“የወልቃይት ዳንሻ ህዝብ ደስታውን ለመግለፅ ባዘጋጀው የድጋፍ ሰልፍ ላይ ምን አለ?”

 በሚል ርዕስ በዝግጅት ክፍላችን የተዘጋጀውን አጭር ዶክመንታሪ የ YouTube አድራሻችንን ሊንኩ ተጭነው ይመልቱ፤
በየጊዜው በ YouTube አድራሻችን የምንለቃቸውን መረጃወች ለመከታተል ይረዳችሁ ዘንድ subscribe ያድርጉ፡፡
የአማራ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት

1 Comment

 1. ፋሽሽታዊዉና ጉግማንጉጉ ትሕነግ /ሕወሀት ምዕራብ ትግራይ ብሎ ሰይሞት የነበረዉ ዞን የሚያጠቃልለዉ ወልቃይትን ፤ጠገዴን ፤ሁመራንና ጠለምትን ነዉ፡፡ይህ ሰፊ አካባቢ ከ 320 ዓ.ም.ጀምሮ አስከ 1968 ዓ.ም.ብሎም 1983 ዓ.ም. ድረስ ይተዳደር የነበረዉ በጎንደር ጠቅላይ ግዛት ነበር፡፡በመሰረቱ የጎንደርና የትግራይ ወሰን የሚለየዉ የተከዜ ወንዝ ነዉ፡፡ይህንንም ታሪካዊ ሂደት “የወለቃይት ጉዳይ” የሚለዉን መጽሀፍ ደርሶ ታሪካዊዉን ዳራዉን አቶ አቻምየለህ ታምሩን አፍታቶታል ፡፡ ለዚህም ሊመሰገን ይገባዋል፡፡
  ወያኔ ትግል ሲጀምር በ 1968 ዓ.ም. ባወጣዉ ማኒፌስቶ አካባቢዉን የትግራይ አካል ነዉ በማለት ተሸቀዳድሞ ጠቅሶታል፡፡ በማስቀጠልም ቀስ በቀስ አካባቢዉን በመሳሪያ ሀይል ተቆጣጠረዉ፡፡
  አካባቢዉ የትግራይ ያለመሆኑን እያወቀ፤ ሆን ብሎ ተከዜን በመሻገር ይህን ያደረገበት ምክንያት የሚከተሉት ናቸዉ፤
  • ትግሉን ሲጀምር ከመንግስት የሚደርስበትን ዉጊያ ለመከላከል ወደ ሱዳን ለመሸሽ ማፈግፈጊያ በመፈለጉ፤
  • ለትግሉ የሚያስፈልገዉን ስንቀና ትጥቅ ከሱዳን ለማጉዋጉዋዝ፤
  • አካባቢዉ በጣም ለም በመሆኑ ለወደፊት የገቢ ምንጪ ያስገንልኛል በሚል እሳቤ በመያዙ፤
  • ከትግራይ ሪፑብሊክ ምስረታ በሁዋላ ከዉጪ ሀገራት ጋር ለመገናኘት፤
  • አካባቢዉ በጣም ለም በመሆኑ ከጻነት በሁዋላ ለታጋዮች እንደዉለታ ለማስፈር በማሰቡ ናቸዉ፡፡
  በትግሉ ጂማሪ ይቃወሙናል ተብለዉ የታሰቡ ባላባቶች አንድ ባንድ እየተለቀሙ ተገድለዋል፡፡
  ከዚያም በመቀጠል እስከ 2013 ዓ.ም. ድረስ ማይካድራ ላይ እንደተፈጸመዉ ሁሉ የአካባቢዉ ተወላጆች ሲታሰሩና ሲገደሉ ኖረዋል፡፡ ከዚህ ድርጊት በመለስ የአፓርታይድ አገዛዙ የዘር መድሎዉና ማሸማቀቁ ላለፉት 45 ዓመታት የቀጠለ ነበር፡፡የዘርማጥፋት ወንጀል በተደጋጋሚ ተፈጽሞአል፡፡በዚህም ተነሳ የአካባቢዉ ተወላጅ የትዉልድ አከባቢዉንና ቦታዉን ጥሎ እንዲሰደድ ተደርጉዋል፡፡በእርሱ ምትክ የዴሞግራፊ ቅያሬ ተከናዉኖአል፡፡
  በ1984 ዓ.ም. ከትግሉ ፍጻሜ በሁዋላ 85 ሺህ ታጋዮችን እስከነመሳሪያቸዉ በአካባቢዉ አስፍሮአል፡፡
  ከዚህም በተጨማሪ ወደ ሁለት ሚሊዎን የሚጠጋ ህዝብ ከትግራይ በመመምጣት አስፍሮአል፡፡
  በመሀሉም አንዳንድ ቆራጥ አካባቢዉ ተወላጆች በህግ ይመለስልናል በሚል እሳቤ ለተለያዩ የመንግስት መስሪያ ቤቶች አቤቱታ ያቀረቡ ቢሆንም ጀሮ ዳባ ከመባላቸዉ ባለፈ ተሳደዋል ፤ታስረዋል ፤ተገድለዋል፡፡
  ከሁለት ዓመት በፊትም የተቁዋቀመዉ የወሰንና ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ ግዳዩን ይፈታዋል ተብሎ ቢታሰብ አንድም ነገር ጠብ አላለም፡፡ይህም፤ የወሰንና የማንነት አስመላሽ ኮሚቴ ማየት የሚችላቸዉ ጉዳዮች በሕገመንግስቱ የተካለሉትን እንጅ ከዚያ በፊት በግዳጅና በሀይል የተነጠቁትን አይደለም፡፡የተቁዋቀመበት ሕጉም አይፈቅድም፡፡ ይፍታዉ ተብሎ ቢታሰብ እንኩዋን ሂደቱ ትግራይን ክልል ዉሳኔ የሚጠይቅ በመሆኑ ሂደቱ በፍጹም የሚቻል አይደለም፡፡
  እንደሚታወቀዉ በአሁኑ ወቅት አካባቢዉ በአማራ ልዩ ኀይልና ሚሊሸያ ተጋድሎ ከአረመኔዉ እጅ ነፃ ወጥቶዋል፡፡ በሀይል የተነጠቀዉን በሀይል አስመልሱዋል፡፡
  ስለሆነም ትህነግ በጦርነቱ ሰለተሸነፈ የትግራይ ሕዝብ በማኩረፉ ብልጽግናና የፌደራሉ መንግስት እንደገጸበረከት በመስጠት ለማባበል እንደዘዴ ለመጠቀም ያሰበዉ አካባቢዉን እንደነበረዉ ማስቀጠል ነዉ፡፡ የወልቃይት፤ጠገዴ፤ሁመራና ጠለምት ሕዝብ ጥያቄ የማንነት እንጅ የወሰን አይደለም፡፡ ማንነታቸዉ ተክዶ ትግሬ ናችሁ ነዉ ተባሉት፡፡
  በመሆኑም፤ለመላ ወልቃይት፤ጠገዴ፤ሁመራና ጠለምት ሕዝብ ሆይ !!!!!
  ትግልህ ላለፉት 45 ዓመታት በትህነግ/በሕዉሀት የደረሰብህን የአፓርትይድ አገዛዝ ለማስወገድ ተጠናክሮ መቀጠሉ አይዘነጋም፡፡በዚህ ጊዜ ዉስጥ ቁጥራቸዉ የበዛ ወገኖችህ በገዛ ትዉልድ ሀገራቸዉ ተገልለዋል፤ታስረዋል፤ተሰደዋል፤ተገድለዋል፡፡ ሌላዉን ለጊዜዉ ብንተወዉ እንኩዋን በቅርቡ ማይካድራ ላይ ደረሰዉን ጭፍጨፋ መላዉ ዓለም አስተጋብቶታል፡፡ በዚህ ምድር ናዚዎች በአይሁዶች ላይ ያደረሱት ግፍና በደል በአንተም ላይ ደርሶብሀል፡፡የግፍ ጽዋዉ ሞልቶ በመፍሰሱ በአለማራ ልዩ ኃይልና ሚሊሺያ ተጋድሎ ነጻነትህን ለመቀዳጀት በቅተሀል፡፡ ይሁን እንጂ የተቀዳጀኸዉን ነጻነት ነጥቀዉ፤ በነበረዉ መልክ ተመልሰህ ወደባርነት እንድተገባ የሚመኙና የሚያመቻቹ እንዳሉ መዘንጋት የለብህም፡፡በህግ ስም በሚደረግ የማታለያ ዘዴ በምንም ዓይነት እነዳትታለል፡፡የብልጽግና ፓርቲ -የፌዴራል መንግስት ሆነ የአማራ ብግጽግና የሚያቀርቡልህን መንገዶች በሙሉ እንዳትቀበል፡፡በመሸንገያ ሊቀርቡህና ሊያታልሉህ ይችላሉ፡፡በምንም መልኩ እምቢይ በላቸዉ፡፡ነጻነት እጅህ ዉስጥ ስለገባች አሳልፈህ እንዳትሰጥ!!!!!!!!
  ስለሆነም ፤ይህ የአፓርትይድና ባርነት ሁኔታ ተመልሶ እንዲመጣ እንደማትፈልግ ከፈለግህ ተደራጅ፤ንቃ፤ታጠቅ ከዚያም ሌት ተቀን ነቅተህ የተቀዳጀኸዉን ድል ጠብቅ ብሎም ታገል፡፡
  በጊዜያዊ ፈንጠዝኛና የመደለያ ንግግር እንዳትታለል፡፡እሱን ድልህን ስታረጋግጥ ትደርስበታለህ፡፡ የማዕከላዊዉን መንግስት ስልጣን የተቆናጠጠዉ አብይ አህመድ የሚጨነቀዉና ሙሉ ጊዜዉን ትኩረት ሰጥቶ የሚሰራዉ ስልጣኑን ለማደላደልና ለማስጠበቅ ነዉ፡፡ ኢትዮጵያ፤ኢትዮጵያ በማለት ሲዘላብድ ልትታለል አይገባም፡፡የእሱም አጎብጎብጉቢ ተከታዮች እንደሱ ሁሉ በሚሰጡት አስመሳይ ንግግር ልንታለል አይገባም፡፡
  ይህ የአስመሳይ ፖለቲከኞች ዘዴ ነዉ፡፡ወቅቱን ጠብቀዉ መገለባበጥ የተለመደ ባህሪያቸዉ ነዉ፡፡
  የአንድን ፖለቲከኛ ሀቀኝነት መመመዘን ያለብህ በሚወስዳቸዉ ተጨባጭ እርምጃዎች ነዉ፡፡
  አብይ ለፓርላመዉ ንግግር ለማድረግ በቀረበበት ወቅት ከፓርላማ አባላት ከቀረቡለት ጥያቄዎች መሀከል ዝባዝንኬ በሆነ ንግግር አለባብሶ አዘናግቶና አድበስብሶ አልፎታል፡፡
  ከጥያቄዎቹ መሀከል፤
  • “ትህነግ/ሕዉሀትና ኦነግ ለምን በአሸባሪነት አይፈረጁም?
  • “የሰሜን ዕዝ በዚህ መልኩ ሴራ ሲጎነጎንበት ደህንነቱ ምን ይሰራ ነበር? ”
  • “ትህነግ/ሕወኀት ለጦርነት ይዘጋጅ ስለነበር ማዕከላዊዉ መንግሥት አስፈላጊዉን ዝግጅት ለምን አላደረገም?”
  • የአማራ ልዩ ሀይልና ሚሊሽያ ያደረገዉ ተጋድሎ ታሪክ ሊዘክረዉ የሚገባዉ ነዉ በማለት ከፓርላማ አባላት አስተያየት ሲሰጡ አብይ ግን አንድም ጊዜ ምስጋናም ሆነ አድናቆት ሳይሰጥ ቀርቶአል፡፡በተቃራኒዉ ምንም ዓይነት አስተዋጽኦ ላልነበረዉ “ለኦሮሚያ” ልዩ ሀይልንና ሚሊሽያ አድናቆት ሀጥቶአል፡፡ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ፡፡
  • ትግሬዎች ሳይሆኑ በግድ ትግሬ ናችሁ ተብለዉ ትግሬነት የተለጠፈባቸዉና ማንነታቸዉ የተካዱት “ወልቃይት፤ጠገዴ፤ሁመራና ጠለምትና የራያ ሕዝብ ለወደፊቱ በምን መልኩ ይተዳደራሉ ?”
  • ሌላም ፤ትህነግ/ሕወኀት በጦርነቱ እየተሸነፈ ሲያፈገፍግ በዕስር ላይ የነበሩና በእቅድ ያፈናቸዉን ወደ 10 ሺህ የሚጠጉ የወልቃይት፤ጠገዴ፤ሁመራና ጠለምትና የራያ እስረኞች የደረሱበት አልታወቀም እየተባለ ነዉ፡፡ይሁን እንጅ ትህነግ/ሕወኀት ፋሽስታዊ ቀንደኛ መሪዎች ያሉበትን ቦታ በስዌችሽናል ሩም በድሮን በሚተላለፍ መረጃ በቀጥታ መከታተል ችለናል ከተባለ ለምን እነዚህ ታጋች እስረኞች ያሉበት ቦታ መታወቅ አልቻለም ?

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.