በማይካድራ (ትግራይ) ለወደቁት

Maykadra 2 1
አንች ከተማ፣ አንች ሲኦል፤
የዋይታ ሰፈር፣ የሞት ማዕበል፤
ነዋሪዎችሽ፤ ውድ ልጆችሽ፤
የወለዱብሽ፣ የዋሉብሽ፣ የማሰኑብሽ፤
አንቺ ምድር፣ ወይ ማይካድራ፤
አጥልቶብሽ የሞት ጅግራ፤
አጥልቆብሽ ልብሰ-አማራ፤
የሰቆቃ የሞት አዝመራ፤
በማይካድራ ሞት ተዘራ፡፡
 
ረጅሙ፣ ጨካኙ የትህነግ እጅ፤
መላእከ-ሞት፣ ሰውን አራጅ፤
ሃሞተ-ቢስ ተራ ወንበዴ፤
ስርዓት-የለሽ ብኩን መደዴ፡፡
 
ብዙ መቶ ንጹሃን ሲያርድ፤
ራሱ ሙት ነው እንዲያ ሲወርድ፤
ወደ ፅልመት ወደ አውሬነት፤ 
እርግማን ነው የወጣ ከሰውነት፡፡
 
ነፍስ ይማር ለብርቆቹ ለወደቁት፤
ለእኒያ ወርቆች ለቀለጡት፤
ለወገኖች ህይወት ላጡት፤
ይዳብሱ፣ ይዳሱ የግዜርን ፊት፡፡
**************
ፈ.ፉ. (26 Nov 2020)

1 Comment

  1. የወያኔው ቡችላ፤ ማይካድራ ጎንደር አማራ ነው፡፡ ከዚህ በኋላ ትግራይ በአማራ ጀኖች ደም የድሯዋን የጫማ ቁጥር ተስጥቷታል፡፡ ከትከዜ ማዶ ማለት ነው፡፡ አሁን እምበር ተጋዳላይ አይሰራም ለምን አሁን 1983 አይደለም፡፡ አማራ ነቅቷል፡፡ ስለዚህ እየተቀበሩ ላሉት ቁረቆነዳ ባንዳ አጎቶችህ ይህን ግጥም ጻፍላቸው፡፡ ማይካድራ ላይ የተጨፈጨፈው አማራ ነው ወያኔን አይመለከትም፡፡

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.