ማሳሰቢያ  ለጠ/ሚ አብይ አህመድ እንዲሁም ሌሎች – ሰርፀ ደስታ

44 ማሳሰቢያ  ለጠ/ሚ አብይ አህመድ እንዲሁም ሌሎች  ሰርፀ ደስታጠ/ሚኒስቴር አብይ አህመድ ዛሬ በመቀሌ ያደረጉትን ንግግር ሰምቻለሁ፡፡ የንግግሩ ይዘት በጥቅሉ መልካም የሚያስብል ሲሆን አንዳንድ ቦታዎች ላይ ግን አሁንም እርምት መወሰድ አለበት እላለሁ፡፡ እንደምሳሌ አማራው ለኦሮሞው ኦሮሞው ለሱማሌው ምናምን እያሉ የተናገሩት ንግግር ስህተት ነው፡፡ ብዙዎች ዛሬ ሚዲያን የሚከታተሉት በደጋፊነትና በተቃዋሚነት ነው፡፡ በመሆኑም ብዙ አደማጭ ሊያስገኝልዎት ይችል ይሆናል፡፡ ነገሮችን በጥልቀት ለሚያስተውል ግን እንዲህ ያለ ንግግር ቢቻል ከዛሬ ጀምሮ እንኳንስ ኢትዮጵያን እመራሉ ከሚል ጠ/ሚኒስቴር ይቅርና ከየትኛውም በፌተደራል ደረጃ ሥልጣን ያለው ሰው ከንግግሮቹ እንዲያስወጣ ቢደረግ እላለሁ፡፡ ሲጀምር አሮሞው ወታደር ለአማራው አማራው ለሱማሌው አይነት ንግግር ለምን አስፈለገ? ሁሉም በኢትዮጵያዊነት ተሰልፈዋል ከተባለ እንዲህ ያለ የዘር ሀረግ ዝርዝር ውስጥ መግባት ምን ያለበት ምን አይችልም ካልሆነ የኢትዮጵያ መከላከያ ይሆናል ተብሎ ተስፋ ለተጣለበት ወታደራዊ ተቋም አባላት መነሳቱ ስህተት ነው፡፡ ይሄ ከወያኔ የተወረሰ እንጂ በታሪክ የኢትዮጵያ ጦር ሠራዊት ዛሬ እርሶ በገለጹበት አይነት ሳይሆን እርስ በእስርስ ወዳጅነቱ በአንዲት እናት አገሩ ኢትዮጵያ ነው፡፡ የወያኔን የውርስ ቃል የውርስ ዘይቤ የውርስ ምልክት የውርስ ማንነትና ሁሉንም ከወያኔ የተወረሱ እርግማኖች በፍጥነት ቢያንስ እንዲህ በአደባባይ በአለመናገር እንዲጠፉ ማድረግ ግድ ይላል፡፡ እርም የሆነውን ነገር ከመካከላችሁ አውጡ እላለሁ፡፡  ይህ ወሳኝ ነገር ነው፡፡

በቃን ኦሮሞ፣ አማራ፣ ትግሬ፣ ሱማሌ መሆኑን እያስታወስን የኢትዮጵያ እያልን ብንደልል አይሆንም፡፡ ኢትዮጵያዊነት በእነዚህ አናሳ የወያኔ የማንነት መስፈርቶች አይለካም፡፡ እኔ በሙያዬ የመለዘር (ጄኔቲክስ) ጥናት ባለሙያ ነኝ፡፡ የኢትዮጵያውያንንም የዘር ግንድ ምንነትና ማንነት ጥንቅቄ አውቃለሁ፡፡ እነዚህ በወያኔና እንደ ኦነግ ባሉ መስል እርግማኖች ወደ ሰው አእምሮ ገብተው ዛሬ ሁሉንም አእምሮውን በክለውት የሚገኙ ማንነቶች ቀደም ባለው ጊዜ ከእሴትነታቸው የዘለለ የጥላቻና ዘረኝነት መገለጫ ባይሆኑም አሁን ላይ ወደ እርግማንነት ተቀይረዋል፡፡  የኢትዮጵያውያንን ማንነት ማወቅ ካስፈለገ ግን ዛሬ ምሁራን ሳይሆኑ አክቲቪስትና ተራ የፌስቡክ አምደኞች ስለሆኑ የሚተነትኑት ለወደፊቱም እንዳንድን እየሆነ ነው፡፡ በሚኒሰቴር ደረጃ አለው የሚለው የሰላም የተባለው ሚኒስቴርም በልዩ ሁኔታ የተዘጋጁ ሕዝብን ወደ አንድነትና መፈቃቀር የሚመልሱ ዝግጅቶችን በባለሙያዎች በመታገዝ ቢያንስ በመንግስት ሚዲያዎች በስፋት ከማሰራጨት ይልቅ ይሄው ጭራሽ ይሄ ሚኒስቴር ከተቋቋመ ጊዜ በኋላ የባሰ የጥላቻና ዘረኝነት ስብከቶች ገዝፈው ሕዝብ አብሮ ወደማይኖርበት ደረጃ ደርሶ አይተንው የማናውቀው አረመኔያዊነት ተስፋፍቶ እናያለን፡፡ አሁንም ይታሰብበት ሚኒስቴር ሆነ ሲባል ከጅምሩ እኔ አላስፈላጊ እንደሆነ ጠቅሼ ነበር፡፡  ምክነያቴ እንዲህ ያለ ድሪቶ ሳይሆን የሚያስፈልገው ቁርጠኛ የሆነ የፍትህ፣ የሕግ ማስከበርና ደህንነት ተቋማቱን ማጠናክር ነበር፡፡ ሆኖም በአለፉት ሁለት ና ከግማሽ ዓመታት ሆኖ ያየንው የባሰ ወሮበላነት ነው፡፡ አዝናለሁ፡፡  ጉዳዩ ከትግሬ ወያኔ ወደ ኦሮሞ ኦነጋውያን ተተካ፡፡ እዚህ ላይ ምንም አይነት ማስተባበያ መሥጠት አያስፈልግም ነበር፡፡ የአዲስ አበባን የመንግስት፣ የፍትህና ሌሎች ተቋማትን ሳይቀር ከትግሬ ወያኔዎች በኦነጋወያን ኦፒዲ ተክቶ አገር እመራለሁ በሚል ቀልድ የተጀመረው ሂደት የት ከማይካድራው ባልተናነሰ ለአዲስ አበባ ቅርብ በሆኑት የዝዋይና ሻሸመኔ ከተሞች አይተናል፡፡ ወያኔ ሁሉንም በትግሬነት ስታግበሰብስ እንደነበር በኦሮሞነት በወያኔም ከሰማናቸው በላይ ዝርፊያና ወሮበላነት አይተናል፡፡ ይሄን የተቃወሙ  ሰዎችም የደረሰባቸውን አይተናል፡፡ እንግዲህ እርምት ይደረጋል ከተባለ ዛሬ ሆኖ ማየት እንፈልጋለን፡፡

131029120 10220751495351959 5336264190163105399 n ማሳሰቢያ  ለጠ/ሚ አብይ አህመድ እንዲሁም ሌሎች  ሰርፀ ደስታለመሆኑ ግን እስክንድር ነጋና ጓደኞቹ ለምን ታሰሩ? በሐጫሉ ግድያ? እነእስክንድር ሲናገሯቸው ከነበረው በኦሮሞነት አዲስ አበባ ላይ ሆነ ካሉት ነገር የቱ ነው ውሸት? ይህን ዛሬ ሁሉም በይፋ የሚያውቀውን እውነት ለምን ተናገርክ በሚል አደለም እስክንድርና ጓደኞቹ የታሰሩት? እስኪ የፌደራሉን ጨምሮ አዲስ አበባ ውስጥ የሉ ተቋማት ምን ይመስላሉ? ዳውን ዳውን ኢትዮጵያ እያሉ በዓለም ዙሪያ የሚጮሁት ኦሮሞ ኦነጋውያን አደለሙ ሆን ተብሎ የተሰየሙባቸው? ጤነኛ  (ኢትዮጵያዊ) ኦሮሞ እንኳን  ምን ያህል ይሆናል እንኳንስ ሌላው?  ስልት እንኳን መቀየር ያባት ነው፡፡ እንደወረደ ተበልቶ ያለቀበትን የወያኔን ስልት ዛሬም በኦሮሞ ኦነግ/ኦፒዲ ተተክቶ አይተናል፡፡ ጥምቀትና መስቀል አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ጥለት ያለው ልብስ አትለብሱም እያለ ሕዝብን በክብረ በዓላቶች የሚያውክ ወሮበላ ሠላም አስከባሪ በሚል መሣሪያ ተሰጥቶት ያሰማራው ማን ነው? በኦሮሚያ ልዩ ኃይል በሚል ሲሰለጥን የነበረው እውን ለሰላም ማስከበር ነበር? ከወያኔ የተወረሰን የኦነግ/ኦፒዲን የጥላቻና ዘረኝነት ከዘረፋ ጋር ለማስከበር አደለም? ስብሐት ነጋን በአባዱላ ተክቶ እንደወረደ የወያኔን ግልባጭ አደለም እየተሰራ ያለው? ጠ/ሚኒስቴሩ በቀጥታ ሰዎችን በሚሾሙባቸውስ መስሪያ ቤቶች ሆን ተብሎ ኦሮሞነት አልተሸመም? ደጋግሜ አንስቼዋለሁ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን መጥቀስ በቂ ነው፡፡ ይሄን ተቋም ደጋግሜ የምጠቅሰው ከገንዘብ ኪሳራውና ዘረፋው በላይ ለአሸባሪዎች ዋና የገንዘብ መተላለፊያ እንደሆነ ስለሚሰማኝ ነው፡፡ በዘረፋ መልክ ለኦነግ  በተደጋጋሚ ገንዘብ ተላልፎ እንደተሰጠ እናውቃለን፡፡

ጉዱ ብዙ ነው፡፡ ሆኖም ለምልክት ከላይ የተቀስኳቸው ጉዳዮች እንዲህ አይን አፍጠው እያየናቸው በየትኛውም መለኪያ አመኔታ ይኖረኛል ብለው ካሰቡ አዝናለሁ፡፡ ኦሮሞ ቁጥሩ ብዙ ነው የሚለውም ሂሳብ ውስጥ ገብቶ ከሆነ አዝናለሁ፡፡ ጉዳዩ የቁጥር ጉዳይም አደለምና፡፡ በአለፉት ሁለትና ከመንፈቅ ዓመታት ብዙ አስከፊ ዘረኝነትና አረመኔነት አይተናል፡፡ በወያኔም ሲሳበቡ የነበሩ አሉ፡፡ ዛሬ ወያኔን ሰበብ ማድረግ አይቻልም፡፡ ድሮም ለሆነው ሁሉ ወያኔ ሰጠቀስ ይገርመኝ ነበር፡፡ በይፋ ስልጣን ላይ ያሉት መሪ ነን የሚሉት እኮ ናቸው የጥላቻና ዘረኝነቱ ዋና ተዋናይ፡፡ የኦሮሞ ባለስልጣናት አእምሯቸው ዛሬ ወያኔን ሊዘልፉ በመድፈሩ አዝናለሁ፡፡ ከወያኔ የባሰ አረመኔነትን አውቅባቸዋለሁና፡፡ አሮሞን ሁሉ የንግድ እቃ አድርገው ዛሬም ስለ ነጻነት ያወሩለታል፡፡ ጨቋኝ የተባለው አማራ ገዥ ነበር የተባለበትን ዘመን (ያም የውሸት ትርክት እንዳለ ሆኖ) ላሰበ ዛሬ 50 ዓመት እየሆነው ነው፡፡ እንግዲህ በ50 ዓመቱም የኦሮሞ ሕዝ ጥያቄ እያሉት ሕዝቡን ከቀን ወደ ቀን በእነሱ የአስተሳሰብ ባርነት እየከተቱት ዛሬ ላይ ብዙ ሕዝብ ድሮ የነበረውን ነጻነት አጥቶ በጥላቻና ዘረኝነት ባርነት ወድቆ የኦሮሞ ወሮበላ ባለስልጣኖች መነገጃ ሆኗል፡፡  መሬቱ ተነጠቀ፣ ተፈናቀለ ምናምን ብለው ሲጮሁ ይገርመኛል፡፡ ለምሳሌ አዲስ አበበባ እንበልና ወያኔ አፈናቀለች ተብሎ ይታሰብ ለመሆኑ የኦሮሞን (ኦሮሞም ላይሆን ይችላል) ገበሬ ቡራዩን ጨምሮ ከኢስ አበባ ዙሪያ ካሉ ከተሞች ሲያፈናቅል የነበረው ማን ነው? ገበሬውን እያፈናቀል መሬቱን ሲሸጥ የነበረው ማን ነው? ትግሬ ወያኔ ወይስ ኦፒዲ ኦሮሞ? የሚገርመኝ ነገር ግን እዚህ ውስጥ ምነም የሌለበት አማራ ነው ዛሬም ኦሮሞን እንደሚጨቁን እየተነገረ የኦሮሞ አእምሮ የመረቀዘ ጥላቻ ባርነት ውስጥ እየገባ ያለው፡፡  አዝናለሁ! ኦሮሞን ገደሉት ዘረፉት የተባሉትን ወያኔዎችማ ይሄው ባለፈው ሁለትና ከመንፈቅ ዓመት መቀሌ ድረስ እየሄዱ ስሳለሙ አይተናል፡፡ የጋራ ጠላት ባሉት አማራ ላይ ግን ወራዳ በሆነ አእምሮ አንድ ሆነዋል፡፡  አዝናለሁ፡፡

ለጠ/ሚኒስቴሩ ዛሬም በቁማር ያዋጣል ብለው ካሰቡ አዝናለሁ፡፡ አያዋጣም፡፡ እስከዛሬ ቢዙ ሰበቦች ነበሩ፡፡ አሁን ግን ሰበብ የሚሆን ያለ አይመስለኝም፡፡ ዛሬ ቀድሞውንም በኢትዮጵያ ጥላቻና በዘረኝነት ከመረቀዙ ኦነጋውያን (ኦፒዲ ባለዝልጣናትን ጨምሮ)ና የወያኔ ቅሪቶች ካልሆነ ኢትዮጵያውያን ሁሉ አንድ ሆነዋል፡፡ በዚህ አጋጣሚ ወያኔን በመፋለም የአማራና አፋር ክልሎች ወያኔ ርስቴ በሚላት ትግራይ አዋሳኝ በመሆናቸው በቀጥተኛ ሚናቸው የሚደነቅ አስተዋጽዖ ሲኖራቸው የሱማሌ መስተዳደርና ባለስልጣናቱ እንዲሁም ምሁራኖች ወያኔን በመዋጋት ጥረት ከኋላ ያሳዩት ደጀንነት የሚደነቅ ነው፡፡ የክልሉን አስተዳዳሪ ሙስጠፌንና ጓደኞቹን ማድነቅ እፈልጋለሁ፡፡ በአጭር ጊዜ ውስጥ በክልሉ ከነበረው የለየለት ወሮበላነት ዛሬ ወደምናየው የሰከነ ሰላማዊነት የተቀየረበት እውነትም ከእነዚሁ ኃላፊነት ከሚሰማቸው የሕዝብ ልጆች የሚመነጭ በጎ ሐሳብና ተግባር እንደሆነ አይተናል፡፡ ይሄ እውነት የአሳዳጊያቸው የወያኔን ሞት ውስጥ ውስጡን እያቃጠላቸው ካሉትና አሁንም የወያኔን ሥርዓት ካላስቀጠልን ብለው ከሚያላዝኑት የኦሮሚያ ባለስልጣናት በተቃራኒ ነው፡፡

በመጨረሻም አደባባይ ሚዲያ የወያኔንና የናዚን አረመኔነት በማመሳሰል የበላይነት ስሜት ሲል ሲተነትን ሰምቼ የተንታኝ ነን ያሉትን አስተያየት ግድፈት ለመጠቆም ወደድኩ፡፡ ሲጀምር ናዚም ሆነ ወያኔ ችግራቸው የበታችነት እንጂ የበላይነት ስሜት አደለም፡፡ ናዚ ጀርመኖች የአርያን ዘር ነን ያለው ጀርመኖች በተለይ ናዚዎቹ የወጡበት በብዙዎች ዘንድ ስለሚናቁ ለብዙ ዘመንም ከሌላ ቦታ በሚመጡ ነገስታት ስለሚገዙ ያንን የበታችነት ስሜታቸውን ለማከም ሲሉ ነበር ራሳቸውን ከምርቱ የአርያን ዘር ነን በማለት የተነሱት፡፡ እርግጥ ነው የአርያን ዘር በምድራችን የተባረከና የተቀደሰ ዘር እንዲሁም ውቦች ናቸው፡፡ እኔ ይሄን የማውቀው ስለናዚ ሳይሆን ስለ መጻፈ ቅዱስ ከሚያውቀው ፈላስፋው አባቴ ገና በሕጻንነቴ ነው፡፡ የጌታ እናት እመቤታችን ማርያም ከዚህ ዘር እንደሆነች ይነገራል፡፡ ይሄን ዘር ለመሆን ብዙዎ ስለሚመኙትም ነው ናዚ የመናቀቸውን መጠን ለማካካስ የዚህ ዘር ነን ያሉት፡፡ ከእነሱ ይልቅ አይሁዶች የአርያን ዘሮች ናቸው፡፡  አርያን በመጽሐፍ ቅዱስ የቱ ጋር እንዳለ አላስታውስም ግን ይሄ እውነት የሚገናኘው ከእስራኤላውያኖቹ እንጂ ከጀርመኖቹ አደለም፡፡ በኤቦር እብራውያን እንደሚባሉት ከእነሱ ውስጥ አርያን የሚባሉ አሉ፡፡ እንግዲህ እውነታው ደግሞ እኛ ኢትዮጵያውያንም ከዚህ ዘር ድርሻ አለን፡፡  ዛሬ ዘመናዊ ሳይንስ ኢትዮጵያውያን በእርግጥም ከእነሰሎሞን ዘሮች ደም እንዳላቸው ያረጋግጣል፡፡ የአርያን ዘር የሚባለው ደግሞ የጌታ እናት ዘር የሆነው የዳዊትን ዘር ጭምሮ ነው፡፡

ወደ ወያኔ ስመጣ የሚገርመው ከቤተሰቦቻቸው ጀምሮ በባንዳነት በግልጽ የሚታወቁ ሲሆኑ በባንዳነታቸው በቀደሙ የኢትዮጵያ አርበኞች ሲሸማቀቁ ከነበሩ የተወለዱ ናቸው፡፡ ለምሳሌ የመለስ ሚስት አዜብ መስፍን አያቷ የሞቱት በባንዳነት ሲያገለግሉ በነበረበት ወቅት በአንድ የጎንደር አርበኛ ነው፡፡ ለእነዚህ ሰዎች ኢትዮጵያ ውስጥ ሲኖሩ እየተሸማቀቁ ነበር፡፡ ዛሬ አማራና ኦርቶዶክስ ላይ ልዩ የጥላቻ ዘመቻ የመካሄዳቸው ሚስጢርም የሚቀዳው በባንዳነት ቤተሰቦቻቸው ሲያገለግሉት ከነበረ የጣሊያን ምክር ነው፡፡ የትግሬን የበላይነት ከመጠን በላይ የሚሰብኩትም በአካባቢው እነሱ የእኛ የሚሉት ትግሬ እንደ እውነቱ የበላይነት ኖሮት ስለማያውቅ ነው፡፡ ይልቁንም በሰሜኑ ሐማሴን በደቡቡ ጎንደሬዎች (ከተከዜ ወዲህ ማዶ ያሉት ሁሉ) እነሱ የወጡበትን ትግሬን ይንቃሉ ተብሎ ስለሚነገር ያን የበታችነት ስሜታቸውን ያስቀሩ እየመሰላቸው ነበር ትግሬን ሥሙን ወደ ትግራዋይ ከዛም ተጋሩ ምናምን በሚል በመቀየር ከአቅም በላይ የሆነ ድንፋታን ያበዙት፡፡ በእርግጥም በሰሜኖቹ ሐማሴኖችም ይሁን በጎንደሬዎቹ ወያኔዎች የወጡበት አጋሜ በሚል በማይወደድ ሥም ይጠሩ እንደነበር እንታዘባለን፡፡ አጋሜ ማለት ምን ማለት እንደሆና ባላውቅም ጥሩ አይመስለኝም፡፡ የሆነ ሆኖ እውነቱ ታላቁ መጻፍ እንደሚለው ነው፡፡ የባርነት መንፈስ ክፉ ነው፡፡ የአረመኔነታቸውም ምክነያት በእርግጥም የበታችነት ስሜታቸው መጠን መገለጫ እንጂ የበላይነት የሚያሳይ አደለም፡፡ ከትግራይ ጀግኖች ነበሩ እነሱ ግን አንድ በአንድ ተመንጥረዋል፡፡ ፈሪዎችና እጅግ አረመኔዎች ስለሆኑ ወዳጅ በመምሰል ነው ጀግኖቹን የጨረሷቸው፡፡ ባሕሪያቸውን ዛሬ በመከላከያ በፈጸሙት ድርጊት ማየት በቂ ነው፡፡ አብረው በወንድማማችነት ቆመው ማረድ ልዩ መገለጫቸው ነው፡፡ ከድሮ ጀምሮ በዚህ ማንነታቸው ይታወቃሉ፡፡ ይሄ የፈሪነታቸውና፣ የበታችነት ማንነታቸውን የሚያንጸባርቅ እንጂ በየትኛውም መለኪያ የበላይነት ምልክት አደለም፡፡ ስለዚህ አደባባይ ሚዲያ ላይ ወያኔ ከመጠን በላይ የበላይነት ስሜት ተለክፈው ነበር የሚለው ስህተት ነው፡፡ ወያኔም ናዚም ችግራቸው የበታችነት እንጂ የበላይነት አደለም፡፡  ይሄን ሚዲያው በተሳሳተ ትንታኔ የተሳሳተ አስተሳሰብ እንዳያመጣ እንጂ መናገር የምፈልገው ጉዳይ አልነበርም

ቅዱስ እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ! አሜን!

ሰርፀ ደስታ

 

4 Comments

 1. “እኔ በሙያዬ የመለዘር (ጄኔቲክስ) ጥናት ባለሙያ ነኝ፡፡”
  How many journal articles have you published? What have you contributed to Ethiopia’s development with this knowledge? just curious, and I would appreciate if you can put the reference link in the reply section. Thank you!

 2. ትግሬዎች እጅግ የበታችነት ስሜት ይሰማቸው እንደነበር እኔ እራሴ በ መሥሪያ ቤቴ የታዘብኩትን ልግለጽ። ጊዜው 1966 – 1967 ዓ.ም. ነበር። በ ዩኒቨርሲቲ አገልግሎት እርሻ ሚኒስቴር ውስጥ አክሱም እና አድዋ ቅርንጫፍ ተመድቤ ስሠራ ትግሬዎች እና ኤርትራውያን አብረውኝ ይሠሩ ነበር። ታዲያ ኤርትራውያኖቹ ትግሬዎቹን በ ትግሪኛ አነጋገራቸው በጣም ይስቁባቸውና ይዘልፏቸው ነበር። ደረቅ እና ለዛቢስ ትግሪኛ ነው የምትናገሩት እያሉ ይዘልፏቸው ነበር። በ እርግጥ የበታችነት ስሜት ይሰማቸው ነበር። በዚያም ላይ ኤርትራውያኖቹ በ ጣልያን ተገዝተው ስለነበር በጣም ሥልጡን ነን ብለው ይኩራሩ ነበር። ስለዚህ ነበር እንደ ኤርትራውያን እነሱም ኢትዮጵያውያንን አህያ ማለት እና መናቅ የጀመሩት። ከ በታችነት በ መነጨ እብሪት በ ህባችን ለ 27 አመታት የፈጀ ግፍ ፈጸሙብን። በ መጨረሻም እግዚአብሔር ፍርዱን ሰጣቸው።
  ሌሎችም ከ እነሱ ሊማሩ ይገባል። ይዋል ይደር እንጂ ፈጣሪ ይፈርዳልና።

 3. በመቀሌ ጠ/ሚ አብይ አህመድ የተናገሩት “አማራው ወታደር ለኦሮሞው አማራው ለሶማሌው” ምናምን አይነት ንግግር የትግራይ እና የአማራ ክልል ልዩ ኃይሎች ተዋህደው ሀለቱ ክልሎች አንድ ክልል ለመሆን በቅርቡ ያሳዩትን ተነሳሽነት ያላበረታታ ንግግር ነበር።

  በአሁኑ ጊዜ መቀሌ መስማት ፈልጋ የነበረው አንድነትን ነበር እንጂ የብሄር ቆጠራ ለመስማትማ ወያኔ አለ።

  የሀገሪቱ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ የሁለቱ ክልሎች ልዩ ኃይሎች ተዋህደው በአንድ የክልል መንግስት አስተዳደር ሊተዳደሩ የአማራ እና የትግራይ ክልሎቹ ነዋሪዎች መምከራቸውን ሊደግፍ ቀርቶ እራሱ የመከላከያ ወታደሮቹን ሲያዘምት የዘማች ወታደርን ዘር እየገመገመ መሆኑ አስተዛዝቦናል።

  ለመከላከያ ወታደርነት ማመልከቻ ላይ የዘር ብሔር መስፈርት ጥያቄ መጠየቅ ሀገሪቱን እየጎዳ በመሆኑ ብሔር መጠየቅ ሊወገድ ይገባዋል።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.