ከዳግም ጥፋት መዳን ምርጫ ሳይሆን የህልዉና ጉዳይ መሆን አለበት ! – ማላጂ

በዓለም የሰዉ ልጆች ታሪክ የራሱን አገር እና ህዝብ ለጥቃት እና ዉርደት አሳልፎ በመስጠት ልማድ በኢትዮጵያ የስነ መንግስት ዑደት ኢህዴግን የሚስተካከል የፖለቲካ ድርጅትም ፤መንግስት አልነበረም ወደፊትም እንዳይኖር የኢትዮጵያ ህዝብ እና አሁን ያለዉ አሻጋሪ እና ለዉጥ ተጋሪ መንግስት ከፍተኛ ጥምረት እና ህብረት ፈጥረዉ ለአነዴ እና መጨረሻ ጊዜ ከስሩ ለማድረቅ የሞት ሽረት ትግል በማድረግ ላይ ናቸዉ፡፡

fg3793479 jdw 8959አሁን ላይ የሚገኘዉ ከህግም  በላይ የአገርን እና ህዝብን ህልዉና ለዳግም አደጋ ሊዳርግ በሚችል የርዕዮተዓለም መስመር ልዩነት መፈጠሩ ጅምሩም ሆነ ዉጤቱ በዉጣ ዉረድ እና ችግር የሚታጀብ ቢሆንም ከ27 ዓመታት በፊት የተተከለ ዕንቅፋት ዳግም እንዳያነቅፍ ለማናሳት በመልካመረ አጋጣሚነቱ ሊወሰድ ይገባል፡፡

በአገራችን በ1960 ዎች. ዓ.ም .አጋማሽ  በወፍ ዘራሽ በአገሪቷ የተበተነዉ የተዉሶ የጥፋት ዘር“ የብሄር ጭቆና ” እና ራሳቸዉን “ያ ትዉልድ ” እያሉ የሚጠሩ  ዕርስ በዕርስ ሳይግባቡ እና ሳይናበቡ ለቡድን እና ለጥቅም ፍላጎት ሲራኮቱ አገሪቷን በደም አበላ ዘፍቀዉ ወደ አደራሳቸዉ መንገድ እግሬ አዉጭኝ አሉ ፡፡

እንግዲህ እነዚህ ነበሩ በከተማ ትግል የብዙሃኑን ኢትዮጵያ ህዝብ ልጅ ጭዳ እንዲሆን ያደረጉት እነዚህ ዛሬም በዘመን ሂደት በዚያን ዘመን በነበር አስተሳሰብ ዛሬም ራሳቸዉን የነጻነት ፋና ወጊ እና ጠባቂ የሚያደርጉት ፡፡

ዳሩ ግን ህዝባዊ ይዘት እና መልክ የነበረዉ  ትግል ስላልበር ከጅምር አስካሁን የዜጎችን ህይዎት እና የአገር ደህንነት አደጋ ላይ ከመጣል ዉጭ ያስከተለዉ አንድም ፋይዳ አለመኖሩን በተግባር ታይቷል፡፡

የብሄር ጭቆና ብለዉ ተነስተዉ እነርሱ ግን ሶስት እና በላይ የብሄር ፣ የመደብ  እና ጉልተኝነት  ስርዓት ተክለዉ የራሳቸዉን እና የመሰሏቸዉን ጥቅም ለማስጠበቅ የሚደረግ በአገር እና በህዝብ ላይ የሚደርስ ጉዳት ሁላ የተቀደሰ ተግባር እንደሆነ ሲቆጠር መባጀቱን እነርሱም ያዉቁታል ፍላጎታቸዉም አላማቸዉም ያ ስለነበር ፡፡

ይህ አልበቃ ብሎ ሰሞኑን በአገራችን ተርፎ እና ገንፍሎ እሳት ላይ የወደቀዉ ግፍ እና ግፈኞች ከዘመነ ትጥቅ ትግል ጅምር አስካሁን የሆነዉ በአገር እና ህዝብ ላይ የደረሰዉ መጠነ ሰፊ በደል ሽብርተኝነት ነዉ አይደለም በሚለዉ በአንድ ራስ  ሁለት ምላስ መሆኑ ባያስገርምም አሳኝነቱ ግን ከትዝብት ጋር ምን ያህል ከአገር እና ህዝብ ርቀት ላይ የሚገኙ እና ከዕዉነት እና ሠባዊነት አስተሳሰብ የራቁ የመቀመጫ ቁስሎች እናዳሉ ያሳየናል ፡፡

በእኛ አገር መንግስት በራሱ ህዝብ እና አገር ላይ ምን ያህል ደባ ይፈፅም እንደነበር ክቡር ጠ/ሚ በመጋቢት 24/2010 ዓ.ም. በዓለ ሲመት ላይ ያሉትን ማስታወስ የማይፈልግ ቢኖርም እዉነትነቱን መካድም ሆነ መረሳት እንደ ሠዉ ለሚያስብ አይቻለዉም፡፡

እርሳቸዉ እዉነቱን ብለዋል ግን ኃላፊነት የወሰደ እና በዕዳ የተጠየቀ ስለሌለ ዛሬም ሽምጥ መሸፋፈኑ ቀጥሏል፡፡

ታዲያ ዛሬ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ትህነግ እና ተከታዮች በሽብርተኝነት ይወከሉ አይወከሉ የሚለዉ ይህን ያህል የሚያነጋግርመሆኑ እንዴት ማለት ለጋራ እና አንድ ቤታችን በአንድነት ማሰብ ነዉ፡፡

የአስቸኳይ ጊዜ ቃል አቀባይ የሆኑት ረድዋን ሁሴን  በግል እንጅ በተቋም ደረጃ አሸባሪ የለም ሲሉ ለህዝብ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

መዝገበ ቃላቱን ወይም ፍችዉን ግን ከምን እና እንዴት እናዳገኙት ለህዝብም ሆነ ለዓለም አላሳወቁም ወይም ዋቢ አልቀሱም፡፡

በሰዓታት ልዩነት አገሪቷን እየመራ ያለዉ የፖለቲካ ተቋም ክንፍ የሆነዉ ከፍተኛ አመራር ክቡር አቶ ዓብርሃም አለህኝ ደግሞ ሽብር እና አሸባሪ ከእኛ አገር ተጨባጭ ሁኔታ ሲታይ በዓለም በይዘቱም ሆነ በዓይነቱ አቻ-የለሽ እንዲያዉም የክፍለ ዘመኑ የምድር ሲኦል መገለጫ ብለዉታል፡፡

ይህ እንግዲህ ፀሀይ የሞቀዉ ፣አገር ያወቀዉን እና ዓለም የሚረዳዉን ዕዉነት ይህ ነዉ ያ ነዉ ትክክል ማለት መባዘን ነዉ፡፡

አስኪ ከሠባዊነት እና ከእዉነተኛ ህዝባዊነት አስተሳሰብ አንጻር ከብዙ በጥቂት በግርድፉ በእኛ አገር ዕዉን የነበሩ መራር ሁነቶችን ለመንቀስ የሚከተሉትን መጥቀስ ስለ ሽብርተኝነት፣ ዘር ፍጅት እና ብሄራዊ ክህደት ጋር የሚኖረዉን ዕንደምታ ማየት ይቻላል ፡፡ ይኸዉም ፡-

 • በየትኛዉ ዓለም እና አገር ነዉ የአንድን አገር ህዝብ ጠላት እና ወዳጅ፣ ታማኝ እና መናኝ አድርጎ ትግል የተጀመረዉ በዕኛ አገር ካልሆነ በሌላ አይኖርም ቢኖርም ብሄራዊ ወነጀል እና ጥፋት ነዉ፣
 • አንድን የነበር ስርዓት በህዝብ ስም  መታገል  እና ለግል እና ቡድን ስልጣን ቅድሚያ መስጠት ቢለያይም በህዝብ ስልጣን ሽፋን አገርን እና ህዝብ ምርኮኛ አድርጎ መዉሰድም ህዝባዊ እና ታሪካዊ ጥፋት እና ስህተት ነዉ ይህም በዕኛ አገር ነባር ዕዉነት ነዉ፣
 • የትኛዉ ዓለም እና አገር ነዉ ለአንድ አካባቢ ህዝብ ነጻነት ታጋይ ነኝ ብሎ የራስ ገዝ ለመመስረት ትጥቅ ትግል ካደረገ በኋላ በህዝብ ድጋፍ እና ዕቅፍ ወደ ማዕከላዊ የስልጣን ማማ ከወጣ ማግስት ጀምሮ  አገርን እና ህዝብን በባርነት ለማስተዳደር እና ለማስገበር ሀ ብሎ የጀመረዉ መንግስትን የወከለዉ አዉራ ድርጅት እንጅ ግለሰቦች አይደሉም ፤አልነበሩም ፣
 • ወደ ማዕከላዊ መንግስትነት በሽግግር ላይ እያለ በኢትዮጵያዊነት እና በብሄራዊ አንድነት ላይ ልዩነት መፍጠር የጀመረዉ ድርጅቱ እና ተባባሪዎች አንጅ ግለሰቦች አይደሉም ፤አልነበሩም ፣
 • በህገ መንግስት ረቂቅ ፣ በክል አደረጃጀት እና በስልጣን ክፍፍል ላይ በብቸኝነት ከተባባሪ ድርጅቶች ጋር በማሴር ብዙሃን በአገራቸዉን የበይ ተመልካች እንዲሆኑ የተፈረዳባቸዉ በየትኛዉ የመንግስት አስተዳደር ስርዓት ነበር፤ይህስ እንዴት በግለሰብ ደረጃ ዝቅ ይላል፣
 • በመንግስት ፍላጎት እና ዓላማ በአገር ደረጃ ዕቅድ አዉጥቶ ህዝብን በህዝብ በማሳደም ጠላት የሚለዉን ታላቅ እና ብዙሃን ህዝብ አከርካሪዉን መምታት ፣አንገት ማስደፋት እና ማሳደድ ነዉ የሚለዉ ማን እና እንዴት እንደነበር ለሚረዳ ይህ እንዴት ነዉ የግለሰብ የሆነዉ፣
 • የአንድ ወይም የሁለት ብዙሃን ማህበረሰብ ከብሄር በላይ ሠዉ ሆኖ መፈጠር ፣ ሠባዊነት እና ኢትዮጵያዊነት እያሉ እንዲከስሙ ሌት ተቀን ሲሰራ ይህ እንዴት የግለሰቦች ጉዳይ ሆነ ፣
 • አንድን ህዝብ ፣ዕምነቱን ፣የዕምነት ተቋሙን እንዳልነበር ለማድረግ በዕቅድ ሲንቀሳቀስ የነበር አካል የግለሰቦች ማለት ዕዉነቱን ከመፍራት ወይም ቸልተኛ  ከመሆን በቀር የግል አይሆንም ፣
 • በአገሪቷ በየትኛዉም አቅጣጫ ፍትህ እና ርዕትህ ርቆት የዳኛ እና የመንግስት ያለህ ሲል የማርያም ጠላት ይባል የነበረዉ ማህበረሰብ የደርስበት የነበረዉ ስደት፣ ሞት እና ዉርደት በማን እንደነበር እና ይህም ተቋዊ ይዘት የለዉም ለማለት እንዴት ይቻላል፣
 • የአንድ ህዝብ ፣ማህበረሰብ እና ግለሰብ መብት ጥያቄ ማንሳት በወንጀለኝነት በሚጠየቅባት የአገዛዝ ስርዓት ዉስጥ ያለፈ ማህበረሰብ በህይወት የመኖር፣ ሰርቶ ሀብት ንብረት የማፍራት /የማደግ ፣   አያት ቅድመ ዓያቱ ባቆዩት አገር እና ምድር ባይተዋር እንዲሆን በመንግስት በጎ ፈቃድ ሲወሰንበት ይህ ተቋማ አልበረም ሊባል አይችልም ፣
 • የአንድ አገር ህዝብ በአገሩ የመኖር መብቱ እየተነጠቀ ሂድ ፤ተሰደድ ምን ወሰደህ ምን አመጣህ በሚባልባት ብቸኛ ለዜጎቿ የማትሆን አገር በመፍጠር የግል እና የቡድን ጥቅም ማሳደድ የግለሰቦች ዉሳኔ እና ስልጣን ነበር ማለት የማይሆን ነዉ ፣
 • የራሱን ቅየ እና መንደር በኃይል ተነጥቆ ስደተኛ ሲሆን፣ ሰርቶ መኖር ሲችል ለልመና እና ድህነት ሲጋለጥ ይህ ህግ እና ፍትህ ስለነበር ወይም ስላልበር ይሆን ወይስ ምን፣
 • አገር አቀፍ የብሄር እና የመደብ ጭቆና ተስፋፍቶ ፤ የአንድ አዉራ ፓርቲ ወይም ማህበረሰብ አገዛዝ አዛዥ ናዛዥነት በቃ የሚል ህዝብ በተነሳ ቁጥር ለዕሳት እና ሞት የሚዳረገዉ ፣በሽብር ስም የአገር እና ህዝብ ቅስም ሲሰብር የነበር ያለ መንግስት ወይም ቁንጮ ድርጅት ትዕዛዝ ዉጭ የግለሰቦች /ግለሰብ ጉዳይ ነዉ ማለት ሀሰት ይሆናል፣
 • ከ1970 ዓ.ም.ጀምሮ የሞት እና የስደት ፅዋ እንዲጎነጭ ሲደረግ የነበረዉ እና እናት ምድር አገር ወይም ሞት ያለዉ ሁሉ(ጎንደር -ሁመራ ፣ወልቃይት……) አሸባሪ፣ ፀረ ሠላም ሲባል የነበረዉ በማን እና እንዴት እንደነበር አሁን የሚዘነጋበት ሳይሆን ታረክ ሆኖ የሚዘከርበት ጊዜ መድረሱን መዘንጋት ነዉ ፣
 • ኢትዮጵያ ማለት እና ኢትዮጵያዊነት እንደ ብሄራዊ ክህደት ይቆጥር የነበር ተቋም /ፓርቲ መንግስት ሆኖ አገር እና ህዝብ በአስተዳደረባት የሆነዉን ግፍ እና ሰቆቃ ሁሉ የግለሰብ ጉዳይ ማድረግ ለዳግም ጥፋት እና ክህደት መነገድ ማመቻቸት ከመሆን ዉጭ ምን ይባላል፣
 • በኃይማኖት ተቋማት፣ ዓማኒያን እና መናኞች ላይ ሳይቀር አሸባሪ እና አድኃሪ የሚሉ ተቀፅላ በመለጠፍ በሽብርተኝነት እና በተካደ አገር እና ህዝብ አገር ክህደት እየተባለ የዜጎች የስቃይ ምድር በማድረግ  የአገዛዙን  የስልጣን ዘመን ለማስቀጠል እና የአገሪቷን ህዝቦች የመከራ ዘመን ለማራዘም የተደረገዉ የግፍ እና ጭካኔ ተግባር የግል ሲሆን ባለቤትነት የሚወስደዉ ማን ነዉ ፣
 • የአንዲት ታሪካዊት አገር ልዑላዊነት ከማስደፈር እና ዳር ድንበር ቆርሶ እና ቀንሶ ለባዕድ እና ለጠላት አገር አሳልፎ ከመስጠት በላይ ጥፋት ምን ሊጠቀስ ይችላል፤የየትኛዉ ዓለም እና አገር ስርዓተ መንግስት ነዉ የራሱን ህዝብ ለድህነት ፤ባርነት ፤አገሩን ለዉርደት እና ጥገኝነት አሳልፎ የሰጠ ፤እኮ ይህ የግለሰብ ጉዳይ ነዉ ወይ ፣
 • በዓለም ላይ ባለንበት ዘመን የራሱን አገር በታሪክ እና በዓለም ፊት የነበራትን ወደብ በማሳጣት የባህር በር አልባ አገር እንድትሆን ያደረገ ስርዓት ወይም የመንግስት አስተዳደር ተቋም/ድርጅት ከእኛ ዉጭ ማን ነዉ ፤ ይህም ግለሰብ ነዉ እንል ይሆን ፣
 • የኢትዮጵያ ጉዳይ የዕኛ ጉዳይ ነዉ የሚል ኢትዮጵያዊ ሁሉ ጎንደር ለሀረር ፤ሀረር ለጎንደር ምኑ ነዉ በሚባልባት አገር ይህን ብሄራዊ ትስስር ለመቁረጥ ሌት ተቀን ሲማስን የነበር በተቋም ደረጃ አልነበረም ማለት ትዝብት እንጅ እዉነት አይሆንም፣

በሰበብ አስባብ ምርጫ መጣ ጡጫ ፣ ራብ ሲባል ጥጋብ፣ ምን ልብላ ሲባል ዱላ  እየተጋበዘ የኖረን ህዝብ መከራ እና ስቃይ የግለሰብ ጉዳይ ማድረግ በምን መለኪያ እንደሆነ ግልጥነት ይጎድላል፡፡

በራስ አገር በህይወት እና ሰርቶ መኖር በድርጅት በጎ ፈቃድ ብቻ ይወሰንባት በነበረች አገር የሆነዉ የዘመናችን ዕኩይ ኢሰባዊ ድርጊት ሁሉ ለጥቂቶች መግፋት ዉሃ በወንፊት መያዝ ነዉ ፡፡

ከሁለተኛዉ የዓለም ጦርነት ማግስት በነበረ የግዛት ማስፋፋት እና ሀብት የማጋዝ ፍላጎት እና እሽቅድምድም በግንባር ወደምትነት በዓለም የሚጠቀሱት የሚጠቀሱት አገራት እና  መሪዎች ነካከል ፡-

 • ሞሶሎኒ፣
 • አዶልፍ ሂትለር ……የመሳሰሉት የነበረዉ ትንቅንቅ አገራቸዉን ለማሳነስ ሳይሆን የግዛት አድማሳቸዉን በማስፋፋት ለህዝባቸዉ እና ለአገራቸዉ ዕድገት እና ታላቅነት ሲሉ የተከተሉት ህዘባዊ እና ብሄራዊ የወቅቱ የየአገራቱ አቋም እንደነበር ከታሪክ ድርሳናት እንረዳለን ፡፡

ቅኝ ግዛት ስር ያስተዳድሩት በነበሩት አገራትም ቢሆን ያደረሱት ግፍ በእኛ አገር በራሱ መንግስት እና ግዛት መከራ እና አሳር የከፈለዉ እና እየከፈለ ያለዉ ህዝብ እና አገር በቁጥርም ሆነ በዓይነቱ ቅኝ ገዥዎች ካደረሱበት ከዕጥፍ በላይ ግፍ እንደተሰራበት ሊናገር ፤ለመሰክር የሚችለዉ የደረሰበት ብቻ ነዉ ፡፡

ከዚህ ጋር ሳይጠቀስ የማይታለፈዉ ትልቁ የራስ ወዳዶች እና ግፈኞች ችግር ራሳቸዉን እና ግብረ አበሮቻቸዉን ከህዝብ እና ብሄራዊ የአገር ጥቅም በላይ በማድረግ ዕኩል የማይሆነዉን ዕኩል ነዉ እያሉ ራሳቸዉ የልዩነት እሾክ ዕየዘሩ (ለብ ወለድ የብሄር ጭቆና ) የጥላቻ እና የልዩነት መጋረጃ በማሰፋት ስለተጠመዱ ይህ ራሳቸዉን ከቀጥታ ዕይታ በላይ ዓይነ ህሊናቸዉን ስለሚጋርድባቸዉ አሁንም ነገም በእነረሱ መለኪያ የአገር እና ህዝብ ሞት ለእነርሱ ህይወት ፣ሲኦል እና ገነት ተለዋዋጭ እንደሆኑ በሌላዉ ላይ መጫን እና በመታበይ ክፉ የማን አህሎኝ ልክፍት ቁራኛ ሠለባ መሆናቸዉ ነዉ ፡፡

ለዚህ ሁሉ ዝርዝር መነሻ ሽብርተኝነትን በሚመለከት የብልፅግና ፓርቲ ባህርዳር ጽ/ቤት ኃላፊ  በመግለጫ እናዳስገነዘቡት የትህነግ እና መሰል ተባባሪ አካላት በሽብርተኝነት አለመወከል ትልቅ ታሪካዊ ስህተት ነዉ ማለታቸዉ ተገቢነቱም ሆነ ወቅታዊነቱ አጠያያቂ ባለመሆኑ ብሄራዊ እና አሁናዊቱን  ለማለባበስ መሞከር  ለአገር እና ህዝብ የሚጠቅም አይደለም ፡፡

በኢትዮጵያ እና ህዝቧ/ዜጎች ላይ የደረሰዉ የዓመታት ስቃይ እና መድሎ የበዛበት የግፍ አስተዳደር ባለቤትነት  በግል ወይም በቡድን ደረጃ ዝቅ ማድረግ ለምን ሲባል እንደሆነ ከነበረዉ እና ካለዉ ነባራዊ ሁነት አኳያ መጣኝ እና ሁነኛ መፍትሄ አይደለም ፡፡

ከዚህ እና ከላይ ከተጠቀሱት ዕዉነታወች በተጨማሪ ጥቂት ይታከልበት ፡-

 • የቀድሞ መንግስት (ከህወሃት-ኢህዴግ በፊት የነበረ) ህዝባዊ ሠራዊት ያለምን ቅድመ ሁኔታ እንዲበተን ፣አንዲፈርስ የሆነዉ እንዴት ነበር ፣
 • ያ ከሆነ ለምን የኢትዮጵያ ብሄራዊ እና ህዝባዊ ሠራዊት በግለሰብ ምክነያት ለአገር እና ለወገን የከፈለዉ የህይዎት እና የደም ዋጋ በባዶ እና ደመ ከልብ ሆኖ  እንዲቀር ሆነ እንዴት የቡድን ፍላጎት እና ዉሳኔ ተግባራዊ ሆነ ፣
 • ብዙ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ጥቅማጥቀሞች በዜጎች መካከል በልዩነት ሲስተናገዱ ይህ የግለሰብ ጉዳይ ወይስ የድርጅት ዉሳኔ ነዉ የሚባለዉ ፣
 • የቀድሞ ስርዓት ቅሪት፣ናፋቂ፣ ዓምላኪ……እያሉ ራስን ወደ ጣዕት ከፍ የማድረግ አባዜ የግለሰብ እንጅ የድርጅት አይደለም ማለት እንዴት ይሆናል፣
 • ባለራዕይ ማለት ማምለክ የግለሰቦች ከሆነ በድርጅት ደረጃ የነበረዉ ማስተጋባት እንዴት ግል ጉዳይ ይሆናል ፣

መቸም ያልተነካ ግልግል ያዉቃል ትናንት ገዳማት እና ተቋማት በጭፍን እና ጥላቻ በሽብርተኝነት እየፈረጁ የህዝብን የመኖር ህልዉና እና የለዉጥ ጎዳና ፍላጎት ማፈን ቀላል እና አዋጭ አማራጭ አድርጎ ይገለገል የነበረን ኃይል ዛሬ ጉዳዩም ሆነ ችግሩ የተቋም ሳይሆን የግለሰብ ነዉ ማለት አንድም የአገር እና የህዝብ መስዋዕትን እና ሰማዕትነት ማሳነስ ፣ማድበስበስ ወይም ለማስታወስ ካለመፈለግ ሲሆን በሌላ አገላለጽ በአገር አቀፍ ደረጃ የፈረሰን ተቋም ዕዉቅና በመስጠት ሁለት መልክ ይዞ እንዲቀጥል እና እንደ አሜባ በመቆራረጥ  በአገሪቷ ያለዉን የስነ መንግስት/ፖለቲካ ተቋማት ቁጥር  ከመጨመር ዉጭ ሌላ ትርጉም ሊኖረዉ አይችልም  ፡፡

እዚህ ጋ በግለሰብም ሆነ በቡድን ደረጃ ጥፋተኝነት እና ተጠያቂነት አይኖርም ማለት አይቻልም ፤ይኖራል ግብ በአገር አቀፍ ደረጃ ለሆነ ሁሉ አገራዊ እና ህዝባዊ ክብደት ያለዉ ዘላቂ መፍትሄ የሚያስገኝ ተጠያቂነት እንደሚያስፈልግ እና ለዚህም ኃላፊነት ማሳነስ ከችግር አዙሪት አያወጣም፡፡

ብልፅግና የኢህዴግ ተከታይ እና ተኪ አስከ ሆነ ድረስ እና ግንባር ድርጅቶች ከስመዉ አንድ ብሄራዊ ድርጅት ሆኖ አገር በሚያስተዳድርበት ሁኔታ ላይ እያለ የቀድሞዉን ግንባር እና አዉራ ድርጅት አባል እንዳለ እና አንደነበር መዉሰድ በምን ምክነያት ይቻላል፡፡

ለግጭትስ መነሻዉ አንዱ ሌላዉን የመቀበል እና ያለመቀበል ችግር መሆኑ እየታወቀ  በህግ ከታገዱ ህጋዊ ነኝ ብሎ ሲንቀሳቀስ የነበር የህግ የበላይነት ለማስከበር በተካሄደ ብሄራዊ ተልዕኮ እና የተገኘ ዉጤት ላይ ድርጅቱ ህልዉናዉን አጥቶ ሳለ  አለ ብሎ እንደ ድርጅት አይከሰሰስም ፤አይወቀስም ማለት በምን ስሌት ይሆን የሚለካዉ ፡፡

ለማንኛዉም በአገር ደረጃ ለተፈጸመ ዕዉነታ ማንኛዉም ጥፋት የአገር ህደት፣ የጦር ወንጀል፣ የዘር ፍጅት ወይም ሽብርተኝነት (  ወዳጅ  እና ጠላት ፤ ታማኝ እና መናኝ ፣ ጨቋኝ እና ተጨቋኝ ወዘተ በሚል መከፋፈል ) ይባል ማን እንደ እኛ አገር ህዝብ እና መንግስት ሊኖር ይችላል ፡፡

ለዓብነት የጎረቤት ሱዳን መንግስት የመንግስት ለዉጥ ከአልበሽ ወደ በሄራዊ ሽግግር መንግስት ሲሆን የፖለቲካ ስርዓቱን እና ህገ መንግስቱን ለማገድ ሳምንት አልፈጀም ፡፡ ዕኮ እኛ አገር የሆነዉ በሌላዉ እና ዕዉነተኛ ፍርድ በሚሰጥበት ምድር ቢሆን ከእኛ አገር የከፋ የአሰተዳደር ብልሹነት (በስልጣን መታበይ፣ ምዝበራ፣ በዘመድ አዝማድ የህዝብ አገልግሎት ማዛነፍ፣ በአቅም አለመኖር)፣ የአገርን እና ህዝብን ጥቅም አሳልፎ በመስጠት፣ በሰባዊ አየያዝ ፣ በጅምላ ፍረጃ እና ለይቶ ማሳድደድ ፣የራስን ህዝብ ቁም ስቅል ማሳየት ……..በዓለም አቀፍ ችሎት የሚታይ፣ የጉዞ እና የዓለም ዐቀፍ ግንኙነት መብት የሚሳጣ ጥፋት ከዚህ በላይ ምን ሊሆን ይችላል፡፡

ከዚህ እና ከሌሎች ምክነያታዊ ሁነቶች አንጻር  እዉነተኛ እና ዘላቂ ብሄራዊ የዕርቅ እዉን እንዲሆን በማድረግ አገርን እና ህዝብን ከተመሳሳይ ሊደርስ ከሚችል ጥፋት የመታደግ የሀቅ ስራ መስራት ከተፈለገ በብልጽግና ፓርቲ የክልል የድርጅት ኃላፊ  የሆኑት አቶ አብርኃም አለኸኝ የሰጡት የተጠያቂነት መግለጫ  እዉነትነቱ የማያነጋግር ነገር ግን ለጥቂቶች መራር ቢሆንም ለህዝብ እና አገር ብሄራዊ አንድነት ፣ዕድገት እና ብልፅግና ሲባል  ይህን ዕዉነታ መቀበል እና ከዳግም ጥፋት ራስን መታደግ ምርጫ እና ፍላጎት   ሳይሆን  ህዝባዊ ቁርጠኝነት የሚጠይቅ የህልዉና  ጉዳይ መሆን አለበት ፡፡

                                                     ማ

እናት አገር ለምንጊዜም ትኑር !!!

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.