“እኛም ሲጀምረን እንዲህ ነበር ያደረገን” አለች ትህነግ – ደሳለኝ ሀገረሰላም

130104843 123726729563588 498527932603079041 nየወልቃይት ጠገዴና የራያ ጉዳይ ከተነሳ የአማራ ህዝብና የክልሉ መንግሥት ምን ስላደረጉ ነው በእነ ታየደንደአ እና አዲሱ አረጋ የሚሰደቡና የሚንጓጠጡት??? ለሚሞት፣ ለሚሳደድ፣ በጅምላ ለሚገደል፣ በአፍ መፍቻ ቋንቋው እንዳይማር ለሚደረግ፣ በማንነቱ ለሚሸማቀቅ፣ መሬቱ እንጂ ማንነቱ ለተናቀ፣ እኔ ትግሬ አይደለሁም አማራ ነኝ እያለ ለሚጮሆ ህዝብ ፍትህ በመቆሙ ነው የሚንጓጠጠው፡፡

ይህ ጥያቄ በአንድ በኩል አንባገነኖች በሠሩት የፌዝ ፌዴራሊዝም ምክንያት ከህዝብ ተነጥሎ በኃይል የተካለለው ህዝብ ከጅምሩ ለመለስ ዜናዊ ደብዳቤ በማስገባት ነበር ተቃውሞውን ያሰማው፡፡ ከዚያም በኋላ ለዓመታት ኮሚቴ አዋቅሮ ለሚመለከተው ሁሉ የህዝቡን ስደት፣ ሞትና ጭቆና አቤት ብሏል፡፡

በሌላ በኩል ከእነዚህ አካባቢ ተነጥሎ፤ የዘመኑ ባለጊዜዎች የአንተ “አማራ ክልል” ይህ ነው ብለው በሰጡት ቦታ ሁኖ፤ ከወገኑ በቅርብ ርቀት መላው የአማራ ህዝብ በያለበት የህዝብ ታሪክን፣ ባህልን፣ መልክዐ ምድርን፣ ቋንቋን ፣ እና ሌሎችን ማኅበራዊ እሴቶች መሰረት አድርጎ ለወገኑ ሲጮህ ኑሯል፡፡ ይህ ሁሉ ነገር ዓለም የሚያውቀው ሀቅ ነው፡፡

የአማራ ክልል መንግሥት የትኛውንም “ጽንፈኛ ለማስደሰት ብሎ ጽንፈኛ” አልሆነም፡፡ የህዝቦችን የወሰንና የማንነት ጥያቄ ለመፍታት የወሰነው ቀደም ብሎ ነው፡፡ በተለይ 12ኛው የብአዴን ድርጅታው ጉባኤ ውሳኔዎችን ማስታወስ ያስፈልጋል፡፡ የወሰንና የማንነት ጥያቄዎች ለመፍታት እሠራለሁ ብሏል፡፡ ስለዚህ ዛሬም ነገም የህዝብ ጥያቄ እንዲፈታ ይሠራል፡፡
ይህንን ነባራዊ ሁኔታ ክደው አንዳንድ የብልጽግና ሰዎች እጩ ጁንታዎች ለመሆን ሲሯሯጡ እንደመመልከት የሚያሳፍር ነገር የለም፡፡ ትህነግንም ይህ የአንባገነንነትና የኢዲሞክራሲያዊነት በሽታ ሲጀምራት እንዲህ ነበር ያደረጋት፡፡ ማስፈራራት፣ ማንጓጠጥ፣ ለስህተቱ ድርጅታዊ (ፓርቲያዊ) ሽፋን በመስጠት ስህተት እንዳልሆነ ለማሳየት መጣር፡፡ እንዲህ ነበር ያደረጋት፡፡

የኦሮሞ ብልጽግና አመራሮች አደብ ግዙ የአማራን ህዝብ ጥያቄዎች እንደራሳችሁ ህዝብ ጥያቄዎች ማየትን፤ በአማራ አመራር ቦታ፤ ተጨቁኖ በኖረው የአማራ ህዝብ ቦታ ሁኖ ማሰብን ልመዱ፡፡ ካለዚያ ዝም ብሎ መፈራገጥ ከመላላጥ ውጭ መፍትሄ አያመጣም፡፡ ሌላው ሁሌም የሚያሳዝነኝ ጉዳይ ትልቅ ሁናችሁ እያላችሁ ስታኮርፋ ይዛችኋት ብቅ የምትሏት inferiority complex ነች፡፡ ታየ ደንደአ በጻውፈው ጽሁፍ ውስጥ “ስለኢትዮጵያዊነታችን ከማንም ማረጋገጫ አንጠብቅም!” ብሏል፡፡ ድሮስ ማን ይሰጥሃል!? ኢትዮጵያዊነትን ማን ለማን ሊሰጥ ይችላል!? ወደህ ፈቅደህ የምትኖረውና የምትቀበለው እንጂ!!!

ትህነግ በዚህ ሃገር ላይ በሠራችው ስሁት ፌዴራሊዝም ምክንያት ከሶማሌ ጋር የሚቆራቆስ፣ ከአፋር ጋር በሀብት ይገባኛል የሚጋጭ፣ ከሲዳማ ጋር በወንዶ ገነት በኩል ደም ተፋሶ የሚያውቅ፣ ከጌዲኦ ጋር ምስቅልቅል ውስጥ የገባ፣ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጋር በወሰን ይገባኛል የሚነታረክን ….. ክልል የሚመራ መሪ ስለወልቃይት ጠገዴና ራያ ሲነሳ እየየውን ያስነካዋል! ይገርማል፡፡ …. ለዚያውም ነፍሰጡር ሴት ማኅጸኗ ተቀዶ ህፃኑ ወጥቶ የሚበላበት ደረጃ የደረሰ ግፍ የሚሠራበትን ክልል የሚመራ ቡድን ጋር ተደራጅተህ፡፡

#አደብ_እንግዛ #አደብ_ግዙ፡፡ ለትህነግ እምቢ ያለ ትከሻ የእናንተን ማስፈራሪያ እንዴት ሊሸከም ይችላል???

ደሳለኝ ሀገረሰላም

6 Comments

 1. ከወያኔ ግብአተ መሬት መልስ፣ ሀገራችን ኢትዬጵያ የሚኖራት ፈተና “ተማርን” ብለው የተኮፈሱ ደናቁርት እና በስግብግብነት የታጀለ stereotype d የሆነ ፓለቲካዊ አመለካከት ጋር መፋለም ነው። ወያኔ እና የባህርይ ወንድሙዋ ኦነግ በኦሮሞ ምሁራን ተብዬዎች ላይ ያሳደሩት ለከት የሌለው ስግብግብነት እና መስፋ ፋት ስነልቦና ራሱን የቻለ የአስተሳሰብ አብዬት የሚፈልገው ነው።
  በታሪክ አጋጣሚ ውያኔ እና ኦነግ ጡንቻቸውን ተጠቅመው በፈጠሩት አድሎአዊ አይን ያወጣ አከላለል በሌላው ኪሳራ የተገኘን ኢፍታዊ ጥቅም ለማስጠበቅ የሚደርግ መውተርተር በራሱ ፀረ ህዝብነት ነው።
  የአማራ ወጣት ከሌሎች ዲሞክራሲያዊ ሀይሎች ጋር በመተባበር በራሱ ወላጆች ላይ “መሬት ላራሹ”በሚል መፈክር ለትግል ሲነሳ ህይወቱን ሰውቶ የኦሮሞን ገበሬ የመሬት ባለቤት ሲያደርግ የወላጆቹ ጥቅም እንደሚቀር ሳያውቅ ቀርቶ ሳይሆን ለፍታዊነት ትልቅ ዋጋ በመስጠቱ ነው። ዛሬ ያለ አግባብ የተነጠቀውን መብቱን ለማስከበር የሚያደርገውን ፍታዊ ትግል ከማገዝ ይልቅ ፣ የወያኔን ቃል በመዋስ በአሽሙር የኦሮሞ ብልፅግና ሀላፊዎች አማራውን ለማሸማቀቅ ሲሞክሩ እየተስተዋለ ነው።
  የሀገሬ መከላከያ ሰራዊት ! መተኪያ የሌላትን ህይወትህን ያጣሀው ስግብግብ ፣ተስፋፊ እና ፅንፈኛ በሆኑ ዘረንኞች መሆኑን አውቀህ፣ የወያኔ የመንፈንስ ልጆች የሆኑትን ከመሪህ ጋር ሆነህ ካለቀምካቸው እና ካላጠፋሀቸው ነገም ተመሳሳይ እጣ ፋንታ እንደሚደርስብህ ትንቢት ተናጋሪ መሆንን አይጠይቅም።

 2. የኦሮሞም የአማራም “ፖለቲከኞች” መርሳት የሌለባችሁ ነገር ቢኖር በተናጠል ሁለታችሁም ትህነግን አታሸንፉም ነበር፤፡
  Res ipsa liquotur!

 3. ይመስለኛል ዛሬም አለ ምን አትሉኝም ሁሌም ምዝገባ አለ ሁሌም ትምህርት አለ ሁሌም ምረቃ አለ አሉ የግል ኮሌጆች፡፡በረሀ ላይ እየደረሰ ያለውን ውጥረት፣ድንጋጤ፣መፈናቀል መደብደብ የመሞት የመበተን የመደንገጥ፣በየዕለቱ የመራድ አደጋ፣ሴሜቱ ይጋባብን ከቻልን በወገናዊነት በሰዋዊነት ስሜት እንሰጥ፣ከቦታው ደርሰን ስሜቴን እንጋራ ካልቻልን ዝም እንበል ዛሬም ሰዓታትን ጠብቀን በምንበላው በየደቂቃው በምንጠጣው በምንዝናናበት በስላቅ /የሕዝብ ወንበር/ ውስጥ ተወሸሽቀን ባናላግጥ፡ሠው ሆይ መልካሙን ነግሮሀል በገደምዳሜው አትፍረድ በመደዴው አታውራ አ ስ ብ !

 4. It has been said many times by many scholars the ethnic federalism constitution needs to be abolished. Despite the fact that many had fought tooth and nail to abolish the ethnic federalism constitution in Ethiopia, the fact of the matter is the constitution supporters had won overwhelmingly, kept the constitution in place this far.

  Political parties such as Arena-Tigray and NAMA currently got a historic opportunity in their hands to ignite a movement that would potentially end the ethnic federalism. Opposition political parties who operate in the Tigray region and in the Amara region need to work together to create a unified State region, which unites the Amara region and the Tigray region. The Tigray people and the Amara people got more commonality than differences , they should seize this moment to bring an end to the ethnic border lines that had divided the civilised people of Amara and the civilised people of Tigray. If Tigray and Amara region achieve harmonious unity eventually other ethnicities can also follow their suite so Ethiopia can be saved from the ethnic tribal “conflicts” which is sweeping the entire Ethiopia.

  • Very constructive and feasible suggestion ! Thank you !
   ከዚህ ዉጭ በአረመኔ ገጀራ እና ቀስት የመጨፍጨፍ scenario ን ልብ ልትሉ ይገባል ።
   God bless Ethiopia !

 5. ኣይተ መላኩ ግርማ፣
  በተለይም DC and surrounding areas ዘንዳ የሚገኙትን ‘ኣምሓሮችን’፣ ነፃነት ማለት የሌላኛው ነፃነት ነው የሚለውን ቢሂል የራሳቸው እንዲያደርጉትና ከሌላኛው ጋራ በሰላም አብሮ መኖርንም የራሳቸው እንዲያደርጉ ለማስገንዘብ ከተሳካልህና (ከተሳካልንና) Unity in diversity’ን ካለምንም precondition ከተቀበልን ብቻ ነው ሀገራችንን በተባበረ ክንድ ጠብቀን ወደፊት እያደግን የሃገራችንን ሂይወት የምንጠብቀው፣ መሆኑን መገንዘብን ለማስተማር ከተሳካልን የማይሆን ነገር የለም………….!! ቅድሚያን ለእኔ ሳይሆን ለእኛ እንስጠው………..! ‘ድር ቢያብር አንበሳን ያስር’ እንዲሉት……..!
  በርግጥ በፅዮን ልጆች ተጋሩ አእምሮ ውስጥ፣ areas of አለውሃ-ማሳዋ ቤቴ ሆኖ፣ ከሌሎች ወንድም ጎረቤቶቼ መላ ኢትዮጵያውያን ጋር ተቃቅፌ መኖር እፈልጋለሁኝ ባይነት አሁንም እንዳለ እንደሆነ አጥብቀው ያስገነዝባሉ……!
  ኢትዮጵያ ታበፅህ ኢደውሃ ሃበ መላ ልጆችዋ………..! ታሪክ ሰሪነትን በ’Vernunft ጎዳና አልፈን ለ’Nirvanam ገና እንበቃለን፣
  ከተስማሙ ዘጠኝ (9) ቂጣ ለባልና ሚስት ይበቃል………!

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.