በሱዳን የአረመኔዎች ካምፕና ከወያኔ ያልተናነሱት የኦነጋውያን

127655321 111581797444748 8742625421250343266 n
የዘር ማጥፋት ተጠርጣሪዎቹ የ”ሳምሪ” የህወሓት ገዳይ ወጣቶች ቡድን በሱዳን ስደተኞች ጣቢያ  – የማይካድራ ነብሰ ገዳዮች እና ጨፍጫፊዎች!!
ማይካድራ ላይ ጭፍጨፋ ፈፅመው ሱዳን የገቡትን እኚህን ወጣቶች ኢትዮጵያ በአስቸኳይ ተላልፈውላት እንዲሰጡ መጠየቅ አለባት። ይመስገነው በ27 አመት ውስጥ ትህነግ ኢትዮጵያውያንን የሚያሰርበት በሽ እስር ቤት አለ። እነዚህ ወንጀለኞችን ለፍትህ ቀርበው የእጃቸውን ማግኘት አለባቸው እንጂ በስደተኝነት ወደ አውሮፓ መሻገር የለባቸውም። – ማይካድራ ፕሬስ

የማይካድራው አረመኔያዊ ጭፍጨፋ ከታሰበውም በላይ ዘግኛኝና አስደንጋጭ እየሆነ መጥቷል፡፡ አሁንም ብዙ ያልተሰሙና ቆይተው ሊወጡ የሚችሉ ዘግኛኝ እውነቶች እንደሚኖሩ ይገመታል፡፡ አሁን እየሰማንና እያየን ያለንው ደግሞ እነዚሁ አረመኔዎች በስደተኝነት ስም ወደ ሱዳን እንደገቡና በተባበሩት መንግስታት መጠለያና ምግብ እየተሰጣቸው ለሌላ አረመኔያዊ ዕቅድ እያሰሉ እንደሆነ ነው፡፡ ይሄ እንደቀላል መታየት ያለበት ጉዳይ አደለም፡፡ የስደተኛ መጠለያ ኃላፊዎችን እስከሚያስደምም ድረስ ከዚህ በፊት ከተለመደው የሴቶች ሕጻናትና አቅመደካሞች በተቃራኒ አሁን ወደ መጠለያ ካምፖቱ እየጎረፈ ያለው ነብሰገዳይ አረመኔ ወጠምቻ ወንዶች እንደሆኑ እየተነገረ ነው፡፡  በፎቶም የሚታየው ይሄው ነው፡፡ እነዚህ ሰው በላ ፍጡራን በሰብዓዊነት ሥም የስደተኞች መጠለያን መሸሸጊያ፣ ለሌላ ጥፋት መደራጃ አሊያም ከወንጀል ማምለጫ እንዳያደርጉት ከወዲሁ ይታሰብበት፡፡ በእነዚህ በተባሉት መጠለያ የሚገቡ በተለይ ወንድ ወጣቶች በልይ ሁኔታ ክትትል እንዲደረግባቸውና የኢትዮጵያ መንግስትም ወደቦታው በመዝለቅ ወንጀለኞቹን ለፍርድ ማቅረብ ይገባዋል፡፡ ዓለም ዓቀፉ ማህበረሰብም ይሁን ሱዳን ለዚህ ሙሉ ትብብር ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡

127739187 111581807444747 23622898456933033 n
የዘር ማጥፋት ተጠርጣሪዎቹ የ”ሳምሪ” የህወሓት ገዳይ ወጣቶች ቡድን በሱዳን ስደተኞች ጣቢያ  –

ባለፉት 30 ዓመታት በወያኔ አረመኔ አሸባሪ ቡድን የተፈጸመው ወንጀል እንኳንስ ወያኔን በአጋር ይሁን በዋና ተባባሪነት ከወያኔ ጋር ሲሰሩ የነበሩ ድርጅቶችና ግለሰቦች በሕግ ፊት መቀረባቸው አይቀርም፡፡ ይህ ዓለም ዓቀፉን ማህበረሰብ ውስጥ ያሉትንም የሚጨምር እንደሚሆን አገምታለሁ፡፡  ብዙ ማይካድራዎች ነበሩና፡፡ የወንጀሎቸ አሰቃቂነት ምን ዓልባትም ከዚህ በፊት ያልተሰሙ እንደሚሆኑ እናስባለን፡፡ በተለይ ደግሞ አማራ ላይ የተፈጸመው ወንጀል ከጅምሩ ከአርባጉጉና  ከበደኖ ጀምሮ እሰከ ማይካድራ አሁንም ያላባራ ግፍ እየደረሰበት ነው፡፡ ሱማሌና ጋምቤላ የወያኔ አረመኔዎች ከፍተኛ ግፍ የፈጸሙበት ነው፡፡ ኦሮሞ ከወያኔ የአረመኔ ግፍ ባይድንም የወያኔ ትልቁ ጉልበቷ አሁንም ድረስ ኦሮሞ ነው፡፡ በጣም እየመረረኝ ይህን ደጋግሜ ተናገሬያለሁ፡፡ ኦሮሞ  ከወያኔ የባሰ አረመኔ ኦነግንና ኦነጋውያንን ፈጥሯል፡፡ አዝናለሁ፡፡ ሰሞኑን በዚህ ወሳኝ በሆነ ወቅት እንኳን እየተቆመረ ያለውን ነገር ስናይ ልባችን ይደማል፡፡ ስንት ኦሮሞ በጽዱ ኢትዮጵያዊነት እንዳለ ባላውቅም በጣም ብዙ የሚባል ኦነጋውያኑ ግን በጥላቻና ዘረኝነት እጅግ በከፋ ሁኔታ ተመርዘዋል፡፡ የአማራ የወልቃይትንና ሁመራን እንዲሁም ራያ አላማጣን በደሙና በጀግንነቱ ነጻ ማውጣት ብዙ ኦነጋውያንን እብድ አድርጎ ታዝበናል፡፡ በዚህም አልበቃም የራያ ኦሮሞን ለመደለል ይሄው ጦርነቱ ሳያልቅ ዘመቻ ተጀምሯል፡ ሲዳማ የኦሮሞ ኦነጋውያን ተከታይ ነው፡፡ ኦሮሞ ኦነጋውያኑ ወያኔን እንደተከተሉ ማለት ነው፡፡ ጉሙዝ ከኦነጋውያንም ከወያኔም በመታገዝ አረመኔነቱን ቀጥሏል፡፡ ቀሪው የኢትዮጵያ ሕዝብ አንሰም በዛም ወደልቦናው ተመልሷል፡፡

ቀጥሎ ያለው ጊዜ ያሳስበኛል፡፡ አሁን ሁሉም ለራሱ ሲል ከማን ጋር መቆም እንዳለበት ማሰብ ይገባዋል፡፡ ከአሳዳጊያቸውና ከፈጠራቸው እየተማሩ ያይደሉት የኦሮሞ ባለስልጣናት ኢትዮጵያን ወደ ሌላ አደጋ እየመሩ እንደሆነ ላፍታም ቢሆን መዘንጋት የለበትም፡፡ በግልጽ የምናያው እውነት ይሄ ነውና ሁሉም ያስብበት፡፡ ውጤቱ ለማንም ባይጠቅምም ከራሱ ከኦሮሞ በላይ ግን ተጎጅ እንደማይኖር አውቀለሁ፡፡ ኦሮሞ እንደማህበረሰብ ይሄን መርዛማ አመለካከት ከራሱ ካላወጣ አደጋው የከፋ እንደሚሆን አትጠራጠሩ፡፡ ዛሬ ስብሐትን በአባዱላ ተክቶ የሚንቀሳቀሰው የኦሮሞ አረመኔ ቡድን አጋጣሚውን ሁሉ ከወያኔ በባሰ ሊጠቀም እንደሚችል ጥርጥር አይግባችሁ፡፡ ዘረፋው ከሆነ ይሄው በሁለት ዓመት ውስጥ ብዙ ነገር ሆኗል፡፡ ኦሮሞ አራተኛ ባንክ እያቋቋመ ነው፡፡ አዋሽ፣ ኦሮሚያ ኢነተርናሽናል ባንክ፣ ኦሮሚያ ሕብረት ባንክ አሁን ደግሞ ገዳ ባንክ፡፡ በጥላቻና ዘረኝነት እጅጉን ስለተመረዘ ዓላማው ሁሉ ሌሎችን በተለይም አማራን ጠላት ማድረግ ስለሆነ ግን ሁሉም አንድ ቀን እንደ እምቧይ ካብ ሲደረመስ እናየዋለን፡፡ ከዛ በኋላ ኦሮሞ እንደሕዝብም ጥሩ የማይሆን ጊዜ ሊገጥመው ይችላል፡፡ ዛሬ ቁጥሩን ከየት እንደመጡት ባይታወቅም 50 ሚሊየን እያሉ ያቅራራሉ፡፡ ኦሮሞ ግን በየትኛውም መለኪያ ከአማራ የበለጠ ቁጥር እንደሌለው ግልጽ ነው፡፡ ይሄን ቆይተን እናየዋለን፡፡ ለማንኛውም ሁሉም ኢትዮጵያዊ ከዚህ በኋላ የሚታገስ አይመስለኝም፡፡ በተበላ ቁማር ማሰብ ስለማይችሉ አሁንም እዛው ቁማራቸው ውስጥ ለሚኖሩ ይብላኝላቸው እንጂ፡፡

ሰሞኑን በተደጋጋሚ ሲሰራጭ ያየሁት የቀድሞው የኢትዮጵያ መሪ የመንግስቱ ኃይለማሪያም ንግግር ነው፡፡ እኔ መንግስቱን በንግግራቸው ብዙም አላውቃቸውም፡፡ የመጨረሻ ስንብታቸው የነበረ ጊዜ ከአሰሙት ንግግር ውጪ ሌላው ትዝም አይለኝ፡፡  ዛሬ የእኝህ ሰው ንግግር ስሰማ እጅግ እየተደመምሁ ነው፡፡ ሰውዬው ብዙ ምሁር ነን የሚሉ ማይህምናን መንግስቱን መሀይም ሲሉ ሰምቻለሁ፡፡ ሰውዬው ግን መሪ ብቻም ሳይሆኑ ፈላስፋና ነገሮችን አርቀው የመገመት አቅም እንደነበራቸው የተረዳሁት በላፉት 30 ዓመታት በወያኔና ቅጥረኞቿ የሆነውን ሁሉ ልክ እንደ ነብይ አንድ በአንድ ቀድመው ተናግረውት ነበር፡፡ በጣም ድንቅ እይታና ፈላስፋም እንደነበሩ ተመለከትሁ፡፡ መንግስቱ ዛሬ በሕወት ሆነው ያን የተናገሩትን ሁሉ እየሆነ እየተመለከቱት ነው፡፡ ይሄ እንደ አሸን የፈሉት ሚዲያዎች አንዱም በዚህ ወሳኝ ወቅት መንግስቱን ሲያነጋገር አልሰማሁም፡፡ እንዲህ ያለ ሰውና አጋጣሚው ከብዙ ሚኒሊዎኖች አንዴ የሚያጋጥም ቢሆንም አንዳቸውም የእኚህን ፈላስፋ ስለመሯት አገርና የአረመኔዎቹን ሴራ ቀድመው እንደ በአንድ የተናገሩትን ሰው አስተያየት ለሕዝብ ለማድረስ አንድም ሚዲያ ጋብዟቸው ባለማየቴ አዝናለሁ፡፡ ምን እልባትም እኝህ ሰው እግዚአብሔር ልባቸውን ያውቅ ስለነበር ብዙዎች ግፍ ፈጽመዋል እንደሚላቸው ሳይሆን ቅን ሰው ሳይሆኑ ልቀረም፡፡ ዛሬ በሕወት መኖራቸው ብቻም ሳይሆን በከፍተኛ ክብር ድምጻቸውን አጥፍተው እየኖሩ ነው፡፡ ምን ዓልባትም በሚኖሩባት ዝምባዌ ወሳኝ ሰው ሳይሆኑ አልቀረም፡፡ እንደሰማንው ደግሞ ልጆቻቸውን በከፍተኛ ኢትዮጵያዊነት አሳድገዋል ይባላል፡፡

ቅዱስ እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ! አሜን!

 

 

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.