አዲስ አበባ ሌላዋ የኢትዮጵያ ወልቃይት ! – ፊልጶስ

addis ababa 1ከዘመናት የወያኔ ግፍና ስቆቃ በኋላ ወልቃይት “ነፃ “ ወጥታለች። ወልቃይት ለዚህ ለመብቃት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ተገለዋል፣ ተሳደዋል፣ አካለ ስንኩል ሆነዋል፣ በጅምላ ተቀብረዋል፣ በአጠቃላይ ወያኔ በኢትዮጵያ ላይ የፈፀመው ግፍ ሁሉ በደቦ ተፈፅሞባታል። ታዲያ ወልቃይት ከወያኔ ነፃ ስትወጣ ፣ አዲስ አበባን ተክታ ነው።

እንደ ወልቃይት አዲስ አበባም ተመሳሳይ ታሪክና ትርክት እያስተናገደች ነው። ወልቃይት፤ ወያኔ ትግል እንደጀመረ 1966 እስከ 1967 ድረስ ወደ ሱዳን የሚያደርገው ማንኛውም ደርሶ መልስ ጀብሃ በሚቆጣጠረው በኤርትራ ክፍለ ሃገር አድርጎ ነበር። በ1967 መጀመሪያ አካባቢ ወያኔ ከ’ርዳታ ድርጅት የዘረፈውን ቁሳቁስና የጭነት መኪናዎች ይዘው ወደ ሱዳን ለመሻገር ሲሞክሩ ጀብሃ.. “ከዘረፋችሁት ሃብት ግማሹን አካፍሉኝ” አለ። ወያኔ ስግብግብ ዘራፍ! አለ። ብሎም አልቀረ:: የዘረፈውን ሃብት ከነመኪናዎቹ አቃጠላቼው። እናም ተከዜን ተሻግሮ ወደ ወልቃይት ፊቱን አዞረ። ቀስበቀስም አካባቢውን ተቆጣጥሮ ከሱዳን ጋር ለሚያደርግ ግንኙነት ብሎም ወያኔ ለህልውናው የደም ስር ወልቃይት ሆነች።

አዲስ አበባ ፤

ወያኔ አዲስ አበባን የኔ የግሌ ነች ለማለት ምክንያት ስላልነበረው ከተማዋን አራቁቶ በልቶ ተቃውሞው ሲያስፈራው በተለይም 1997 ምርጫ በኋላ ኦህዴድ ከናዝሪት አውጥቶ አዲስ አበባ ያንተ ነች አለው። ወያኔ የአዲስ አበባን ህዝብ ለመበቀል ከሄደበት መንገድ አንዱ ይህ ነበር ። በእርግጥ ወያኔ የአዲስ አበባን ህዝብ በተዘዋዋሪ የመቆጣጠሪያም ስልት መቀየሱ ነበር::

ልብ እናድርግ!…. ወያኔ ጀበሃ በ’ኔ ግዛት አታልፍም ሲለው የሄደው ወደ ወልቃይት ነበር። የአዲስ አበባ ህዝብ የወያኔን ጸረ ኢትዮጵያዊነት ቀደሞ የተረዳ በመሆኑ፤ የሱን ወንቶ- ፈንቶ የጎሳ ፓለቲካ “አር የነካ እንጨት” ሲያደርግበት ለኦህዴድ አዲስ አበባን በእጅ መንሻ ሰጠው። ወያኔ ፈንጅ ለመቅበሩ እርግጠኛ ነበር:: ለምን እና እንዴት? ብለው የማይጠይቁት የኦህዴዲ ጽንፈኞች ደግሞ እንደ ትልቅ ድል ቆጥረውታል::

ወልቃይት፤

ወያኔዎች የወልቃይትን ማንነት ለማጥፋት ከግድያ ጀምሮ የትግራይ ተወላጆችን በተለያየ መንገድ በማስፈር ዲሞግራፊውን ቀየሩት። ማስፈር በሱዳን የተሰደዱ ስደተኞችን ከመመለስ ጀምሮ፤ ከጦሩ የተሰናበቱትን በመቶ ሺ የሚቆጠሩ እና ከተለያዮ የትግራይ ወረዳዎችን ይጨምራል ኢኮኖሚውን ተምተቆጣጠሩት። ስራ እየተመረጠ ለወያኔና መሰሎቹ ብቻ ተሰጠ። ዜጋው ከአፓርታይድ በከፋ ከምድር በታች ያለ ኢሰባአዊ ሁሉ ተፈፀመበት።

አዲስ አበባ፤

የትላንቱ ኦህዴዲ የዛሬው ኦዲፓ – ብልፅግና አዲስ አበባ የኦሮሚያ ዋና ከተማ ብቻ አይደለችም፤ ኦሮሚያ ልዩ ጥቅም ማግኘት ይገባታል አለ፣ አደረጋትም ፤ ዜጎች ልፍተውና ደክመው ያስገነቡትን ቤት በማን አለብኝ ለኦሮሞ ተወላጅች አደሉት።

የአዲስ አበባ ህዝብ በልማት ስም ቤት ንብረቱ እየፈረስ እንደ አሮጌ ቁና የትም ተወረወረ ፤በምትኩ ተረኞቹ የኦሮሚያ ብልጽግናዎች ከየቦታው እየተጠረሩ ሁሉንም ነገር ተቆጣጠሩት:: አዲስ አበባ ዜጎች ተወልደው ባደጉበት ባይተዋር ሆኑ ወጣቶቹ ተምረው ስራ ማግኘትና ኑሮ መመሰረት ህልም ስለሆነባቼው መሰደድና በባዕድ አገር መከራተት እጣ ፈንታቼው ሆነ:;

የአዲስ አበባ ህዝብ በግልጽ በኢትዮጵያዊ ማንነቱና ለዘመናት በገነባው ማህበራዊ እሴት ላይ ጦርነት ታወጀበት:: በወልቃይት እንደተደረገው ሁሉ በአዲስ አበባም ከሱማሌ ክልል ተፈናቀሉ የተባሉት ከግማሽ ሚሊዮን ህዝብ በላይ አሰፈሩበት። ይህም አልበቃቼው፤ በአንድ ቤት ውስጥ እስክ 170 የሚደርስ መታወቂያ ከአዲስ አበባ ውጭ ለመጡ የእነሱ ተወልጆች በገፍ አደሉ።

በወልቃይት ወያኔ እንዳደረገው ሁሉ ኦዲፓ – ብልፅግና የከተማዋን ማንነት ለማጥፋት ከስም መቀየር ጀምሮ እስከ አዲስ ክፍለ ከተማ መፍጠር ድረስ ሄዱ። በከተመዋ የእነርሱን ቋንቋ የማይናገር የስራም ሆነ የኢኮኖም ተጠቃሚ መሆን እንዳይችል በመንግሥት ደረጃ መዋቅር ዝርግተው ይሰራሉ።

ወልቃይት፤

ወልቃይቶች በማንነታቼው ወያኔ ሲዘምትባቼው ጮሁ፣ ታሰሩ ፣ ተገደሉ ፣ ታገሉ ፣ በኢትዮጵያም ወያኔን የማስወገድ የትግል ፋና ወጊ ሆኑ ፣ ትግሉን አገር አቀፍ እንዲሆን ሰቆቃቼው በዓለም ዳርቻ እንዲሰማ ከፍ አድርገው ጮሁ ። ያ ትግላቼው ፍሬ አፍርቶ ዛሬ ለነፃነት በቁ።

አዲስ አበባ ፤

አዲስ አበባሜ በማንነቱ ላይ በግልጽ ጦርነት እንደታወጀበት ሲያውቅ መታገል ጀመረ። በህዝቡ ያልተመረጠ ከንቲባ ሲሾምበት አጥብቆ ተቃወመ:; ግን ወያኔዎች እንዳደረጉት ሁሉ የአዲስ አበባ በባለተረኞቹ ኦሮሚያ ብልጽግናዎች ሰላማዊ ታጋዮችን ከብዙ ማገላታት በኋላ ወደ ዘብጥያ አወረዷቸው::

ለግዜውም ቢሆን አዲስ አበባን ታጋይ አልባ ያደረጓት መሰላቼው። ወያኔንም ወልቃይቶችን የቻለውን ያህል ገሎና አሳዶ ታጋይ አልባ ያደረጋት መስሎት ነበር። “ግን ታጋይ ይሞታል ፣ ትግል ግን አይሞትምና “ ወልቃይቶች ለዚህ በቁ። የአዲስ አበባ የአሁኑ ትግል የህልውና ትግል ነው:: ለአዲስ አበባ ህልውና መከበርና ስለ ፍታዊነት በሰለጠነና በሰላማዊ የጠየቁ ዜጎችን በግፍ አስሮ ሰላም አይኖርም::

የአዲስ አበባ ህዝብ “መዲናችን የማንም ሳትሆን የሁላችን የኢትዮጵያዊያን ብሎም የአፍሪካ ነችና ‘ራስን በራስ የማስተዳደር የተፈጥሮ መብታችን አትከልክሉን :: ለዘመናት ከመላው ያአገሪቱ ክፍል በተውጣጡ ዜጎች የተገነባውን ማንንነት አትንኩብን አክብሩልን “” አለ እንጂ፣ የራሱ ያልሆነውን አልጠየቀም።

ለባለተረኛ ገዥዎቻችን የምናስተላልፈው መልእክት፤ ትላን ት ጎሰኝነትንና ጸረ- ኢትይጵያዊነትን እንደ ጡጦ አጥብቶ ካሳደጋች ሁ ወያኔ ተማሩ::ምንም ይሁን ምንም ኢትዮጵያዊነት ለሁላችን መደሃኒትና መዳኛችን መሆንኑ አሁንም ከወያኔ ስህተት ተማሩ ! ብለን እንመክራለን :;  አዲስ አበባ ለሁላችንም ትበቃለች:: አቅፋ ደግፋ ትይዘናለች:: ግን የአንድን ጎሳ የበላይነት የምትሸከምበት ጫቃ የላትም::

ወልቃይቶች “ወልቃይት! ብረሳሽ ቀኘን ይርሳኝ !”እንዳሉት ፤

 

እኛም “አዲስ አበባ፦ ብረሳሽ ቀኘ ይርሳኝ”።
ፊልጶስ
E-mail: [email protected]

ይቀጥላል

1 Comment

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.