ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በመቀሌ ከከፍተኛ የጦር መኮንኖች ጋር ተወያዩ

131006526 3019266541643991 2619344835819065244 n
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የሕግ ማስከበር ሂደቱን ከመሩ ከፍተኛ የጦር መኮንኖች ጋር መቀሌ ላይ ተወያይተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በአካባቢው ለሕዝቡ እየተደረገ ያለው ሠብዓዊ ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።
መቀሌ ላይ በተካሄደው ውይይት ጄኔራል አበባው ታደሰና ሌተናል ጄኔራል ባጫ ደበሌን ጨምሮ በርካታ ከፍተኛ የጦር መኮንኖች ተሳትፈዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ድሉ የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ መሆኑን በውይይቱ ላይ ተናግረዋል።
በጁንታው ላይ የተገኘው ድል የሚያኩራራ ሳይሆን ‘የምንማርበትና የኢትዮጵያን ቀጣይነት የምናረጋግጥበት ነው’ ማለታቸውን ኢዜአ ከስፍራው ዘግቧል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የትግራይን ክልል መልሶ ለማቋቋም መንግስት በሙሉ ትኩረት ይሰራል ብለዋል።
በአካባቢው ለሕዝቡ የተጀመረው ሠብዓዊ ድጋፍ እንደሚቀጥልና መንግስት በሕግ ማስከበሩ ወቅት ጉዳት የደረሰባቸውን እንደሚደግፍ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ተናግረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተጨማሪም ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር አመራር አባላት ጋር በወቅታዊ የክልሉ ሁኔታ ላይ ተወያይተዋል።
በተለይም ክልሉን መልሶ ለማቋቋም በሚሰሩ ስራዎች ላይ መምከራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
#EBC

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.