ወያኔ ያችን ሰዓት  – ሙሉጌታ አቦሰጥ    

ሙሉጌታ አቦሰጥ
November 26, 2020

128208322 1446219968903926 4788124417046839352 nለምንድን ነው ወያኔዎች የመጨረሻ ሰዓት ላይ መድረሳቸውን እያወቁ እጃችሁን ስጡ ሲባሉ ጥሪውን መቀበል ያቃታቸው?

አብዛኛው የትግራይ መስተዳደር ከቁጥጥራቸው ስር ወጥቶ ጥሪውን ከመቀበል ይልቅ በዚህ ግንባር ይህን ያህል ወታደር ማረክንና ደመሰስን ማለቱን ለምን ፈለጉት? የጀግንነታቸውን ልክ 27 ዓመት ሙሉ ስንሰማው እንዳልቆየን አንድ የትግራይ ወታደር የሚዋጋው ከሁለት አገር ጦር ጋር ነው ይሉናል። አንዱ የዐብይ ሌላው የሻቢያ እያሉ በተደበቁበት ዋሻ ሆነው የቁራ ጩኽት ያሰሙናል። “አንበር ተጋዳላይ “ ሊደልቁብንም ይከጅላሉ።

woyaneየወያኔ ቱባ ባለሥልጣናት ያልተገነዘቡትና የረሱት ነገር ቢኖር የጊዜ እንጅ የሰው ጀግና የሌለው መሆኑን ነው። ሻቢያና ወያኔ ያን ያህል ጊዜ ሲዋጉ ደርግን ለማሸነፍ ያልቻሉት ከሕዝብ እቅፍ ባለመውጣቱ ፤የኢትዮጵያ ሕዝብ መንግሥቴ ነው ብሎ እውቅና ስለሰጠውና ከጎኑ ስለቆመ፣ ወታደሩም በአገር ፍቅር ስሜትና ወኔ ስለሚዋጋ ነበር።በኋላ ግን መንግሥቱ የጦር መሪዎችን ሲገደል፣ የዓለም የፖለቲካ አቅጣጫ መቀያየርን ተከትሎ የጎራ አስላለፍ በመቀያየሩና ሕዝብም በሥርዐቱ ላይ ፊቱን በማዞሩ ወያኔ አጋጣሚውን ተጠቅሞ ወደ አራት ኪሎ ለመግባት ችሏል።ሌላው ለዚህ ሥልጣን እንድትበቁ ያደርጋችሁ ደግሞ  ወገኔና ዘመዴ ብሎ፣ በምትነዙት የውሸት ትርክት ተታሎ፣ ያላወቃችሁንና ያላያችሁን እናንተን (ወያኔዎቹን) ከደርግ ትሻሉ ይሆናል በሚል ፊት ለፊት እየመራና እየተዋጋ 4ኪሎ ይዟችሁ በመግባት ለሥልጣን ያበቃችሁ የአማራ ገበሬና በምርኮ የተያዘ የደርግ ወታደር እንደሆነ ማንም የሚአውቀው ሃቅ ነው።

ከዚያማ በአገራችን ኢትዮጵያና ሕዝቧ ላይ ይህን 30 ዓመት የተፈጸመበትንና ያሳለፈውን መከራ ለማን ይንገሯል። ለእናንተና ከናንተ ጎን በጎሳ ፖለቲካ አጥምቃችሁ ላሰለፋችኋቸው ለባለተራ  የዘር አቀንቃኞች፤ ወይንስ “ የልማት መንግሥት” ነን በሚል የአገር አንጡራ ሀብት መዝባሪዎችና  አፈቀላጢዎች ፣ ወይስ በባዶ ዲስኩር ልጆቿን ለጦር ግንባር ልካ ለሞቱባት ሚስኪኗ የትግራይ አናት ፤ካልሆነስ የናንተንና ቤተሰባችሁን ኪስ ለአደለበው ሚስኪኑ የኢትዮጵያ ሕዝብ ። ወይስ አገሬ ብሎ ባለማና ያለውን አካፍሎ ባበላ እንደ ጠላት ተቆጥሮ መሬቱ ለተነጠቀው፣አንገቱ ለተቀላው፣ ለተገደለውና አገር አልባ ሆኖ ለተሳደደው ስፍር ቁጥር ለሌለው አማራ፤ ወይስ ሰላሙ ለተናጋበት፣ ወጥቶ መመለስ፣ ተዘዋውሮ መነገድ ለተቸገረውና ላቃተው ኢትዮጵያዊ፤ እነዚህን ሁሉ የዘረዘርናቸውን እጅ ነካሽ  ጥላሸት አልባሽ ብለን እንድንወቅሳቸውና እንድንኮንናቸው ፈልጋችሁ ይሆን ጦርነት የከፈታችሁብን ? ወይስ የናንተን ዲሞክራሳዊትና ልማታዊ ኢትዮጵያን ‘ማን የማያውቅ አለና ነው ተበደልን ብላችሁ ጦርነት ማንሳት የፈለጋችሁ?

ስሙኝ እናንት ወያኔዎች! ወጣንበት ላላችሁት ለትግራይ ሕዝብ ምን ያህል እንደምትቆረቆሩና እንደምታስቡለት የሰሞኑ ድርጊታችሁ ብቻ በቂ ማስረጃ ነው።ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጉሮሮ ነጥቃችሁና በአገሪቱ ስም ተበደራችሁ አለማንልህ የምትሉትን “ለስሟ መጠሪያ ቁና ሰፋች” እንዲሉ፣  የአውሮፕላን ማረፊያ፣ መንገድና ድልድይ ገና ለገና እናንተ ቀስቅሳችሁ ባመጣችሁት ጦርነት  ከፍራታችሁ የተነሳ መልሳችህ ስታፈርሱት ያየ ሰው በቃ ተከተተ እውነትም ወያኔ የትግራይ ሕዝብን ትወክላለች ብሎ የሚቀበል ይመስላችኋል? ምናልባት ካለ ያው ሰው እንደ እናንተ እኔ ከሞትኩ እንደምትለዋ እንሰሳ የወረደ መሆን አለበት ።

እናንተ የትግራይ የእንግዴ ልጆች!! ለስሙ  ጦርነት እንሰራለን ከእኛ ወዲያ ላሳር በሚል በሞኖፖል የያዛችሁት አስኪመስል ድረስ ስትኮፈሱ ስንሰማችሁ ባጀን ከረምን። የቁርጡ ቀን ሲመጣ ግን ግማሾቹ ቤተስባቸውን ይዘው እግሬ አውጭኝ ብለው ሸሽተዋል። ቀሪዎቹ ደግሞ ያ ሁላ ድንፍታ እንደተነፈስ ኳስ ሟሾ ሰማዩ ተደፍቶባቸዋል። ብዙዎቻችሁ አማራንና ተዋህዶን አጥፍተናታል እያላችሁ ሲትመጻደቁባት ወደነበረችው የነፍጠኛ ቤትክርስቲያን ተደብቃችሁ ስትማጽኑ እንደምትውሉ ሰማን ።አወ በመጨረሻው ሰዓት ጻዲቅ ለሞቱ ይባላል አይደል፤ ማን ያውቃል፣ ድንገት ብትጸድቁስ

ዓለማችን ብዙ ጦርነቶችን አካሄዳለች።ብዙ አምባገነን መሪዎችም ታይተዋል፣ አልፈዋል።ብዙዎቹ ሕዝብ ይሁንታውን ሲነፍጋቸው፣አገዛዛቸው ሲአንገፈግፈውና በቃኝ ሲል የሚአደርጉትን ከንቱ መፍጨርጨር ትተው የሚሰጣቸውን የማሪያም መንገድ አንድም እወደዋለሁ ለሚሉት ሕዝባቸው ሲሉ፤ አለዚያም ቤተሰባቸውንና ከተማቸውን ታድገው  በአገኙት ቀዳዳ ተጠቃሚ ለመሆን የሚቀርብላቸውን ጥሪ ይቀበላሉ።

አፄ ቴዎድሮስ ለሞሞታቸው ምክንያት የሆኑትን አስረው የያዟቸውን እንግሊዞች በመጨረሻ ሰዓት ሊገድሏቸው ሲችሉ ፈትተው የለቀቋቸው ለነፍሳቸው ፈርተው አልነበረም። በዚያን ዘመን ከነበረው ንቃተ ኅሊና በተሻለ አርቆ ለማስብ በመቻላቸው የናፔር ጦር በበቀል ተነሳስቶ የኢትዮጵያን ሕዝብ  እንዳይገድል ታድገዋል።እሩቅም ሳንሄድ ኮሮኔል መንግሥቱ ኃይለ ማሪያም ሥልጣናቸውን በሰላም ለቀው ወያኔ 4ኪሎ እንድትገባ የተደረገው የአዲስ አበባ ሕዝብ (ሽማግሌ፣ ሴትና ሕጻናት) ያላግባብ በእናንተ አረመኔዎች  እንዳይጨፈጨፍ  ስለተሰጋ ነበር።

ሌላው ደግሞ በ2ኛ የዓለም ጦርነት እብሪተኛው የናዚ ፋሽስት ዓለምን ለመቆጣጠር ጎረቤት የሆኑ የአውሮፓ አገራትን በአጭር ቀናት እያጠቃ ከተማቸውን እያቃጠለና እያወደመ ሲጓዝ ያዩ የቸከ አርበኞች ያነሱትን መሳሪያ ጥለው፣ሕዝቡን አሰልፈው አበባ ይዘው ነበር የሂትለርን ጦር የተቀበሉት።ይህን በማድረጋቸው ለብዙ ዓመታት በንጉሦቻቸው የተገነቡ ውብና ማራኪ የቱሪስት መስህብ ያላቸውን  የቤተመንግሥት ሕንጻዎቻቸውን፣ሥነ ሕንጻና ኪነጥበባቸውን ለማስጠበቅ ወይም ለማትረፍ በቅተዋል።

ሰሙኝማ!   ወያኔ ያችን ሰዓት ያልኳችሁ በናንተ የጎሳ ፖለቲካና የጥላቻ አገዛዝ ሲመራ የቆየው  የኢትዮጵያን ሕዝብ ቤተሙከራ አድርጋችሁት በተለይ የአማራው መሬትና እርስት የሆነውን ወልቃይት፣ ጠለምት፣ሁመራና ራያን ቀምታችሁ የጥቃት ዒላም አድርጋችሁ በድፍን ኢትዮጵያ አብሮና ግንባር ቀደም ሆኖ ባለማት አገሩ እንደመጤ ተቆጥሮ ስታስጨፈጭፉት አመታት አስቆጥራችኋል።

አላወቃችሁበትም እንጅ ዶክተር ዐብይ ለእናንተ የማሪያም መንገድ ስጥቶ፣ የዘረፋችሁትንና ያጠፋችሁትን ሁሉ ይቅር ብሎ፣ የክልል ሥልጣናችሁንም ሳይነካ፣መከረኛ አማራውንም እያስገደላችሁ እንድትቀጥሉና  አብራችሁት እንድትሠሩ ዕድል ሰጥቷችህ ነበር። ግን የናንተ ነገር የአህያውና የውሻ ጓደኝነት አይነት ሆነ ። አህያዋ ከተጠበቀ ክልክል ሳር ውስጥ ገብታ በልታ በልታ መሸት ሸት ሲል ጥጋብ አላስችል ይላታል። የሚበላው አጥቶ እርቦት ተቆራምዶ የተቀመጠውን ጓደኛዋን ቡቸን ልጮህ ነው አለችው። ቡቸም ተይ አይሆንም አያ ጅቦ ስምቶ ይመጣና ይበላሻል ሲላት ግድየለህም ልጩህ ብላ ከዚያ በኋላ የሆነችውን ብዙዎቻችን የምናውቀው ተረት ያመስለኛል። የወያኔም ነገር አጥብቆ መጮሁ እንደ አህያዋ ለመሆን ካልሆነ ሌላ ምን ፋይዳ ያመጣ ብላችሁ ነው።

ዶክተር ዐብይ ለወያኔ ያሳዩት ከመጠን ያለፈ ተለሳሳሽነትና ትዕግሥት አሁን ለገባንበትና እያስከፈለን ላለው ሁሉ ችግር መንስሔው እንደሆነ ቢታወቅም፤ ለአገር ደህንነትና ሰላም ሲባል የተከፈለ ዋጋ (Sacrifice ) ነው በሚል በይቅርታ የታለፈ ጉዳዩ ነው።እናንተ ወያኔዎቹ ግን የተስጣችሁን እድል በአግባቡ በመጠቀም ፈንታ ትዕግሥቱን እንደ ፍርሃትና አቅም ማነስ በመቁጠር 27 ዓመት የሰራችሁት ግፍ አነሰና ሌላ ጦርነት በአማራውና በመንግሥት ወታደሮች ላይ ከፍታችሁ። ስለዚህ ከላይ እንደገለጽኳት እንሰሳ የዘረፋችሁት ገንዘብና ያአጣችሁት ሥልጣን ሲታወሳችሁ በቁማቸሁ አይደለም በእንቅልፋችሁም ጭምር እያራጀ እረፍት እየነሳቸሁ መጣ ።ጥጋባችሁ ልክና ጥግ አጣ። የተሰጣችሁንም የማሪያም መንገድ ዘጋችኋትና አረፋችሁ።

የመረገም ይሁን ወይም ከዚያ ከመነሻችሁ ደደቢት በረሃ የተጸናወታችሁ ድድብና አለቅ ብሏችሁ፤ ከአንድም ሁለት ሶስት ጊዜ በውይይትና በሽምግልና መግባባት ላይ እንዲደረስ የቀረበላችሁን የሰላም ጥሪ አንቀበልም አላችሁ።”ከተራበ ለጠገብ አዝናለሁ” ሆነና የቀደሞው ግፍና በደል አነስና ድፍን ሁለት ዓመት ተኩል በየክልሉ በአስተባባሪነትና በመሪነት ሰላምችንን ስታውኩ፣ ስታስገዱሉንና ስታርዱን ከቆያችሁ በኋላ፤ ሰሞኑን ደግሞ በማይካድራ የአማራ ተወላጆች ላይ የለየለት የዘር ማጽዳትና ጅምላ ግድያ ፈጸማችሁ። ሳሚራ የትግራይ ወጣት ጨፍጫፊ ቡድን የተሰጣቸውን ትዛዝ ከፈጽሙ በኋላ ወደ ሱዳን እንዲሰደዱና እንዲአመልጡ ታስቦበትና ታቅዶ ተሰራ።

የአገሪቱን ዳር ደንበር ለማስከበር ሌትና ቀን የፀሐይ ሀሩርና ብርድ እይተፈራረቀበት 20ዓመት በላይ በትግራይ ምድር ላይ የቆየን የመከላከያ ሠራዊት፤በገንዛ የሥራ ባልደረቦቹ በማንነታቸው ተለይተው እንዲታረዱና እንዲገደሉ ያደርጋችሁት ትውልድ ሁሉ ይቅር የማይለው የጦር ወንጅል ነው።እነሱ በሚጥብቋት አገር፣ በሚአስከብሩት ሰላም  እናንተ ጌቶች እየተዝናናችሁ በየሆቴሉ ስክራችሁ ስታቀረሹ ታመሻላችህ ታድራላችሁ።የእነሱ ወንጀል አገር መክዳት፣በብድር የመጣን የአገር ሀብት ማሸሽና ንጹሃንን ማስገደል አልነበረም። ለሞት ያበቃቸው ወንጀል ቢኖር ለአገርና ለባንዲራ ታማኝ ሆኖ መገኘት ብቻ ነው።

በአጠቃላይ በእናንተ አስተባባሪነትና አጋፋሪነት እነዚህ በአገራቸው ላይ እንደመጤ ተቆጥረው በሐረር በበደኖ ፣በባሌ ጎባና አገርፋ፣ በአሪሲ ሻሻመኔ፣ በቤንሻንጉል፣ በወልቃይት በማይካድራና በጦሩ ላይ ያፈሰሳችሁት የንጹሃን ደም ይጮሃል!! አሁን ግን  ጽዋው ሞልቶ በመፍሰሱ መሰለኝ ጥጋባችሁን ሊያበርድ ከላይ የመጣ የፈጣሪ ጥሪ ወይም ቁጣ ወርዷል።ከእንግዲህ  አጉል አንቡር እንቡሩን ተውት። የትግራይን ሕዝብ ከልብ የምትወዱት ከሆነ እጃችሁን በመስጠት ከዳግም ጥፋት ታደጉት።

በተረፈ በዓለም ላይ እንደ ወያኔ የመንግሥት ሥልጣን ይዞ በሚገዛው ሕዝብና በሚአስተዳድረው ምድር ላይ  ቁማር የተጫወተ ይኖራል ብሎ ለመገመት ይከብዳል። ለሰው ልጅ ሕይውት፣ለአገር ወሰንና ደንበር የሰጣችሁት ግንዛቤና ዋጋ value የቱን ያህል የወረደና የዘቀጠ መሆኑን በሥልጣን በቆያችሁበት ዓመታት ሁሉ ታዝበን ታዝበን፤ ቋቅ ብሎን ዳግም አያሳየን ( Never again )ከውስጣችን አንቅረን አወጥተናችኋል።ምናልባት  በኢትዮጵያችን ከብዙ ዘመናት በኋላ እንደሚከሰት ቀሳፊ በሽታ የምትታወሱ የምድር ሲኦል አጋንት( Evil of the evil ) ተብላችሁ በጥቁር መዝገብ የምትታወሱ ጉዶች ሳትሆኑ ትቀራላችሁ? ስለዚህ ወደዳችሁም ጠላችሁም እንደ አባቶቻችሁ የአገርን ጥቅም፣ የሕዝቡን ሰላምና አንድነት በባንዳነት እንደቆመራችሁበት ግባተ መቃብራቸሁ ይፈጸማል።

በመጨረሻም “ ወያኔ ያችን ሰዓት”ያልኳትን ተጠቀሙባት፤ ከንግዲህ የኢትዮጵያ ሕዝብ እናንተን 4ኪሎ ሊአያችሁ ይቅርና ልታፈርሷት የፈለጋችሁትን የመቀሌን ከተማ  የሰላም አየር እንኳ አየተነፈሳችሁ እንድትንቀሳቀሱ በፍጹም አይፈቅድም። ወደ ልቦናችሁ ተመልሳችሁ ጥሪውን ከተቀበላችሁ ይህን ደግ፣አስተዋይ ፣ መከራ ቻይና ትዕግሥተኛ የኢትዮጵያን ሕዝብ ምን ያህል እንደበደላችሁት ይቅርታ ብትጠይቁት መልካም ነው።ከዚያ ጉዳያችሁ በሕግ አግባብ ታይቶ ውሳኔውን ብትቀበሉ  የተሻለ አማራጭ ነው ብየ እገምታለሁ ። ከዚህ ውጭ ሌላ አማራጭ መፈለጉ  “ጨው ለራስህ ብትል ጣፍጥ  ካለዚያ ድንጋይ ነው ብለው ይጥሉሃል “ ነውና የቀረቻችሁን የመጨረሻ ሰዓት እውቁባት። ታሪክ ስሩና እለፉ። አበቃሁ አዲዮስ።

ሙሉጌታ አቦሰጥ

 

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.