ከ300 በላይ ቤተ-እስራኤላውያን ከኢትዮጵያ እስራኤል ገቡ

Untitled
በአብዛኛዉ ህጻናትን ልጆቻቸውን በጃቸዉ የያዙና አበሻ ቀሚስ የለበሱ ሴቶች የሚገኙበት የቤተ -እስራኤላዉያን ቡድን ዛሬ በቤንጎርዮን ዓለም አቀር አውሮፕላን ጣቢያ ሲደርሱ የእስራኤልን ሰንደቅ ዓላማ በማዉለብለብ መሬት መሳማቸዉን አሶሽየትድ ፕሬስ ዘግቦአል። በእስራኤል አዲስ ገቢዮች ሚኒስቴር በፒና ታምኖ ሸቴ የተመራዉ እና የቤተ-እስራኤላዉያኑ ቡድን በቤንጎርዮን ዓለም አቀር አውሮፕላን ጣቢያዉ ሲደርስ የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔትናኛሁ እና ተተኪያቸዉ ቤንጋንዝን ጨምሮ የእስራኤል መንግሥት ከፍተኛ ባለስልጣናት አቀባበል አድርገዉለታል።ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔትኒያሁ ለቤተ እስራኤላዉያኑ አዉሮፕላን ማረፍያ በተካሄደዉ የአቀባበል ስነስርዓት ላይ «ባለቤቴ ሳራ እና እኔ ዓይናችን በእንባ ተሞልቷል» ሲሉ ደስታቸዉን ገልፀዋል። የኮሮና ተኅዋሲ ስጋትን በተመለከተ አዲስ ገቢዎቹ ለሁለት ሳምንታት ያህል ማቆያ ከተቀመጡ በኋላ ወደ ተዘጋጀላቸዉ መኖርያ ስፍራ እንደሚሄዱ ታዉቋል። ቤተ-እስራኤላዉያኑ ወደ እስራኤል የገቡት በቅርቡ የእስራኤል መንግሥት 2000 ቤተ እስራኤላዉያንን ከኢትዮጵያ ለማምጣት ያሳለፈዉን ዉሳኔ ተከትሎ ነው። ዛሬ እስራኤል የገቡት ቁጥራቸው 316 ሲሆን ዛሬ ማታ ተጨማሪ ቤተ- እስራኤላዉያን ከኢትዮጵያ ወደ እስራኤል ይገባሉ ተብሎም ይጠበቃል።
DW

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.