የእጅ አዙር የኦሮሙማ ፕሮጀክት በቤንሻንጉል

OLF and Benshangulወያኔ ቤንሻንጉል ብሎ በፈጠረው ክልል ውስጥ አሁን ላይ በተባባሰ ሁኔታ እየተካሄደ ያለው የንጹሃን አማራወች፡ ጉምዞች፡ አገዎች ወዘተ ጭፍጨፋወች በአማራና በቤንሻንጉል ክልል መካከል እንደተፈጠረ ውጥረት አድርጎ መውሰድ ፍጹም የተሳሳተ ነው፡፡ የቤንሻጉሉም ሆነ የወለጋና የሌሎች ቦታወች የአማራዎች ጭፍጨፋ ምስጢር አንድና አንድ ብቻ ነው፡፤ ይህም ወያኔ ጀምሮትና ብዙ ግፎችን ሰርቶበት ያልተሳካለትን አማራን የማዳከምና የማጥፋት ዘመቻ ቅጥያ ነው፡፡ የአሁኑ ተረኛ ኦሮሙማም በማፍዘዝም ይበሉት በማደንዘዝ ወይንም አረመኔያዊ ድርጊታቸውን በፈለጉት በሌላ ስም ይጥሩት አላማው አማራን አዳክሞና አጥፍቶ ኦሮሞን በአማራ ላይ የበላይ፡እንደዚሁም አማርኛን አዳክሞ ኦሮሞኛን በአማርኛ ላይ የበላይ አድርጎ ኢትዮጵያን እንደ አዲስ በኦሮሞ ቅርጽ፡ ወርድና ስፋት የማበጀትና የመስራት ስራ ነው፡፡ የማይሆን የኬኛዎች የቀንም የማታም ቅዠታቸው ነው፡፡ ይህ ሴራ ሁሉም ኦሮሙማወች ተማምለው የጀመሩት ያልተቀደሰ ብቻ ሳይሆን ሊሳካ የማይችል መጨረሻው የአገር መውደቅን የሚያስከትል ሴራ ነው፡፤ በመጨረሻም ራሳቸው ኦሮሙማወች እርስ በርስ ተበላልተው ድራማው በውድቀት እንደሚጠናቀቅ ፈጣሪ እድሜ ይስጠን እንጅ በእርግጠኝነት ሲፈጸም እናየዋለን፡፡

131208852 10223919045714774 569981346701348210 n

ለዚሁ የኦሮሙማ ፖለቲካ ቁማር መሪውና ኮማንደሩ ዶ/ር አብይ አህመድ እንጂ ሽመልስ አብዲሳ/ ጃዋር/ መራራ/ ዳዉድ ኢብሳ/አዲሱ ቂጤሳ ውይንም ሁለቱ ሌንጮዎች ……ወዘተ አይምሰሏችሁ፡፡ እነሱ ታዛዦች ናቸው፡፡እንዳትሳሳቱ፡፡ብዥታም አይኑርባችሁ፡፡ በጀግኖቹ የአማራ ልዩ ሀይል (ነፍጠኞች) በየአውደ ውጊያዎቹ ቆራጥና አኩሪ ፍልሚያ የተሽመደመደው የወያኔ ጦር ከግስጋሴው በወሳኝነት ከተገታ በኋላ ፈጥኖና መልሶ በተደራጀው የሀገር መከላከያ ሰራዊት ላያንሰራራ ድባቅ ተመትቷል፡፡ይህ ሁሉ በመገባደድ ላይ እያለ አሁን ላይ የሚቀር አንድ ታላቅ አገራዊ ጉዳይ በእንጥልጥል ላይ አለ፡፡ይህም የአገሪቱ ፖለቲካ ከእንግዲህ ወዴት የሚለው ነው፡፡ለዚሁ አብይ ጉዳይ ጠ/ሚ/ሩ የቀሩት ሁለት ተጻራሪ አማራጮች ብቻ ናቸው፡፡ሌሎች ማጭበርበሪያ ካርዶች ከወያኔ ጋር ተቀብረዋል፡፡

አማራጭ አንድ፦ ለአገሪቱ ይህንን ሁሉ ውድቀት ያመጣባት መሰረታዊ ችግር በዘር ላይ የተመሰረተው የደደቢት ህገ መንግስት መሆኑን በማመን ይህንን ህገመንግስት ዛሬዉኑ ማገድና በምትኩም በዘር ላይ ያልተማከለ ፌደራላዊ ህገመንግስትን በቶሎ ተግባራዊ ማድረግ፡፡ ከዚያም የወያኔ ታናሽ ወንድም የሆነውን ኦነግን በኦነግ ሸኔ ስም ለመቀባባት ከመሞከር ይልቅ ህወሀትንና ራሱን ኦነግን በአሸባሪ ድርጅትነት መዝግቦ ከፖለቲካ እንቅስቃሴ ማገድ፡፡የተረኛውን የኦሮሙማ አስተሳሰብንና አደረጃጀትንም ሆነ ሌሎች በአገሪቱ ውስጥ በዘር ላይ የተመረኮዘ አስተሳስብ/አደረጃጀት የሚያራምዱትን በሙሉ ድርጊቱን በወንጀል ተግባር ፈርጆ በህግ እንዲታገዱ ማድረግ፡፡

አማራጭ ሁለት፦አሁን ያለዉን በዘር ላይ የተዋቀረ ህገ መንግስትን ማስቀጠልና በተረኝነትም የመሪነት ቦታ ላይ ያለው የኦሮሙማ ፖለቲካ አገሪቱን ወደ ማትወጣው አዘቅት ይዟት እንዲወድቅ መፍቀድ፡፡ አማራጭ አንድ የሚበጅ፡ የሚፈለግ፡ ለአገሪቱ በሽታዎች ሁሉ ፈውስን የያዘ ብቸኛ አማራጭ ነው፡፡ በአማራጭ ሁለት ከተሄደ ግን አሁን በመፍረስ ጠርዝ ላይ የምትገኘው አገራችን እንደአገር መቀጠል ስለማትችል ትፈራርሳለች፡፤ የእርስ በእርስ ጦርነቱም የሰው ልጅ በታሪክ አይቶት ያማያውቅ ዘግናኝ ይሆናል፡፡ በውጤቱም ማንም አይጠቀምም ብቻ ሳይሆን ማንም በሰላም ሊኖር አይችልም፡፡

ከሁለቱ ውጭ ሌላ አማራጭ በመሀል የለም፡፡ ህዝቡ የሚሻለውን ያውቃል፡፤ የመሪነቱን ቦታ የያዙት ዶ/ር አብይም የሚጥማቸውን እራሳቸው ያውቃሉ፡፡

 

1 Comment

 1. በ ኢትዮጵያ ሰላም ሊሰፍን የሚችለው ከሥር የተዘረዘሩት መስፈርቶች ሲሟሉ ብቻ ነው።
  1) የ ጎሳ ስብስቦች ሁሉ ሲታገዱ፣
  2) የ ህዝብ ብዛት በ መተካካት ሲያድግ፣ ማለትም የ ወሊድ ቁጥጥር ሲደረግ፣
  3) አድልዎን ለ ማጥፋት የ ሥራ ዕድሎች በ አደባባይ በ ሎተሪ እንዲቀጠሩ ሲደረግ፣
  4) የ እርሻ መሬት ከ ትውልድ ወደ ትውልድ ለ ገበሬዎች ሲረጋገጥ፣
  5) ሰዎች ከ መኖሪያ ቤታቸው በ ምንም ምክንያት እንዳይፈናቀሉ ሲደርግ፣
  6) ፍትህ ሲረጋጋጥ፣ ወዘተ ናቸው።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.