የአማራ ህዝብ በማንነቱ ምክንያት እየተጎነጨ ያለውን መራራ ፅዋ በማለባበስ ኢትዮጵያን የሚያድን የሚመስለው ብዙ ነው

Meskerem Abera
መስከረም አበራ

በአማራ ህዝብ ላይ የሚወርደውን የመከራ ዝናብ እንዳያባራ ያደረገው ይህ በግልፅም በስውርም ሞት የታወጀበት ህዝብ ሰላሳ አመት ሙሉ ስልጣን በያዘው ቡድን ውስጥ በሚገባ ባለመወከሉ ነው።

የአማራ ህዝብ በማንነቱ ምክንያት እየተጎነጨ ያለውን መራራ ፅዋ በማለባበስ ኢትዮጵያን የሚያድን የሚመስለው ብዙ ነው። እኔ በዚህ አላምንም! አማራው ኢትዮጵያን በማለቱ መገደሉ እውነት ነው።በመቀጠል ኢትዮጵያን ባሉ ሞት የሚከፈላቸው ሌሎች ወገኖች ጉራጌ ፣ ጋሞ ፣ወላይታ ዋናዎቹ ናቸው።
አሁን በተያዘው ፈሊጥ ግን የኢትዮጵያ ብሄርተኝነት አቀንቃኝነት የሚለካው በእነዚህ ዘውጎች ላይ በተለይ በአማራው ዘውግ ላይ የሚያደርሰውን ዘግናኝ ጭፍጨፋ ባለማጋለጥ፣ጭራሽ ስለ ጉዳዩ ባለማውራት አንዳንዴም ራሱን ሰለባውን (አማራውን) በማብጠልጠል ሆኗል።
ስለዚህ የአማራውን መከራ በቶሎ ለማስቆም ስልጣን በያዘው መንግስት ውስጥ ደንዝዞ የተቀመጠው የአማራ ብልፅግና ፓርቲ በያዘው ወንበር ልክ መንቀሳቀስ መቻል አለበት። ይህ ሲሆን እንደ አማራው ሃገሬ ብለው በኢትዮጵያ ዳርቻ በመበተናቸው ለሚታረዱ ሌሎች ኢትዮጵያዊያን ተስፋ ሰጭ የፖለቲካ ምህዳር ማስፈን ይቻላል።ይህን መሰለኝ አቶ መላኩ አለበል ” ወቅቱ ታሪክ መስሪያ ነው” ያለው። በእውነት፣ከልብ፣በቁርጠኝነት የተባለ ከሆነ ትልቅ ነገር ነው።
ሁል ጊዜም በአማራ ፖለቲከኞች ላይ ያለኝ መተማመን ጎደሎ ነው። ሆኖም በስልጣን ላይ እስካሉ ድረስ ለእነሱው ዕድል ከመስጠት የተሻለ አማራጭ ያለ አይመስለኝም። አጥንት ማብቀል እስከቻሉ ድረስ ህዝብ ከጎናቸው ነው!
130188498 3678872645512312 4205529401863910475 n
ተጨማሪ ያንብቡ:  የሚኒስትሮች ምክር ቤት በኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ

4 Comments

  1. አይ ቲቸር መስከረም! ሌሎች ካንቺ ያነሱት ላይ ለምደሽ፤ ብርሃኑ ነጋን ኢንተርቬው አደርጋለሁ ብለሽ ድንቁርናሽ ከተጋለጠ ወዲህ ብዙም አላማረብሽ፡፡ አቢይም አምታታብሽ፤፤ እሱን ሲያቅትሽ ፡ የአማራ ብልጽኛዎችን “ለምን አቢይን ታግዙታላችሁ” ማለቱን ተያያዝሺው፡፡ ምስኪን!

    • kedir,

      You may worship, the AMHARA hater, serpent, cun artist, superficial and showy abiy ahmed as that is your democratic right. However, comparing the most bright and examplary woman, MESKEREM ABERA, who can be named as modern times “Tayitu”, with your wishy washy ahmed is unfair and a crime at large.

  2. መስከረም በሀሳብ ሞገተች።በሀሳብ መሸናነፍ የሰለጠነ ፓለቲካ ነው።ሀሳብን በሀሳብ ከመሞገት ይልቅ ዘለፋና ለማሸማመቅ መሞከር ኋላ ቀር ፓለቲካ ነው።የወረዳችሁ አንድ ደረጃም ቢሆን ከፍ በሉ።

  3. ,ሀሳብን በሀሳብ መሞገት ዘመናዊነት ነው።መስከረም ከዚህ አንፃር ድንቅ ተሳታፊ ነች። ከዚያ ይልቅ ሰዎቾን መዝለፍና ማሸማቀቅ የኋላ ቀር አስተሳሰብ ውጤት ነው።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.