ሰውየው ! ገና ተዓምር ይሠራል (ዘ-ጌርሣም)

Abiy 7 ሰውየው ! ገና ተዓምር ይሠራል     (ዘ ጌርሣም)ሰውየው !

ገና ብዙ ተዓምር ይሠራል
የዘመናትን ቁስል ያሽራል
የትግል አድማሱ ሰፍቶ
ኦሮሞና አማራን አግባብቶ
ደቡብና ሱማሌን አስማምቶ
ጋምቤላና አፋርን አደራጅቶ
ትግሉን እጅ ለእጅ አስተሳሰሯል
ወጣቱን በአንድ አቁሟል
ድልም በቄሮ፣በፋኖ፣በዘርማና በኢጀቶ ተበስሯል
የድልና ሰላም ዜማም ተዘመሯል
ህዝቡም ለድጋፍ ሰልፍ ተመመ
የዓለምን ህዝብ በአድናቆት አስደመመ
የዘመናችን ልዩ ክስተት
የሰላምና የፍቅር ብሥራት
የሙሴ ፀጋ ተደገመ
የፈርዖንን ክንድ አዝሎ ያደከመ
በቃሽ መከራው ሊል ይመስላል
የጠላቶቿን ክንድ አዝሏል
ህዝቧን በአንድነት አቁሞ
የሰላም መሪውን አስቀድሞ
ቀኑና ጊዜው በመድረሱ
የፈሰሰውን ዕንባ ሊያብሱ
መላዕክታን ዙሪያውን ከበውታል
በሀቅና በትጋት ሥራ ይሉታል
ሃይሉ ከእነሱ ከተቸረው
የህዝብ ድጋፍ ካልተለየው
ገና ብዙ ተዓምር ይሠራል
የዘመናትን ቁስል ያሽራል
የጥላቻ ግንቡን አፍርሶ
የፍቅር ዓውዱን አንግሶ
መገንባት ጀምሯል ድልድዩን
የብሩህ ተስፋ ማለፊያውን
ሰውየው !
ገና ብዙ ተዓምር ይሠራል
የዘመናትን ቁስል ያሽራል
ኢትዮጵያን ከፍ ያደርጋታል
ቦታዋም ላይ ይመልሳታል
ግን የሕዝብን ድጋፍ ይፈልጋል
ሁሉም አለን ሊለው ይገባል
ሰውየው !
ገና ብዙ ተዓምር ይሠራል
ኢትዮጵያን ማማዋ ላይ ያወጣታል
እንደነበረች ያደርጋታል
የዓለም አድናቆት ይቸረዋል
ኢትዮጵያንም ያከብሯታል
የርስ በርስ ግጭት ይቆማል
ጣልቃ ገብነት ያከትማል
ሕዝቧን በህብረት ያቆማል
የሰላም ሐውልት ያስገነባል
ሰቆቃው በቃሽ ይላታል
ዕንባዋንም ያብሳል
ፈጣሪ ዓምላክ ይታደጋታል
ሰወየው !
ገና ብዙ ተዓምር ይሠራል
ኢትዮጵያና ሕዝቧን ይታደጋል
የሀገር መከላከያውን
የሰላምና ደህንነት ዋስትናውን
በአንድ ውቅት የተገፋውን
ሜዳ ላይ የተበተነውን
መልሶ ይገነባዋል
እንደ ወርቅ ያነጥረዋል
የወደቀ ሞራሉን መልሶ
ለደረሰበት ግፍ ክሶ
የጀግና ኒሻን ሸልሞ
በክብር ልብሱ አሽሞንሙኖ
ያቀርበዋል በህዝብ ፊት
ክብር እንዲሰማው በኩራት
ሰውየው !
ገና ብዙ ተዓምር ይሠራል
ዕድሜ ከሰጠን ያሳየናል

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.