ስልጣን ላይ ያላችሁም ያሰባችሁም ከወያኔ ተማሩ – ሰርፀ ደስታ

woyaneየኢትሐዮጵያ ጉዳይ በሰው ሳይሆን በእግዚአብሔር እጅ እንደሆነ ሁሉም ኢትዮጵያዊው ያስተውል፡፡ ብዙዎች ግፍን ሲፈጽሙ በሌሎች የሰሩት ግፍ ያለ ፍትህ የሚቅር ይመስላቸዋል፡፡ በኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ላይ የሆነው ግፍ ሁሉ አንድ በአንድ እየተቆጠረ ለፍርድ እየቀረበ እንደሆነ ብዙዎቻችን እያስተዋልን አይመስለኝም፡፡ በ60ዎቹ እግዚአብሔር የለም ብሎ የተነሳው ከሀዲና አረመኔ ትውልድ እርስ በእርስ ተበላልቶ ከማለቅ የተረፈው ዛሬም ድረስ በዛው በተጠመቀበት የከሀዲነትና አረመኔነቱ ቀጥሏል፡፡ የበለጠ እሱን መሰል ትውልድም አፍርቶ ኢትዮጵያን እንደአገር የእርግማንና ደም ምድር አድረጓታል፡፡  አረመኔያዊ ግፍ የተፈጸመባቸው የኢትዮጵያውያን ደም ጸባዖት ደርሶ እግዚአብሔርን እስከመቼ ትታገሳለህ ይለዋል፡፡ ለእግዚአብሔር እንደተባለው ነው የራሱ መለኪያና መስፈርት አለው፡፡ ግፈኞችንም በብዙ ምልክት ከግፋቸው ተመልሰው እንዲጸጸቱ ይፈልጋልና፡፡ ይሄ ሊሆንላቸው ግን ከቶውንም አልቻለም፡፡ ከጅምሩ እንዲህ ተጽፎባቸዋልና፡፡ እግዚአብሔርን (እውነትን) በአልወደዷት መጠን የማይገባውን ያደርጉ ዘንድ ለማይረባ አእምሮ አሳልፎ ሰጣቸው ይላል ፈላስፋው የእግዚአብሔር ሰው፡፡ ፈርኦን በእስራኤል ላይ ያደረሰውን ግፍ እግዚአብሔር ለጡብ የሚሆን ጭቃ ስታቦካ እጭቃው ላይ የወለደቻቸውን መንታ ልጆች ከጭጋ ጋር አብራ እንድትረግጥ የተደረገችው ራሔል እንባዋን በእፍኟ ሞልታ ወደሰማይ ብትረጨው የሷንና የወገኖቿን ሁሉ ግፍ ተሸክሞ እግዚአብሔር መንበር እንደደረሰ ለግፈኛው ፈርኦን ከግፉ እንዲመለስና እስራኤልን ነጻ እንዲያወጣ ብዙ ምልክት ተሰጠው፡፡ አንድ ጊዜ ለማይረባ አእምሮ ስለተሠጠ የፈለገውን ምልክትም ቢያ ሊያስተውልና የታዘዘውን ሊፈጽም አልፈለገም፡፡ በመጨረሻም እግዚአብሔር በፈርዖን ግዛት ትውልድ ሁሉ መቅሰፍትን አዘዘ ተገዶ እስራኤልንም ለቀቀ፡፡ እሱም ወደራሱ ሳይመለስ በክፋቱ ቀጠለ፡፡

ከ60ዎቹ የተሳው ትውልድ ነገር እንዲህ ነው የሆነው፡፡ የዛን ትውልድ አረመኔነት ዛሬ በወያኔና ኦነጋውያን ለትውልድ ደርሶ  እናያለን፡፡  ሕግ ፍትህ የሚባለውን ሁሉ አውድመው የአረመኔነታቸውን ሥርዓት ተክተው የግፍን ጥግ እየፈጸሙ በትእቢታቸው ኖሩ፡፡ እግዚአብሔር ግን አየ፡፡ የአረመኔነታቸውንና ትዕቢታቸውንም ሁሉ ልክ ሰፈረ፡፡ ከክፉ ሥራቸው እንደማይመለሱ በሥራቸው ከአረጋገጡ በኋላ እግዚአብሔር ከላይ ፍርዱን ቀጠለ፡፡

TPLF 2ዛሬ  ወያኔዎች ግፍ በፈጸሙባት አገር የመጣባቸውን ብዙ ጊዜ  ሰዎች ከክፉ ሥራቸው እንዲመለሱ ምልክት ተሰጥቷቸው ነበር፡፡ ጭራሽ አረመኔነታቸውንና ግፋቸውን እያከፉት መጡ፡፡ ወደኋላ ስለሆነው ብዙ ታሪክ ማንሳት አልፈልግም፡፡ ብዙ ምልክቶች ነበሩና፡፡ የመጨረሻውንና የዛሬ ሁለት ዓመት ከ6ወር ከደማ የሆነው ምልከት ትልቁ የእግዚአብሐየር ማስጠንቀቂያ ነበር፡፡ ወያኔና ጀሌዎቿ ከቶውንም እንዳያስተውሉ ለማይረባ አእምሮ ስለተሰጡ ማስተዋል አልቻሉም፡፡ ወደራሳቸው ተመልሰው እንዲጸጸቱ የነበረውን ምልክት ጭራሽ ከዛች ቀን ጀምሮ ሌላ የአረመኔነት ጥግ የሆነውን ሴራቸውን ማሰብ ተያያዙት፡፡ ወያኔ ከዛሬ 20 ምናምን ቀን በፊት ስትፎክር የነበረው በባዶ እጇ አልነበረም፡፡ ትቢቷንም ጣሪያ ያስነካው ለ27 ዓመት ያከማቸቸውና ኋላም የሄው አሁን ደግሞ ከመከላከያው የዘረፈችውን ዘመናዊ ያለቸውን መሣሪያ እንደያዘች አስባ ነበር፡፡ ወያኔ የዛሬ ሁለት ዓመት በፊት ከጎንደር ትግሬዎችን በአውሮፕላን እየጫነች ስትወስድ በነበረበት ወቅት ትግሬዎቹ እናንትን (ጎንደሬዎቹን ማለት ነው) በያዝነው መሣሪያ እምሽክ አድርገን ተመልሰን ጎንደርን ለብቻችን እንኖርባታለን እያሉ ነበር፡፡ ከጎንደርም የሄዱበት ምክነያት ችግር ገጥሟቸው ሳይሆን (ቢገጥምስ የራስን አገር ትቶ ወዴት ይኬድ ነበር) በደስታ ነበር፡፡ መቀሌ ከደረሱ በኋላ ግን እንደተነገራቸውና እንዳሰቡት የሆነ አልመሰለኝም፡፡ እንደገባኝ እዛ እንደደረሱ በታጠቁት መሳሪያ ጦርነት ለመክፈት ነበር፡፡  ሆኖም በወቅቱ ስጋት ስለነበረባቸው እስከዛሬ ሲዘጋጁ ቆዩ፡፡

በዚህ ሁለት ዓመት ራሳቸውን ሲያደራጁ ነበር፡፡ አዲስ አበባን ጨምሮ በብዙ ከተሞችም የመጨረሻ አረመኔያዊ ጭፍጨፋንና ሁከትን ሲያዘጋጁ ነበር፡፡ ብዙ ትግሬ ይሄ ተነግሮታል፡፡ ለዛም ነበር አንዳንዶች ከጥቂት ሳምነታት በፊት ለአእኛ ጦርነት ባሕላዊ ጫወታ ነው ሲሉን የነበረው፡፡ ውስጥ ለውስጥ ለብዙ ትግሬ ተነግሮታል፡፡ ከአዲስ አበባም ወደመቀሌ ቤተሰባቸውን ያጓጓዙ እንዳለ እየሰማን ነው፡፡ እሳቤው የነበረው አዲስ አበባ የጦር አውድማ ስለምትሆን ቤተሰባቸውን አስተማማኝ ደህንነት ይኖራታል ተብሎ ወደተነገራቸው መቀሌ ማሸሻቸው ነበር፡፡  መቀሌ ለደህንነታቸው የሄዱት ዛሬ አጣብቂኝ ውስጥ ገብተዋል፡፡ ያሳዝናል፡፡ የተንኮልን ጉድጓድ አታርቃት! በዚህ ነገር ብዙው ትግሬ አለበት፡፡ አዝናለሁ ይሄን በማለቴ! እኔ በዘር ልክፍት የተለከፉ ሰዎችን በየትኛውም መስፈርት በስብዕና ልክ አላስባቸውም፡፡ ዛሬ የኢትዮጵያን ሕዝብ ለምን እኛ ስናልቅ ዝም ትላለህ ይሉታል፡፡ የኢትዮጵያን ሕዝብ ለመጨረስ ሲያሴሩ ከርመው የራሳቸው ሴራ ጠልፎ የጣላቸው፡፡

tigray tplf 40ወያኔ ረጅም ርቀት የሚመታ ሚሳኤል አለኝ እያለች ነበር ስታቅራራ የነበረው፡፡ ይሄን ነበር ለትግሬ ሁሉ እንደ ማስተማመኛ ነግራ ስታስደነፋው የነበረው፡፡ ያላወቀቸው ግን ጠላት ባለቸው በኢትዮጵያውያን በኩል ምን እነዳለ ነበር፡፡ በአለፈው በወታደሩ ላይ በተፈጸመው ጥቃት እጅግ አድርጌ ባዝንም የኢትዮጵያ መንግስት በወያኔ ላይ ምንም ዓይነት ድርድር የሚባል ነገር በለመቀበልና ባለፉት 2 ዓመታት ወያኔ ያለሰበቸውንም ዝግጅት ያደርግ እንደነበር ሳሰብ ሳላደንቃቸው አላልፍም፡፡ ወታደሩ የተጠቃበት ክፍተትን ግን አሁንም ደግሜ በጣም አደገኛ የሆነ ስህተት እንደነበር መጠቆሜን አልተውም፡፡ እንቅልፍ ላይ ሆኖ ምናምን የሚባ ነገር ከቶውንም በወታደራዊ ተቋም ሊነገር የማይገባው ነውና፡፡ ወያኔ ቀደም ብላ ስትደነፋ ባለችበት ሁኔታ ወታደር እንቅልፍ ተኝቶ መሳሪያውን ተነጠቀ ብሎ ወሬ ባልሰማ ጥሩ ነበር፡፡ ወታደሮቹ እንቅልፍ ላይ ሆነው ሳይሆን ይልቁንስ የወታደራዊው ተቋም ሰንሰለት በጠላት እጅ መግባቱ ነበር ችግሩን የፈጠረውና ለብዙ ወታደሮቻችንም ሞትና ስቃይ ምክነያት የሆነው፡፡ ለወያኔም ተጨማሪ መሳሪያ ለማግኘት እድል የገጠማት፡፡ ይሄ ስህተት መማሪያ ሆኖ ያልፋል የሚል ግምት አለኝ፡፡ ጦርነቱ ከታወጀበት ቀን አንስቶ እየተደረገ ያለው የአመራርና የአወቃቀር ብቃት ግን እጅግ አስደስቶኛል አኩርቶኛልም፡፡ ያም ቢሆን ኃይል የእግዚአብሔር ነው! በቅንነትና ከተንኮል በጸዳ ከኆነ  እንዲህ ብቃት ባለው ሁኔታ እንድታስብ ያደርጋልና፡፡ የወያኔም ትዕቢት ከራሽዳሸን ተራራ ታች ሸለቆ ዛሬ ደግሞ ጉድገጓድ ውስጥ እየተንደረደረ ሲገባ አየን፡፡ እነዚያ ታንኮችና ሚሳኤሎች በቆሙበት እንደ ሎጥ ሚስት ድንጋይ ሆነው ሲቀሩ አይተናል፡፡ ሕጻናት የወያኔ ምልምሎች ባልጠነከረ ክንዳቸውና ባልበሰለ እእምሯቸው የምርም ጫወታ ይሆንላችኋል ተብለው ሊሆን ይችላል እሳት ውስጥ ገብተው ብዙዎች ሊጎዱ እንደሚችሉ እንገምታለን፡፡

tplf 1ከላይ የጠቆምኩት ሂደት ሁሉም እንዲያስተውለው ነው፤፡ በተለይ ዛሬ አገርን እየመራችሁ ላላችሁ ይህ ድላችሁ ሳይሆን አደገኛ የሆነ ማስጠንቀቂያ እንደሆነ ተረዱ፡፡ የዛሬ ሁለት ዓመት በፊት የነበረው ክስተት ለእናነትም ምልክት ነበር፡፡ ይሄ ሁለተኛችሁ ነው፡፡ የዛሬ ሁለት ዓመት በፊት ሕዝብ በአንድነት ከልቡ ደግፏችሁ ከጎናችሁ እንደሆን አስተማማኝ በሆነ ሁኔታ አረጋግጦላችሁ ነበር፡፡ በዛን ወቅት እናንተ ወደ ስልጣን ከመምጣታችሁ (አሁን ያላችሁበትን ማለቴ እንጂ ከወያኔ ጋር እንደነበራችሁ አልዘነጋሁትም) ከመምጣታችሁ በፊት በትግሉ ወቅት የኢትዮጵያ ሕዝብ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ አንድ ሆኖ 27 ዓመት ሲሰራበት የነበረውን የዘረኝነትና ሴራ ግንብ ጥሶ ሲነሳ በባዶ እጁ ማን ይደፍረዋል ብለው ብዙዎች የሚያምኑት የዛሬው ጁንታ ያላችሁት ቡድንን ከአዲስ አበባ ወደ መቀሌ እንደገፈተረው አስታውሱ፡፡ በተለይ ኦሮሞና አማራ አንድ መሆን ሲጀምር ብዙዎች ብርክ ይዟቸው እንደነበር አስታውሱ፡፡   ከዛ ግን ብዙም ሳይቆይ ነበር ያንኑ የወያኔ ሴራ በኦሮሞነት ያነሳችሁት፡፡ የኦሮሞ ምሁራንና ፖለቲከኞች ከወያኔ በከፋ እጅግ ተቅበዘበዙ፣ ተስገበገቡ፡፡ ከ27 ዓመት በኋላ አንድ መሆን የጀመረንና ወደ ማንነቱ እየተመለሰ የነበረን ሕዝብ መልሰው አዳጋች ወደሆነ አረንቋ ከተቱት፡፡ በአጭሩ ኦነጋውያን በትግሬ ወያኔ ቦታ ተተኩ፡፡ ለ50 ዓመት ሲያሴሩት የኖሩትን ሴራ በፍጥነት ተሰማሩበት፡፡ ዛሬ ማይካድራ ለዓለም ሁሉ ግልጽ የሆነ በሰብዓዊ ፍጡር ላይ የተፈጸመ ወንጀል ሆኖ እየተነገረ ነው፡፡ የኦነግ-ወያኔ የጣምራ የአርባጉጉና በደኖ፣ በዚህ ሁለት ዓመት በኦነጋውያን የተፈጸመው አረመኔያዊ ግድያዎች ሁሉ ሰውና ፍርድ ባይሰጣቸውም ከላይ ፈርድ ሰጫቸው ከቶውንም የሚተወው አይምሰላችሁ፡፡ የጊዜ ጉዳይ ነው፡፡

Woyane 1 1አሁን ስልጣን ላይ ያላችሁ ዛሬ ለሁለተኛ ጊዜ የገጠማችሁን እድል አስተውሉ፡፡ ይሄን እድል ደግማችሁ ላታገኙት ትችላላችሁና፡፡ ዛሬ በኢትዮጵያዊነቱ የሚተማመን ሁሉ ከአብይ ጎን እንደቆመ አብይና ቡድኑ እያስተዋለው ይመስለኛል፡፡ ከሁለት ዓመት በፊት እንዲሁ ነበር፡፡ በፍጥነት ደብዛውን አጠፋችሁት እንጂ፡፡ ይሄን ለሁለተኛ ጊዜ የገጠማችሁን እድል ብትጠቀሙበት የሚል ማስጠንቀቂያ አዘል ምክሬን ቸል አትበሉት፡፡ እግዚአብሔር ጊዜንና ግፍን የቆጥራል፡፡ ከዚህ በኋላ በኦሮሞነት ወይም በሌላም ማንነት የሚደረጉ ቁማሮች አደጋቸው ምን ሊሆን እንደሚችል አለማሰብ በራስ ላይ ሸምቀቆ እንደማጥበቅ ነው፡፡ የመንግስት መዋቅሮች ወደ ኢትዮጵያዊነት እንዲመለሱ መሥራት ግድ ነው፡፡ ለኢትዮጵያ ጠላት የሆኑን ለማባበል ይሆን በወገንተኝነት ቦታ እየሰጡ አገርን ለአደጋ የመዳረግ ቁማር እስከዛሬ በልተንዋል እንዳላችሁት እንደማይቀጥል እወቁ፡፡ ወያኔም እንዲህ አስባ ነበር፡፡ እንግዲህ ከዚህ ሁሉ መማር ካልቻላችሁ ውርድ ከራሴ፡፡ አሁን ኢትዮጵያውያን ከሌሎች ለመምረጥ ጥሩ አጋጣሚ ነው፡፡ ኦነጋውያን የኦሮሞ ምሁራንና ፖለቲከኞች  ኦሮሞን ሲያዋርድ ከነበረ ወራዳ ጋር ተሰልፈዋል፡፡ አዝናለሁ፡፡ ከረጅም ጊዜ ጀምሮ ይሄን ስጠቁም ነበር፡፡ መሆን የሚገባውን በበጎነት መናገሬ ነበር፡፡ ይልቁንም በኢትዮጵያ ታላላቅ ምልክት የሆኑት የቀደሙ ከዚሁ ኦሮሞ ከሆነው ማህበረሰብ የወጡ ጀግኖችንና መሪዎችን እየሰብኩ እየተበሳጨሁ ጭምር፡፡ ወራዳና ለገዳዮቹ ባሪያ የሆነ ትውልድ መጥቶ የገዛ ጀግኖች አባቶቹን እየሰደበ ከአዋረዱት ጋር ሊያውም በጸረ-ኢትዮጵያዊነት ሲቆም ምን ማለት ይቻላል ነብስ ይማር ከማለት ውጭ፡፡ የሞት ሞት ነውና
የሚከተሉትን የወያኔ አርግማኖች የለምንም ቅድም ማንገራገር ሊሰራባቸው ይገባል፡፡ የወያኔ የሆነውን ሁሉ ከምድራችን ማጽዳት አለብን

  1. የዘር ክልል፡-ለአስተዳደር በሚመች መልኩ ወደ ክፍለሀገርነት እንዲቀየር፡፡ እያንዳንዱን ክልል በጎሳ ሸንሽኖ ዘረኝነትን ተጸየፉ እያሉ ቀልድ ይቁም፡፡ የእያዳንዱ ክልል ሕገ መንግስት ላይ የተጻፈው ምንድነው?
  2. በኢትዮጵያ ባንዲራ ላይ ያለው ኮከብ እንዲነሳ፡- ይህ ኮከብ የአርግማን ኮከብ ነው፡፡ ኮከቡንም ያስቀመጡት ወያኔና ሌሎች የእርግማን ቡድኖች ናቸው፡፡ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ መቼም ቢሆን ከአረንጓዴ ቢጫና ቀይ ሌላ አንዳችም ምልክት ተደርጎበት አያውቅም፡፡ አንዳንዶች ሲያምታቱ በንጉሱ ጊዜ የዘውዳውዊ አንበሳ፣ በመንግስቱ ጊዜ የሶሻሊዝም ዓርማ እንደነበረበት ይናገራሉ፡፡ ይሄ ሆን ተብሉ የሚተረክ ወሸት ነው፡፡ የንጉሱ ጊዜም ይሁን የደርግ የኢትዮጵያ ባንዲራ ከሶስቱ ቀለማት ውጭ አንዲት ነጥብ ምልክት የለውም፡፡
  3. የኢትዮጵያ መዋቅሮች በኢትዮጵያውያን ይያዙ፡- የኢትዮጵያ የመንግስት መዋቅሮች ከማንነት መስፈርት ወጥተው በችሎታና አግባብ ባላቸው ከዘር የጸዱ መስፈርቶች እንዲሆን ይሰራ፡፡ ያኔ አጋሮችም ዋናዎችም እኩል ይሆናሉ፡፡ አሁን የምናየው ብልጽግና በሚል ሊታለፍ የተመከረው ቁማር ይታሰብበት፡፡ አሁንም አጋሮች ከአጋርነታቸው አልወጡም፡፡ የፕሮቲስታንታኒው ብልጽግና የአማራ ብልጽግና፣ የኦሮሚያ ብልጽግና ምናምን እያለ የተቀመጠ እንጂ በወጥነት እንድ ፓርቲ አለመሆኑንም እየታዘብን ነው፡፡
  4. በብሔር ሥም ያሉ ፓርቲዎች በሕግ ይታገዱ፡- በብዙ አገሮች በተለይም በአፍሪካ በብሔር ሥም የፖለቲካ ፓርቲ መመስረት ወንጀል ጭምር ነው፡፡ ይሄን የወያነን እርግማን እያስቀጠሉና እያስተናገዱ ዘረኝነትን እንጸየፋለን የሚል ቁማር አይሰራም፡፡
  5. የወልቃይት ሁመራና ራያ መሬቶች፡- ሰሞኑን በተለይም በማይካደራ ሆኖ ያየንው ላለፉት ብዙ ዓመታተም ሆኖ ሊሆን ይችላል፡፡ በእነዚህ ስፍራዎች ነጋሩን ሕዝብ እያሳደዱ መሬቱን የነጠቁ ዘራፊዎች ባለቤት የሆኑበት እንደሆነ እየታወቀ ዛሬም በትግራይ ክልል ሥር ሆኖ ይቀጥላል የሚል ወሬ መሰማኑትን ቀጥሏል፡፡ በምን ሞራልና የሰብዓዊ ሕሊና ይሄ እየታሰበ እንደሆነ አይገባኝም፡፡ በፌዴሬሽን ምናምን የምትሉትን ቁማር አቁሙ፡፡ ከዚህ በኋላ በእነዚያ መሬቶች ላይ የሚኖሩ አማራዎች በየትኛውም ሕግ በሉት ሞራል በትግራይ ሥር የሚተዳደሩበት አግባብ ኤኖርም፡፡ በአረመኔነት የጨረሳቸውን ክልል መንግስት ዳግም ያስተዳድራቸው ብሎ ማሰብ ከሰብዓዊነትም የወጣ ነው፡፡ ወያኔ ማለት አባይ ጸሐይዬ ብቻ እኮ አደለም፡፡ ዛሬ ማይካድራ ላይ ያየንውን አረመኔነት የፈጸመው እኮ በሕዝብነት ያለ በወያኔ አረመኔያዊ ስብከት ያደገ ነው፡፡ የትኛውም ትግሬ ቢሆን ለጊዜውም ቢሆን አመኔታ ሊሰጠው የሚችል አደለም፡፡ በምንኖረባቸው ከተሞች ለረጅም ጊዜ ጎረቤት የሆናቸው ሳይቀሩ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሁሉ ሳያውቅ ብዙ ትግሬዎች ወያኔ ስላቀደቸው ሴራ ተነግሯቸው ተዘጋጅተውብን እንደነበር አስተውሉ፡፡ እኛ እንደነሱ አንሆነም፡፡ ሕሊናችንም አይፈቅድልንም፡፡ ሆኖም ሁሌም እያረዱን እንዲኖሩ ከዚህ በኋላ እድል አንሰጣቸውም፡፡ እነዚህ ቦታዎች ከዚህ በኋላ ወደ ትግራይ የተባለው ክልል የሚመለሰበትና ሕዘቡ ማንም ይሁን ማን የክልሉን አስተዳዳሪዎች አምኖ የሚቀበልበት ስነልቦና አይኖረውም፡፡ ከጅምሩም እነዚህ ቦታዎች በግፍ የተወሰዱ እንጂ ከትግራይ ጋር የታሪክ ዝምድናም ኖሯቸው አያውቅም፡፡ አዝናለሁ ትግሬን ሁሉ እንደዛ ለማለት አልችልም ሆኖም አብዛኛው ትግሬ ከወያኔ የተለየ አስተሳሰብ ያለው ሆኖ ለማየት አልቻልኩም፡፡

ቅዱስ እግዚአብሔር ኢትዮጵያወንና ሕዝቧን ይባርክ! አሜን!

ሰርፀ ደስታ

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.