እንደሀገር የተጀመረው የህግ የበላይነት መከበር የሚጠናቀቀው ወያኔ ትህነግ በሽብርተኝነት ሲፈረጅ ብቻ ነው !!!

128924121 3011765105727468 4274833871457749738 o
የወያኔ ትህነግን ሽብርተኝነት አምና ያልተቀበለች ሀገር ሽብርተኛንም ሆነ ሽብርተኝነትን የመቃወም የህግም ሆነ የሞራል ብቃት የላትም። ወያኔ ትህነግ አስተሳሰቡም፣ አርማውም፣ መላ መዋቅሩም በመላው አለም ጥቅም ላይ መዋል የለበትም።
በወያኔ ትህነግ ስም የተመዘገበ ማንኛውም ንብረት ምንጩ ዘረፋ ስለሆነ ተወርሶ ለኢትዮጵያ ህዝብ ገቢ መሆን አለበት።
በአለም ታሪክ የወያኔ ትህነግን ያህል በሰብአዊነት ላይ ወንጀል የፈጸሙ ግለሰቦችም ሆኑ ቡድኖች አሉ ከተባለ ሁሉም በአሸባሪነት ተፈርጀዋል።
ስለሆነም ወያኔ ትህነግን አሸባሪ ብላ ያልፈረጀች ሀገር ለዜጎች ክብር ፣ ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ሁለንተናዊ ደህንነትና ለሀገር ሉአላዊነት ደንታ ቢስ ስለሚያደርጋት በራሷ ፈቃድ ታሪካዊ ነፃነቷ እንዲገረሰስና ክብሯ እንዲደፈር ፈቅዳለች ማለት ነው።
ወያኔ ትህነግን ሽብርተኛ ብሎ ያልፈረጀ ሀገርና ህዝብ ለህግ የበላይነት መከበር የተከፈለውን ሁሉንም መስዋዕትነት ፈቅዶ ዝቅ እንዳደረገው (እውቅናና ክብር እንደነፈገው) ይቆጠራል።
እንደሀገር የተጀመረው የህግ የበላይነት መከበር የሚጠናቀቀው ወያኔ ትህነግ በሽብርተኝነት ሲፈረጅ ብቻ ነው። ይህ ባልሆነበት ነባራዊ ሁኔታ በግፍ የተከፈተብን ጦርነትና የዘር ጭፍጨፋ እንዳልተጠናቀቀ ይቆጠራል ።
አቶ አብርሃም አለኸኝ
የአማራ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ሀላፊ

2 Comments

  1. እንግዲህ ይህን የሚያውቀው የርሶው ፓርቲ መሰለኝ፤፡ ቢሆን እኔም ደስ ይለኛል [ህግ አዋቂ ባልሆንም] ፡፡ እንደው ግን ባይሆንስ? ምን ሊያደርጉ አሰቡ? ያለዎት ምርጫ እኮ 1) ፒፒን መልቀቅ እና ይህን ሃሳብ የሚያራምድ ፓርቲ ጋር መቀላቀል (እስከማውቀው ድረስ አብን ብቻ ነው ይህን ሃሳብ በድፍረት ያቀረበ)፡ 2) ፒፒን ለቀው አርፈው መቀመጥ;; [though it is far fetched] 3) አማራን ከኢትዮጵያ ለመገንጠል መታገል፤፤ ያለበለዚያማ፤ እንደዚህ ተማረው ሃገርን የሚያህል ነገር “የሞራል ብቃት የላትም” ብለው በአፍ ብቻ ከቀሩ ጓደኞችዎም ቢሆኑ ይታዘብዎታል ብዬ ነው፡፤

  2. የወንድሜን ሀሳብ ማንም ስብእናን የተላበሰ ጤናማ ሰው ሊለው የሚገባ ሀሳብ ነው። ናዚም ሆነ፣ ፋሽስት ከዚህ የበለጠ ግፍ ምን ሰርተው ነው የተወገዙት? ወያኔ ራሱግንቦት 7 ን፤ ኦነግን፣ እነ ታማኝን በአሸባሪነት የፈረጃቸው በጦራችን ላይ፣እና በማይካድራ ሌላውን ት ተን ከተፈፅመው አረመናዊ ድጊጉት የበለጠ ምን ሰርተው ነው ? ይህን ለማውገዝ አማራ፣ ኣሮሞ፣ ሶማሌ …ወዘተ መሆን አያስፈልግም።ሰው መሆን በቂ ነው።
    አማራው ግን በተለየ ሁኔታ እንዲጠቃ፣ እንዲዋረድ ስላረጉት ፣ ” ነፍጠኛ ” እያሉ አንቁዋሸው ለባለጌዎች አፍ መፍቻ ስላረጉት፣ በርግጥ አማራው ወያኔን ሳይቀብር መተኛት የለበትም። እርግጥ ነው የወያኔ አባላት ሁሉ ወንጀለኛ ላይሆኑ ይችላሉ፣ ግን ደግሞ ከኢትዬጵያ ህዝብ የሱዳን ህዝብ ይሻለኛል የሚሉ፣ ጎጃም ከሚለማ፣ የሲናይ በረሀ ቢለማ እመርጣለሁ የሚሉ ግልልገ ጁንታዎች እንዳሉ በተለይ አማራው ላፍታም ሊረሳው አይገባም።
    ከዚህ ውጭ ፣ ትህነግ ተፈር ጆ አይፍረስ የሚል ቀለቡ የቀረበት ወይንም የነሱን ገቢር ሊወርስ ያሰበ ብቻ ነው።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.