ውድ የሃገራችን ህዝቦች! እንኳን ደስ አላችሁ፤ እንኳን ደስ አለን

127981350 2844075892519696 8590599340721795184 n
Office of Deputy Prime Minister of Ethiopia

እነሆ ዛሬ! በሃገር መከላከያ ሰራዊታችን በሳል የውጊያ ጥበብ እና የትግል ወኔ የህውሃት ጁንታ ቡድን የከተመባትን የመቀሌ ከተማ ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሯል።
በክልሉ መንግሥት በጥንቃቄ እና በፍጥነት እየወሰደ የሚገኘው ህግ የማስከበር እርምጃ በስኬት ታጅቦ ወሳኝ የድል ምዕራፍ ተቀዳጅቷል።
ለዚህ ዘመን ተሻጋሪ ድል ላበቁን ለጀግናው የመከላከያ ሰራዊታችን፣ ለአማራ ክልል ልዩ ሃይል እና ሚሊሻዎች ታላቅ ምስጋና እና ክብር ይገባቸዋል።
በዚህ ህግ የማስከበር ዕርምጃ በኢትዮጵያዊነት ለአፍታ ለማይደራደረው የትግራይ ክልል ህዝብ ለመከላከያ ሰራዊታችን ብርቱ ደጀን በመሆን ለተጫወተው ታሪካዊ ሚና ልዩ ክብር እና ምስጋና ይገባዋል።
በመቀጠል የጁንታውን ቡድን አድኖ ለህግ የማቅረብ ተልዕኮ በተቀጣጠለው የድል ስሜት እስከመጨረሻዋ ሰዓት ተጠናክሮ ይቀጥላል።
መንግሥት በደረሰበት ወሳኝ የድል ምዕራፍ ዜጎችን ከጥቃት የመጠበቅ እና የመከላከል ተግባሩን በጥንቃቄ፣ በንቃት እና በሃላፊነት ስሜት የሚወጣ ይሆናል።
በቀጣይ በትግራይ ክልል እና በአከባቢው ፍፁም ሰላም እና መረጋጋት እንዲሰፍን አስፈላጊውን ሁሉ በመንግስት በኩል ተፈፃሚ ይደረጋል።
በአጭር ሂደት በትግራይ ክልል በጁንታው ቡድን ሴራ የፈራረሱ መሰረተ ልማቶችን መልሶ የመገንባት እና የማቋቋም እንዲሁም በሂደት በክልሉ ዘላቂ ሰላም እና ልማት የማረጋገጥ ስራዎች በትኩረት ይከናወናሉ።
በጠንካራ የአመራር ጥበብ የተመራው ህግ የማስከበር እርምጃችን መሪ ዓላማ የጁንታውን ቡድን ካለበት ለቅሞ ለህግ ማቅረብ ተልዕኮ በመሆኑ፤ አሁንም እስከመጨረሻው ድረስ ለዓላማው የተሟላ ተፈፃሚነት የትግራይ ክልል ህዝብ ወንጀለኞችን ከተደበቁበት ፈልፍሎ የማጋለጥ ታሪካዊ ሃላፊነቱን እንዲወጣ ጥሪዬን አቀርባለሁ።
አለ ገና ~ ኢትዮጵያዊነት ያሸንፋል!!
~~~~~~~
የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ
ሚኒስትር ክቡር አቶ ደመቀ መኮንን መልዕክት

ተጨማሪ ያንብቡ:  የማለዳ ወግ ...በሳውዲ የኢትዮጵያውያን ተመላሽ ዜጎች ፈተና

4 Comments

  1. መቀሌን ነፃ አወጣን ቢባልም እያንዳንዱ የትህነግ መሪ የት እንደደረሰ መታወቅ አለበት።

  2. ጁንታው ከሸወደ ስንቱ አልቆ መሆን የለበትም። የትም ባለበት ቦታ ተንኮል ስለሚጠነስሱ በአለም አቀፍ ወንጀለኝነት ተመዝግበው ለህግ መቅረብ አለባቸው። ስንቱን አሰጨርሰው።

  3. በሰጣችሁት ትክክለኛ አመራር። ሀገራችንን ከመበጣጠስ አድናችሁዋል። ክብር ይገባችሁዋል፣ታሪክም ያከብራችሁዋል።
    በመቀጠልም ወያኔ የተከለችውን ኢትዬጵያን አፍራሽ በማር የተለወስ መርዝ ህገ መንግስትን አፍርሳችሁ ሁሉም የሀገሩባለቤት ሆኖ በእኩልነት የሚተዳደርበትን አዲስ ህገ መንግስት አውጥታችሁ ብሄራዊ ምርጫ ማካሄድ ይጠበቅባችሁዋል።
    በወያኔ ህገ መንግስት እና በዘር በተዋቀረ ክልል ኣይ ተመስርቶ ምርጫ ማካሄድ ሳልሳዊ ወያኔን ማዋለድ ይሆናል።ታጥቦ ጭቃ ።
    የመከላከያችን የፈሰው ደም ከንቱ ሆነ ማለት ነው ።

  4. ገና ድሉን ሳናጣጥም የቃላት አጠቃቀምህ ደም ያፈላል። ህወአት ትቶልህ የሄደውን ባንድራና እምነት መተው ከብዶሀል ። ህዝቦች ምንድነው? ካሁኑ መለያየት ይዘሀል በማይመጥናችሁ ወምበር ቁጭ ብላችሁ ተሰቃያችሁ።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.