ከሰሜን እዝ ከተለያዩ ብርጌዶችና ክፍለ ጦሮች ታግተው የነበሩ የመከላከያ ሰራዊት አባላት በዱር በጫካው አቆራርጠው ወደ ሰቆጣ በመግባት ላይ ናቸው

128447971 4749603791778456 4104219401397542735 n ከሰሜን እዝ ከተለያዩ ብርጌዶችና ክፍለ ጦሮች ታግተው የነበሩ የመከላከያ ሰራዊት አባላት በዱር በጫካው አቆራርጠው ወደ ሰቆጣ በመግባት ላይ ናቸውህዳር 20/2013 ዓ.ም ከ 8 ሰዓት ጀምሮ መግባት የጀመሩ ሲሆን ትላንት 223 አካባቢ ድረስ ገብተው ሲያድሩ እስከ ዛሬ 11፥30 ሰዓት የትላንቱን ጨምሮ 588 መከላከያ ሰራዊት ከዋጎች ጋር ሰቆጣ እራት በጋራ እየበላ ነው። አሁን ከመሸ የመጣውን የሰው ሀይል ቁጥር ነገ የምንገልጸው ሆኖ እየተወያየን ካገኘነው ተነስትን ግን እስከ 2800 መከላከያ ሰራዊት አባላት በየጫካው ወደ ዋጎች መዲና ሰቆጣ ሊመጡ ይችላሉ ሲሉ ቅድመ መረጃ ሰጥተውናል።
ያለው ሁኔታ ይህ ሆኖ ከገሀነም አምልጠው የመጡ የመከላከያ ሰራዊታችን አባላት እንዳይመስሉት መስለው ግን ወደ ሰማይ እየተመለከቱ “ተመስገን ለካስ ወገን ዘመድ አለን!” ሲሉ ስትሰማ በተዘጋጀው የማረፊያ ቦታ ሁሉ ማህበረስብ አፍ ላፍ ገጥሞ መከላከያችን ጋር ሲጠያየቅ የገጠማቸው ጉድ አድቬንቸር ፊልም አይሉት እውነት እሺ ይሆን ተብሎ ለማመን ኢተገማች ጉድ ጉድ ጉድ ነው!
የመከላከያ ሰራዊታችን አባላት አሁንም በድንገት “ተመስገን ለካስ ወገን ዘመድ አለን!” ነው ቃላቸው!
ከሰሜን እዝ ከተለያዩ ብርጌዶችና ክፍለ ጦሮች ታግተው የነበሩ የመከላከያ ሰራዊት አባላት በዱር በጫካው አቆራርጠው ወደ ሰቆጣ በመግባት ላይ ናቸው
128547082 4749603955111773 7432218319683178112 n ከሰሜን እዝ ከተለያዩ ብርጌዶችና ክፍለ ጦሮች ታግተው የነበሩ የመከላከያ ሰራዊት አባላት በዱር በጫካው አቆራርጠው ወደ ሰቆጣ በመግባት ላይ ናቸው
እዛው ያለው ሰውም አንድ ጊዜ ከጠየቀ ተመልካች እና አድማጭ ብቻ የመሆን እድል ነው ያለው ምኑን አውርተው ጨርሰው ሌላ ሊጠይቅ ይሰማ ይሰማ እና ግን ይህ ሁሉ ኢትዮጵያ ውስጥ ነው እውነት ይላል። የተቀረው ዝም ብሎ እንባውን ያዘንባል።
እጅግ መላ አካላትን ስብርብር የሚያረግ ሰው ሆኖ መፈጠርን እንድትረግም የሚያሰገድድ ስሜት ነው የሚፍጥረው በፈጣሪ!
ነገሩ አዲስ ሁኖ አይደለም በምድር ያለ ሁሉ ከጥቅምት 24/2013 ዓ.ም ከምሽቱ 5፥20 አካባቢ ጀምሮ ይህ እንደተከሰተ ይታወቃል። ግን በእቶነ እሳቱ የነበሩ የመከላከያ ሰራዊታችን አባላትን አግኝተህ ስትሰማ አይደለም አሁን እነሱ አይመስሉት መስለው እያየህ ከዓመታት በኋላ ነበርኩ ብሎ ቢነግርህ ደንዝዘህ እንድትቀር ሊያረግህ ይችላል።
128650292 4749604361778399 2736106334873791086 n ከሰሜን እዝ ከተለያዩ ብርጌዶችና ክፍለ ጦሮች ታግተው የነበሩ የመከላከያ ሰራዊት አባላት በዱር በጫካው አቆራርጠው ወደ ሰቆጣ በመግባት ላይ ናቸው
ኢትዮጵያ የፈጣሪ ከተማ ነች!
ዛሬም አልጠፋችም ነገም አትጠፋም!
ሰቆጣ, ህዳር 21/2013 ዓ.ም
(Waghimra Communication)
128705476 4749604158445086 2543672174009828443 n ከሰሜን እዝ ከተለያዩ ብርጌዶችና ክፍለ ጦሮች ታግተው የነበሩ የመከላከያ ሰራዊት አባላት በዱር በጫካው አቆራርጠው ወደ ሰቆጣ በመግባት ላይ ናቸው

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.