ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ምሑራን ለፍትህ

eee

በኢትዮጵያ ውስጥ በንፁሃን ወገኖች ላይ የዘር ማጥፋትና የሰብዐዊ መብት ጥሰት እየፈፀሙ ያሉ ወንጀለኞች በዓለም አቀፍ የወንጀል ፍርድ ቤት ተጠያቂ አንዲኾኑ ክስ ቀረበባቸው። የማይካድራውን ጭፍጨፋ ጨምሮ፤ በሻሸመኔ፣ ወለጋ፣ በቤንሻንጉል በተደጋጋሚ የደረሰውን እልቂት በተመለከተ መረጃ እያሰባሰቡ እንደነበረም ምሁራኑ ጠቅሰዋል።

በኢትዮጵያ ውስጥ በንፁሃን ወገኖች ላይ የዘር ማጥፋትና የሰብዐዊ መብት ጥሰት እየፈፀሙ ያሉ ወንጀለኞች በዓለም አቀፍ የወንጀል ፍርድ ቤት ተጠያቂ አንዲኾኑ ክስ ቀረበባቸው። ከሰብዐዊ መብት ጋር በተያያዘ የሚሠሩ ኹለት ምሁራን ከዶይቸ ቬለ ጋር ባደረጉት ቆይታ በኢትዮጵያ አሳሳቢ ኾኖ የቀጠለው የሠብዐዊ መብት ጥሰት ዐለም አቀፍ ትኩረት እንዲያገኝ በመንቀሳቀስ ላይ መኾናቸውን ገልጠዋል። የማይካድራውን ጭፍጨፋ ጨምሮ፤ በሻሸመኔ፣ ወለጋ፣ በቤንሻንጉል በተደጋጋሚ የደረሰውን እልቂት በተመለከተ መረጃ እያሰባሰቡ እንደነበረም ምሁራኑ ጠቅሰዋል። በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ከዚህ ቀደም የተከሰቱ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን እና ግድያዎችን በሚመለከትም መረጃዎችን ማጠናቀራቸውን ዐሳውቀዋል። መረጃዎቹ ተሰባስበው ወንጀለኞች የተባሉት ለፍርድ እንዲቀርቡ ለማስቻል አቤቱታ ለተባበሩት መንግሥታት ዓለም አቀፍ የወንጀል ጉዳዮች ተመልካች ፍርድ ቤት እንተላከ እና ምላሽ በመጠበቅ ላይ እንደኾኑም ጠቅሰዋል። በሌላ በኩል በትግራይ ተወላጆች ላይ የሰብዐዊ መብት ጥሰት እንይደርስ በትኩረት መሥራት እንደሚገባም አሳስበዋል።

ታሪኩ ኃይሉ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ነጋሽ መሐመድ

ተጨማሪ ያንብቡ:  ቃለምልል ጫካ ከገባው የጀነራል ተፈራ ማሞ ወንድም አደራጀው ማሞ ጋር | ስለ ትጥቅ ትግሉ ይናገራል

1 Comment

  1. Please provide us the contact informations of the individuals who filed the charges so we can send them more follow up evidences in the future when (not if) more similar incidents occur.

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.