር ቁማር ጫወታ መብት ከማስከበር ወይም ጥቃት ከመከላከል ጋራ ምንም ግንኙነት የሐውም።የዘር ፖለቲካ ነዳጁ ድህነት ነው። ከድህነት የወጡትማ በሃገራቸው የዘር ፉክቻን አሥወግደው ጭራሹኑ ከሌላ አገር ጋር እየተቀናጁ ታላላቅ ዓለም አቀፍ ማህበረሰቦችን እየመሠረቱ ነው። ”  ( “ከታፋኙ ማሥታወሻ “ ገፅ 249 የአንዳርጋቸው ፅጌ  “ግለ ታሪክ ” መፅሐፍ የተወሰደ ።

ህውሃት /ኢህአዴግ  በሥውር ሤራው ለራሱ ዓላማ ማሥፈፀሚያ ሲል ፣በየጊዜው የሚፈነዳ ፣በዘረኝነት የተቀመመ የጥላቻ ቦንብን በቋንቋ አማካኝነት  ቀብሮ ፣የባህል አንድ ዘርፍ የሆነውን ቋንቋን የፖለቲካ ንግሥና እንዲያገኝ በማድረግ ፣እያንዳንዱ ግለሰብ በቋንቋው የመናገር ተፈጥሯዊ መብት እንዳለው በመካድ ና ብዙሃኑንን ኢትዮጵያዊያን የሚያግባባውን ራሱ በምክር ቤት እና በዕለት፣ዕለት ሥራው የሚጠቀምበትን  የአማርኛ ቋንቋን እንደ ጠላት ቋንቋ በማሥቆጠር ፤ በጣት የሚቆጠሩትን የጎሳ ቋንቋዎች ብቻ የበላይ አድርጎ በማወናበድ ሲገዛ እንደነበር ይታወቃል።ባረቀቀውና ባፀደቀው ህገመንግሥት ከለላ   ጥቂት “ዘሮች ” ለይሥሙላ በቋንቋቸው ተናጋሪ ” እየተገዙ ” እንዲኖሩ በማደረገ ቦንቡን በብዙሃኑ ጎሣ ላይ፣ በተለያየ ጊዜ በእቅድና በፕሮግራም እያፈነዳ መቆየቱ ይታወቃል። …

ዛሬም ይኸው በዘር እና በቋንቋ በጥላቻ የተቀመመ አውዳሚ ቦንብ አያሌ ንፁሐን፣ምሥኪን እና በሰላም ሰርቶ የእለት ጉርሥና የዓመት ልብሥ አሟልቶ ከመኖር ውጪ ሥለፖለቲካ ግድ የሌላቸውን ወይም ጥልቅ ግንዛቤ የሌላቸውን ያለርህራሄ በግፍ እየጨረሰ ነው።በሻሸመኔ፣በጅማ፣ በቤንሻጉል ጉምዝ ፣ በምእራብ ወለጋ ፣በአሩሲ ፣በባሌ፣በቡራዩ ዛሬ ደግሞ በትግራይ _ በማይካድራ …የተፈፀመው እኩይ ተግባር የሚያሳየን የዚህን በዘረኝነት የተቀመመ የጥቂት ፀረ ኢትዮጵያውያን የጥላቻ  ቦንብን አጥፊ  ግብሩን ነው።

ህውሃት የወለደው ፣ የቋንቋና የዘር ፖለቲካ ግብር ሰዋዊ አሥተሳሰብን የሚጠላ ነው። የራሥን ቋንቋ ና ዘር ብቻ ፣ እንደ ሰው በመመልከት፣  የሌለውን ሰው ፣ጎሣ ና ዘር እንደ በረሮ በመቁጠር ፣አያሌ ቀፋፊ፣አሥደንጋጭ እና ከሰው የሞራል አሥተሳሰብ ባፈነገጠ መንገድ የሰው ህይወት እንዲጠፋ አድርጓል። በተደጋጋሚ በመላው ኢትዮጵያ ግፍ እንዲፈፀም ሰበብ መሆንን በቅጡ መረዳት አለብን ። ( ከላይ  የጠቀሥኩት የአንዳርጋቸው ሃሳብ ይህንን  ያጠናክርልኛል።)

ይህ ኢ_ሞራላዊ  የዘር ፖለቲካ ፣ ከራሱ ዘር ውጪ ያለውን ሰው የተባለ ፍጡር በመግደል ለተሰማሩ የእኔ ለሚላቸው ቡድኖችና ግለሰቦች ፅድቅን የሚቸር ሆኖ እናገኘዋለን።ወይም የሌላው ዘርን የሚገለው ሰው የሆነውን አምሳያውን እንደበረሮ በመቁጠሩ ነው። ዘረኛ ሰው ሰው ሲገድል ከቶም የማይፀፅተው ለዚህ ነው።

በረቂቅና  ከፋፋይ አሳቡ በብሔርና ብሔረሰቦች እኩልነት ሰበብ (የብሔርና ብሔረሰብ ትርክትን እሱ በፈጠረው ተረታት ፣በማሥጮኽ) ጨቆኝና ተጨቆኝ ብሔር በመፍጠር እና ያ ተጨቋኝ የተባለው ከብሔር ይልቅ ዘርና ቋንቋ እንዲሆን በማድረግ  አንዱን ዘር ከሌላው ዘር የሚለያይ የጥላቻ   ቦንቡ በፈጠራቸው ቡድኖች አማካኝነት አሥታጥቆ ህዝቡ ውሥጥ በማፈንዳት ዜጎችን አጫርሷል። እያንዳንዱ ቋንቋና ዘር ከራሱ ዘር ውጪ ሌላው አራት እግሩን ለምን አይበላም ብሎ እንዲያሥብም አድርጓል።

ህወሓት /ኢህአዴግ  መራሹ የዘር ፖለቲካ ፣  እያንዳንዱ ጎሣ  ከእራሱ  ውጪ ፣የሌላው ዘር በሙሉ ቢያልቅ ደሥ ብሎት እንዲጨፍር የሚያደርግ አሳፋሪ ዘረኛ አሥተሳሰብን በቋንቋ  ና በጎሣ ፖርቲ ሥም ፈጥሮ እንደነበረም አይዘነጋም።

ኢትዮጵያውያን በዚህ   ከፋፋይ በሆነ ፋሺሥታዊ  የዘር ና የቋንቋ ሥርዓት  በመመራታችን ለ27 ዓመት ሰብዓዊ ክብራችን ተረግጦ እንደኖረም ይታወቃል። ዛሬ ይህ ዘረኛና ከፋፋይ የቋንቋ ሥርዓት ሰንኮፉ ተነቅሏል ። ” አክትሞል..” ማለት አንችልም። እውነተኛ የዜጎች ህጋዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶችም ተከብረዋል።እውነተኛ የሆነ ሥልጡን የፊደራሊዝም ሥርዓትንም ገንብተናል። በማለት የለውጥ ኃይሉ ለመናገር የሚችልበት ደረጃም ገና አልደረሰም።

ትላንትና  “አሥር ” ዛሬ ደግሞ አሥራ አንድ ቋንቋዎች አብረዋቸው የሚኖሩትን የተለያየ ቋንቋ የሚናገሩ ሆኖም ግን በአማርኛ ቋንቋ ከሁሉም ጎሳዎች ጋራ የሚግባቡትን ኢትዮጵያዊያን የመመረጥ መብት ከልክለው እነሱ ብቻ …የፌዴሬሽን  ምክር ቤት አባላት ሥለሆኑና በተወካዮች ምክር ቤትም  ተወካዮች ሥላላቸው” በኢትዮጵያ ያለው ሥልጡን እና በብዙሃኑ ቅቡልነት ያለው የፌደራል ሥርዓት ገንብተናል ማለት አይቻልም።

በየክልሉ ከተሞችና ገጠሮች የሚኖሩ ፣ ዜጋን መሠረት ባላደረገ እና ኢ _ዴሞክራሲያዊ የዘር አወቃቀር ባለው በእያንዳንዱ የክልል ምክር ቤት ተመርጠው መሳተፍ ባልቻሉበት ሁኔታ ውሥጥ እያለን የዚች አገር የፌደራሊዝም ሥርዓት ጤነኛ ነው ማለት አይቻልም። ከአውዳሚው የወያኔ የዘር ፈንጂ ነፃ የወጣ ፣በዓለምአቀፉ ማህበረሰብ የሚሞካሽ ነው ለማለትም የሚያሥችል  እውነት በዚች በፈጣሪ አገር የለም።

ህወሃት/ኢህአዴግ  በዘረኛው አውዳሚ ፣የጥላቻ ቦንቡ አማካኝነት ከዚች ከፈጣሪ  አገር ላይ ፍቅርን ለመደምሰስ ብዙ ርቀት መጓዙ ይታወቃል።  የሰዎችን እኩልነት ፣ ወድማማችነት እና ማህበራዊ ትሥሥር ደምስሶ፣ ሰዎች ቋንቋን መሠረት አድርገው፣  በዘራቸው አንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ዜጋ ሆነው በ10 ቋንቋ ተናጋሪዎች እንዲተዳደሩ ማድረጉ ይታወቃል። የ27 ዓመቱ የጥላቻ ቦንቡ ጦሥም አንድ ተጨማሪ የቋንቋ ክልል ፈጥሮልናል።

ይህ የመከለል፣የማጠር፣የመለየት፣አንዱን ልጅ ሌላውን የእጀራ ልጅ አድራጊ ቋንቋ መር አሥተዳደር   በመላው አገራችን የፈጠረው ጦሥ ዛሬም አላባራም። ኢትዮጵያዊነትን የሚያኮሥሥ በመሆኑም በጊዜ ካላረምነው ነገም ከዛሬ የበለጠ ጦሥ በኢትዮጵያውያን ላይ ያመጣብናል። ይህንን  በጠመንጃ አፈሙዝ አሥገዳጅነት ፣በፍርሃት ተሸብበን ሳንወድ በግድ የተሸከምነውን ጦሰኛ    የዘርና የቋንቋ ንግሥናን   ከጫንቃችን ላይ ያወርድልናል ብለንም የለውጥ ኃይሉን መደገፋችን አይዘነጋም።

እንደምናሥታውሰው ኢትዮጵያዊያን ያኔ ከሁለት  ዓመት በፊት በአገር ውሥጥና በውጪ አገር  በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ለሚመራው ለውጥ  በነቂሥ በመውጣት ለኢትዮጵያ ያላቸውን ቀናኢነት ማሥመሥከራቸው ይታወቃል።

ኢትዮጵያዊያን በመላው ዓለም በነቂሥ በመውጣት የጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድን እና የትግል አጋሮቻቸውን ፣የፍቅር፣የይቅር ባይነት፣የመተሳሳብ፣የአንድነት፣የመደመር ና የኢትዮጵያዊነት ሃሳብን በመደገፍ ከዶ/ር አብይ የለውጥ ሃይል ጋር መቆማቸውን  በታላቅ ሥሜት በየአደባባይ ሲያንፀባርቁ የነበረው፣ ነገ በኢትዮጵያዊ ዜግነታችን እና በኗሪነታችን ታውቀን እና  ተከብረን ፣የመመረጥ እድል አግኝተን ፣ በምርጫ ተወዳድረን ፣በአገራችን ጉዳይ በአገራችን ጉዳይ ለመመከር ፣  በእያንዳንዱ ክልል ምክር ቤት ተሳታፊ እንሆናለን ብለው በማሰብ ፣ አርነታቸው በመታወጁ ደስ ብሏቸው ነበር።

ሆኖም   ሁለተኛ ዜግነታቸው ዛሬም በመፅናቱ መምረጥ እንጂ ተመርጠው በዘር ሥም በተመሠረቱት የክልል ምክር ቤቶች መግባት አይችሉም።

አማራ በተባለው ክልል አማራ ብቻ እንዲኖር እሥካልተፈቀደለት ድረሥ እና የአማራ ክልል የኢትዮጵያ አሥተዳደራዊ ክልል እሥከሆነ ድረሥ ትግሬው ፣ሀመሩ ፣አፋሩ፣ ቦዲው፣ሺናሻው፣ ሲዳማው ኦሮሞው ፣ቤንሻጉሉ፣ሐረሬው፣ ጋቤላው ፣ሱማሌው  ፣ወላኢታው … በአጠቃላይ መላው የኢትዮጵያ ዜጋ ለምን ተሳታፊ አይሆንም።በቋንቋ ካየነውም ከ85 ቋንቋ በላይ የሚናገረው ቋንቋውን ይዞ ለምን በእያንዳንዱ የፊደሬሽን ምክር ቤት ተመራጭ መሆን አይችልም?…በተወካዮች ምክር ቤትም በሚኖርበት አካባቢ ህዝብ ከተመረጠ ለምን ህዝቡን ወክሎ የምክር ቤት አባል አይሆንም??

ትላንት ዜጎች ፣ በፍፁም ነፍሱ ሊያገለግለኝ ይችላል የሚሉትን ዜጋ ሳይሆን የሚመርጡት የማያውቁትን እና በቋንቋ ሰበብ ከቀበሌያቸው፣ከወረዳቸው፣ከዞናቸው ውጪ የመጣላቸውን ሰው ነው። ቋንቋቸውን ቢናገር እንኳን ሰው ይሁን የሰው ጅብ ከቶም አያውቁትም።ዛሬሥ ?

ዛሬ ከህገ መንግሥቱ አንፃር የተቀየረ ነገር የለም። የለውጥ መንግሥቱ ደጋፊዎች፣ የትህነግን የዘረኝነት ሴራ እና የባንዳ አገልጋይነት ከመተረክ በዘለለ፦ ” በአንደኛ ና ሁለተኛ ደረጃ ዜግነት ዜጎች መፈረጃቸው እና በሁሉም ክልሎች የቋንቋ ንግሥና መኖሩ አላከተመም።

እናም ብልፅግና  መካከለኛውን መንገድ ለመምረጥ ዝግጁ ከሆነ፣ ለምን ከ70% በላይ ተናጋሪ ያለውን የአማርኛ ቋንቋ የየክልሉ የሥራ ቋንቋ በማድረግ ዜጎች በሚኖሩበት አካባቢ የፖለቲካ ፣ የኢኮኖሚ እና የማህበራዊ ተሳትፎቸው እንዲጎላ አያደርግም ?  ከከፋፋዩ የወያኔ የባንዳ መንገድ ከነአካቴው  በመውጣት ብልፅግና የራሱን  የአገር ብልፅግና  የአገር  ማበልፀጊያ መንገድን ለምንሥ አያደላድልም ?

የዚህን ጥያቄ መልሥ የምናገኘው ምናልባት በሥድሥተኛው አገር አቀፉ ምርጫ ነው።በዚህ አጠቃላይ ምርጫ ፣በሚደረገው  የምረጡኝ ቅሥቀሳ ወቅት ሊሆን ይችላል ብዬ አሥባለሁ። መቼም ብልፅግና የ1997 ዓ/ምቱን የምርጫ ታሪክ ለመድገም ሲል በ2013 ዓ/ም  በቋንቋ ፖለታካ ላይ ሙጭጭ እንደማይል ተሥፋ አደርጋለሁ።

ይህንን ጉዳይ በዋዛ ማየት አይገባንም።  ኢትዮጵያዊያን ምሁራን እና ሊቃኖች እንዲሁም በሳል ፖለታከኞች  ወደ አራገፍነው ቀንበር መልሰን እንዳንገባና እንዳንጠመድ ፣ህዝብን የማንቃት፣የማደራጀት የፖለታካ ትጥቅ የማሥታጠቅ ሥራ ሊሰሩ ይገባል።ይህንን ሥራ ለኢትዮጵያ ህልውና ሲሉ ነው የሚሰሩት። ይህንን ኢትዮጵያን የማዳን ሥራ በትጋት መሥራት  ካልተቻለ ፣ ነገ ባለሳምንቱ  ጁንታ  ብቅ ማለቱ አይቀርም።

ባለሣምንቱ  ጁንታም ፣ በዘር ሥም ፣ ልክ እንደ ወያኔው ጁንታ ፣ ቋንቋ እንጂ ፣ የፖለታካ ብሥለት፣ተጨባጭ እውቀትና የሚታይ ችሎታ ሥለሌለው   ባልተገባ እና ህገ ወጥ በሆነ መንገድ  ሀብት ለማጋበሥ እንጂ ሥለአገር እድገት ደንታ የላውም።

ሁሉም የዘር ፖለቲከኛ ፣ዘረፎ መብላት ሱሱ ነውና ይህ የሱሱ ማርከሻ  እንዳይቆረጥበት ሥለሚፈልግ በተቻለው አቅም ከፍቅር ይልቅ ጥላቻ እንዲነግሥ ይጥራል። እንዲህ ዓይነቱ ዘረኛ፣ሰለዓለም እና ሥለሰው አፈጣጠር ያለው እውቀት ዜሮ በመሆኑ ህሊናው መጥፎውን እና ጥሩውን ከቶም ማመዛዘን አይችልም። መሐል ሆኖ ነገርን ግራና ቀኝ በማየት በጥልቀት የመፈተሽ አቅም የለውም።እንዲህ ዓይነቱ ዘረኛ ነው፣  ህሊና ሥለሌለው በእኩይ ደርጊቱም ሥለማያፍር  ፣ የቋንቋና የዘር  ፖለቲካ ቀጣዩ ጁንታ  በመሆን አገር አውዳሚ የሚሆነው።

ምክንያቱም ፣ ”  የያዙኩት ይበቃኛል። ለምን ከእጅ ወደአፍ በሚኖረው የቋንቋዬ ተናጋሪ አሾፋለሁ ? እኔም እንደ አንድ ዜጋ ራሴን ከቆጠርኩ፣ የሌሎች ዜጎችን መብት ማክበር አለብኝ።በኢትዮጵያ ውሥጥ የሚኖር ዜጋ ሁሉ መብቱ ሳይሸራረፍ መከበር አለበት።የአካባቢውን ቋንቋ ባለማወቁ ብቻ ከፖለቲካዊ ተሳትፎ መገለል የለበትም። በብልፅግና መሐከለኛ መንገድ ሁሉም ዜጋ በአገሩ ጉዳይ ያገባዋል።የበይ ተመልካችም ሊሆን አይገባውም። …” ከቶም አይልምና የለውጡ አደናቃፊ መሆኑ አይቀርም ።

ይህ እውነት ነው።ለጠቅላይ ሚኒሥተር አብይ አህመድ የአገሬ ተጨባጭ እውነት ግልፅ ቢሆንም ፣ ዛሬ በህውሃት  የባንዳ ቡድን አማካኝነት ኢትዮጵያን ለማፈራረሥ በህገ መንግሥት ሥም የተሰራው ደባ እና የከሸፈው  የሰሞኑ ግልፅ አገር የማፈራረሥ እኩይ ሤራ  ለሌሎች ባለህሊና የለውጥ ኃይሎች የባንዳነትን ግብ ግልፅ ያደረገላቸው ይመሥለኛል።

ይህ የባንዳነት ግብ ፣ የዘር ፖለቲካ ወደ እርስ በእርስ ጦርነት እንዲያመራ ለማድረግ የሚገፋፋ እንደሆነ በህወሃት እኩይ ተግባር ተረጋግጧል ።

የአገር ተከላካዩን ፣ድንበሯ እንዳይደፈር ቆቅ ሆኖ የሚጠብቀውን  የኢትዮጵያን ልጅ በጭካኔ ያሳረደው ይህ የዘር ፖለቲካ ነው።  ድንገቴው እጅግ ያሳዘነው  የኢትዮጵያ ሠራዊትም ..”አገሬ ነው፣ማን በአገሬ ላይ አዘናግቶ ይደፍረኛል ብዬ አሥባለሁ ?ከቶሥ እንዴት ጨክነው ህዝብን እየጠበቅሁ ከህዝብ ውሥጥ የወጡ የእናት ጡት ነካሾች እኔኑ መሥለው በማዘናጋት ዘና ባልኩበት ወታደራዊ ካንፕ ውሥጥ ገብተው ያርዱኛል ብዬ እጠረጥራለሁ ?ምንም ዘረኝነት ቢያሳብዳቸው እንዲህ ዓይነቱን ለጆሮ የሚቀፍ ፣ የውጪ ወራሪ ጦር እንኳን በምርኮኞች ላይ  የማይፈፅመውን የጭካኔ ተግባር  ለመፈፀምስ  የሚያሥችል ልብ ሊኖራቸው ቻለ ?…”በማለት አሁን እየተጎዝንበት ያለውን የፖለቲካ መንገድ ቆም ብለን እንደናሥብ የሚያደርግ ጥያቄ መጠየቁንም አንዘንጋ ! ቆም ብለንም መንገዳችንን እንመርምርና ዘረኝነትን ለማውደም እንነሳ።

1 Comment

  1. ያፋኙን ማስታወሻ ዋቢ አድርገህ አቀረብክልን የማፈኛዉን ህገ መንግስት እኮ ከመለስ ጋር ያረቀቀዉ እሱ ነዉ አይ የኛ ነገር

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.