ባለፉት ዓመታት የማንነት ጥያቄ በማንሳታቸው ብቻ በርካታ ዜጎች በህወሓት የጥፋት ቡድን መረሸናቸውን የሁመራ ከተማ ነዋሪዎች ገለፁ

130016413 3013163288920983 6518261414144031887 n
ባለፉት ዓመታት የማንነት ጥያቄ በማንሳታቸው ብቻ በርካታ ዜጎች በህወሓት የጥፋት ቡድን መረሸናቸውን የሁመራ ከተማ ነዋሪዎች ገለፁ
አርሶ አደርና ባለ ሀብት የነበሩት አቶ አማራ ጥሩነህ የዕድሜ ዘመናቸውን ሁሉ በሁመራ ከተማ ሲያሳልፉ ለስራ ያላቸው ክብርና ጠንካራ ማህበራዊ ተሳትፏቸው በከተማው ማህበረሰብ ተወዳጅነታቸውን እንዲያተርፉ ምክንያት መሆኑን የቅርብ ሠዎቻቸው ህያው ምስክር ናቸው።
ያም ሆኖ ግን የግለሠቡ ቅንነትና ለችግር ቀድሞ ደራሽነት በትህነግ የጥፋት ቡድንና አመራሮች ዘንድ እንደ ጥፋት ተወስዶ የአይንህ ቀለም አላማረንም የሚል ተደጋጋሚ ጥቃቶች ይሰነዘርባቸው እንደነበረ ቤተሰቦቻቸው ያስረዳሉ።
በመጨረሻም የግፍ ፅዋዉ ሞልቶ ፈሰሰና ቡድኑ ሁመራን ከተማ ከመልቀቁ በፊት አቶ አማረንና የልጃቸውን ባለቤት ጨምሮ ስምንት ሰዎችን እንድሪስ በምትባል ከተማ አንድ ቦታ ላይ በግፍ ገድሎ አስከሬናቸውን የክብር ሽኝት ነፍጎት በጫካ ቀርተዋል።
129857476 3013163198920992 4851619332420901712 nበአካባቢው የማንነት ጥያቄን ማንሳት በዚህ የጥፋት ቡድን የሚያስቀይፍ ወንጀል መሆኑን የሚናገሩት የሟች ቤተሰቦች አሁን ላይ በአንድ ቤተሠብ ሁለት አባውራን በሞት ተነጥቀውና ከማይናገረው ፎቶ ግራፍ ጋር ፊት ለፊት ተፋጠው በሀዘን ድባብ ውስጥ ይገኛሉ።
በተለይ ደግሞ በሁመራ ከተማና አካባቢው በግለሰቦች ቤት ለሀይማኖታዊና ሌሎች ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ የሚደረጉ ማህበራዊ ግንኙነቶች በትህነግ የጥፋት ቡድን አለቆች በሙሉ ዙፋንን እንደ መነቅነቅ ተግባር ተቆጥሮ ሲያስረሽን ቆይቷል ይላሉ።
የጥፋት ቡድኑ ልብ ሰባሪ ተግባርን እንደ ማሳያ በዚህ ቤተሠብ አንደበት ይገለፅ እንጅ ልቆ መስፈርት ዜጎች የጭካኔ ሰይፍ ተመዞባቸው ላይመለሱ አሸልበው የጫካ ሲሳይ ሁነው ቀርተዋል።
129501630 3013163242254321 2050255980330414712 n
ግፍና በደል በርትቶባቸው ክብር ተነፍጎት በዱር በገደሉ ወድቀው የቀሩ ንፁሀን ዜጎች ታሪክ እንዲቋጭና ትውልድ እንዲድን ግፈኛው ቡድን በሰራው ልክ ሊቀጣ ይገባል ብለዋል ሲል ማዕከላዊ ጎንደር ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን መምሪያ በዘገባው አስፍሯል።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.