የታሪካችን ጥቁር ጠባሳ የሆነው የማይካድራ ጭፍጨፋ ካላስተማረን ምን ሊያስተምረን ይችላል? (ኢዜማ)

ezemaየኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) አመራር እና አባላት በማይካድራ በተፈፀመው የብሄር ማንነትን መሰረት ያደረገ የንፁሃን ዜጎች ጭፍጨፋ የተሰማንን መሪሪ ሀዘን ለመግለፅ እንወዳለን።
በሀገራችን በህወሓት አመራርነት የተተገበረው የዘር ፓለቲካ መጨረሻው መልክ እየተለየ፣ ቋንቋ እየተሰማ፣ ሥም እየተጠየቀ እና መታወቂያ እየታየ መተራረድ እንደሚሆን ሳይታለም የተፈታ ነበር። ብዙዎች ይህን እና ከዚህም ሊብስ የሚችለውን ግዜ በማሰብ ነበር ከጀመርነው የጥፋት መንገድ በግዜ እንድንወጣ ሲያሳስቡ የቆዩት። ዘርን መሰረት ያደረገ ፓለቲካ ማንም ይተግብረው ማን ትላንትም፣ ዛሬም ፣ ነገም አጥፊ ነው።
#ኢዜማ ከገባንበት አዙሪት መውጫው መንገድ የችግሩ ምንጭ የሆነውን የዘር ፓለቲካ ለአንዴና ለመጨረሻ ግዜ በማስወገድ ዜግነት ላይ ብቻ መሰረት ያደረገ ፓለቲካ መመስረት መሆኑን ያምናል። ለዚህም ይታገላል።
የኢዜማ አባላት እና አመራሮች በተደጋገሚ በሚፈጠሩ የንፁሃን ዜጎች ሞት ሀዘናችን ጥልቅና መራር ነው። ለመላው ኢትዮጵያዊያን መፅናናትን እየተመኘን በዚህ አሰቃቂ ጭፍጨፋ ላይ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ተሳታፊ የሆኑ ወንጀለኞች ሁሉ ከአገር ውስጥም ይሁን ውጪ ከየተደበቁበት ተይዘው ለፍርድ እንዲቀርቡ እንጠይቃለን።

3 Comments

 1. Yes, you are asking the very challenging but not easy question and it is good to do so!
  However, this question should be first and foremost addressed to and to you because it is the so called opposition political entities like yours that have terribly failed the people of Ethiopia and contributed significantly to this very nonsensical war which could have been prevented from the very beginning of its inception in the very minds of evil-driven politicians 0f TPLF and the very not only negligent but highly hypocritical, dishonest, cynical, conspiratorial, and narcissist ruling circle of ODP-led politicians .
  Are you really surprised because the very bloody ethnocentric political system created and well planted by the two factions now fighting and consuming the very priceless lives of citizens on both sides was not unexpected? Have you tried with your own independent mind set and action to be a reliable and persistent force of democratic change instead of presenting yourself as “good guys” of the very hypocritical and disingenuous politicians of so called agents of change? What did you do to prevent or stop the imaginably horrifying politically motivated crimes happened and continued to happen rampantly?
  How your stupid way of political thinking and behavior that has been and is being used for the appeasement of your “good friends” of palace politics can be an asset to prevent nonsensical wars of power struggle and to make peoples’ dream for a democratic system a reality?
  Aren’t you tired of being the guys of the politics of producing and posting very monotonous and self-deceiving political statements while millions and millions of innocent citizens are terribly exposed to untold sufferings and lost their lives in a very inhuman manner?
  Do you really believe that one faction of EPRDF which is controlling the palace politics and playing its own version of the same deadly politics of ethnocentrism is a reliable asset for taking the country to the very desirable destination of political system? Have you seen and can you see things going from bad to good or bad to worse with the leadership of this faction of EPRDF who now calls itself Prosperity? By the way, how claiming yourself as independent and reliable alternatives to a true democratic change while you are victims of the palace politics even in terms of facilities such your office and may be some more make sense?
  Please slow down, take deep breath and critically search your own very inner soul and take what is right to the people, not what is convenient to those highly deceiving politicians of EPRDF//Prosperity who are not willing and able to genuinely get out of the political quagmire they found themselves in and cleanse their hands stained with the very blood of innocent citizens for so many years and continued in a very horrifying manner.

 2. ኢዜማ ይህን አቋዋም የዘር ፖለቲካ ከምርጫ በፊት እንደቅድመ ሁኔታ በመያዝ መታገል አለበት፡፡ ግድ አቋም ሊሆን ይገባል፡፡ ሌሎችም ፓርቲዎች የአማራ፣ኦሮሞ፣ ሱማሌ፣ ትግራይ፣ ጋምቤላ፣ አፋር፣ ነፃ አውጪ ግንባር የሚሉ በህግ ሊከለከሉ ይገባል፡፡ ህዝብ እኮ በቀጣይ ከትህነግ/ህዋአት ግንባር ነፃ ከወጣ ሌላ ነፃ አውጪ ግንባር ወይም ፓርቲ አያስፈልግም ብልፅግና ፓርቲም ቢሆን ለዚህ ሊያመቻች እና መፍትሔ አያስፈልግም፡ የዛሬ 40 ዓመት በፊትም እነ ህውአት/ትህነግ ይህንን ነፃ የማውጣት Ideology ይዘው ተነስተው ከእራስ ጥቅም ውጪ ህዝብን ወደ መቀመቅ ነው የከተቱት ሌላውስ ነፃ አውጪ ግንባር ፓርቲ ለህዝብ ምን ጠቀመ፡፡

  ስለዚህ ኢትዮጵያን አንዳንድ ፓርቲ ይህን ባይፈልግም ወይም ዜግነትን የሚያመለክት ፓርቲ ነው አገሪቷ የሚያስፈልጋት፡፡ አለዚያ የስም ለውጥ ለህዝብ አይጠቅምም፡፡ ሁሉም ያስብበት:: እንደው ከአሁን በኃላ ለስልጣን የሚሻማ ፓርቲ ወይም ግለሰብ ይኖራል?? መቼም አይታሰብም ከትህነግ/ህውአት ሁሉም ሊማር ይገባል፡፡ ምን ያደርጋል ስልጣን፣ ፓርቲ፣ ዝርፍያ፣ ግድያ … ወዘተ ይልቅ ታሪክ ለህዘብ መስራት፡፡

  ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር፡፡ ድል ለኢትዮጵያ!!

 3. ኢዜማ ይህን አቋዋም የዘር ፖለቲካ ከምርጫ በፊት እንደቅድመ ሁኔታ በመያዝ መታገል አለበት፡፡ ግድ አቋም ሊሆን ይገባል፡፡ ሌሎችም ፓርቲዎች የአማራ፣ኦሮሞ፣ ሱማሌ፣ ትግራይ፣ ጋምቤላ፣ አፋር፣ ነፃ አውጪ ግንባር የሚሉ በህግ ሊከለከሉ ይገባል፡፡ ህዝብ እኮ በቀጣይ ከትህነግ/ህዋአት ግንባር ነፃ ከወጣ ሌላ ነፃ አውጪ ግንባር ወይም ፓርቲ አያስፈልግም ብልፅግና ፓርቲም ቢሆን ለዚህ ሊያመቻች እና መፍትሔ አያስፈልግም፡ የዛሬ 40 ዓመት በፊትም እነ ህውአት/ትህነግ ይህንን ነፃ የማውጣት Ideology ይዘው ተነስተው ከእራስ ጥቅም ውጪ ህዝብን ወደ መቀመቅ ነው የከተቱት ሌላውስ ነፃ አውጪ ግንባር ፓርቲ ለህዝብ ምን ጠቀመ፡፡

  ስለዚህ ኢትዮጵያን አንዳንድ ፓርቲ ይህን ባይፈልግም ወይም ዜግነትን የሚያመለክት ፓርቲ ነው አገሪቷ የሚያስፈልጋት፡፡ አለዚያ የስም ለውጥ ለህዝብ አይጠቅምም፡፡ ሁሉም ያስብበት:: እንደው ከአሁን በኃላ ለስልጣን የሚሻማ ፓርቲ ወይም ግለሰብ ይኖራል?? መቼም አይታሰብም ከትህነግ/ህውአት ሁሉም ሊማር ይገባል፡፡ ምን ያደርጋል ስልጣን፣ ፓርቲ፣ ዝርፍያ፣ ግድያ … ወዘተ ይልቅ ታሪክ ለህዘብ መስራት፡፡

  ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር፡፡ ድል ለኢትዮጵያ!!

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.