የኢፌዴሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዓመት የሥራ ዘመን ሁለተኛ ልዩ ስብሰባ

የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 2ኛ ልዩ ስብሰባ

5 Comments

 1. ምንም ሳይገባው አንተን የወቀሰ ያብጠለጠለ ኢትዮጵያዊ በሙሉ በራሱ ይፈር:: ታላቅ መሪነትህን አረጋግጠሀል

 2. እውነት ብለሃል፡፡ ሲያጠፋ መተቸት ያባት ነው፡፤ በጣም የሚገርመኝ የአቢይን ቅንነት እና ኢትዮጲያን የሚወድ ሰው መሆኑን መጠራጠር እንዴት ይቻላል? ከዚህ በኋላ በጥላቻ ታውረው የርሱን ስም ለማጥፋት (መተቸት መብት ነው!) በዚህ መድረክ የሚንቀዠቀዡትን ያለምንም ርህራሄ እና ይሉኝታ ተከታትሎ ማሳፈር ያስፈልጋል፤፡ ኢትዮጵያን የምንል ሁሉ ከአቢይ ጎን መቆም ያለብን ሰኣት ነው፡፡ ቢያንስ ሃገር ተረጋግቶ ለምርጫ እስክንደርስ ድረስ፤፡

 3. ወንድማችን አብይ ልባችንን አቆሰልከው ፤ ስምህን በከንቱ ላጎደፍነው ፀፀትን አለበስከን !
  የሀገራችን የዘር ፓለቲካ ሄዶ ሄዶ ጥጉ ምን እንደሆነ ለኛ ብቻ ሳይሆን ለአለም መማሪያ እንድንሆን አብቅቶናል። የታሪክ ተመራማሪዎች በስፋት ጥናታዊ ፅሁፍ እንደሚያቀርቡበት አምናለሁ። የማንን አላማ ማስፈፀመያ መሳሪያ መሄኑን አሳይቶናል።
  ከጦርነት መልስ ወያኔ ያረገውን ሀገር የመበተን ስራዎች ህገ መንግስቱን ጨምሮ እንዳልነበር ማረግ ነው።
  በመጀመሪያ ደረጃ ክልሎች ተመጣጣኝ እና ለአስተዳደር አመቺነት በሚበጁ ክፍለ ሀገሮች እንደገና ይዋቀሩ። አሁን የሚታየው እጅግ የተንቦረቀ ቀ ክል ሎች/ አማራ፣ ኦሮሚ ያ / ከፌደራላዊ መሰረታዊ ” ነዋሪው ለሚ መራው አካል ቅርብ መሆን አለበት ” ከሚለው መርሆ / Increased citizens’participation /ተፃራረ የሆነ አደረጃጃት ባንድ ወገን፣ በሌላ በኩል ራሱን በራሰ ገቢ መደጎም የማይችል እጅግ አናሳ ክልል/ሀረሪ / ያለበት ሀገር የፌዴራል ስርአት መስርቻለሁ ማለት አይቻልም።
  ህዝብን እርስ በርሱ በዘር ለማባላት ብሎም ሀገርን ለማፍረስ እና የባንዳዎች ጥቅም ለማስተበቅ እና ሀገራችንን ለውጭ ሀይል አሳልፎ ከመስጠት ውጭ አንድ ቁዋንቁውን ተናጋሪ ዘርን ባንድ ላይ ማጨቅ ፍምፀ ስህተት ነው። የባሌ ባለጉዳይ ‘ፊንፊኔ” መሄድ ይቀለዋል ወይስ ጎባ ? ይተዋወቃሉ ወይ ? ችግሩን ይረዳዋል ?? የውልዲያው ባለጉዳይ ደሴ መሄድ ይቀለዋል ባህር ዳር? መሪዎቹንስ አይቶአቸው ያውቃል ?? ፌ ዴራል ተባለ እንጂ ከአሀዳዊ አይለይም !
  አንድ ቁዋንቁዋ የሚናገር የግድ አንድክልል ውስጥ መኖር የለበትም። በስዊዘርላንድ ፌዴራላዊ ስርአት ጀርመንኛ የሚናገርሩ በ19 ክፍላተ ሀገር/ክልል ይገኛሉ ። ተመሳ ሳይ ልምድ በናይጄሪያም ይታያል። ይህ በመሆኑ የክልሉ ነዋሪ በራሰ ቁዋንቀዋ መማርን፣መዳኘትን፤ የመንግስት ስራ ማከናወንን፣ባህሉን ማዳበርን፣ ራሱን በራሱ ማስተዳደረን….ወዘተ አልከለከለውም።
  ምርጫ ወያኔ በቀደደልን ቦይ ከፈሰስን ምናልባትም እስከ ወዲያኛዉ ልንፈታዉ የማንችለው ችግር ዉስጥ ልንገባ እንችላለን።

 4. የጠቅላይ ሚ/ሩ ጥሩ ገለፃ ነበር፡፡ በትህነግ ምን አይነት ጫና ሲደረግ እንደነበረ እና የጠቅልለህ ግዛ፣ Merit መሰረት ያላደረገ የቡድን አደረጃጀት አገራችንን ለዝርፍያ እና ወደ መቀመቅ ወስዷት እንደነበረ ገሃድ የወጣበት ነው፡፡ በነገራችን ላይ ህዝብ ስለታፈነ እና ስለተጨቆነ ነው እንጂ ይደረግ የነበረውን ሳያውቅ ቀርቶ ኤደለም፡፡

  እንደው ፓርላመው ውስጥ አገርን ህይወቱን መስዋአት አድርጎ የታገዳት መከላከያ ሰራዊት፣ አማራ ሚኒሻ ክልል ፖሊስ፣ ጄኔራሎች ገድል እና ጀግንነት ሲወራ እንደው ሁሉም ማጨብጨብ አልነበረበትም?? ምንድነው ዝምታ፡፡ አሁንም ፓርላማ ውስጥ ሻጥር አለ?? እንደውም በሰለጠኑት አገር እንዳለው ፓርላማ አባል መሆን ባይቻልም ቢያንስ ለአንድ ደቂቃ ከወንበር ተነስቶ ለጀግኖቹ ጭብጨባ ሊደረግ በተገባ ነበር፡፡ ግን ምን ያደርጋል እነሱ አውነተኛ የአገር ፍቅር እና ፍትህ ማጣት ነው ለዚህ ጀግነነት ያበቃችሁ፡፡ ለወደፊቱም በዚች አገር ለአለ የፖለቲካ እና ስልጣን ሽኩቻ መፍትሔ ለመሆን እና አገሪቷን ለማስቀጠል በናንተ ትክሻ ላይ ነው መሆን ያለበት፡፡ ለጠላትም ማስፈራሪያ ነው የሆናችሁት፡፡ ብራቮ!!!

  ይህ ምክር ቤትም በቀጣይም አገርን የሚያስቀጥል እውነተኛ ኢትዮጵያዊ ያሉበት መከላከያ ሰራዊት ስለሆነ ውስጡን በማጥራት በህግ ችግሮች ሲፈጠሩ በማንኛውም ጊዜ አገሪቷን በመቆጣጠር በጊዚያዊነት እንዲያስቀጥል ስልጣን ሊሰጠው ይገባል፡፡ አለዚያ እንደ አብይ አይነት መሪዎች እና ቁርጥዬ ጀግኖች ባይኖሩ ይህቺ አገር ወዴት እንደምትሔድ መገመት አይከብድም፡፡

  ለቀጠይ ከምርጫ በፊት በሁሉም አከባቢ ማረጋጋት ያስፈልጋል፡፡ እስቲ መነቋቆር፣ ግለኝነት፣ እኔብቻ ልብላ የመሳሰሉት ቀርቶ የዲሞክራሲ መሰረት ለቀጣይ ትውልድ እናስቀምጥ፡፡ ልጆችም ስለጦርነት፣ ግድያ፣ ሽብር የማይሰሙባት እንድትሆን ሁሉም በውስጡ ያለውን አውጥቶ ቢሰራ፡፡ ለልጆች ምን አይነት አገር እና አስተዳደር ነው የፈጠሩልን መባልን ሁሉም መቼም ይጠላል፡፡ እንደ ሰለጠኑ አገራት ምክር ቤት/ፓርላማም/ በቀጣይ ለአገር የሚጠቅም የሃሳብ ፍጭት የሚደረግበት እንዲሆን ሁሉም ምኞቱ ነው፡፡

  ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!

 5. የጠቅላይ ሚ/ሩ ጥሩ ገለፃ ነበር፡፡ በትህነግ ምን አይነት ጫና ሲደረግ እንደነበረ እና የጠቅልለህ ግዛ፣ Merit መሰረት ያላደረገ የቡድን አደረጃጀት አገራችንን ለዝርፍያ እና ወደ መቀመቅ ወስዷት እንደነበረ ገሃድ የወጣበት ነው፡፡ በነገራችን ላይ ህዝብ ስለታፈነ እና ስለተጨቆነ ነው እንጂ ይደረግ የነበረውን ሳያውቅ ቀርቶ አይደለም፡፡
  እንደው ፓርላመው ውስጥ አገርን ህይወቱን መስዋአት አድርጎ የታገዳት መከላከያ ሰራዊት፣ አማራ ሚኒሻ ክልል ፖሊስ፣ ጄኔራሎች ገድል እና ጀግንነት ሲወራ እንደው ሁሉም ማጨብጨብ አልነበረበትም?? ምንድነው ዝምታ፡፡ አሁንም ፓርላማ ውስጥ ሻጥር አለ?? እንደውም በሰለጠኑት አገር እንዳለው ፓርላማ አባል መሆን ባይቻልም ቢያንስ ለአንድ ደቂቃ ከወንበር ተነስቶ ለጀግኖቹ ጭብጨባ ሊደረግ በተገባ ነበር፡፡ ግን ምን ያደርጋል እነሱ አውነተኛ የአገር ፍቅር እና ፍትህ ማጣት ነው ለዚህ ጀግነነት ያበቃችሁ፡፡ ለወደፊቱም በዚች አገር ለአለ የፖለቲካ እና ስልጣን ሽኩቻ መፍትሔ ለመሆን እና አገሪቷን ለማስቀጠል በናንተ ትክሻ ላይ ነው መሆን ያለበት፡፡ ለጠላትም ማስፈራሪያ ነው የሆናችሁት፡፡ ብራቮ!!!

  ይህ ምክር ቤትም በቀጣይም አገርን የሚያስቀጥል እውነተኛ ኢትዮጵያዊ ያሉበት መከላከያ ሰራዊት ስለሆነ ውስጡን በማጥራት በህግ ችግሮች ሲፈጠሩ በማንኛውም ጊዜ አገሪቷን በመቆጣጠር በጊዚያዊነት እንዲያስቀጥል ስልጣን ሊሰጠው ይገባል፡፡ አለዚያ እንደ አብይ አይነት መሪዎች እና ቁርጥዬ ጀግኖች ባይኖሩ ይህቺ አገር ወዴት እንደምትሔድ መገመት አይከብድም፡፡

  ለቀጠይ ከምርጫ በፊት በሁሉም አከባቢ ማረጋጋት ያስፈልጋል፡፡ እስቲ መነቋቆር፣ ግለኝነት፣ እኔብቻ ልብላ የመሳሰሉት ቀርቶ የዲሞክራሲ መሰረት ለቀጣይ ትውልድ እናስቀምጥ፡፡ ልጆችም ስለጦርነት፣ ግድያ፣ ሽብር የማይሰሙባት እንድትሆን ሁሉም በውስጡ ያለውን አውጥቶ ቢሰራ፡፡ ለልጆች ምን አይነት አገር እና አስተዳደር ነው የፈጠሩልን መባልን ሁሉም መቼም ይጠላል፡፡ እንደ ሰለጠኑ አገራት ምክር ቤት/ፓርላማም/ በቀጣይ ለአገር የሚጠቅም የሃሳብ ፍጭት የሚደረግበት ምክር ቤት እንዲሆን ሁሉም ምኞቱ ነው፡፡

  ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.