በሀገር ክህደት እና የሀገር መከላከያና የፌደራል ፖሊስ አባላትን በማሳገት የተጠረጠሩ ከፍተኛ የቀድሞ የኢትዮጵያ አየር ሃይል፣ የሀገር መከላከያና የፖሊስ አመራሮች ላይ የመያዣ ትዕዛዝ ወጣ

በሀገር ክህደት እና የሀገር መከላከያና የፌዴራል ፖሊስ አባላትን በማሳገት የተጠረጠሩ ከፍተኛ የቀድሞ የኢትዮጵያ አየር ሃይል፣ የሀገር መከላከያና የፖሊስ አመራሮች ላይ የመያዣ ትዕዛዝ መውጣቱን የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
ከመንግስት እና ህዝብ የተጣለባቸውን ከባድ ኃላፊነት ወደ ጐን በመተው መቀመጫቸውን ትግራይ ክልል ካደረጉ ፀረ-ሠላም እና ፀረ-ህዝብ የህዋሃት ከፍተኛ አመራሮች ተልዕኮ መቀበላቸውን ነው ኮሚሽኑ የገለጸው፡፡
4544የመያዣ ትዕዛዝ የወጣባቸው ጥቅምት 24 በሀገር መከላከያ ሰራዊትና በፌዴራል ፖሊስ አባላት ላይ የተካሄደውን የእገታ ተግባር እንደመሩና እንዳስተባበሩ በምርመራ የተደረሰባቸው 40 የከዱና በጡረታ የተገለሉ የኢትዮጵያ አየር ሃይል፣ የሀገር መከላከያና የፌዴራል ፖሊስ ተጠርጣሪ አመራሮች ላይ መሆኑን ኮሚሽኑ ገልጿል።
በዚህም መሰረት ሜጀር ጀነራል ፃድቃን ገ/ትንሳኤ ፣ኮሎኔል በርሄ ወልደ ሚካኤል ገብሩ፣ኮሚሽነር ይህደጎ ስዩም ወልደማርያም ጨምሮ 40 የኢትዮጵያ አየር ሃይል፣ የሀገር መከላከያና የፌዴራል ፖሊስ ተጠርጣሪ አመራሮች ላይ የመያዣ ትዕዛዝ ወጥቶባቸዋል።
በመሆኑም መላው የሃገሪቱ ህዝብ በተለይም ደግሞ ሰላም ወዳዱ የትግራይ ህዝብ፣ የሀገር መከላከያ ሰራዊት፤ የአገራችን የፖሊስ ሰራዊትና የደህንነት ተቋማት እነዚህን የጁንታው ህዋሃት ጥፋት ቡድን አባላት አድኖ ለህግ ለማቅረብ እየተደረገ ባለው ጥረት ህብረተሰቡ የድርሻውን እንዲወጣ ኮሚሽኑ ጥሪ አቅርቧል፡፡
በቀጣይም መቐለ ከተማ የገባው የኮማንዶና የወንጀል ምርመራ ቡድን በሚያደርገው አሰሳና ኦፕሬሽን የሚገኙ ውጤቶችን እየተከታተለ በመገናኛ ብዙሃን በኩል ለህብረተሰቡ ይፋ የሚያደርግ መሆኑን ገልጿል፡፡
FBC

1 Comment

  1. Question: Should there be forced heavy labor in the current Ethiopia’s prison system or are the tax payers expected to pay it all for the Juntas quarantine health , room , legal and board expenses if or when, all the Juntas are captured?

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.