ይድረስ ለኢትዮጵያዊው ሙሴ ጠ/ሚር አቢይ አህመድና አገር  ወዳዶች  (ከአባዊርቲ)

Abiy 7መግቢያ!
የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት: ያሸለባችሁም ይሁን በህይወት ያላችሁ ፣ ከኮሪያ እስከ ካራማራ  ናቅፋና ቃሩራ ፣ በአራቱም መአዘናት : ከሱማሌ እስከ ፅልመት ጉጅሌ የተዋዳቃችሁና ኢትዮጵያዊነትን በደማችሁ ያቆያችሁልን ድንቆች – አንረሳም!!!!
ክቡር ኤታማዦር ድንቁ መሪያችን፣ ልጃችን፣ ወንድማችን፣  የኢትዮጵያ ትንሳኤ ባለሙሉ እንደራሴው አቢይ አህመድ – በአንቱታ ጀምሬው እጨርሰዋለሁ – ክብርና መለዮ ላንተ ይሁን!!!!
የፓርላማውን ውሎ ተከታተልኩት:: በሀዝንና ደስታም አዳመጥኩት:: ግን ብዙም አልገረመኝም ምስጢር ሆኖ የቆየው ጉዳይ:: ባለፉት ሁለት አመታት ኢትዮጵያውያንን አጥብቄ እለምን የነበረው ይህንኑ ልቤ ጠርጥሮ በመሆኑ ነው:: የአቢይን ችግርና ያለበትን ውጥረት ከፈጣሪና ከእመቤት ዝናሽ በቀር ማንስ ያውቃል ብዬም ነበር:: የፅልመት ጉጅሌዎቹ እንኳ እንደተጠበቀ ሆኖ ኢትዮጵያዊ ጠረን ይኖራቸዋል ብለን ያሰብናቸው ሁሉ አፍቃሬ አቢይ ብለው አሉን:: ያጨለመባቸው ቢኖር እንጅ በቀላሉ መረዳት አይከብድም ነበር የዚህን ድንቅ ወጣት መሪ ስብእና:: ይሁን አሁን አልፏል:: የኢትዮጵያ አምላክ ከነዚህ አጋንንት መዳፍ አውጥቶ በክብር ላገራችን ድል ስላበቃህና ስላበቃን ምስጋናዬ ላንተም ለፈጣሪም የላቀ ነው::
ክቡር መሪያችን ጠ/ሚር አቢይ!
እኔ በበኩሌ እነዚህን የፅልመት ጉጅሌዎች ክብር ሰጥቼ ጁንታ አልላቸውም:: እነ ጄኔራል ፍራንኮ አይነቶቹ ናቸው ጁንታዎች:: ትንሽም ብትሆን አገራዊ ራእይ ነበራቸውና:: የራሱን ወገን ያውም ጨለማን ተገን አድርጎ ያውም ያበላውን: ያጠጣውን ህዝባዊ አለኝታ ከጀርባ በጩቤ የሚበልት ጁንታ ሊሆን? በጭራሽ! የፅልመት ሎሌ ነው እንጅ!! እናም በመሚመጥናቸው ይጠሩልን ክቡር ጠ/ሚር::
በቀደም በፓርላማው ፈረንጆቹ ጆሮ ያደረስክልኝ የፍፁም የጥንት የድንቆቹ ስመጥር የኢትዮጵያ እውነተኛ ፖለቲሻንስ : የነ አክሊሉ ሀብቴ: ምናሴ ሀይሌ: ከቴ ይፍሩ አይነት ቀጠን ብላ ከብረት ዘንግ የከበደች የኢትዮጵያዊነት መገለጫን ትዝብታዊ ” ፍራንካችሁ ይቀራል እንጅ ኢትዮጵያዊነትን በዶርሲሳ አይመቸኝም ” አይነት ያልካት በታሪክ መዝገብ ሲወሳ ይኖራል – እኔም ደግሜ መለዮብያለሁ!!!
ውድ አቢይ!
ፈጣሪ የህዝባችንን የ ሰላሳ አመታት መከራና ሰቆቃ ተገንዝቦ አንተን የመሰለ ድንቅ መሪ ባይሰጠን ኖሮ እንደነዚህ የክፉውች ሴራ እንዲህ በቀላሉ አንገላገላቸውም ነበር:: የኢትዮጵያ አምላክ መቼስ አሸልቦ ያውቃል? እነዚህ ከይሲዎች ያጣመሙትን ለማቅናት አንድ ትውልድ ያህል የሚፈጅብን ቢመስልም ያንተን የ ሁለት አመት አካሄድ ላጤነ በ አምስት አመት ብቻ ለአገራችን ተአምር እንደምትፈጥር ቅንጣት አልጠራጠርም:: ብዙ ሀተታ ሳላበዛ ደስታዬን እንዲህ ካልኩ በሁዋላ ለመንግስትና ኢትዮጵያን ለሚል ዜጋ ሁሉ ከድል በሁዋላ ምን ላይ ማተኮር እንዳለብን ለማሳሰብ እወዳለሁ::
ሀ) ዳያስፖራውን በተመለከተ:
በትምህርትና በመሳሰሉት ፕሮፌሽን የተሰለፋችሁ የኢትዮጵያ ልጆች እናት አገር ትፈልጋችሁዋለች:: አገር መግቢያው ዘመን አሁን ነው:: ስደት ወደ  እናት ሀገር እንዲሉ:: 26 ሚሊዮን ወጣት ቤት ከዋለ ሰነባበተ:: እንኳንስ በኮረና ምክንያት ቤት ውሎ ቀርቶ ለ 30 አመታትም ቢሆን በበኩሌ ከቤት እንደወጣም አልቆጥረውም – በተለይም በገጠሪቱ ኢትዮጵያ በአራቱም ማእዘን:: እነዚህን ወያኔዎች  ሆን ብለው  በራሳቸው አምሳል ለ 3 አስርተ አመትት ያደነቆሩብንን ትውልድ መመለስ እንኩዋ ባንችል አሁን የተወለዱትን ይሁን ወደፊት የሚወለዱትን ለመታደግ ይቀላልና ነው። እናም ወገኖቼ የኢትዮጵያን ትንሳኤ ለማፋጠን ዛሬ ነገ የማይባል ጉዳይ ስለሆነ የሚመለከተው ክፍል ከልብ ይምከርበት አደራ::
ለ) በውጭው አለም ትውልደ ትግራይ የሆናችሁ የወያኔ አቀንቃኞች፣ ንብረት ተካፋዮች፣ አሽቃባጮች በሞላ!
በነዚህ የምድር ጉዶች መቃብርም ላይ ዛሬም እንደትላንቱ ማላዘኑን አቁሙና ደሀውን የትግራይ ህዝብ ተመልከቱ:: እባካችሁን ይቺ አለም አላፊ ናት። በየስርቻው የተቀባበላችሁትን የኢትዮጵያ ሀብት መልሱ አልተባላችሁ፣ ምኑ ነው አሁንም የሚያወራጫችሁ? በናንተው ስም የፈሰሰው ደም ይሆናል እንዲህ አቅላችሁን አስቶ ለነዚህ የሳጥናኤል ጉጅሌዎች አሁንም የሚያከራክራችሁ። የኢትዮጵያ ትንሳኤ እውን ይሆናል፣ እኛም ሰላማችንና ብልጽግናችንን እውን እናደርጋለን። በከንቱ ባትደክሙ ይሻላል። እነ አሉላ ሰለሞን አይነት ማፈርያዎችን ነው እያልኩ ያለሁት። እናንተን ብሆን የሆነ ደሴት ሄጄ እደበቃለሁ። የናንተን ውራጅ ወይም “ጃላባቴ” ተላብሰው ሚዲያ መሳይ 360 ዲግሪ የዞረባቸውን ፍርፋሪ ለቃሚዎችን እንኳ ከቁምነገር ቆጥሬ ርእስ አንቀጽ ስለማልሰጣቸው ይዛችሁዋቸው እዛው ተጠቃለሉ – አስነዋሪዎች!
ሐ) ተፎካካሪ ፓርቲዎች
እናንተን ብሆን ወቅቱ የመሰባሰቢያ እንጅ የመለያያ ባለመሆኑ ጠቅለል ማለቱ ብልህነት ይመስለኛል። ለምሳሌ፣ ከዚህም ቀደም ደጋግሜ እንዳሳሰብኩት የነ ኦባንግ፣ ዶር ብርሀኑ፣ ፓርቲዎች የሆነ ቅንጅት ፍጠሩ እስቲ ። የ 97ቱን ቅንጅት መድገሙ ምን ሀጢያት አለው ቅንነቱ ካለ? ሌሎች የነ መረራ አይነት ግልቦች እራሳችሁን በጡረታ ብታገሉ እንዴት በክብር በተሸኛችሁ። ሁሉን ታዝቤ እንደ ፕሮ መረራ ጉዲና ያነሰብኝን ሰው አላገኘሁም። ለምን? አንድ ዘመን በአስተዋይነቱና ግልጽነቱ ብሎም ኢትዮጵያዊ ጠረኑ እጅግ አድናቂው ነበርኩና። ምን ያደርጋል! ጁዋር ከሚሉት ቅጥረኛ ዋለና አጋጉል ሆነ። ሁላችንንም አሰደበን፣ አዋረደንም – አንረሳም!  ። እናም ጡረታው ምናልባት በቅርብ የሞተውን ክብሩን ይመልስለት ይሆናል ከሚል እሳቤ ነው።
መ) የጎሳ ፖለቲካና መጪው ፈተና!
የሳጥናኤል በትር በአገራችን ካረፈ ከ 83 ጀምሮ በጎሳ ክፉኛ ስለታመስን እንዲህ በቀላሉ ቶሎ አንላቀቀውም። ብዙ ስራ ይጠብቀናል። የቀበሩልንን ፈንጂዎች ለመልቀምና ለማክሸፍ ገና ብዙ ይቀረናል። ጠባሳውም እንዲህ በቀላሉ የሚሽር አይሆንም ። የሁላችንንም ህብረትና አንድነትን ይጠይቃል ። የራያና ወልቃይት ጉዳይ እጅግ ለማሰብ የሚከብድ ፈተና ይመስለኛል። ሆኖም ቅንነቱ ካለና ከተደማመጥን የማንወጣው ችግር አይኖርም ። እዚህ ላይ ነው የየጎሳው ተጠሪዎች ቆም ብለው ማሰብና ማቀድ ያለባቸው። ለጠባቡዋ ደሳሳዋ የጎሳ ጎጆ   የከፈቱትን ልብ ፣ ለባለጉልላቱ ታላቁ የኢትዮጵያ ቤተመንግስት ቦታ አያጡም ብዬ አስባለሁ። የተሞከረብንን የ 30 አመታት እርባናቢስ ፖለቲካ ልኩን አየነው። ይብቃን ስለወደመው ነፍስና ንብረት!! ልብ ያለው ልብ ይበልልኝ።
ሰ) ምስጋና!
በዚች ሶስት አመታት በየቤታችሁም ይሁን በየስራ መስካችሁ ለኢትዮጵያ የቁርጥ ልጆች በሙሉ ከልቤ እጅግ እንዳመሰግን ይፈቀድልኝ። ሁላችሁንም በጽሁፍና በስራችሁ እንጅ በነፍስ አላውቃችሁም። ተስፋ ስቆርጥና የአገሬ ጉዳይ ሰላም ሲነሳኝ በተለየ ሁኔታ ሞራሌን የምታድሱ (የዶር አቢይ እንደተጠበቀ ሆኖ) ሁለት ጀግኖች አላችሁ በኔ እሳቤ፣
1) ጦማሪና መምህር ስዩም ተሾመ፣
ስለዚህ ጀግና ሰው ለመናገር አንደበት የለኝም። እንደው በአጭሩ እንኳን የስራህን ፍሬ ምንም ክፉ ነገር ሳያገኝህ ለማየት አበቃህ። በተለይ የዊኪና የልዩ ትንታኔህን አይቶ ባንተ የማይኮራ ኢትዮጵያዊ አይኖርም ። የኢትዮጵያ አምላክ ረጅም እድሜና ጤንነት ይስጥህ። የትንታኔህንና ወኔህን፣ ቁጭትህንና አገር ፍቅርህን መገለጫዎችህን በስስትና ጭንቀት ነበር የምከታተለውና እንኳን ለዚህ አበቃህ፣ አበቃን ስዩሜ። ያ መልኬ የምትለው ለግላጋ ልጅም የዋዛ አይዶለችም። ፈጣሪ ይጠብቃችሁ
2) ኦቦ ታዬ ደንደአ – ሌላው ፊታውራሪና ግልጹን ተናግሮ የመሸበት የሚያድር ጀግና። የደቦ ፖለቲካ ምኑም ያልሆነ፣ የማያስመስል ወንዳታ። ጁዋር የሚሉት ባለጊዜ ምንደኛ በሚፈራበት ዘመን ፊትለፊት የተጋፈጠ፣ እውነቱን ለመናገር ወደሁዋላ የማይል ድንቅ ሰው – አንተም እንኳን ደስ አለህ። የተዋለዱኝ ይሁኑ አብረውኝ ያደጉት የዖሮሞ ልጆች ያንተ አይነቱ እንጅ የወያኔን የእስር ቤት ገፈት ቀምሰው ተመልሰው የወያኔን የውስጥ ጫማ ሶል የላሱ አይነት አልነበሩም። አንተን አንድ ካልኩ ሌሎች ብዙ የማላውቃቸው የአንተው አይነቶች ትኖራላችሁ ብዬ ተስፋ ስለማደርግ ባንተ በኩል አድናቆቴ ይድረሳቸው።
በመጨረሻም!
ኢትዮጵያዊነት ሁልጊዜም ረመጥ እሳት ነው:: አይጠፋም በመጨረሻም አሸናፊ ነው:: ህውሀት ኢትዮጵያዊነት ላይ ለ30 አመታት ዘመተ ሆኖም በኢትዮጵያዊነት ድባቅ ተመታ። አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ትክክል ነው ” ኢትዮጵያዊነት አሸነፈ”። የኢትዮጵያዊነት ጸጋቸው የተገፈፈ ሁሉ በመጨረሻም ኮስምነው ሳያምርባቸው ተነው ይጠፋሉ። ይህው ነው።
ክብርና ሞገስ ለኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት!! ልኡል እግዚአብሔር አገራችንና ህዝባችንን ከክፉ ይጠብቅልን !!!

5 Comments

 1. የመከላከያው በተለይም የአማራው ኃይል ለጊዜው መብቱን ያስከበረ ይመስላል። ያንተ ሙሴ የሚቀጥለው እርምጃው ፣የኢትዮጵያ ህልውና ወሳኝ ያደርገዋል ። የፓርላማው ንግግር አዲስ ምእራፍ ከፋች ሳይሆን አይቀርም ብለን ተመኝተን ነበር።በተረኝነት ወታደራዊ ባለህበት እርገጥ ልምምድን እያየን ነው። የጠቅ /ሚሩ ምንነቱን ያወቅነው አሁን በወያኔ የተወሰደው እርምጃ ብቻ ሳይሆን ያለፈዉን አመታት ምን እርምጃ እንደወሰደ በማጤን ነው።ኢትዮጵያ፣ኢትዮጵያ በማለቱ ማንም ደስ ይለዋል። በተረኝነትና ፣አብረውት በስም ጠቀስህ የጠራሀቸው ጨምሮ ፣ ከዚህ በፊት ምን እንዳሉና. እንደፃፉ ስለምናውቅ አምልኳቸው ባይ አያስፈልገንም።
  ምናልባት ከገባህ አንድ በኢትዮጵያ ምድር በኃይለሥላሴ ዘመን የሆነውን ነግሬ ላብቃ።
  ያው መቼም በ16 ኪዳነምሕረት ትከበራለች። በተባለው ቀን በልጅነቴ እናቴን ተከትዪ ከሽሮ ሜዳ በላይ የእንጦጦ ኪዳነምሕረት ሄጄ ነበር።የቤተክርስቲያኑ ቅጥር ግቢ ሞልቶ ህዝበ አዳም በውጭ ተትረፍርፏል።በግቢው ውስጥ አንድ. ብጫ የለበሱ ባህታዊ ይሰብካሉ ፣እንደሁሌም ሌላው ሰባኪ እንሚያደርገው ሁሉ ሲያሳርጉ ኢትዮጵያን አወድሰው፣ እግዜርን ሲማፀኑ ።አፄ ኃይለሰሥላሴን ሺህ ዓመት. አኑርልን ” ብለው ሲደመድሙ ያልታሰበ ጉድ ተፈጠረ። ሕዝበ አዳም እልል ሲል ፣ከየት መጡ ሳይባል ባህታዊዉን እያዳፉ ፣በጥፊ እያጮሉ ይዘውት ሲሄዱ ፣ህዝቡ ሲያጉረመርም. ዞር ብለው ፣ከሺ ዓመትስ በኋላ ማን ይግዛ ብላችሁ ነው።ለዘልዓለም ነው እንጂ ብለው ባህታዊውን እየረገጡት ወሰዱት። በልጅነት አይምሮ ስላልገባኝ ሲከነክነኝ አርፍዶ ፣በቁርስ ላይ እናቴን ስለሁኔታው ጠየቅኋት። ለመሆኑ ሰው ለዘልዓለም ይኖራል ወይ ብዪ ስጠይቃት፣በቅርብ ያረፈችው አያቴ ወድያው ናፈቀችኝ።አይ እሱማ የትአለ ብላ ሳትጨርስ አምባዋ ቅርር አለ። አይ ደብዳቢዎቹ አሽቃባጮች ናቸው ስትለኝ፣አባቴ ነገሩን በትዕግሥት ከሰማ በኋላ፣አይደለም ዦሮ ጠቢዎች ናቸው አለ። የአፄ ኃይለሥላሴንም መጨረሻ ያው አይተነዋል ከነአሽቃባጭዎቹ ጋር።

 2. Wirti:

  Stop your propaganda. If you are such a low life creature, you may continue to worship the con artist abiy ahmed. After so much sacrifice by the gallant Amhara forces, your wishy washy ahmed is saying that wolkait/raya belong to agames. While all the attention is on agame land, so many innocent Amharas are slaughtered in benshangul, woillega and other so called oromo lands.
  Sooner or later, you people will pay the price like the agame cowards.

 3. አቶ አባዊርቱ፣
  ስለጠፋህ የተገላገልንህ መስሎኝ ነበር። ውስጥ ውስጡን ስትተበትብ ከርመህ እንደገና ብቅ ብለሃል። ሙሴአችሁ ችግር የገጠመው ሲመስላችሁ ተሰባስባችሁ ፕሮፓጋንዳ ታራግባላችሁ። ምናለ ፊት ለፊት ምን መሆናችሁን ተናግራችሁ ብንወያይ።የሰፊው ድምፅ አስመስሎ ማራገብ ግን ትንሽነትን ይዘክራል ።

 4. አባ ዊርቱ ሲመቾት ኢትዮጵያ ይላሉ እንጂ ልብዎ ዉስጥ ያለዉ ኦሮሙማ ነዉ በሱ ሲመጡቦት እንደ እብድ ያደርጎታል። ታየ ደንዳ የእርሶ አርበኛ መደበኛዉን የኢትዮጵያ ባንዲራ አይኔን አያሳየኝ ብሏል እርሶስ ዘመን ስለተሻገረችዉ የኢትዮጵያ ባንዲራ ምን ይላሉ? አብዲሳ አጋ፤ጃገማ ኬሎ እና ስፍር ቁጥር የሌላቸዉ ኢትዮጵያን የሞቱለትና የተቀበሩበት ነዉ እዉን እንዲህ ክብሩ ከደመቀዉ የኢትዮጵያ ባንዲራ የግብጽና የአረብ ባንዲራ ይሻላችሗል? እርሶስ አይበለዉ እንጂ ቢያርፉ ኢራቅ ነዉ በኢትዮጵያ ባንዲራ የሚቀበሩት? የኦሮሙማ ባንዲራ የኢራቅና ግብጽ ባንዲራ ነዉ ገጀራዉን አላሳሉትም እንጂ እየተጠቀሙበት ነዉ።

  36 ጊዜ የሰለጠነዉ የኦሮሞ ጦር ምነዉ ልምድ እንኳን እንዲያገኝ ወደ ሰሞኑ ጦርነት ጎራ ያላለዉ? አዩ ነገ ችግር በየት እንደሚመጣ አያዉቁም አንድነቱ ይሻላል። ባለፈዉ እስክንድር ነጋን ምን እንዳሉት እናዉቃለን። እስክንድር ሊያጨናግፍብን ይችላል ብለዉ ጠመዱት እንጂ እስክንድር ብሄር የሌለዉ ጥሩ ኢትዮጵያዊ ነበር። መቼም ታየ ደንዳን ወድዶ እስክንድርን መጥላት ሂሳቡ ይገባናል አዳነች አቤቤንም ልእልቷ ብሎ ሰማይ መስቀል ክፉ በሺታ ነዉ። ይመቾት እስቲ መልካም አመትበአል ፈረንጂ በደካማ ጎናችን እየገባ መቀለጃ ያደርገናል ከኢትዮጵያዊነት ወርዶ መከስከስ ያሳዝናል። እርሶ ኢትዮጵያዊነትን ያጠነክራሉ ስንል እርሶ ኢትዮጵያዊነት ከኦሮሞ በሗላ ነዉ ይሉናል እስቲ ይሁን ይመቾት።

 5. አሉላ ሰለሞን አንብብ ብርሀነ ምናምን የተባልከዉ አንብብ ቴድሮስ አዳኖም አንብብ ምን ይዋጣችሁ። ፈረጂን አታስቸግሩ አታጨናንቁ። እናንተ ነብሰ ገዳዮች የኦትዮጵያ አምላክ እድሜ ልክ ያቃጃችሁ እፍረት የላችሁም ተደበደብን ብላችሁ ሰልፍ ትወጣላችሁ ይሉኝታ እናንተ ዘንድ ከጠፋ 100 አመት ሞላዉ በአሜሪካ ድምጽ አምባሳደር ፍስሀ የተባለዉ ትግሬ በዛ እድሜዉ እንደዛ ሲዋሺ ማንን እንመን? የኢትዮጵያ አምላክ በሰራችሁ ግፍ ልክ ይስጣችሁ ከዚህ በላይ ቅጣት የለም መቼም። ሌላዉ ተረኛ ዘረኛም ከዚህ ካልተማረ ይለበለባል። ለፈረንጆቹ የሰራችሁትን ስራ በቪዲዮ እንልካለን እናንተ እፍረተ ቢሶች
  አባ ዊርቱ የወልቃይት ጉዳይ ምኑ ነዉ ችግሩ አሁን ትላንት አይደለም እንዴ የትግሬ ፋሺስት ወታደር መጥቶ እንዲሰፍርበት የተደረገዉ? ከሻቢያ የተወሰደዉ አለሀገሩ ሲመለስለት ለባለ ርስቱ ለወልቃይት ህዝብ መመለስ ምንድነዉ ችግሩ? ትግሬም ከዚህ ሁሉ ወንጀል በሗላ ወልቃይት ዉስጥ መኖሩ ለሱም ጥሩ ስላልሆነ ጠጠር ወርዉሮ መመለስ ነዉ ያለበት። ነገር አያክብዱ እንጂ አካባቢዉ ነጻ ወጥቷል ኢትዮጵያን ከዛ በኩል ሊጠብቅ የሚችል እንዳዩት ያ ህዝብ ነዉ ህዝባዊ ድጋፋችሁን ስጡት አታዋክቡት።
  ዶ/ር አብይ ድልን አትደልቁ ብሏል የጦሩን ነብስ ያዳነዉን ሀይል ሊያሸማቅቅ ጦርነት ተገጥሞ ድል ካልተደለቀ ምን ይደለቃል ሰዉ በማሸነፉ መሬት ወርዾ ሙሾ ያዉርድ? ምነዉ እንደዚህ ለትግሬዎች ስስ ልብ ኖራቸዉ ለሌላዉ ያላደረገዉን? አሁንም ይፈሯቸዋል እንዴ

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.