በቆላ ተንቤን የሚገኘው የጁንታው የመጨረሻ ምሽግ ተከቦ እርምጃ እየተወሰደ ይገኛል

130238269 10219143993972504 827634990371082512 nበቆላ ተንቤን የሚገኘው የጁንታው የመ ጨረሻ ምሽግ በሀገር መከላከያ ሰራዊት በሶስት አቅጣጫ ተከቦ እርምጃ እየተወሰደበት እንደሚገኝ ተገለጸ። በቆላ ተምቤን የጁንታውን አመራር ለመያዝ የሚ ደረገውን ዘመቻ እየመሩ ያሉት በመከላከያ ሰራዊት የ31ኛ ክፍለ ጦር ምክትል ኦፕሬሽን አዛዥ ኮሎኔል ሻምበል በየነ እንደገለጹት፤ ከመቀሌ ቢሮው ለቆ የሸሸው የጁንታው አመራር በቆላ ተንቤን የመጨረሻ ምሽጉ ላይ ይገኛል።
የመከላከያ ሰራዊትን የጁንታውን የመጨረሻ ምሽግ በተለያዩ አቅጣጫዎች ከቦ እርምጃ እየወሰደ ይገኛል። ቆላተምቤን ወርቅ አምባ ከተማ ላይ የመጨረሻ ምሽጉን ያደረገውን የጁንታውን አመራር ለመያዝ አሊያም ለመደምሰስ መከላከያ ሰራዊት በመረጃ የተደገፈ እርምጃ እየወሰደ ይገኛል ያሉት ኮሎኔል ሻምበል፤ ከአድዋ መስመር የመጣው ሰራዊት አካባቢውን ለመቆጣጠር እየገሰገሰ እንደሆነ እና ከሃውዜን እና መቀሌ መስመር ያለውም ወደ ቦታው በከፍተኛ ወኔ እየተጠጋ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
መከላከያ ሰራዊቱ ወርህ የሚባል ትልቅ ወንዝ መሻገር አይችልም በሚል አካባቢ የጁንታው ታጣቂዎች ማጥቃት ቢፈጽምም ሰራዊቱ ወደ አካባቢው ተጠግቶ ከወርቅ አምባ 10 ኪሎ ሜትር ላይ እንደሚገኝ አመልክተዋል። እንደ ኮሎኔል ሻምበል ከሆነ፤ በቆላ ተምቤን ወርቅ አምባ አካባቢ የመሸገው ጁንታው በምድር ከሚወሰድበት እርምጃ ባለፈ በአየር ጭምር እርምጃ ተወስዷል። በአየርና በድሮን አውሮፕላኖች በተወሰደ እርምጃ ወርቅ አምባ አካባቢ ሲንቀሳቀሱ ከነበሩ ሰባት የጁንታው ዘመናዊ ተሽከርካሪዎች ወድመዋል።
Ethiopian Press Agency /የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት/
(ኢ ፕ ድ)

1 Comment

 1. Shouldn’t the Abiy Ahmed’s failed federal government be held accountable too, for failing to properly address the Raya Welkait questions in time?
  if the question was addressed properly in time it would have resulted in preventing the massacres and the kidnappings the residents faced during his leadership’s time , so Abiy Ahmed need to get included in the list of people who are responsible.

  We should ask why did the Abiy Ahmed’s failed federal government continue to fail to capture all of the Woyane “Junta” in a one day upto a week days time maximum operation , by mobilizing desperately needed special forces ልዩ ኃይሎች from additional regions ክልሎች besides from the Amara region special forces ልዩ ኃይሎች?

  It should be noted in the past three years Abiy did not reform as much as he should , actually it is questionable if he even reformed anything in the country’s defence forces and state police in the past three years. Currently as each day passes the TPLF junta is recuperating and getting stronger because Abiy’s regime failed to capture the “Woyane Junta”. As more days passes the risky it is to ensure justice because Abiy is not a great leader as many hype him up to be.
  Abiy Ahmed should resign ASAP.
  Abiy Ahmed’s administration is a liability which allowed this recent loss of innocent civilians lives to the residents in places such as Maikadra and Raya .

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.