የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ምቹ የንግድ እና የኢንቨስትመንት 7 ፖሊሲዎች

129912098 821438678426117 4309226854668920987 n
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ምቹ የንግድ እና የኢንቨስትመንት ከባቢ እና የተረጋጋ ማክሮ ኢኮኖሚ መፍጠርን ዓላማ አድርገው የተዘጋጁ 7 ፖሊሲዎች ላይ የኢዜማ ከፍተኛ አመራሮች እና ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት የሚደረገው የሁለት ቀን ውይይት በጌት ፋም ሆቴል መካሄድ ጀምሯል።
ኢዜማ ከ40 በላይ በሆኑ የተለያዩ ዘርፎች የፓርቲው አባል የሆኑ እና ያልሆኑ ባለሙያዎችን በማሰባሰብ ፖሊሲዎችን ሲያዘጋጅ መቆየቱ ይታወቃል። በሁለቱ ቀን ውይይት ከእነዚህ ፖሊሲዎች መካከል 7ቱን ያዘጋጁት ምሁራን ፖሊሲዎቹን ለተሳታፊዎች አስረድተው አስተያየቶችን የሚቀበሉ ይሆናል።
ኅዳር 26 እና 27 ቀን 2013 ዓ.ም በጌትፋም ሆቴል በሚደረገው ውይይት የኢንቨስትመንት፣ የንግድ፣ የኢንፎርሜሽን፣ ኮሙኒኬሽን እና ቴክኖሎጂ፣ የኢንደስትሪ፣ የገንዘብ እና በጀት፣ የማኅበራዊ ከለላ እና የአካባቢ ጥበቃ ረቂቅ ፖሊሲዎች ቀርበው ውይይት ይደረግባቸዋል።
የተቀሩት ፖሊሲዎች ላይ ተመሳሳይ ውይይቶች በ5 ዙር የሚካሄድ ሲሆን በኢዜማ መተዳደሪያ ደንብ መሰረት የፓርቲው ኮንፈረንስ ሲያፀድቃቸው ለሕዝብ ይፋ ይሆናሉ።

2 Comments

  1. ተዉ እናንተ ምናችሁም አይታመንም እንድትታመኑ ከፈለጋችሁ ብረህኑ ነጋ፤አንዳርጋቸዉን ከጀርባ ሁኖ የሚመራችሁን፤ ግርማ ሰይፉ የተባሉትን ካላባረራችሁ ልትታመኑ አትችሉም ሊቀ መንበራችሁንም መስዋትነት የከፈለዉን ታላቁን ጀግና አንዱአለም አራጌን አድርጉት የምን ብልጣብልጥነት ነዉ ማኪያቶዉን ሲያጣጣም ከርሞ መለስ ዜናዊን ሲያማክር ከርሞ አሁን የድርጅት ሊቀ መንበር የምታደርጉት። ትንሺ አስቡ እንጂ ህዝቡንም አትናቁት።

  2. የፕሮስፐርቲ ፖርላማ ካላፀደቀው ፖሊሲዮቻችሁን በአሁኑ ወቅት የኢዜማ ብቻችሁን ውይይት ወና የሰነበተውን የሆቴል አዳራሽ ከማሙዋሙዋቅ በስተቀር ምን ሊፈይድ? ኤፈርትን ትተኩ ይሆን?

    ባይሆን የኢትዮጵያ ንግድ ምክር ቤት በጠራው ስብሰባ እንዲህ ቢያወያይ እይገርምም።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.