በማይካድራ የዘር ጭፍጨፋ የተገደሉት ቁጥር ሊያሻቅብ እንደሚችል ቦርዱ ገለፀ – ጌታቸው ሽፈራው

በማይካድራ ጭፍጨፋ የተገደሉ አማራዎቸ ቁጥር ሊያሻቅብ እንደሚችል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አፈፃፀም እየመረመረ ያለው ቦርድ ገልፆአል።
ወንጀሉ እጅግ ዘግናኝና ዘርን መሰረት ያደረገ ስለመሆኑ የመርማሪ ቦርዱ አባላት ያነጋገሯቸው የአይን እማኞችና ከግድያ ሙከራው የተረፉ ወገኖች እንዲሁም የሟች ቤተሰቦች አስረድተዋል፡፡
129035367 4062146900480945 6536646221640882811 n
የመርማሪ ቦርዱ አባላት ከ50 እስከ 60 አስከሬኖች በአንድ ላይ የተቀበሩባቸውን ቦታዎች ተዘዋውረው የተመለከቱ ሲሆን፤ በማይካድራ አቡነ አረጋዊ ቤተ ክርስቲያን ያሉት መቃብሮችም ቢሆኑ ከ6 እስከ 12 አስከሬኖች በአንድ ላይ የተቀበሩባቸው ናቸው፡፡
የሟቾችን ቁጥር በተመለከተ ቀደም ሲል የተለያዩ ሚዲያዎችና የሰብኣዊ መብት ተቋማት 600 መሆኑን ባወጡት ሪፖርት የጠቀሱ ቢሆንም፤ መርማሪ ቦርዱ ባገኘው መረጃ ግን የሟቾቹ ቁጥር ሊያሻቅብ እንደሚችል ነው፡፡
128892296 4062147390480896 7130071993019348535 n
ቦርዱ የምርመራ ስራውን እያከናወነ ባለበት ወቅት በአከባቢው የሚገኘው ጊዜያዊ አስተዳደር ገና ያልደረሰባቸውና አፈር ያልለበሱ አስከሬኖች በአከባው ከሚኖሩ ሰዎች እየተጠቆመ የምርመራ ቡድኑ አባላት እንዲያዩት የተደረገ ሲሆን፤ በተለይ “ሸለላ መውጫ” በተባለው አከባቢ በአንድ ገደል ውስጥ ተጨምረው የተገኙት አስከሬኖች የተደራረቡ በመሆናቸው ብዛታቸውን ለማወቅ እንኳን አልተቻለም፡፡
በወቅቱ በአከባቢው የነበረው የሚሊሻና የፖሊስ ጸጥታ መዋቅር የፌዴራሉን የሀገር መከላከያ ሰራዊት እርምጃ ሸሽቶ አከባቢውን ለቆ ከመውጣቱ በፊት “ሳምሪ” ከተባለ መደበኛ ያልሆነ የትግራይ ወጣቶች ቡድን ጋር በማበር የፈጸሙት ወንጀል ስለመሆኑ ማረጋገጥ ተችሏል፡፡
ከተወካዮች ምክር ቤት ፌስቡክ ገፅ የተወሰደ
mai kaydra
128172392 112261470710114 8774204863917931428 n
128298874 112261477376780 6208667027711801796 n

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.