“የዘመቻ ማይካድራ” ድግፍ ሰጪ የአመራር ቡድን ተልኮውን በስኬት አጠናቆ ባህር ዳር ገባ፤

129115783 3011652525738726 4442482384303738332 o
የትህነግ ሽፍታ ቡድን ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም በሰሜን ዕዝ የመከላከያ ሰራዊትና በዳንሻ ቅራቅር ደግሞ በአማራ ልዩ ሀይል ላይ ጥቃት በመፈፀም ወረራ የቃጣ ሲሆን የመከላከያ ሰራዊቱ፣ የአማራ ልዩ ሀይልና ሚሊሻ በመቀናጀት ጥቃቱን በመመከት መልሶ የማጥቃት ስራ በመስራት የስግብግቡን ጁንታ ፍላጎት በማክሸፍ ትልቅ ስራ መስራቱ የሚታወስ ነው።
ስግብግቡ ጁንታ ቡድን በእብሪት ተወጥሮ እራሱ በለኮሰው ጦርነት ክፉኛ የተመታ ሲሆን ጦርነቱ ከተከሰተ ጀምሮ ስግብግብ ጁንታውን አድኖ በመያዝ ህግን ለማስከበር እየተደረገ ባለው የትግል ሂደት ውስጥ ሽፍታው ቡድን ባጋጠመው ከፍተኛ የሞራልና ሰብአዊ ኪሳራ ምክንያት በማይካድራና አካባቢው የሚኖሩ የአማራ ተወላጆችን በመለየት የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ አድርጎ ሸሽቷል።
ይሁን እንጂ ሽፍታው ቡድን በገጠመው ከፍተኛ ሽንፈት ምክንያት ንፁሀን ወገኖቻችንን በግፍ እየጨፈጨፈና እያፈነም ጭምር በመሸሹ ምክንያት ቡድኑን ታግሎ በማሸነፍና አድኖ በመያዝ ለህግ ማቅረብ ካልሆነም ከምድረገፅ በማጥፋት የ
ወገኖቻችንን ከሰቆቃ ለመታደግ ብሎም የሀገራችንን ሰላም ለማረጋገጥ ሰፊ መላ ኢትዮጵያዊያን በአንድነት በመቆም ሰፊ ትግል የተደረገበት ወቅት ነበር።
129721489 3011652409072071 6460771192946503854 o
በወቅቱ ሽፍታው ቡድን ድንገት ጥቃት የጀመረና የዜጎችን ብሎም የሀገርን ክብር ያዋረደ በመሆኑ ይህን ቡድን ለማስወገድና ህግን ለማስከበር በማይካድራ በተጨፈጨፉ ንፁሀን ወገኖቻችን ስም “ዘመቻ ማይካድራ” በሚል የድጋፍ ሰጪ የአመራር ቡድን ለመከላከያ ሰራዊታችን፣ ለአማራ ልዩ ሀይልና ሚሊሻ ድጋፍ እንዲያደረሰግ በአማራ ብልፅግና ፓርቲ አማካኝነት ተልዕኮና ስምሪት ተሰጥቶት ወደስፍራው እንዲያቀና ተደርጓል።
የዘመቻ ማይካድራ የድጋፍ ሰጪ ቡድን በወልቃይት፣ ዳንሻ፣ ማይካድራ፣ ከተማ ንጉስ (ማክሰኞ ገበያ)፣ በሰቲት ሁመራና ሌሎችም ጦርነት በተካሄደባቸውና ከሽፍታው ቡድን ነፃ በወጡ አካባቢዎች ከሃያ ቀን በላይ በርካታ ድጋፎችን በመስጠት ታሪካዊ ስራ ሰርተዋል።
በቆይታቸውም ለሰራዊቱ ድጋፍ ከማድረግ ባለፈ ነፃ በወጡ አካባቢዎች ተቋርጦ የነበረው የመብራት አገልግሎት፣ የውሃ አገልግሎት፣ የጤና ጣቢያና ሌሎች መሰረታዊ አገልግሎቶች ለማህበረሰቡ እነዲደርሱ የማስጀመር ስራ የሰሩ ሲሆን ወቅቱ የሰብል መሰብሰቢያ ወቅት በመሆኑ ማህበረሰቡን በማረጋጋት እና በማስተባበር ሰብል እንዲሰበሰብ ትልቅ ስራ ሲሰሩ ቆይተዋል።
በተጨማሪም በአካባቢው ስርዓት አልበኝነት እንዲወገድና ህግ እንዲከበር አካባቢውን በማረጋጋት ከፍተኛ ስራ ሰርተው ተልኳቸውን በብቃት በማጠናቀቅ ዛሬ በክብር ባህዳር ከተማ ገብተዋል።
ይህ የዘመቻ ማይካድራ ድጋፍ ሰጪ የአመራር ቡድን ስምሪቱንና ተልዕኮውን በስኬት አጠናቆ ሲመለስ ከቆየበት የአካባቢው ማህበረሰብ ትልቅ ምስጋናና ሽኝት የተደረገለት ሲሆን ትናንት ጎንደር ከተማ ሲገባ ደማቅ አቀባበል ተደርጎለት ወደ ባህር ዳር ተሸኝቶ ዛሬ ባህር ዳር ከተማ ሲገባ ደግሞ የአማራ ብልፅግና ፓርቲ አመራሮች በተገኙበት የጀግና አቀባበል ተደርጎለታል።
የሃያ ቀን ቆይታውን በስኬት አጠናቆ ለመጣው የድጋፍ ሰጪ ቡድን በአማራ ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት አማካኝነት የአቀባበልና ዕውቅና ፕሮግራም የተደረገለት ሲሆን የአማራ ብልፅግና ፓርቲ የአደረጃጀት ም/ዘርፍ ሀላፊዎች አቶ መስፍን አበጀ እና አቶ አማኑኤል ፈረደ በፕሮግራሙ ላይ ተገኝተው መልዕክት አስተላልፈዋል።
ም/ዘርፍ ሀላፊው አቶ መስፍን አበጀ “የአማራ ብልፅግና ፓርቲ በእናንተ ኮርቷል፤ እንደ አማራ አዲስ ታሪክ እየፃፍን ነው፣ በዚህ የታሪክ መታጠፊያ ላይ መሳተፋችሁ ትልቅ ዕድልና ታሪክ የሚዘክረው ታላቅ ጀብድ ነው፤ ስለሆነም ነገም ከፓርቲያችን እና ከመንግስት ጎን በመሰለፍ የአማራን ታሪክ ወደ ከፍታው ለመመለስ በምናደርገው ትግል ውስጥ የበኩላችሁን እንድታበረክቱ” ልክ እንደ ዘመቻ ማይካድራ ሁሉ “ዘመቻ ሁመራ” ሌሎችም የአመራር ቡድኖች ተልኮ ተሰጥቷቸው ስራ ላይ ይገኛሉ በማለት የገለፁ ሲሆን በመጀመሪያው ዙር በመሄድ ተልኳቸውን አጠናቀው ለተመለሱት ደግሞ ምስጋናና መልዕክትም ጭምር አስተላልፈዋል።
“የተሰጣችሁን ተልዕኮ ለመፈፀምና አስፈላጊውን መስዋትነት ለመክፈል ሂዳችሁ በድል አሳክታችሁ ተመልሳችኋል” ያሉት ደግሞ ም/ዘርፍ ሀላፊው አቶ አማኑኤል ፈረደ ሲሆኑ ” በዚህ የታሪክ ምዕራፍ ውስጥ የሰራችሁት ገድል የሚያኮራ ሲሆን ታሪክ የማይረሳውና ጀግንነታችሁ ለልጅ ልጅ የሚተላለፍ አኩሪ ታሪክ ነው፤ ምክንያቱም ይህ ታሪክ ዳግማዊ የአድዋ ታሪክ ነው፣ የዚህ ታሪክ አካል በመሆናችሁ ልትኮሩ ይገባል ስለሆነም የአማራ ብልፅግና ፓርቲ ልባዊ ምስጋናውን ይገልፃል ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ተልኳቸውን በስኬት አጠናቀው ለተመለሱ የዘመቻ ማይካድራ የአመራር ቡድን የአማራ ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት የእውቅናና የምስክር ወረቀት አበርክቶላቸዋል።
የድጋፍ ሰጪ ቡድኑ አባላትም የዘመቻው አካል በመሆናቸው ትልቅ ኩራት እንደተሰማቸውና ከጎንደር ጀምሮ ለተደረገላቸው አቀባበል ምስጋና በማቅረብ በቀጣይም ወደ ነበሩበት ስፍራ ሌሎች አመራሮች እንዲያመሩና መሰረታዊ የህብረተሰቡን የአገልግሎት ተቋማት እንዲከፍቱ ብሎም ተሰብስቦ ያልተጠናቀቀው የሰብል ምርት እንዲሰበሰብ ለዚህም ፓርቲው በጀመረው አግባብ በትኩረት እንዲሰራ አሳስበዋል።
APP

1 Comment

  1. በተገኘዉ ድል ሳትሰክሩ አሻግሮ ማየትንም ተማሩ የተዋደቃችሁለትን ወልቃይትና ጠገዴ ሁመራ ሰቲት ራያ አብይ ባድሜን ለኢሳይያስ ሰጥቶ እንዚህን ቦታዎች በማካካሻነት ለትግሬ ሊሰጠዉ ስለሆነ ነቅተህ መጠበቅ ይኖርብሀል ትግሬ ከሰራብህ ግፍ በላይ ወደፊት ሌላ ግፍ እንዲደርስብህ ካልፈለግህ ትግሬ ተከዜን አልፎ እንዳይመጣብህ አስተዳደረህን ሙሉ በሙሉ ያለ አብይ ጣልቃ ገብነት ማስከበር መቻል አለብህ። አብረችሁ ኑሩ የሚለዉ በመከላከያ ሀይሉ የትግሬን ማንነት ስለ ተመለከትክ ከአጋም የተጠጋ ቁልቋል ስለምትሆን አይሆንም በላቸዉ አምርረህ ታገላቸዉ አንተ ተኛህ እንጂ እነሱ አልተኙም።
    የማንነት ኮሚቴ የተባለዉ ትያትር ዉስጥ ይህንን ግፍ በግምባረ ቀደምትነት ከሰነዱልህ ሰዎች አንዱ አረጋዊ በርሄና ሌንጮ ለታ የመሳሰሉ ብዙ መርዞች ስለሚኖሩ (ዶክተር ሙላቱን) ጨምሮ ካሁኑ እዉቅናን ንፈገዉ ሰላም እንደነሱህ ሰላም ንሳቸዉ ካላከበሩህ አታክብራቸዉ ኢዜማ የሚሉት ሸለምጥማጥ በብረሀኑ ነጋና አንዳርጋቸዉ ጽጌ የሚመራዉ ድርጅት የሚበጅህ ስላልሆነ አማራ ክልል ድርሺ እንዳይል አድረገዉ። ይህን ካላደረክ በግፍ ብትማቅቅ በግሌ ዉርድ ከራስ ብያለሁ።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.