አክሱም ተያዘና አውሮፕላን ተመታ መባሉን መንግሥት ሐሰት ነው አለ

105635609 3962228d 2414 4c47 aa70 72e39f7cd9aa አክሱም ተያዘና አውሮፕላን ተመታ መባሉን መንግሥት ሐሰት ነው አለየህወሓት ኃይሎች ትላንት [እሁድ] ምሽት አክሱም ከተማ መልሰው እንደያዙና የፌዴራል መንግሥት ንብረት የሆነ ተዋጊ ጄት መትተው መጣላቸውን ገልጸው ነበር። ነገር ግን የኢትዮጵያ መንግሥት ከፍተኛ ባለስልጣን የሆኑት አቶ ዛዲግ አብርሃ ለቢቢሲ እንደተናገሩት በህወሓት በኩል ተባሉት ነገሮችን “ነጭ ውሸት” ሲሉ አጣጥለውታል።

ሚኒስትር ዛዲግ ጨምረውም “የህወሓት የመጨረሻ ይዞታ የነበረችው መቀሌ ናት፤ ይህንን ሊያደርጉ አይችሉም” ሲሉ ተናግረዋል።

ከሦስት ሳምንት በላይ የኢትዮጵያ ሠራዊት በትግራይ ክልል ውስጥ ያካሄደው ወታደራዊ ዘመቻ ዋና ከተማዋን መቀለን መቆጣጠሩን ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ መከላከያ “ሕግ የማስከበሩ ዘመቻ” መጠናቀቁን ይፋ ማድረጋቸው ይታወሳል።

የህወሓት ሊቀመንበር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ከመቀለ መያዝ በኋላ ለሮይተርስ ዜና ወኪል በአጭር የጽሁፍ መልዕክት እንደገለጹት በውጊያው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል። በተጨማሪም የቡድኑ ኃይል መቀለ ከተማ አቅራቢያ ውጊያ እያካሄደ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

ይህንን በተመለከተ ህወሓት የሽምቅ ውጊያ እያካሄደ እንደሆነ በቢቢሲ የተጠየቁት ሚኒስትሩ ዛዲግ አብረሃ ሲመልሱ “የህወሓት አመራሮች በአሁኑ ጊዜ ሕይወታቸውን ለማዳንና በሕግ ከመጠየቅ ለማምለጥ እየሸሹ ነው እንጂ ውጊያ ላይ አይደሉም” ሲሉ መልሰዋል።

ትናንት ምሽት ከየት ቦታ እንደሆነ ካልታወቀ ስፍራ ከህወሓት በኩል ወጣ በተባለ መግለጫ ላይ የቡድኑ ተዋጊዎች ከሳምንት በፊት በፌደራሉ ኃይሎች የተያዘችውን የአክሱም ከተማን መልሰው እንደተቆጣጠሩና አንድ ተዋጊ አውሮፕላን መትተው መጣላቸውን ገልጸዋል።

BBC

1 Comment

  1. ይሄም እራሱ የተመቸዉ ጊዜ የሚጠበቅልን ትግሬ ነዉ ጎበዝ አትዘናጋ ቢመረመር ብዙ ጉድ አለዉ ስሁል ብሎ ስም አላምንም እኔ

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.