ደስታችን ገደብ ይኑረው፤ ጦርነቱ አሁንም አልተገባደደም! – ይነጋል በላቸው

Amhara 7ሕወሓትን ማጥፋት እንደዚህ ቀላል የሆነበትን ምክንያት መመርመር አስፈላጊ ነው፡፡ ወያኔ ግማሽ ምዕተ ዓመት ለሚጠጋ ረጂም ዘመን የገነባው የጦር ኃይልና የመሣሪያ ጋጋታ እንዲሁም ምሽግና የመሬት ውስጥ ለውስጥ ዋሻ አንድ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ እንኩቶ የሆነበትን ምክንያት መርምሮ ማወቅ ከተደጋጋሚ ውድቀትና ሽንፈት ይታደጋል፡፡ አሸናፊው እውነትና ወኔ እንዲሁም ጊዜ እንጂ የመሣሪያና የወታደር ብዛት እንዳልሆነ ማወቅ ጠቀሜታው እጅግ የጎላ ነው፡፡ እኔ በበኩሌ እንደ አንድ አንጋፋ ዜጋ የሚሰማኝን ከአሁን በፊትም ሆነ አሁን እናገራለሁ፡፡ እኔና መሰሎቼ ባለፉት 30 ዓመታት ውስጥ አስቀድመን ተናግረን በኋላ ላይ በተግባር የተከሰተውን “የትንቢት” ቃል ሁሉ አንድ በአንድ ከነተጻፈበት ዓመት ለትውስታ ያህል ጊዜው ሲደርስ መዘከራችን አይቀርም – ለዚያ ይበለን፡፡

ሰሞነኛ ወሬዎች ብዙ ናቸው – የቱ ተነስቶ የቱ እንደሚጣል ማወቅ እስኪቸግረን ድረስ በሀገራችን ብዙ ነገር በየቀኑ በሚባል ሁኔታ እየተከሰተ አግራሞታችንን ሲያንረው ይታያል፡ ሁሉን መናገር ያስቸግራል፤ ከተለያዩ ምክንያቶች አንጻርም ሁሉንም ነገር ዘርግፎ መናገርም እንደዚሁ አስቸጋሪ ነው፡፡ ግን ሊነገሩ ከሚችሉ ውስጥ አንኳር አንኳሮችን መጥቀስ መጥፎ አይደለም፡፡

ወያኔ በፖለቲካም በጦርነትም ተሸንፏል፡፡ የተሸነፈ ኃይል መንፈራገጡ አይቀርምና በተለያዩ ግልጽና ድብቅ ሥፍራዎች የወያኔው ርዝራዘዦች ለተወሰነ ጊዜ መስዋዕትነትን ማስከፈላቸው አይቀርም፡፡ ወደ ሱዳን የሄደ ኃይላቸውም ከውጪ ጠላቶቻችን ሁሉን አቀፍ የገንዘብና የጦር መሣሪያ ድጋፍና ዕርዳታ በመታገዝ ችግር መፍጠራቸው የሚጠበቅ ነው፡፡ የኢትዮጵያን የማይቀር ትንሣኤ ግን ሊያደናቅፍ የሚችል ምድራዊ ኃይል የለም፡፡ ይህ ተብሎለት ተብሎለት ያለቀ ወርቃማ ዘመን ሊብት መሆኑ ደግሞ በጣም ግልጽ ነው – አንድዬ የተመሰገነ ይሁን ከዋሻው ጫፍ ደርሰናል፡፡ የብርሃን ጭላንጭሉም መታየት ጀምሯል፡፡

እነ ታዬ ደንደኣ ቢጠነቀቁ ይሻላቸዋል፡፡ በሽሮና በጎመን ጥጋብ የሚደነፉ ሁሉ አደብ ቢገዙ የራሳቸውን ታሪክ ከማበላሸት ይቆጠባሉ፤ ደግሞም ለማያውቃቸው ይታጠኑ፡፡ በኢትዮጵያ ታሪክ አንዱ ነገድ ተለይቶ አንድን ጦርነት ያሸነፈበት አጋጣሚ አልተመዘገበም፤ ሁሉም በኅብረት ሆኖ ነው የውጪውንም ሆነ የሀገር ውስጡን የከሃዲዎች ጦርነት ድባቅ ሲመታ የኖረው፡፡ ጀግንነትና ፍርሀት ደግሞ ግለሰብኣዊ እንጂ ቡድናዊና ነገዳዊ ወይም ጎሣዊ የኮታ ቅርጫ የለውምና ከዚህ ዓይነት የተሳሳተ ግንዛቤ በአፋጣኝ እንውጣ፡፡ እርግጥ ነው – ብዙ የተበደለና የተገፋ ወገን ብሶት የሚወልደው ብርታትና ኃይል ስለሚኖረው የተለዬ በሚመስል ጀግንነትና ወኔ ጠላቱን የማንበርከክ ልማድ በየትም ሀገር የነበረና ያለ በመሆኑ ይህን እውነት ልብ ማለት ክፋት የለውም፡፡ ለማንኛውም ጎሣና ነገዱ ምንም ይሁን ምን ኢትዮጵዊነትን የያዘ ኃይል አሸናፊ ስለመሆኑ ታሪካችን ኅያው ምሥክር ነውና ወፍ ዘራሾች አንደበታቸውንም ብዕራቸውንም አደብ ቢያስገዙ የመጀመሪያዎቹ ተጠቃሚዎች ራሳቸው ናቸው – ለምሣሌ በሁሉም ተሣትፎ የተሸነፈውን ወያኔ “በኛ የአመራርና የውጊያ ብቃት ነው የተሸነፈው” በሚል ዕብሪት አገር ይያዝልኝ ማለት ትልቅ ነውርና የጮርቃነት ውጤት ነው – የታሪክና የድል ሽሚያ ውስጥ ገብቶ መነታረክ ዓላማን መዘንጋትና ለቀጣይ ወያኔነት ራስን እንደማዘጋጀት የሚቆጠር ግብዝነት ነው፡፡ አክራሪዎች የዱባ ጥጋብ ካለስንቅ ማዘመቱን ተረድተው ረጋ ይበሉ፡፡ ሀብትና ገንዘቡንም፣ ሥልጣኑንም፣ መሬቱንም … ሁሉንም ጠቅልለው መያዛቸውን ይግፉበት (መቼስ ማልጎደኔ!) – እንደወያኔ ግን ግድያና እሥሩን ይተውት፤ በፍጹም አይጠቅማቸውም፡፡ አላበሳቸው ያሰሯቸውን የኅሊና እስረኞችም በአስቸኳይ ይፍቱ – ዕድሜያቸውን ክፉኛ የሚያሳጥር ጽላሎት በዲያቢሎሣዊው አክሊላቸው ላይ ወድቆ ይታየኛልና ንጹሓንን ማሰርና መግደል እንደማይጠቅማቸው የምትቀርቧቸው ምከሯቸው፡፡ ወያኔን መኮረጅ የተማሪውን ደብተር ስታበላሽ የነበረችውንና ተማሪው በደንደሱ በኩል አንገቱን ገዝግዞ ያስቀመጠውን ቢላዎ አንስታ በስለቱ በኩል ማንቁርቷን በጥሳ እራሷን እንደገደለችው ሞኝ ጦጣ መሆን ነው፡፡ ዛሬ ቤተ መንግሥቱ በኦነግ/ኦህዲድ ቁጥጥር ሥር ሆኖ አክራሪ ኦሮሞ በኦነጋዊ የኬኛ ፖለቲካው ቢፈነጭበትም ይህ ሁኔታ እንዳለ ይቀጥላል ማለት እንዳልሆነ ግልጽ ሊሆን ይገባል – ተጠየቁ እኮ ቀላል ነው፡- የደርግን መጨረሻ ማስታወስ ነው፤ የወያኔን መጨረሻ ማየት ነው፤ በሌሎች የዓለም ሀገራት ያሉና የነበሩ አምባገነኖችን የመጨረሻ ዕጣ ፋንታ ማስታወስ ነው – የኅዋ ሣይንስ ምርምርን የሚጠይቅ አይደለም ነገሩ፡፡ ከዚህ ከዚህ አለመማር ድፍን ቅልነት ነው፡፡ የሆድ ዘመን እየጨለመበት፣ የኅሊና ዘመን እየፈካና እየጎመራ የሚሄድበት ወቅት ላይ ነን፡፡ ሆድ ውስጥ ወርዶ የተሸጎጠው ኅሊና ወደመደበኛ ሥፍራው ወደ ጭንቅላት መውጣቱ የጊዜ ጉዳይ እንጂ መቼም ቢሆን አይቀርም፡፡ ከሁኔታዎች መገንዘብ እንደምንችለው ይህ የማይቀር ሂደት የጀመረም ይመስላል፡፡ አሽከር ሲያመር ገድሎ ይጠፋል፤ ውሻ ሆድ ብሶት ጌታውን ሲከዳ ቢችል ጌታውን ነክሶ ከግቢ ይጠፋል፡፡ በቅሎ ሲመራት ጌታዋን ጥላ በእግሯ ትረመርመውና ትገድለዋለች፤ ሆድ ለኅሊና ቦታውን የሚለቅበት ጊዜ አለ፤ አዲስ ነገር እየተናገርኩ አይደለም፡፡ እናም መቀናጆውን ብአዴንን የከዳው ኦህዲድ ጌታውንና ጓደኛውን እንደከዳ ሁሉ ሌላ ታሪክ ሊፈጠር እንደሚችልም መዘንጋት አይገባም፡፡ ጊዜ መስታወት ነው፤ ገና ብዙ ነገር እናያለን፡፡

ስለዚህ በተረኝነት ስካር የምትናውዙ አክራሪ ኦሮሞዎች ይህን አቅለቢስ መንታላ(busiest) ልጅ እየተጠቀማችሁ ሕዝብን ከሕዝብ ለማናከስ አትፍጨርጨሩ፤ ልጁ እርግጥ ነው ላይ ላዩን ሲታይ ደህና ይመስላል፤ በዚህም ሳቢያ “የተመረጡትን” ሳይቀር አነሁልሏል – ውስጡ ግን ልዝብ ሰይጣን መሆኑ በጓደኞቹ ማንነት መታወቁ አልቀረም (የሽመልስ አብዲሣ የዓላማና የፍላጎት ባልደረባ ሆኖ ኢትዮጵያን ይወዳል ቢባል በትንሹ ድንቁርና ነው፤ ብዙዎችን በፍቅሩ የሚያጃጅልበት አንዳች ምትሃታዊ ነገር ሳይኖረው አይቀርም (ይባልማል))፡፡

ለማንኛውም የአሁን ተረኞች ሆይ! ኢትዮጵያ የትግሬ፣ የኦሮሞና የአማራ ብቻ እንዳልሆነች ወዳችሁ ሣይሆን ተገዳችሁ በቅርብ የምትረዱበት ጊዜ ይመጣል፡፡ ከአንድ ሚሊዮን ያላነሰ ሥልጡን ጦርና ለብዙዎች ዓመታት የሚያዋጋ ስንቅና ትጥቅ እንዳለው የሚገመተው ሕወሓት በቀናት ፍልሚያ የማሽላ እንጀራ ሆኖ መፍረክረኩ ልቦና ላለው ሰው ትልቅ ትምህርት በሆነው ነበር፡፡ ግን ትዕቢትና ዕብሪት ሁለመናን ያሣውራሉና ብዙዎች ማሰቢያቸውን  ላልባሌ ፍላጎታቸው አዋሉት፡፡ በዚያም ምክንያት ይሄውና አቢይን የተማመነው አክራሪ የኦሮሞ ኃይል በቤንሻንጉልና በሌሎች በርካታ አካባቢዎች አማራን ማረዱን ቀጥሏል፡፡ በተለይ ሽመልስ አብዲሣ የተባለው ፀረ-አማራ ግለሰብ አማራን ያሳረደውን የቤንሻንጉል ጉሙዝ ፕሬዝደንት ጠርቶ ኬክ ሲያስቆርስ ማየት የዘመኑ ታላቅ የትራጂ-ኮሜዲ ተውኔት ነው፡፡ ይህ እየሆነ ያለው ደግሞ በአቢይ አስተዳደር ሥር ነው፡፡ የአቢይንና እርሱ የሚወክለውን የኦነግ/ኦህዲድን መሠረታዊ ፍላጎትና ዓላማ ቁልጭ አድርጎ የሚያሣይ ድርጊት ነው ይህ በዚህ ኅብረትንና አንድነትን በሚሻ አደገኛ ወቅት በድፍረት የተከናወነ የኬክ ቆረሣ ድራማ፡፡  ያሳዝናል፡፡ አማራ ብዙ የቤት ሥራ እንዳለበት አመላካች የሆኑ ወቅታዊ ሁኔታዎችን መርሣት ብዙ ዋጋ እንደሚያስከፍል መረዳት ተገቢ ነው፡፡ ጥጋብ መጥፎ መሆኑን አሁን ይበልጥ ተረዳሁ፡፡ ጥጋብ ጊዜን አይመርጥም፤ ጥጋብ ዐይንንና ጆሮን ይጋርዳል፡፡ ጥጋብ ልብን ይደፍናል፡፡ “ከተራበ ለጠገበ አዝናለሁ” መባሉም ለዚህ መሆን አለበት፡፡

ጦርነቱ እንደተጀመረ እንጂ እንዳላለቀ በርዕሴ ጠቁሜያለሁ፡፡ አዎ፣ ከወያኔ ጋር የተጀመረው ጦርነት ገና ተጀመረ እንጂ አላለቀም፡፡ የወያኔ አባላት የሆኑ ሁሉ “ምነው ወያኔ አርገህ ፈጠርከኝ!” በሚል ፈጣሪያቸውን በጠማማ አንጎላቸው ፊት የሚከሱበት ዘመን በቅርብ ይመጣል፡፡ ወያኔዎች የሠሩት ግፍና በደል እንዲህ በቀላሉ ታጥቦ የሚጸዳ አይደለምና ብዙ የደም ጎርፍ ይጠብቀናል፡፡ በቀላል ደስታ ተውጠው በትናንሽ ድሎች ጥይታቸውንና ደስታቸውን የሚያባክኑ አማሮችን ሃይ እንድትሏቸው በዚህ አጋጣሚ አደራ ማለት እፈልጋለሁ፡፡ ደስታን አላግባብ መደሰት ዋጋ እያስከፈለ እንደሆነም እየሰማን ነው፡፡ ዒላማውን የሳተ ጥይት ሰውን እየገደለ፣ በመቶዎች ብር የሚገዛ ጥይትም አለመላው እየከሰረ እንደሆነ ይነገራልና በዚህ ጉዳይ ዙሪያ ጥንቃቄ ይደረግ፡፡ ዘመድኩን በቀለን የምታገኙ ሰዎች ይህን መልእክቴን እባካችሁን ለርሱ አድርሱልኝ፡፡

በፌዴራል ተብዬው መንግሥት ውስጥ ያላችሁ አፋዳሾችና አክቲቪስት ነን ባዮች ሁላ ወደየኅሊናችሁ ተመለሱ፡፡ ደግሞም አታስቁን፡፡ ቢቻል በምናምን እየመረቀናችሁ የሚሰጣችሁን ሁሉ በሚዲያችሁ አታውጡ፡፡ ሆዳምነታችሁንና ቅጥረኝነታችሁን ከማጋለጡም በተጨማሪ አመኔታን ያሳጣችኋል፡፡ “ሳያጣሩ ወሬ፣ ሳይገድሉ ጎፈሬ” ይባላልና እባካችሁ ለማጣራት ሞክሩ፡፡ ሰሞኑን ከታዘብኩት አስቂኝ መረጃ አንደኛው ለምሣሌ ወያኔዎች ለነኢትዮ360 እና ርዕዮት ሚዲያ በየወሩ ብዙ ዶላር እንደሚከፍሉ የወጣው መሠረተ ቢስ መረጃ ነው፡፡ የሀሰት ፍብረካ ልክ ሊኖረው ይገባል፤ አለዚያ ከፍ ሲል እንደጠቀስኩት አመኔታን ለሚያሳጣ ቋሚ ትዝብት ይዳርጋል፡፡

እውነት ነው – በነዚህ ሚዲያዎች የሚሠሩ ሰዎች ሰው ናቸውና ሊሳሳቱ ይችላሉ፤ ማንም ፍጹም የለምና፡፡ ሽህ ጊዜ ቢሳሳቱ ግን ለነዚህ ሚዲያዎችና ግለሰቦች ወያኔ ቀለብ ይሠፍርላቸዋል ብሎ መዘገብ ሕዝብን መናቅ ነው – አንድ ሰው ካላበደ በቀር በቦምብ ለሚያደባየው ሰው ቀለብ አይቆርጥም፡፡ እንደዚህ ያሉ ማጅራት መቺዎች ያሉበት መንግሥት ደግሞ እንኳንስ ሀገርንና ሕዝብን ሊያሻግሩ ይቅርና እነሱም ከወያኔ የማይሻሉ ተራ አሉቧልተኞችና ሲመቻቸውም ነፍሰ ገዳዮች ናቸው – እያደረጉ ያሉትም ይህንኑ ነው፡፡ ንጹሓንን የሚያስርና የሚገድል “አሻጋሪ” የሰበሰባቸው አክቲቪስቶች ብዙ ተዓምር እያሳዩን ነው፡፡ ነገሩ ያለቃ ገ/ሃናን ተረት ያስታውሳል፡- በቤታቸው ያንገሸገሻቸውን የጎመን ይሁን የሽሮ ወጥ ጠልተው ወደጓደኛቸው ቤት ቢሄዱ እዚያም ተመሳሳይ ወጥ ጠበቃቸውና “በየት ዞረህ ቀደምኝ” አሉ ይባላል፡፡ የአቢይ አካሄድ የገጸ ባሕርያት ወይ የባለታሪኮች ለውጥ እንጂ የድርጊት ለውጥ የለውም፡፡

ለማንኛውም በአሁኑ ወቅት ከነስህተታቸውም ቢሆን ለኢትዮጵያ ከቆሙ የግል ሚዲያዎች መካከል አንዱ ኢትዮ360 መሆኑን በዚህ አጋጣሚ ባልመሰክር እኔም ወያኔ ማነው ኦነግ/ኦህዲድ መሆኔ ነውና ይሄውና መሰከርኩ – መረጃ ቲቪንም ጨምሩልኝ፡፡ ግን ግን በጥሩ ሥራ መኩራት እንዳለ ሁሉ በስህተትም መጸጸትንና ይቅርታን መጠየቅን ማወቅ፣ በከንቱ መታበይንም ማራቅ መልካም መሆኑን በዚህ አጋጣሚ ማስታወስ እፈልጋለሁ፡፡ ትኅትናን እንላበስ፤ መታበይን እንናቅ፡፡ ከከንቱ ውዳሤ ራሳችንን እናርቅ፡፡ የሰይጣን መግቢያ ቀዳዳዎችን ሁሉ በተቻለን መጠን እንድፈን፡፡

በመጨረሻም ፈጣሪ ሳይደግስ አይጣላምና መምህር ዘመድኩን በቀለንና ስማቸውንና ግብራቸውን  እዚህ ዘርዝሬ የማልጨርሰው ወገኖቼን በዚህን ክፉ ዘመን እውነቱን ይዘው እንዲሟገቱና ለተገፉ ብዙኃን አለኝታ ሆነው ሌት ተቀን እንዲደክሙልን እግዚአብሔር ስለሰጠን ስሙ ለዘላለም የተመሰገነ ይሁን፡፡ ይህ ብላቴና በትናንትናው የኅዳር 30 ቀን 2013 ዓ.ም የመረጃ ቲቪ ዝግጅቱ ላይ ያቀረበውን ሃተታ ማዳመጥ እጅግ ጠቃሚ ነውና እባካችሁን ጎብኙት፡፡ ዘመዴን መሰሎችን ያብዛልን፡፡ ጠላቶቻችን ምንም ዓይነት ይሉኝታና ሀፍረት የሌላቸው የፍየል ዐይን በጨው ቀቅለው የበሉ እንደመሆናቸው እነሱን ለመታገል አንዳችም ዳተኝነትና ይሉኝታ እንደማያስፈልግ ከዘመዴ መማር ይቻላልና እግዚአብሔር አብዝቶ ይባርከው፤ ልጅም ይውጣለት፡፡ ዜጋ ማለት እንዲህ ነው፡፡ መጥምቁ ዮሐንስ በበረሃ አንበጣ እየበላ የመንግሥተ ሰማይን መቅረብ ይሰብክ ነበር …

መልካም ዘመን ለሀገራችን!

14 Comments

 1. አቶ ይነጋል! በዋናው ጦርነት ሰኣት ድምጽህን አጥፍተህ አሁን ካለቀ በኋላ መጥተህ “ጦርነቱ አላለቀም” አልከን? ገብቶናል፤ ግን ጉዳዩ “መቼስ ማል ጎደኒ” ሆኖብን አልፈነዋል፡፡

  • ኧረ አልጠፋሁም ከድርዋ! ነበርኩ። አይደለም በጦርነቱ ወቅት ከ1982 ዓ.ም ጀምሮ ለዚች ምሥኪን ሀገሬ በጽሑፍ ረገድ ያቅሜን ተውተርትሬያለሁ። ሙያዎች እንደሚለያዩ ላንተ አልነግርህም፤ ሁሉም ተዋጊ፣ሁሉም አሥተማሪ፣ሁሉም አናፂ፣ሁሉም ግምበኛ፣… አይሆንምና ሰሜን ጦር ግምባር ዳንሻና ራያ ላይ እኔን አያለሁ ብለህ ጠብቀህ ከሆነ መቼም ተሣሥተሃል ከድር ሰተቴዬ! ተግባባን ወንድማለም?

   • አልተግባባንም። ከወቅትም ወቅት አለ እኮ አባ! “በጦርነቱ” ሰዓት አንድም ጽሁፍ አልጻፍክም እኮ፤፡ ከዚአ በፊት ቢያንስ በሳምንት አንዴም ሁለቴም፤ አትጠፋም ነበር፡፡ ልክ ነህ ሙያ ይለያያል፡፤ ዳንሻ መታየትም የለብህም፤ አይጠበቅምም; ነገር ግን እንዴት አስችሎህ ቢያንስ ዳንሻ ላይ ለተዋደቀው ሰራዊት ያለህን ድጋፍ እንኳ በአደባባይ (በዘሃበሻ) ሳታስነብበን ባለቀ ሰኣት ብቅ ብለህ “ጦርነቱ አላለቀም” ስትል ግር አያሰኝም ብለህ አያ፡፡

    • ነበርኩ ያልኩህ ይህ ሃሣብህ ስለገባኝ ነበር። እንዴት እንደነበርኩ አንድዬ ዕድሜ ይሥጠን እንጂ ወደፊት ይገለጣል።

 2. የትኛው ስትድዮ ዘንዳና ለየትኛውስ beauty contest ነው ይሄ ፎቶ የተቀነባበረው ?
  DC, ጎንደር ወይንስ ባህርዳር? አለባበሶቹና የፀጉሮቹ አቀማቀም ሲገመገም፣ ጦር ሜዳ የዋሉ ኢሉታት (ውርንጭሎች) ናቸው ለማለት ያስቸግራል::
  ዲሲዎች፣ stop existing only in the fake world.
  ለመሆኑስ ጥቡቆዎቹና ጥይቶችስ የትኛው Black market ዘንዳ ነው የሚቸበቸቡት?
  ደላለውን ግድ የለም እናውቀዋለን፣ ያ-‘የDC -አ ነኝ ባዩ መሁኑ የታወቀ ነው……!

 3. I wonder how much is the total cost of money spent from the Ethiopian Defence Forces so far for this law enforcement operation fought against the Tigray Junta. I also wonder how much money the Eritrean government claims to have lost so far due to this unfortunate war. Is anybody counting?

  In the modern world these types of informations get relayed to the tax paying public regularly. If not the exact amount, at least releasing an estimate or a ballpark figure once a month is appropriate.

 4. Ato Yenegal Belachew,

  I want to congratulate you on the fall of woyane proper although the branches are still around and the struggle is not yet over. Your contribution to this struggle was immense and you have to be proud of this achievement. I can imagine how much you were happy when you heard that woyane left from Mekele and the city fell under the control of EDF.
  I hope you will continue to write on Ethiopian affairs until the day comes that WE HAVE A GOVERNMENT FOR THE PEOPLE BY THE PEOPLE AND ALL ETHIOPIANS LIVE IN THEIR COUNTRY PEACEFULLY ENJOYING THEIR GOD GIVEN DEMOCRATIC RIGHTS.

  • Mesi, thanks a lot for your time, concern, and invaluable compliment. I am always fond of reading your comments given to any article on amharic.zehabesha.com. The dichotomy is clear; akedir Setete vs. Meseret.
   I believe we are nearer to the end of the tunnel and God willing we will be free of all ethnic based shackles soon. We have been tested harshly for the past half century. One headache is almost gone. The rest is seemingly less dangerous which can be dealt with less effort than the previous one. We have much experience now in combating tribalism and its paraphernalia.

   • “One headache is almost gone. The rest is seemingly less dangerous which can be dealt with less effort than the previous one. We have much experience now in combating tribalism and its paraphernalia.”

    ይነጋል፡፡ ችግርህ ከማን ጋር እንደሆነ እኮ ግልጥ ነው፤፤ አስረግጬ የምነግርህ ግን ያያዝከው አስተሳሰብ እጅግ አደገኛ መሆኑን ነው፡፡ ተረጋጋ ሰውዬ!

    • Setete,
     Do you think Amharas will continue to be hunted and slaughtered in a savage manner in their own country? Believe it or not, the time has come that this savagery will be stopped once and forever. If you have some gray matter left, stop it before the gallant Ethiopian forces knock at your door.

    • ከድሬ የያዝኩት ሃሣብ እጅግ አደገኛነቱ ምኑ ላይ ነው? ዘረኝነት በዘረኝነት መተካቱን መግለጽ ነው አደገኛ? ምንሥ የሚያረጋጋ ነገር አለ? ለመሄኑ በሀገር ውሥጥ ነህ ወይንሥ በውጭ? ጦሩን፣ አየር መንገዱን፣ ባንኩን፣ … ሁሉንም የሥራና የጥቅማ ጥቅም ቦታ በብርሃን ፍጥነት ከወያኔ እጅ ወደ ኦነግ/ኦህዲድ ጉያ ማሥገባት አያሥደነግጥም? የኬኛ ፖለቲካ ሰለባ ሆነን ድፍንት ወርሶን ሣለ እንዴት እንረጋጋ? በል እኮ መልሥልኝ! “ዐይን አይቶ ልብ ይፈርዳል” ይባላል። እውነትን አንሸፋፍን፤ ሁሉም ጥንቅር ብሎ ለሚቀር ነገር የፍትኅን ዐይን አንደንቁል። …

 5. ለቆማጣ አንድ ጣት ብርቁ ናት እንዲሉ
  ገና ጁንታዎች እጅ ለመስጠት ሲከጅሉ
  አልን አሸነፍን ዘፈንን ምኑም ሳይያዝ ከድሉ
  ጁንታዎችም ሾለኩ የኤርትራ ስደተኛን ቀለብ እየበሉ

  የኤርትራ ስደተኛ አለቃ ጋጋሪ ከበረ
  ከካምፕ አውጥቶ ቂጣ ለጁንታ እየቸረቸረ

  የጁንታ ቀላቢዎች ገቡአዲስአበባም
  ሊያማርጡቆንጆዲያስፖራሊያገቡም

  ዛሬማ ጊዜው ከፍትዋል
  አማራ ሞት ሰልችቶታል

  ቋጡ ጠብ ካላለ
  ለምን ልማገድ አለ

  ፋኖ ተብሎ ወልቃይት እና ራያን ካላስመለስክ
  ያለ ውጤት እንዲሁ በከንቱ ደከምክ

 6. ለቆማጣ አንድ ጣት ብርቁ ናት እንዲሉ
  ገና ጁንታዎች እጅ ለመስጠት ሲከጅሉ
  አልን አሸነፍን ዘፈንን ምኑም ሳይያዝ ከድሉ
  ጁንታዎችም ሾለኩ የኤርትራ ስደተኛን ቀለብ እየበሉ

  የኤርትራ ስደተኛ አለቃ ጋጋሪ ከበረ
  ከካምፕ አውጥቶ ቂጣ ለጁንታ እየቸረቸረ

  የጁንታ ቀላቢዎች ገቡ ወደ አዲስ አበባም
  ቆንጆ ሊያማርጡ ዲያስፖራ ሊያገቡም

  ዛሬማ ጊዜው ከፍትዋል
  ትውልድ ሞት ሰልችቶታል

  ቋጡ ጠብ ካላለ
  ለምን ልማገድ አለ

  የፋኖ ዘማች ወልቃይት እና ራያን ካላስመለስክ
  ያለ ውጤት እንዲሁ በከንቱ ደከምክ

  ጁንታን በማያዳግም ሁኔታ ካልደመሰስክ
  ፍትህ ላታገኝ በከንቱ አጥንትህን ከሰከስክ
  ኤፈርትን ካልተቀራመትክ
  በከንቱ ሞትክ

 7. በጣም አስተዋይነት፣እርጋታና ወንድማማችነት የሚያስፈልግበት ጊዜ ላይ የደረስን ይመስላል ፣እን ጠንቅ ፣ግን በትጋት ወደፊት እንራመድ። እንዴት?
  ሀ) ስርአታዊ ለውጥ እናምጣ፣’ አንድ ችግር በተፈጠረበት ሳጥን ውስጥ አይፈታም’ እንደተባለው፣ወያኔን ጠልተን፣ረግመን፣እነርሱ እኛን አባልተው ፣ለመግዛት አዘጋጅተው ላለፋት ሁለት አስርት አመታት የጫኑብንን ዘረኛና ሀገር በታኝ ህገ መንግስት ይዘን የትም ስለማንደርስ፣በአስቸክዎይ መንግስት የህገመንግስት አርቃቂ ኮሚሽን እቕዋቁሞ ለህዝብ ውሳኔ ያቅርብ።
  ለ) ህገመንግስት የጨዋታውን ህግ ሲወስን፣ ተጫዋቾችማለትም ፣ፓርቲዎች ስርአት ባለው መንገድ ተመዝግበው፣ተደራድረውና ተሸጋሽገው፣ ህዝቡ ፈቅዶ ባፀደቀው ህግ መንግስት ላይ ተመስርተው፣እንዴት ሊያስተዳድሩን እንደሚፈልጉ፣በማሳየት፣ይወዳደሩ። በዚህም እንደየድምፃቸው ሀላፊንት ከተጠያቂነት ጋር ህጉ በሚፈቅደው መስፈርት ይረከቡ፣ሀገር ይምሩ።
  ሐ) አሁን ያለው የምርጫ ቦርድ በአዲሱ አሬንጂመንት የጊዜ ስሌዳውን አስተካሎ ምርጫውን ያስፈፅም። ስልጠና ተጨማሪ ስራ ፣ጊዜ ድካም ወዘተሰለሚጠይቅ፣አያመችም የሚለው አስተዳደራዊ ምክንያት ፣ በዚህ መንገድ ሊመጣ ከሚችለው ስርዓታዊ ለውጥ አንፃር ሲመዘን ውሀ የማያነሳ አጉል ክርክር ነው ። የስርዓት ለውጥን ባስተዳደራዊ ችግሮች ምክንያት ማደናቀፍ ታሪክ ይቅር የማይለው ስህተት ነው ባይ ነኝ።

  አዳብሩት፣እንመካከር፣እንደማመጥ።

  ከአክብሮታዊ ሰላምታ ጋር።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.