ህብረተሰቡ በበርበሬ እና በለዉዝ ምርቶች ላይ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ተጠቆመ!!

128623415 3009893465914632 107191804141192238 n
በባህርዳር ከተማ የአማራ አረንጓዴ ንቅናቄ ፎረምና የኢትዮጵያ ምግብና መድሐኒት ቁጥጥር ባለስልጣን በጋራ ባዘጋጁት ፕሮግራም ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ የምግብና የመድሐኒት ቁጥጥር ባለስልጣን የምእራብ ኢትዮጵያ የሰሜን ምዕራብ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ሙሉጌታ የቆየ እንደገለፁት አሁን አሁን ለህብረተሰቡ ጤና ጠንቅ እየሆኑ ባሉት የበርበሬና የለዉዝ ምርቶች ላይ ጥንቃቄ እንዲያደርግ አጥብቀዉ አሳስበዋል::
ባለ ሰልጣኑ የተለያዩ የለዉዝ አምራቾች በክልላችን እየተፈጠሩ እንደሆነ ገልፀዉ ምንም እንኳን የስራ እድል ፈጠራዉ የሚያበረታታ ቢሆንም በቂ የማምረቻ ቁሣቁስ ሳያሟሉና ሳይንሳዊ አካሔዱን ሳይከተሉ የተመረቱት የለዉዝ ምግቦች ለህብረተሰብ ጤና እክል እየፈጠሩ ነዉ ብለዋል::
በተለይም ለዉዝ ጤነኛ አካሔዱን ይዞ ካልተመረተና የቆይታ ግዜዉን ሳይጠብቅ ለምግብነት የሚዉል ከሆነ በኩላሊት ላይ ከባድ ጉዳት በማድረስ በተጠቃሚዉ ላይ የካንሰር በሽታ የሚያመጣ እንደሆነ የገለፁ ሲሆን በዚህ ያልተገባ የአመራረት ሂደት ላይ ተሰማርተዉ በተገኙ አንዳንድ የባህርዳርና የደብረማርቆስ አምራቾችና ተቋማት ላይ ህጋዊ እርምጃ ተወስዷል ብለዋል::
128664888 3009893545914624 7452848843814545489 n
ሌላዉ ለህብረተሰብ ጤና ጠንቅ እየሆነ ያለዉ የበርበሬ ምርት ሲሆን እዉቀቱ የሌላቸዉ ገበሬዎችና ስግብግብ ነጋዴዎች የበርበሬ ዛላ ተፈጥሯዊ ሂደቱን ጠብቆ ከደረቀ በሗላ ሚዛኑ እንዲከብድ በማሰብ ውሃ ረፍርፎ የማርጠብ ሂደት እንዳለና ይሔ ደግሞ እንዲበሰብስና እንዲታመቅ ስለሚያደርግ በህብረተሰቡ ዘንድ ይሔ ነዉ የማይባል የጤና እክል እየፈጠረ እንደሚገኝ ጠቁመዋል::
ስለዚህ ህብረተሰባችን በነዚህ ምርቶችና በተለያዩ የታሸጉ ምርቶች ላይ ተገቢዉን ጥንቃቄ አድርጎ እንዲመገብ ያሣሰቡ ሲሆን በተለይ የተመረቱበትን ግዜና ምርቶቹ ከጥቅም ዉጭ የሚሆኑበትን ቀን በመመልከት ተጠንቅቆ እንዲመገብ እና ጤናዉን እንዲጠብቅ አሣስበዋል::
Amhara Prosperity Party /APP/

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.