መተከል እና መነቀል – ማላጅ

በኢትዮጵያ  የዘመናት ታሪካዊ ጠላት የሆኑት የረጅም ጊዜ ጠላቶች እና የቅኝ ግዛት ተስፋፊዎች እና የጥፋት መልዕክተኞች የዘሩት አረም  አገርን እና ህዝብን የማጥፋት እና ታሪክን የማዛባት ሴራ ዉስጥ የጥፋት አጋሮቻቸዉን ዛሬም በዚህ በ21ኛዉ ክ/ዘ ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያዉያንን ለማጥፋት የሚደረገዉ ትንቅንቅ እንደ ክፉ በሽታ ጊዜ እና ቅርፅ እየቀያየረ አሁን ላይ ተደርሷል፡፡

በ18ኛዉ ክ/ዘ መጨረሻ እና በ19ኛዉ ክ/ዘ መጀመሪያ በተደረገዉ  የቅኝ ግዛት ወረራ ያልተሰካላቸዉ የኢትዮጵያ ጠላቶች ለፍላጎታቸዉ ያልተገዛለቸዉን ኢትዮጵያዊ ሁሉ የማሰደድ እና የማጥፋት ስልት እና አጥፊ እሳት ቀብረዋል ፡፡

131259469 385454966118749 2683515878408084611 nከዚህ የተዳፈነ አጥፊ እሳት ዉስጥ ለመጥቀስ ፡-

የአገሪቷን የቆየ የነጻነት እና ጥንታዊነት ታሪክ ማዛባት

የህዝቡን የማንነት፣የዕምነት እና የባህል ዉርስ መከለስ፤መደለዝ

ዋና ዋና የአገሪቱን ጠቃሚ እና ለም አካባቢዎችን በፀረ ኢትዮጵያ ኃይሎች ፈቃድ እና ይሁንታ ዕዝ ስር ለማድረግ ማቀድ እና ማስፈፀም ነበር ፡፡

በተለይም በእንግሊዝኛዉ “ core / Nuclear Zone ” የሚባሉ ለም እና ዕጥፍ ድርብ አምራች የኢትዮጵያ ክፍሎች እና የባህር በር ለማሳጣት የተደረገዉ በደል አገሪቷ በገንዘብ/ኢኮኖሚ፣ በፖለቲካ እና በማህበራዊ እና የማንነት ገጽታ ላይ መሰረት በማሳጣት ጥገኛ እና ጠባቂ ለማድረግ ያልተፈነቀለ ድንጊያ ፣ያልተማሰ ጉድጓድ የለም ፡፡

ወሳኝ እና ከኢትዮጵያ አልፎ ለአፍሪካ መመገብ የሚችሉ የአገራችን ክፍሎችን ማለትም ኦጋዴን፣ ጋምቤላ እና መተከል  ከስም አስከ ተለያዩ የማደነጋገሪያ እና ማናቀፊያ ስራዎች በቅኝ ገዥ ህልመኞች ምኞት የሚዋኙ የዉስጥ ጠላቶች ብዙ እና ከብዙ በላይ አድርገዋል ፡፡

ለዚህም ከታሪክ እንደምንረዳዉ   ሶማሊያ-ከሞቃድሾ  አስከ አዋሽ ፣ ሱዳን -ከጁባ አስከ ጎጀብ፣ ከሰሜን ሱዳን አስከ መተከል ለም እና ምርታማ (core Zone) እና የዓባይን እና ጣናን ጉረሮ የማቆጣጠር እንደሆነ እዉነት መናገር ኃጢያት በሆነባት አገር ታሪክን ወደ ኋላ በማየት ጥርስ ዉስጥ ያስገባንን

ህዝብ በድህነት፣ በሞት እና በስደት እንዲባዝን ያልተደረገ የ27 ዓመት የጥልመት ዘመን የሆነዉን ክፍ ስራ ከመጥቀስ ያልሰሩትን ድርጊት መጥቀስ ይቀላል፡፡

ያልሰሩት የአገር እና ህዝብ ወንጀል ካለ ሲነቅሉ እና ሲምሱ  የነጋባቸዉ  ዳሽን ተራራ እና ዓባይን  ለመዉሰድ ሲባዝኑ በነበረበት ሁኔታ በተጨባጭ የሚታወቅ ነዉ ፡፡

ከላይ የዜጎች የዘመናት የስቃይ እና የደም መሬት ከነበሩት እና ከራሳቸዉ ህዝብ አልፎ ለአፍሪካ ሲሳይ የሚባሉትን ከምስራቅ ኢትዮጵያ ኦጋዴን ፣በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ -ጋምቤላ  ከሰሜን ምዕራብ- መተከል ዜጎች ስደተኛ ፣ መጻተኛ ፣ ምንዱባን፣ ሞት የረከሰባቸዉ እና ዜጎች የተዋረዱባቸዉ እንደነበሩ ዓለም የሚያወቀዉ ነዉ ፡፡

ሆኖም ክብር እና ምስጋና ለቸሩ መድሃኒት ዓለም እና ለእዉነተኛ እና አገር ወዳድ የኢትዮጵያ ልጆች በስም መጥራት አንዱን ትቶ አንዱን አንስቶ ስለሚሆንብኝ ኢትዮጵያዉያን ዞትር በአንደበታቸዉ የሚነግሩላቸዉ ፤ለምንጊዜም የሚያከብሩአቸዉ ምስጋና እና ክብር ይገባቸዉ እና ጋምቤላ እና ኦጋዴን ወደ እናት ምድር አገር ኢትዮጵያ ጥላ ስር ሆኗል፤ አካባቢዉ ለዓመታት ያጣዉን ሠላም አግኝቷል፣ የህዝቡ ዕንባ ታብሷል፣ ደሙም በዉሃ እና በወተት ይጸዳል ፡፡

ግን መተከል በቀድሞዉ የጎጃም ክፍለ ሀገር የነበር ከሰባት አዉራጃ አንዱ እና ዋነኛዉ የነበር መሆኑ እየታወቀ እና በየጥኛዉም መለኪያ ኢትዮጵያዊነትን ለመበረዝ ከጎጃም አዉጥቶ ለሱዳን ማቅረብ ወትሮም ከሴራ ዉጭ ምንም ምክነያት አልነበረም ፡፡

ጉባ ወረዳ በመተከል የሚገኝ ከመተከል አዉራጃ አንዱ ወረዳ እና ይህም ለሱዳን በቅርብ ርቀት መገኘት ለሱዳን ምን ያህል ማቅረብ እንደሆነ መረዳት የሚቻል ነዉ ፡፡ በዘመናችን  የስልጣን ቅርምት ሽሚያ  በተለይም በቤንሻንጉል በበርታ እና ጉምዝ ለዓመታት የሚታየዉ ሽኩቻ ከኢትዮጵያዊነት ይልቅ ለሌላ ህዝብ ወግ እና ባህል የመኖር ዝንባሌ እንደነበር የዓመታት ሁነቶችን ወደ ኋላ ከታሪክ እና ነባራዊ ጭብጥ ጋር መመልከት ይቻላል ፡፡

በመተከል የነበሩ የቀደሙ ልማት፣ አገራዊ ቅርስ፣ ነባር ዜጎችን እና ምልክቶችን የማጥፋት የዘመናት ጥረት እና ምኞት ባለፉት ሁለት አስርተ ዓመታት በሰፊዉ ሲሰራበት መቆየቱን ስናይ ሰሚ ያጣ የደም ጩኸት መኖሩ ማሳያዎች ናቸዉ ፡፡

አገር በቀል ወይራ እና እና ዝግባ በመንቀል  የእሾክ አረም የሚተክል የጭቃ እሾህ  ለማጥፋት ወይም እዝማሚያዉ ምን እንደሆነ ዛሬ በአንድነት ለመረዳት እና አረም ለማጥፋት በህብረት ካልቆምን ዓለምያን ያደረቀ፣ ጣናን ያነቀ አረም መተከል እና ዓባይን(ጉባን) ላለመነጠቃችን ምንም ዋስትና አይኖረንም ፡፡

መተከል የጎጃም ፣ ጎጃምም ኢትዮጵያ እና የኢትዮጵያ እምብርት ከሆነ መተከልን ከጎጃም ዕቅፍ ለማዉጣት ከድሮ አስከ ዘንድሮ የኢትዮጵያ ጠላትን የሚያቃዠዉ  ምን እንደሆነ ህዝብ እና መንግስት አሁንም ቢረፍድም ጊዜ አለዉ እና ሊያስብበት ፤ሊመክርበት ይገባል ፡፡

መተከል ኢትዮጵያ እንጅ ሌላ ሆኖ አያዉቅም ሊሆንም አይችልም ጥንታዊት ኢትዮጵያ ሲባሉ አሁን ለሚሉን እና ስለ መተከል ማወቅ ከፈለጉ በዚህ በእኛ ዘመን የተጻፉትን ዋቢ  እጠቅሳለሁ ግን ያማቸዋል ፡፡

 

ዋቢ፡

የህዝብ ዓይን – ፶ ዓለቃ ታደሰ ቴሌ ሰልባኖ

የካድሬዉ ማስታወሻ -ሻምበል ገላነህ አስረስ

 

ማላጅ

“ ምንጊዜም እናte  አገር ”!!

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.