ለመላው የኢትዬጵያ ህዝብና ለዶክተር አብይ የቀረበ መረጃ ተኮር ግልፅ ደብዳቤ – ከገብረመድህን አርአያ

በድጋሜ የታተም
ጉዳዩ ፦ የህ.ወ.ሓ.ት.መስፋፋትና መሬት ነጠቃ!!
ክቡር የእትዮጵያ ህዝብ ሆይ ፤
ክቡር የእትዮጵያ ጠ/ሚር ዶ/ር አብይ አህመድ ፡
127710057 10224697834182620 3996076918855153178 n
ገብረመድህን አርአያ

የማቀርበው አብዮቱታየ በኢትዩጵያ ህዝብና በርሶው አስተዋይ መሪነት የእልባት መፍትሄ እንደሚያገኝ በመተማመን ነው ።

ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ ፡በየካቲት ወር 1967 ዓ.ም ደደቢት በረሃ ከመውረዱ ጥቂት ቀደም ብሎ አዲስ አበባ ውስጥ ሆኖ በንድፈ ሃሳብ ያዘጋጀው ማኒፈስቶው ( የትግል ፕሮግራሙ ) ጥር ወር 1967 ዓ.ም. ኤርትራ ሳሕል በረሃ ወርደው የአንድ ወር ወታደራዊ ትምህርታቸው ያጠናቀቁ ቁልፍ አመራረቹ የሚሰጣቸው ትምህርት ጨርሰው የካቲት ወር 1967 ዓ.ም. ደደቢት በረሃ እንደገቡ ፡ተሰባስበው የትግራይ ህዝብ ነፃ አውጪ ድርጅት በሚል የዛሬው ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ መሰረቱ ።
በዚሁ እንዳሉም ይዘዉት የመጡ ፀረ ኢትይዮጵያ አንድነትና ሉአላዊነት ፤ ፀረ ኢትዮጵያ ህዝብ አንድነት ፕሮግራማቸው እጅግ አጠናክረው በመፃፍ አዘጋጅተው ጨረሱ።
ይህ የአቋም ፖሊሲ ፕሮግራም፤በወቅቱ የነበሩ አመራሮች የማ.ገ.ብ.ት ወይም የትግራይ ህዝብ ነፃ አውጪ ድርጅት የዛሬው ህ.ወ.ሓ.ት. ፕሮግራሙ ኢትዮጵያ ዳግም ተመልሳ ሂወት እንዳትዘራ ሃገራዊ አንድነትዋ ፤የህዝብዋ አንድነትና ኢትዮጵያዊነቱ እንዲከስም እንዲጠፋ ተደርጎ የተዘጋጀ ፕሮግራም ፤ከየካቲት ወር 1967 ዓ.ም. እስከ ጥር ወር 1968 ዓ.ም.ጊዜ በመውሰድ የአንድ ዓመት ጥናትና እርምት ፈጀ ፤ተጠናቆ በመዝጋጀት በመጨረሻ በመፅሓፍ መልክ ተሰናድቶ ፤የካቲት ወር 1968 ዓ.ም
1 -በትግርኛ
2 -በአማርኛ
3 -በእንግሊዝኛ ተባዝቶ ተጠርዞ በየአስፈላጊነቱ ተሰራጨ።ይህ የህ.ወ.ሓ.ት. ፕሮግራም በብዙ ኢትዮጵያዊ እጅ ስለሚገኝ ዝርዝር መረጃው አላነሳውም ፤ለአብዮቱታየ መነሻ ሁለት ነጥቦች አቀርባለሁ ።
1ኛ ) ትግራይ ነፃ ሃገር ከአፄ ዮሓንስ 4ኛ ሞት በኋላ በተስፋፊውና ወራሪው ዳግማዊ ምኒሊክ መሪነት ነፃ ሃገር የነበረችው ትግራይ በአማራው ቅኝ ግዛት ሥር ወደቀች::ህዝብዋም ለመክራና ችግር ለስደት ለድንቁርና ወ.ዘ.ተ.ተዳረገ ይላል ።
2ኛ) የዳግማዊ ምኒሊክ ወራርና መስፋፋት ትግራይና ህዝብዋ በቅኝ ግዛቱ ሥር እንደተቆጣጠረ ፤ ዘመቻውን በማስፋት ዛሬ ኢትዮጵያ ተብላ በምትጠራው ሃገር አካባቢ የሚገኙ ነፃ ሃገር ሆነው ራሳቸውን ችለው ህዝባቸው የሚመሩ የነበሩ የተለያዩ ብሄር፤ ብሄረ ሰቦች፤ በአማራው ነፍጠኛ ሠራዊቱ ጥቃት ተፈፅሞባቸው፤ እነዚህንም በአማራው ስርአት ቅኝ አገዛዝ ሥር ከወደቁ በኋላ ኢትዮጵያ ተብላ የምትጠራው ሃገር በ19ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ምኒሊክ የመሰረታት ሃገር ይህች የዛሬዋ ኢትዮጵያ ናት ።
# ትግራይም ከአማራው ቅኝ አገዛዝ ስርአት በብረት ሃይል ትግል ነፃ ወጥታ የቀድሞው ሃገራዊን ነፃነትዋ ታስመልሳለች ።የራስዋንም መንግሥት ትመሰርታለች ። በዚሁ የህ.ወ.ሓ.ት. ፕሮግራም የተካተተው የትግራይ መንግሥት ሲመሰረት ለሚመሰረተው የትግራይ መንግሥት ድንበሩን ማስፋት ከሱዳን ሃገር በድንበር ማገናኘት የድርጅታችን ተግባር ነው።
# የትግራይ መንግሥት ሰፋፊ የእርሻ መሬት በሌለበት ብቁ ሃገር ለመሆን ስለማይቻል ከጎንደር ጠ/ግዛት ሰሜን ጎንደር ወይም በቅድሞ አጠራሩ ሰሜን ቤጌምድር ፤ ወልቃይት ፤ ጠገዴ፤ ጠለምት፡ቃፍታ ሁመራ (ሰቲት ሁመር) ወደ ትግራይ በማጠቃለል ከሱዳን ድንበር በቀጥታ ትግራይ ትገናኛለች ባለ ሰፊ የእርሻ መሬትም እንሆናለን ከዚሁ በማይለይ ከወሎ ጠ/ግዛት ከአለዋሃ ምላሽ እስከ ራያና ቆቦን በማካለል በትግራይ ግዛት ውስጥ ይሆናል ።
የህ .ወ.ሓ.ት. መሪዎች ይህን እቅድና ፖሊሲ ያዘጋጁት
1ኛ )አረጋዊ በርሄ
2ኛ) ግደይ ዘርአፅዮን
3ኛ )ስብሃት ነጋ
4ኛ) አባይ ፀሃየ
5ኛ )ሥዩም መስፍን
6ኛ) መለስ ዜናዊ ሲሆኑ
በፕሮግራሙ እንደ ዋና የትግሉ አቋም አስገብተው ትግሉን ቀጠለ። ይህም በተግባር ለመፈፀም በተለይ በሰሜን ጎንደር እነዚህ የህ.ወ.ሓ.ት. መሪዎች ሙሉ በታጠቀ ኋይላቸው አሰማርተው የሰሜን ጎንደር ነዋሪው አማራው ግፍ ተፈፅሞበታል፤ገደሉት ዘሩን ለማጥፋት ለዓምታት ሰፊ እንቅስቃሴ አካሂደዋል ፤ ገደሉት ፤ አፈናቀሉት ፤ቀሪዉም በስደት ተበታተነ ። በወሎ ጠ/ግዛትም ተመሳሳይ ድርጊት ህ.ወ.ሓ.ት. ፈፅመዋል።
# ድንበር ዘለል የመሬት መስፋፋት ሕገ ወጥ ወራር የመስፋፋት ፖሊሲ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ በህ.ወ.ሓ.ት.መሪዎች ተባራዊ ተደረገ፤ አሁንም አልቆመም ህ.ወ.ሓ.ት.የመስፋፋት ፖሊሲው አጠናክሮ እየቀጠለበት ይገኛል።ይህ ፀረ ኢትዮጵያ አንድነት ፀረ ህዝብ ፤ደም አፋሳሽ ሃገር አፍራሽ ፤ አደገኛ ፋሽሽታዊ ፖሊሲም ነው ።
ህ.ወ.ሓ.ት. ያዘጋጀው ፕሮግራም ወደ ህዝብ ባሰራጨው ወቅት፤ ለመጀመሪያ ተቃውሞ የገጠመው፤ በኢትዮጵያዊነቱ የሚኮራ የትግራይ ህዝብ ነበር ፕሮግራሙን በማውገዝ ጭምር አልተቀበለዉም፤ የከተማውና የገጠሩ ነዋሪ ህዝብ ሁሉ ለማለት ይቻላል እሳት ውስጥ ከቶ አቃጠለው ።
# ወያኔ የትግራይ ሃገር ከአማራው ቅኝ አገዛዝ ስርአት ነፃ ለማውጣት ትግሌን ጀምሬ አለሁ ብሎ ከተነሳበት ጊዜ ጀምሮ ለ5 ዓመታት በፅናትና በጥንካሬ ወያኔን የታገለው ግልፅና ስውር ጥቃቶች አድናቆት በሚሰጥበት የትግል ዘዴ የትግራይ ህዝብ ነው።
ቢታገለዉም አልተሳካለትም ፤በወያኔ ሃብት ንብረቱ እየተወረሰ ቤቱ ፈረሰ፤ እሱም እየታፈሰ ወንድ ሴት ወጣት ሽማግሌ፤ በቀንና ለሊት ከያለበት እየተያዘ እየታፈነ #06 –ሓለዋ ወያነ አስገብተው ጭካኔ በተሟላበት በማሰቃየት የሚቀብርበት ሰፊ ጉድጓድ ራሱን በመቆፈር ፤በቆፈረው ጉድጓድ በጅምላ እያስገቡ በጥይት ረሽነው ገድለው ጨረሱት ።
3ኛ)ከላይ የተጠቀሱ አመራሮች ኢትዮጵያና ህዝብዋም ጭምር አሁን ያሉበት ምስቅልቅልና ችግርም ያደረሱት እነዚህ ሰዎች ናቸው ፤የአማራው የዘር ማጥፋት ወንጀልም ፈፅመዋል። የኢትዮጵያ ሃገር ሉአላዊነት አፍርሰዋል። ዛሬ በኢትዮጵያ ሃገራችን በህ.ወ.ሓ.ት. እየደረሰ ያለው ግፍና መከራ እንዳይደርስ ብሎ አስቀድሞ የተከላከለው የትግራይ ህዝብ የሂወቱ ቤዛ መስዋእትነት ከፍሎ ሂወቱ የገበረው ኢትዮጵያዊ ነው።
ኢትዮጵያ ሃገሬ በወያኔዎች ትፈርሳለች ህዝብዋም ለክፉ የመበታተን አደጋ ይደርስበታል ብሎ ስላመነ ስለ ተነበየ ነበር የመጀመሪያ የወያኔ ግፍ ቀማሽ ያደረገው። ያ የትግራይ ህዝብ ዛሬ የለም፤ ኢትዮጵያዊ ግዳጁ ፈፅሞ በወያኔዎቹ ተገድሎ ከዚች ዓለም ተሰናብቶዋል። የከፈለው ከባድ መስዋእትነት ግን በታሪክ ማህደር ውስጥ መዝገብ ተዘግቦ ይገኛል።
# የኢትዮጵያ ህዝብም ወንድሙ ለሆነው የትግራይ ህዝብ የከፈለው መስዋእትነት ሰሜን ጎንደር ፤ አለዋሃ ምላሽ እስከ ራያቆቦ ያንተ የትግራይ ህዝብ መሬት ነው ሲሉት የኔ አይደለም፡ ይህ መሬት ግዛቱ የጎንደር አማራ፤ የወሎ ግዛት እንጂ የትግራይ ግዛት ሆኖም አያውቅም የትግራይም አይደለም የትግራይ ህዝብ አማራ መሬቴን ቀማኝ ብሎ አያውቅም፤ የሚልበትም ምክንያት የለውም የህ.ወ.ሓ.ት. ፕሮግራም ትልቁ የስህተት ጥፋቱ እዚህ ላይ ነው በማለት አጥብቆ በመቃወሙ ከባድ መስዋእትነት ከፍሎ ያለፈ ኢትዮጵያዊ ነው።
ስለሆነም የኢትዮጵያ ህዝብ ሁሉ በፀሎት ሊዘክረው ይገባል
በሃገራችን ኢትዮጵያ እየታየ ያለውን በጣም አደገኛ የህ.ወ.ሓ.ት. የመሬት መስፋፋት ፖሊሲው የኢትዮጵያ ዘላቂ ሠላምና የሃገር አንድነትና ለክፉ አደጋ የሚዳርግ ይበልጥ የሚጎዳ ደግሞ ንፅሁ ኢትዮጵያዊው የትግራይ ህዝብ ነው።
#የህ .ወ.ሓ.ት መሪዎች የትግራይ ህዝብ ባላቸው የሃይል ጉልበት አፍነው በመያዝ የራሳቸው ፍላጎት መጠቀሚያ ፖሊሲ በማድረግ በስሙ እየነገዱበት እንደሸቀጥ ዕቃ መጠቀም የጀመሩት ደደቢት በረሃ ከወጡ ጀምሮ እንሆ እስከ ዛሬ ድረስ 43 ዓመት አስቆጥረዋል።
ይህ ኢትዮጵያዊ የትግራይ ህዝብ ከባርነት ወለል በታች ሆኖ ፤በባሪያ ስርአት አገዛዝ የህ.ወ.ሓ.ት. ፖሊሲ መጠቀሚያና መነገጃ እያደረጉት ነው ።በማያምንበት በማይፈልገው በሰላማዊ ኑሮው በሂወቱ ከባድ እንቅፋቶች እየፈጠሩበት ነው።
#የትግራይ ህዝብ ህ.ወ.ሓ.ት በተስፋፊ ፖሊሲው በጉልበቱ ከጎንደር፤ ከወሎ፤ ከአፋር፤ ወ.ዘ.ተ.በመስፋፋት ፖሊሲው በወረራ ወደ ትግራይ ያካለላቸው መሬቶች አያምንበትም አይቀበለዉም።
#የህ.ወ.ሓ.ት. መንገድ በኢትዮጵያውያን ወንድማሞች የአንዲት ሃገር ልጆች መካከል ብጥብጥና ህውከት ፈጥሮ ፤የኢትዮጵያን አንድነትና ሉአላዊነት የመበታተነ እቅድና የኢትዮጵያ ህዝብ አንድነትና ኢትዮጵያዊነት የሚንድ ፖሊሲ ነው።ስለሆነም የጥቃቱ ሰለባ የትግራይ ህዝብ ይሆናል።
#የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ ፤
#ክቡር ጠ/ሚር ዶ/ር አብይ አህመድ
የትግራይን ህዝብ ከዚሁ አረሜኔ ፋሽሽት ወያኔ አድኑት ህ.ወ.ሓ.ት. እና ካድሬዎቹ፤ ደጋፊ አባሎቹ፤ ልዩ ፖሊሶቹ፤ የወያኔ ምልሻ፤ በኢትዮጵያ ህዝብ በሚፈጥሩት ችግርና እየፈፀሙት ያለውን ግፍ በተለይ በአማራው በጎንደር ጠ/ግዛት በወሎ ጠ/ግዛት በአፋር ወረዳዎች ፤ ግድያ እስራት ብዙ ነው።
ህ.ወ.ሓ.ት. ወያኔ በመስፋፋት ፖሊሲው የሚፈፅማቸው ያለውን ኢ-ሰብአዊ ተግባሩ በትግራይ ህዝብ ፍላጎት እየፈፀምኩት ነኝ በማለት ፋሽሽታዊ ድርጊቱን ፤ ንፁህ በሆነው ኢትዮጵያዊ በትግራይ ህዝብ እያላከከ ይገኛል። የትግራይ ህዝብ ግን በዚሁ ድርጊት ውስጥ የለበትም ፤እንዲያውም አያውቀዉም ጭምር።
ክቡር የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ
ክቡር የኢትዮጵያ ጠ/ሚር ዶ/ር አብይ አህመድ
ከዚህ በታች የሚታየው ካርታ በህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ የድርጅቱ የቀድሞው አመራርና የአሁኖቹ መሪዎች ተሰባስበው የትግራይ ግዛት ይህ ነው ብለው አምነዉበት ያፀደቁት ነው። ተግባራዊ ለማድረግ በዝግጅት ያለ የተስፋፊ ፖሊሲ እቅድም ይህ ነው። ይህ የወያኔ ህ.ወ.ሓት.የተስፋፊነት ወረራ በይፋ ያወጁት በድርጅቱ ልሳን በሆነው Tigrai on line sep 6 2018 የመስፋፋት ፖሊሳቸው ግልፅ አድርገዉታል ፤ ካርታውን እንመልከት ወይኔ ቀደም ብሎ በወረራ ከይዘው በጎንደር ጠ/ግዛት ወልቃይት፤ጠገዴ፤ቃፍታ
4ኛ) ሑመራ፤ጠለምት ከወሎ ጠ/ግዛት ከላይ አለውሃ ምላሽ እስከ ራያና ቆቦ ፡ በተጨማሪ በሰሜን በኩል የአፋር ወረዳዎች እንደነ በራሕሌ፤ ዳሉል ወ.ዘ.ተ ፤ በጎንደር ከላይ አርማጮህ እስከ ታች አርማጮህ፤ ዓብድራፈዕ፤ መተማ፤ አብርሃ ጅራ፡ወሎ ጠ/ግዛት ደቡቡ ሁሉ ያጠቃለለ ነው ፡እነዚህ ሁሉ የትግራይ ግዛት ናቸው ብሎ የህ.ወ.ሓ.ት. የቀድሞውና የዛሬ መሪዎች የመስፋፋት የሃይል ወራራ በመፈፀምና ለመፈፀም እየተዘጋጁ ናቸው ።
ህዝብና መንግሥት ትክረት በመስጠት ይህ ወራሪው የወያኔ ሕገ ወጥ ተስፋፊነት ማስቆም ግዴታ ነው ። በስንት ሚልዮን የሚቆጠር ህዝብ ከትውልድ ቦታው ተፈናቅሎ ተሰዶስ የት ሊገባ ነው ?
ክቡራን ሆይ ፤ የተስፋፊነት ወረራ ሃገርና ህዝብ ያጠፋል፤ ሃገር ያፈርሳል ፤ ሃገር ስርአተ አልበኝነት ያደርጋል፤ ይህ ከተከሰተ ደግም ሃገር ይፈርሳል ህዝብ ይበታተናል ሃገር የለም ።
# የወያኔ የአሁኑ መስፋፋት የወረራው ፖሊሲም የሚፈፀምባቸው፤ ተፈፅሞባቸው የሚገኙ
1ኛ )የጎንደር አማራው ህዝብ
2ኛ )የወሎ አማራ ህዝብ
3ኛ )የአፋር ህዝብ ዋናዎቹ በሰለባው የተጠቁ ናቸው ።
ይህ የመስፋፋት ወረራ ፤ ፀረ ማንነት መብት ፖሊሲ ነው ፡ወያኔ ህ.ወ.ሓ.ት. በማን አለብኝ ትእቢቱ የኢትዮጵያውያን መብትና ነፃነት በሃገራቸው ውስጥ በጠራራ ፅሓይ እየገፈፈ ነው ።
የኢትዮጵያ ህዝብና መንግሥት ይህ የቅኝ ግዛት መስፋፋት ማቆም አለበት ፡ይህ ካልተደረገ ኢትዮጵያና ህዝብዋ ወደ ክፉ አደጋ ይወድቃሉ ። የወያኔው ፋሽሽት የማፍያ ጥርቅም በኢትዮጵያ ሕግም በዓለም ሕግም ተገዶ ማቆም ይገባል፡ከዚሁ በፊትም በተስፋፊ ፖሊሲው የወረራቸው ቦታዎች ሁሉ የጎንደር ፤የወሎ፤ የአፋር መመለስ ግዴታው ነው። ወያኔ ህ.ወ.ሓ.ት. የኢትዮጵያ ሉአላዊነት እያፈረሰ የኢትዮጵያ ህዝብ አንድነት እየበጠበጠ ፀረ ሰላም ግፈኛ ፋሽሽት ድርጅት መቀሌ መሽጎ መኖር የለበትም ።
ይህ ከታች ካርታ የሚያመልክተው ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ ለመውረር የተዘጋጀበት የአማራ፤ የወሎ፤ የአፋር፤ መሬት፤ ወያኔ የራሱ በሆነው ልሳን( ትግራይ ኦን ላይን) በግልፅ ያወጀው የመስፋፋት ወራር ነው። የኢትዮጵያ ህዝብና መንግሥት ይህ ደም አፋሳሽ ፤ሃገር አፍራሽ ፤ የህ.ወ.ሓ.ት. በጎንደር በወሎ በአፋር የመስፋፋት የሤራ እቅድ ከአሁኑ በሕግ ማቆም አለበት ።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !!!
ጥቅምት ወር 2011 ዓ.ም.

6 Comments

 1. የአድሀሪዎቹ የንጉሣዊ ሥርዓት ሲገረሰስ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝቦች እኩልነት ስላልሰፈነ ደርግን ጥሎ እኩልነት ለማስፈን ህወሀት ብዙ መስዋዕትነት ከፍሎ ያመጣውን ድል ለመንጠቅ እየተደረጉ ያሉ የውሸት ታሪክ ፈጠራዎች ግባቸውን አይመቱም።ህገመንግስቱን የሚጥሱ ውሸታሞች አለምን በአሉባልታ ፈረስ እያዳረሱ ስለሆነ እያንዳንዱን መልዕክት በአንክሮ መገምገም ግድ ይላል ።

  • ቤዛ መለስ ዘራዊ አደንዝዞህ አልፏል መቼም ሰዉ አትሆንም እኛም አንሰለችም አንተን ለማስተማር። የምትዘፍንለት ህገ አራዊቱ ክልሎች ለባለክልሉ ሰጥቷል በዚህ መሰረት ትግሬ ባለ ክልሎቹ ካልፈቀዱለት ከትግሬ ግዛት አይወጣም። ይህ ነገር ይሰማማሀል? ባህርዳርን፤አዲስ አበባን፤ድሬዳዋን ጂማን ለታያት ነዉ ማለት ነዉ ይህ ከተስማማህ ቁለቋልህን እየበላህ ትግሬ ዉስጥ ትኖራለህ። ይመችህ

 2. ጠ/ሚ አብይ አህመድ ልኮት በፌደራል መንግስት የድንበር ኮሚቴ ኃላፊ አቶ ሙላቱ ተሾመ በቅርቡ ወልቃይት መጥቶ እንደተናገረው ከሆነ ደርግ ከመውደቁ በፊት የነበሩት የክፍለ ሀገር ድንበሮች የአብይ አህመድ መንግስት እውቅና አይሰጣቸውም። ማለትም የአሁኑ የፌደራል መንግስት የክልል ድንበሮችን እውቅና የሚሰጣቸው ወያኔ በሳለው ማፕ (map) ብቻ ተመርኩዞ ነው። የአብይ መንግስት ወልቃይት እና ራያ የትግራይ ክልል መሆናቸውን ሙሉ በሙሉ ያምንበታል። አማራ መከራው ሲያካፋበት ከርሞ ሊያባራልኝ ነው ብሎ ሲጠባብበቅ የአማራ መከራ እንኳን ሊያባራ ይኸው ዶፍ ሆኖ መጉረፍ ጀምርዋል።.
  የአማራ ክልል ፀጥታና ደህንነት ቢሮ በኦሮሞዎች እጅ ለመውደቁ ከዚህ በላይ ማሳያ የለም!

  አማራ-ክልል-ፀጥታና-ደህንነት-ቢሮ-በኦሮ/

 3. ቤዛ – ቅራሪ እና አተላ የሆነውን የወያኔ የፓለቲካ አሻጥር መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ያውቀዋል። ወያኔ ማለት ሞትና ጣረሞት ማለት ነው። እንደ እናንተ ያሉ የወያኔ ቡችላዎች ከእውነት ጋር የተጣሉ በውስልትና የተገመድ በመሆናችሁ ምንም ነገር አይገባችሁም። የምታስቡትና የምትተነፍሱበት ጭንቅላትና ሳንባ የተተከለው ዘርና ቋንቋን ተገን በማድረግ ለራሴ ብቻ በማለት ነው። ሃገራዊ ወይም አለም አቀፋዊ እይታ የለውም። የመንደር አስተሳሰብ ነው። ቀኑ ከመሸ በህዋላ ደርግን ደምስሰን ገል መሌ ብትል በሰፈሩት መስፈሪያ መሰፈር አይቀርምና ይኸው እያየን ነው። ገናም ብዙ እናያለን። ሙት ይዞ ይሞታል የሚባለው እንደ ወያኔ ያለው አተላ ድርጅት ራሱን ሊጠብቅ የተሰማራን ጦር በዘር ለይቶ ጥቃት ሲያደርስ እግዚኦ ያሰኛል እንጂ የትግራይ ህዝብ የትግራይ ታጋይ በማለት አያስደነፋም። ሰው አንጋሎ የሚያርድ፤ በሃሺሽ እየተገፋ ወንድሙንና እህቱን የሚገል የሙታን ቡድን ህያዋንን ባላሰቡበት በተኙበት ሰአት መግደሉ የወያኔ ጥልቅ ባህሪ ያሳያል። ስለሆነም በተለያየ የብ ዕርና የፌስ ቡክ በሌሎችም ሚዲያዎች የምትለቁት ውሸት ሰሚ የለውም። ትላንት ዛሬ ባለመሆኑ እንደገና የደፈጣ ውጊያ አድርገን ድል ወደ መቀሌና ወደ ሚኒሊክ ቤተመንግስት እሳቤም ላም አለኝ በሰማይ ወተቷን አላይ እንደሚሉ አይነት ነው። ኦሮማይ ወያኔ … በቃ፤ ቻው!

 4. ጎበዝ ከእንክርዳድም ፍሬ አለ የተባለዉ ብሂል የነጠረ እዉነትነዉ ማሳያዉም ይህ ነዉ። ታዲያ ዶክተር አብይ እንዲህ ያለ እዉነት አለርጅኩ ነዉ ለሱ የሚስማሙት እነ አረጋዊ በርሄ ናቸዉ። አረጋዊ በአንድም መድረክ እዉነትን ተናግሮ የማያዉቅ ከእዉነት የተጣላ ሰዉ ነዉ። ለዚህ ምግባሩም በአብይ ተሸልሟል። እንግዲህ ታሪኩን እኝህ የተከበሩ ኢትዮጵያዊ ቁልጭ አድርገዉ አቅረበዉታል። ክቡር ገ/መድህን ኢትዮጵያ በችግሯ ሁሉ አብረዋት የቆሙ ታላቅ ዜጋ ኖት ክብር ለርሶ ይሁን።
  አረጋዊ በርሄ የተወረሩትን ግዛቶች አስመልክቶ የሚለዉ ህዝቡ ድምጽ ይስጥበት ነዉ። ታዲያ ይህ ቀና የሚመስል ንግግሩ ዉስጡ ሲመረመር በመርዝ የታጨቀ ነዉ አረጋዊ ይህንን የሚልበት ሰይጣናዊ ተልእኮም አለዉ ይኸዉም ህገ አራዊቱን እሱ ስለቀረጸዉ በበጎች መሀል ሁኖ አሁንም ያንኑ መረዙን በተዘዋዋሪ መንገድ ሊተገበር ይዉተረተራል።የወልቃይትና አካባቢ ህዝብ በህወአት ጫና ተባርሮ፤ ተግዞ፤ ተገድሎ ዛሬ በቦታዉ ያሉት ትግሬዎችና ከወልቃይት ሚስቶች የተወለዱ የትግሬ ልጆች ናቸዉ እነሱም መራጭ እድሜ ላይ ደርሰዋል። ታዲያ አረጋዊ በሱ ቤት ብልጥ መሆኑ ነዉ ድምጽ ይሰጥበት የሚልህ። አይ ትያትር አንድ እግርህ መቃብር አፋፍ ላይ ቁሞ መች ነዉ ከእዉነት የምትታረቀዉ።፡
  አማራ ቀበቶህን ጠበቅ አድርግ ድል ባደረግህበት ግዛቶች እነ ቂጤሳ መንጎማለል ይዘዋል ካሁን በሗላ ዉጊያዉ ከኦሮሙማና ትግሬ ጋር ስለሆነ ለጊዜዉ ሀይል አታባክን እንደገና ሀይል አሰባስበህ በርህን ዝጋ። ያለፈዉ ይበቃሀል ፕሮፌሰር አስራት ታላቁ መሪና አርበኛ እንዳሉት “ብትታገልም ትገደላለህ ባትጋደልም ትገዳለህ የቱ እንደሚሻልህ ምርጫዉ ያንተ ነዉ” ነበር ያሉህ። ካሁን በሗላ ሚስትና ልጆችህ ተደፍረዉ የምትኖርበት ክልልና አገር መኖር ስለማይገባዉ ቀበቶህን አጥብቀህ አካቢቢህን ተከላከል። አብይ አንተ ላይ ጤናማ አመለካከት የለዉም። ሔኖክ የሺጥላ በአንድ ወቅት እንዳለዉ “አማራዉ አክብሮ ብቻ ሳይሆን ተከብሮም የሚኖርበትን አገር መፍጠር አለበት። አንዳርጋቸዉ ጽጌ፤ብርሀኑ ነጋ፤ነአምን ዘለቀ የመሳሰሉት ከሌሎቹ ይብሱ እንደሆን እንጂ ስለማያንሱ ነቃ ብለህ መጠበቅ ይገባሀል ስለነሱ በአሁኑ ጊዜ በቂ መረጃ ያለህ ይመስላል።
  በተረፈ የእዉቀት ክፍተት ላለበት ለአማራዉ አካባቢ እራሱን በእዉቀት እንዲያስታጥቅ የተቻለዉ ሁሉ የአቻምየለህን መጽጽሀፍ እየገዛ በስፋት ማዳረስ ይጠበቅበታል። እዉሸት ሲደጋገም እዉነት ሊመስል ስለሚችል አማራዉ በእዉቀት ካልታጠቀ አደጋዉ የከፋ ነዉ።
  ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር

 5. በምንም ጥንቆላም ሆነ ወይንም በምንም Dialectic, In case ካርታው ከምብሓድሽ የመበወዝ እድል ከገጠመው፣ የድሮ ጥያቄአችን ከም ብሓድሽ ለትግሉ መስክ ይቀርባል::
  ዘላለማዊ ሰላም ይሰፍን ዘንዳ፣ ባንዳው መለስ ዜናዊ ያጨናገፈብንን ስርመሰረታዊ አላማችን ዘንዳ መድረስ አለብን፣ ‘እምነ-ፅዮነይ ተደጊፈስ እንታይ’ዶ ከይከውን እየ’ እንዳሉት ንጉሰ ፅዮኑ፣ ግዛታቸው ከአለውሃ እስከ ባፅዕ ድረስ ነበርና፣ በሚቀጥለው የፋሲካ ቅርጫ ክፍፍል ጊዜ ከዚህ የቀነሰ ድርሻ እንደማንቀበል እወቁት::
  Vernunft የሰው ልጆችን በሙሉ globally ካላስተዳደረ በስተቀር፣ ታሪክ መጨረሻ አይኖረውምና፣ እንዲሁም ተጋዳላይ ይሞታል እንጂ ትግል አይሞትምና…..!! እነ የመን እና እነ ቬትናምም በትግል የሚገባቸውን አስመልሰዋና::
  በየቦታው ሆነሽ ሳንቲም እየተወረወረልሽ፣ ‘ኮሎኒያሊስቶቹ ሳይነግሩት፣ ኮሎኒያሊስቶቹ የሚፈልጉትን አዋቂና ሳያዙትም አስተግባሪን’ ሚና ከመጫወት አልፎ Principe የሚባል ተስፋ ተቀዳጅቷችሁ የማታውቁ ባንዳ ሁሏም አፋችሁንና ለንጨጫችሁን ሰብሰብ ማድረግን ተማሩ::
  Unity in diversity, ኢትዮጵያ ታበፅህ ኢደውሃ ሃበ መላ ልጆችዋ…….!

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.