ጌታቸው ረዳ እና ሴኩቱሬ ጌታቸው በደም እና በዘር ትግራዋይ አይደሉም

127788551 1652530298283444 63893224779661569 n
ነገር ግን ከህወሃት በላይ ህወሃት ልሁን ማለታቸው፤ ሌላውን ኢትዮጵያዊ የሚያናድዱትን ያህል፤ ህወሃቶች ደግሞ ምንግዜም በጥርጣሬ አይን… ወይም በአይነ ቁራኛ ይከታተሏቸዋል። እነዚህን ሰዎች የሚፈልጓቸው ለጥቅም ካልሆነ በስተቀር፤ በምንም አይነት ዘላቂ ወዳጅነት ሊኖራቸው አይችልም። ሴኩቱሬ እና ጌታቸው ረዳ ግን ታማኝነታቸውን ለማስመስከር፤ በስህተት ላይ ሌላ ስህተት በመስራት ከኢትዮጵያ ህዝብ ይበልጥ ተራራቁ። የህወሃት ሞት የጀመረው ኢትዮጵያን ለማርከስ መስራት ሲጀምር ነው። የዚህ ስራ ቅጥረኞች ደግሞ ትግራዋይ ወይም ተጋሩዎች ብቻ አልነበሩም። እንደጌታቸው ረዳ እና ሴኮ አይነት ሰዎች ህወሃትን ብታማኝነት አገልግለዋል። ዛሬ ስለሁለቱ ሰዎች ስናወራቹህ፤ እነሱን የመሰሉ በሺዎች የሚቆጠሩ የህወሃት አሽከሮች መኖራቸውን በማሰብ ነው።
እንደናንተ “ማረክን ገደልን” ብለን አንፎክርም (ለምን?)
(ዳዊት ከበደ ወየሳ)
ሴኩቱሬ (ሴኮ) በጨርቆስ ልጅነቱ ብቻ ሳይሆን፤ በጋዜጠኝነት ሙያ መስመር ላይ የተገናኘንበት አጋጣሚ ስለነበር በቅርብ እንተዋወቃለን። ጌታቸው ረዳ ደግሞ ከአላማጣ – ራያ ሲመጣ በከፍተኛ የማትሪክ ውጤት፤ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲን ከተቀላቀለ በኋላ፤ የህግ ተማሪ እያለ አውቀዋለሁ። ከሁለቱም በላይ ግን ጌታቸው ረዳ ያሳዝነኛል። አንድ ቀን መሳሪያ መተኮስ ቀርቶ ተሸክሞ የማያውቅ ሰው፤ ስለጦርነት እና ስለጀግንነት ሲያወራ ሳየው አዝንለት ነበር። በዚያ ላይ.. ሙሉ ለሙሉ በማያምንበት፤ በኋላ ግን ሳይወድ በግድ በተነከረበት የዘር ፖለቲካ ውስጥ መንቦጫረቁም ያሳዝነኛል። በዚያ ላይ ለትግራዋይነት የማይመጥን ደም ይዞ፤ ጉልድፍ ትግርኛ እየተናገረ የህወሃት የበላይ ሃላፊ እስከመሆን መድረሱ በራሱ የሚገርም ነው።
አሁን እንደምንሰማው ከሆነ፤ መቀሌ በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ስር ወድቃለች። “ሴኩቱሬን እና ጌታቸው ረዳ ግን ምን ስር ተደብቀው ይሆን?” በመጨረሻው ሰአት ምን ያስቡ ይሆን? ኖቬምበር 28፣ 2020 – ንጋት ጀምሮ መቀሌ እና ዙሪያዋን በከፍተኛ የተኩስ ድምጽ ተናወጠች። በዚህች ሰአት የህወሃት አመራሮች በመቀሌ ስርቻዎች ውስጥ ተደብቀዋል። የኢትዮጵያ አየር ኃይል፤ ሰው አልባ አውሮፕላኑን (Drone) ወደ በመቀሌ ሰማይ በመላክ በታቀዱ ቦታዎች ላይ መብረቃዊ ጥቃት እየፈጸመ ነው። “እውን ሰዎቹ ከዚህ ተርፈው ዳግም እናያቸዋለን ወይ?” የሚለው ጥያቄ በብዙዎች ልቦና ይመላለሳል።
ወደ ጉዳያችን እንመለስ። ጌታቸው ረዳ እና ሴኩቱሬ ጌታቸው ሁለቱም በድፍረት ህወሃትን መቃወም የማይችሉ፤ ሌላውን ዘር እና ኢትዮጵያዊነትን ለመሳደብ ግን አፋቸው የማይሰለቸው ሰዎች ከሆኑ ብዙ አመታት ተቆጥረዋል። እነዚህ ሰዎች የዘር ሃረጋቸው ሲመዘዝ… ጌታቸው የራያ አላማጣ ልጅ ሲሆን፤ ሴኩቱሬ ጌታቸው ጨርቆስ ተወልዶ ያደገ ሰው ነው። ጌታቸው ረዳ – በወንድ አያቱ በአቶ ካህሳይ በኩል የትግራይ ደም ይኑረው እንጂ፤ ከአድዋ፣ ከሽሬ ወይም ከአክሱም ስላልተወለደ እንደንጹህ ትግራዋይ አይቆጠርም። የህወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ለመሆን ግን የራያ ተወላጅ መሆኑ የጠቀመው ይመስላል። ምክንያቱም ህወሃት የራያን ምድር ወደራሱ ገቢ ለማድረግ፤ ራዩማ የሆነ ሰው ያስፈልገው ነበር፤ ጌታቸው ረዳ ለዚህ ቦታ የሚመጥን… በባህሪው ፈሪና ሁሌም ከአሸናፊ ጋር የመጠጋት ባህሪ የነበረው በመሆኑ፤ ህወሃት ደግሞ በአሸናፊነት መንበር ላይ ስለሆነ፤ ያደገበትን የአማራ አገር በመካድ ከህወሃት ጋር ተወዳጀ።
በሌላ በኩል ደግሞ ሴኩቱሬ ተወልዶ ያደገው ጨርቆስ ክፍለ ከተማ ነው። የሰፈሩ ልጆች ሴኮ ይሉት ስለነበር፤ በታጋይነት ዘመኑም “ሴኮ” የሚለው ስሙ አብሮት ቀጠለ። የሴኮ ነዋሪነት ከፍተኛ 21፣ ቀበሌ 23፤ የቤት ቁጥር 630 ውስጥ ነዋሪ ነበር። በየነ-መርድ እና ተፈሪ መኮንን ነው የተማረው። ለቤተሰቡ የመጀመሪያ ልጅ ሲሆን፤ ታናሽ ወንድሙ ቅዱስ (የደርግ መቶ አለቃ ነበር)፣ ዘላለም፣ ክንፍሽ፣ ዶቃ እና አሸናፊ ወንድም እና እህቶቹ ናቸው። እናቱ ወ/ሮ ጸሃይነሽ ታፈሰ ይባላሉ (አሁንም በህይወት አሉ)። አባቱ ደግሞ የፖስታ ቤት ሹፌር ሲሆኑ፤ አቶ ጌታቸው ጥሩነህ ይባላሉ (የአምቦ ሰው ናቸው)።
በዚህ አጋጣሚ የሴኩቱሬን (ሴኮ) ታሪክ የምናወጋቹህ፤ የትግራዋይነት ጠብታ ማንነት ሳይኖረው፤ እራሱን ለህወሃት አገልጋይነት እንዴት እንዳዘጋጀ ለመግለጽ ያህል እንጂ፤ ዘር የመቁጠር አባዜ ኖሮብን አይደለም። እናም ሴኩቱሬ 12ኛ ክፍል (እንደኢትዮጵያ አቆጣጠር) በ1975 ዓ.ም ከጨረሰ በኋላ በአለማያ ዩኒቨርስቲ ገብቶ፤ ከዚያም በ1978 ወሎ ውስጥ ተመድቦ መምህር ሆኖ እያገለገለ በነበረበት ወቅት በህወሃት ተማርኮ ተወሰደ። ሴኮ ትግርኛ ቋንቋ የለመደው ከነሱ ጋር በርሃ ሳለ ነው። በበርሃ ቆይታው ከዜና አንባቢነት እስከ ሬዲዮ አዘጋጅነት የደረሰ ሲሆን፤ አዲስ አበባ ከገቡ በኋላ ደግሞ የኢህአዴግ ልሳን የሆነው አብዮታዊ ዴሞክራሲ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ሆኖ ሰርቷል።
የሴኩቱሬን ህወሃት ወዳጅነት አንድ ምሳሌ በማንሳት ለማሳየት ልሞክር። ሴኩቱሬ (ሴኮ) አዲስ አበባ ከገባ በኋላ፤ ሰንጋተራ በሚገኘው የቀድሞ የራሺያኖች ካምፕ ውስጥ ይኖር ነበር። በኋላ ላይ ከህወሃት ጋር ተጣብቆ ሃብት በሃብት መሆኑን ሰምተናል። የሆኖ ሆኖ ሁለት እህቶቹን ለምለም እና ክንፍሽን ለሌሎች የህወሃት ሰዎች ድሮላቸዋል። እንግዲህ ምንም ሆነ ምን ሴኩቱሬ (ሴኮ) እና ጌታቸው ረዳ የነሱ ባልሆነ፤ እንደነፍሳቸው ለሚወዱት ነፍሰ በላው ህወሃት ነፍሳቸውን ሰጡ – ያሳዝናል።
በመጨረሻ ስናበታቸው ይሄን ልበል። እነዚህ ሰዎች እንደሁላችንም ወላጆች አላቸው፤ ልጆችም፣ ጓደኛም ይኖራቸዋል። ከመቀሌ ድል በኋላ መጨረሻቸውን እንሰማለን። ሞተው ከሆነ ያሳዝናል፤ አሟሟታቸው ግን የበለጠ ልብ ይሰብራል። “ምናለበት ሳይዋሹ እና ሳይቀጥፉ በኖሩ፤ ጌቾ… ምናለ የላኩልህን ደብዳቤ አንብበኸው ምክሬን ሰምተህ በነበረ? ምናለ ምናለበት በሰላም እጃቸውን በሰጡ ኖሮ? ምናለበት ለቤተሰባቸው ትንሽ በቆዩላቸው ኖሮ?” ያሰኛል። ነገር ግን በተሳሳተ የምድር ዳርቻ ሆነው በተሳሳተ አመለካከት ህይወታቸውን ለማይረባ ነገር ሰጡ። እንዲህ ከመሆን፤ እንዲህ ከመዋረድ ያድናቹህ። አሜን በሉ።
እናም ይህች እለት በህወሃት እና በተከታዮቹ ዘንድ ምንግዜም በሃዘን ትታወሳለች። እኛ ደግሞ የኢትዮጵያ ፀሃይ የወጣባት ቀን ስለሆነች፤ በክብር እናስታውሳታለን። ህወሃት የሞተው ኢትዮጵያዊነትን ለመግደል የሞከረ ቀን ነው። ኢትዮጵያ ከመሞቷ በፊት ግን፤ የኢትዮጵያ አምላክ የህወሃትን ሞት አሳየን። እናም ከሞታቹህ ለቆያቹህ በድናውያን… እንደናንተ “ማረክን ገደልን” ብለን አንፎክርም። በጨዋ ኢትዮጵያዊነት ግን አንድ ነገር እንነግራችኋለን። በህወሃት መቃብር ላይ ኢትዮጵያዊነት ይለመልማል።
EMF ethiomediaforum

1 Comment

  1. የጁንታው ተጠሪ ወደ ደቡብ ሱዳን ሸሽቷል የሚባለው እውነት ከሆነ ሱዳን የወንጀል ተባባሪ ነች ማለት ነው፡፡ ይህ የውጪ አካላት ሻጥር ያለበት ነው፡፡ በአለም አቀፍ ወንጀለኝነት ተጠያቂ የሚሆንን መደበቅ ሱዳን እራሷ ሽብርተኛና ወንጀለኛ ያደርጋታል፡፡

    ለማንኛውም መረጃዎች በአፋጣኝ ተጠናክረው ከ Interpol ጋር በመተባበር ከያሉበት ተለቅመው በዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ የህግ ባለሙያዎች ከመንግስት ጋር መስራት አለባቸው፡፡

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.