የሰሜኑ እዝ ጭፍጨፋ ክሴኩቱሬ ገታቸው አፍና ከእንግዲህስ እንደትና ወዴት ?

tplf 1 የሰሜኑ እዝ ጭፍጨፋ ክሴኩቱሬ ገታቸው አፍና ከእንግዲህስ እንደትና ወዴት ? ህወሀት ገና ሲፈጠር ጀምሮ ኢትዮጵያን ሲመቸው እየዘረፈ ለመግዛት ሳይመቸው አገሪቱን ለማጥፋት ለአመታት ምን ያህል ዝግጅት ሲያደርግ እንደኖረ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ የሚያውቀው ጉዳይ ነው፡፡ ጠ/ሚ/ር አብይ አህመድም በቅርቡ ጦርነቱን አስታክከው ባቀረቡት ሪፖርት ላይ በዘወትር ታዛዥነቱ ለማይታማው ፓርላማ ይህንኑ እንደ አዲስ ሲገልጹለት ታዝበናል፡፡ ማናችንም ብንሆን ግን የትግራይን ክልል በሻእቢያ ሊቃጣ ከሚችል ወረራ ለመመከት በክልሉ ከ20 ዓመት በላይ ተመድቦ የነበረን የአገር መከላከያ ሰራዊት ወያኔ በዘር እየለየና በሌሊት ገዳይ ሀይል መድቦ ይጨፈጭፈዋል ብለን አልገመትንም ነበረ፡፡ ብዙ የሚከነክኑ ጥያቄዎች አሉ፡፡ እዚህ ደረጃ እስከሚደረስ ድረስ የሰራዊቱ የመረጃ ክፍል ምን ይሰራ ነበር? ጦሩ ከአመት በፊት በጠ/ሚ/ሩ ትእዛዝ ከዚያ ክልል ተቀንሶ እንዲወጣ ታዝዞ መንገድ ሲጀምር በወያኔ እምቢ ባይነት መንገዶቹ ሲዘጉበትና ወደ ካምፑ እንዲመለስ ሲገደድ ጥርጣሬ ተወስዶ፡ ስሌት ተሰልቶ፡ አዋጭ የሆኑ የሚሊታሪ ምልከታዎችና ጥናቶች ተደርገው እርምጃ ለምን በጊዜው አልተወሰደም? ስህተቱና ተጠያቂነቱ የማን ነው?? ብዙ ጥያቄ የሚያስነሱ አያሌ ጉዳዮች አሉ፡፡ ይህንን ለጊዜው እንተወውና ጭፍጨፋው በወያኔ እንዴትና ለምን አላማ እንደተካሄደ በአጭሩ እንመልከት፡፡

አቶ ሴኩቱሬ ጌታቸው ከወያኔ ቁንጮ መሪዎች አንዱ ናቸው፡፡ በረዥም ምላሳቸውም ይታወቃሉ ፡፤ አቶ ሴኩቱሬ እትዮጵያ ካላት የጦር ሀይል ውስጥ 70% በላይ የሆነውን ትጥቅ የታጠቀውን ይህንን ሀይል “መብረቃዊ የመደምሰስ ማጥቃት” አድርገንበታል ብለዋል፡፡በእንግሊዝኛው anticipatory self-defense mechanism ተብሎ ይጠራል በማለትም እየተኩራሩ ሰራዊቱን ወያኔ እንደደመሰሰው በግልጽ ተናግረዋል፡፡ ጦሩ ራሱን ለመከላከል በማይችልበት ሁኔታ በጨለማ በዘር ለይተው ያካሄዱትን ይህንን አሰቃቂ ጭፍጨፋ ለማጠናቀቅ 45 ደቂቃ ብቻ እንደፈጀባቸውም በቪድዮው ላይ በኩራት አስረድተዋል፡፡ ይህንኑም የተናገሩት ህዳር 04/2013 ዓ/ም በድምጺ ወያኔ ቴለቪዥን ላይ ቀርበው < እይታ፣የመጀመሪያው ምዕራፍ በድል መጠናቀቅ እንድምታ፣> በሚል ርእስ ባደረጉት የመብረቃዊ ጥቃቱ ውጤታማነት ገለጻቸው ላይ ነው፡፡ ይህንኑ ገለጻቸውን ከእነዚህ ሁለት ቪድዮዎች በእንዱ ማየት ይቻላል፡፡ በዚህ በአንደኛው ቪድዮ ላይ ንግግራቸው በ53ኛው ሰኮንድ ላይ ይጀምራል፡፡https://www.youtube.com/watch?v=NfeX6d09o0o በሁለተኛው በድምጺ ወያኔ ቪዲዮ ላይም ንግግራቸው በ15ኛው ደቂቃ ላይ ይጀምራል፡፡ https://www.youtube.com/watch?v=H1yThWjhYYo&t=119የ8st

በውይይቱ ላይ እንደተገለጸው የመጀመሪያው ምእራፍ በድል ተጠናቋል ተብሏል፡፤ የሁለተኛውስ ምእራፍ እቅድ ምን ነበረ? እንዴትስ እንዲጠናቀቅ ታስቦና ታቅዶ ነበረ ለሚሉት ጥያቄዎች መልስ ያስፈልጋቸዋል፡፤ እነዚህንም መልሶች ለማግኘት በቅድሚያ ምን ታቅዶና ተነድፎ ነበረ የሚለውን ማወቅ ያሻል፡፤ በአጭሩ ወያኔ የአንደኛ ምእራፍ ንድፍ በስኬት መጠናቀቅን መሰረት አድርጎ ለሁለተኛው ምእራፍ አቅዶት የነበረው የሚከተለውን ይመስላል፡፤ የኢትዮጵያ ጦር የመከላከያ ደህንነት ክፍል አሁንም እንደተኛ መሆኑን በማመን፡ እንደዚሁም ወያኔ ክሰሜን እዝ የዘረፈውን ትጥቅ ይዞና ከትግራይ ክልል ውጭ በየነጥብ ጣቢያው በረቀቀና በተቀነባበረ መንገድ የዘረጋውን ኔትዎርክና ድብቅ ሀይል በመጠቀም ከጫፍ እስከጫፍ በዘረጋው መዋቅር እስከ አዲስ አበባ ድረስ ዘልቆ በመግባት አገሪቱን በማተራመስ ወደስልጣን መመለስ ነበረ፡፡ ያ ጉዞ ግን ገና ክጅምሩ በጀግናው በአማራ ልዩ ሀይል ሚሊሽያና ፋኖ ጠንካራ ምት ተሽመድምዶ በቦታው እንዲቆም ተገታ፡፡ አይበገሬዎች የአማራ ነፍጠኞች ወያኔ ላይ ባላቸው ቁጭት በተራ ነፍስ ወከፍ መሳሪያ የወያኔን ግዙፍ ግን ግብዝ ጦር ለበለቡት፡፡ የወያኔ ጦር አፈግፍጎና ብሎም እግሬ አውጭኝ ብሎ እንዲሽሽም አደረጉት፡፡ ዘርፎ ከታጠቃቸው መሳሪያዎች ውስጥ የተወሰኑትን ማረኩት፡፡ የአማራ ነፍጠኞች ድል በድል ሆነው ወያኔን በማሳደድ ላይ እንዳሉና የወያኔ ጦርም እግሬ አውጭኝ ብሎ ሽሽት ላይ እንዳለ የመከላከያ ሰራዊት በቦታው ደረሰ፡፡ የሆነው ይህ ነው፡፡ ሁኔታው በእነዚያ የአማራ ጀግኖች ተመክቶና ባለበት ተገትቶ ቀጥሎም ወደኋላ እንዲያፈገፍግ ባይደረግ ኖሮ ስእሉ አሁን ላይ ምን ይሆን እንደነበረ መገመት አያዳግትም፡፡

እነዚህ ሁሉ መሆን የማይገባቸው ነገሮች ከሆኑ በኋላ በግፈኛው ወያኔ ላይ ቀጥተኛና የማያዳግም እርምጃ መውሰድ ግደታ ነው፡፤ ምክንያቱም ላለፉት 28 አመታት በአገሪቱ ውስጥ ለተፈጸሙት ቀጥተኛና ስውር ወንጀሎች በሙሉ የሁሉም ወንጀሎች መነሻ፡ ፈጻሚና አስፈጻሚ ራሱ ህወሀት ስለሆነ ነው፡፡ ስለዚህም ህወሀትን ከእንግዲህ በፓርቲነት እንዲኖር መፍቀድ ወንጀል ነው፡፤ ከእንግዲህ ወዲያ ከኢትዮጵያ ህዝብ ተዘርፈው መልሰው የዘረፋ ምንጭ የሆኑ እንደ ኢፈርት፡ ዲንሾ፡ ጥረትና ወንዶ የመሳሰሉና በስሮቻቸው ያደራጇቸው ንብረቶችና ድርጅቶች በሙሉ ለኢትዮጵያ ህዝብ እንዲመለሱ አለማድረግ ወንጀል ነው፡፡ ወያኔ አማራን በዘር ማጥፋት ወንጀል ፈጅቶና አፈናቅሎ ከአማራው ወስዷቸው የነበሩትን አሁን ላይ ግን በአማራው ከባድ መስዋእትነት ነጻ የወጡ የአማራ መሬቶችን ወደ ትግራይ ክልል ለመመለስ ማሰቡና መሞከሩ ፍጹም የማይሳካ ቢሆንም ሙከራው በራሱ ወንጀል ነው፡፡ ከእንግዲህ ወዲያ በዘር ላይ የተመሰረተውን ህገ መንግስት አግዶ ፌደራሊዝምን እንዲለመልም የሚያደርግ የትክክለኛ ፌደራሊስት ህገመንግስት አለማቋቋም የአገሪቱን ስቃዮች ከማብዛት ዉጭ ሌላ ትርጉም ሊሰጠው አይችልም፡፡ የህዝቦችን ስቃይ ማስቆም ሲቻል አለማስቆም ደግሞ ራሱን የቻለ ወንጀል ነው፡፡ ዘረኝነት የአገሪቱ ነቀርሳ መሆኑን አውቆ ዘረኝነትን በወንጀለኛነት አለመፈረጅ በራሱ ወንጀልን ደግፎ መቆም ማለት ስለሆነ ይህም ራሱ ወንጀል ነው፡፡እነዚህ ሁሉ ወንጀሎች ካልተወገዱ አገሪቱን መልሶ ወደማትወጣው መቀመቅ ይከቷታል፡፡አሁን በመንግስት ስልጣን ላይ ያሉትንም ሀላፊዎች በወንጀለኝነት ያስጠይቃል፡፡ የወንጀል ተጠያቂነትን ይርጋ አይሽረውም፡፡ በሀይማኖትም ኩነኔ ነው፡፤ ስለዚህ በተግባር ወያኔ ላይ የሆነውን አይቶ መማር ብልህነት ነው፡፡

እውነቱ ቢሆንስ

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.