የትግላችን ግብ ሕዝቡን የሥልጣን ባለቤት ማድረግ ነው!

amhara06/6/2020

ሕገ-መንግሥቱን ከሚሻሻል እንደገና መጻፍ ተቀባይነቱን አሳድጎ ሥራውን ያቀለዋል !

ዓለም አቀፉ የሣናባ ቆልፍ (ኮቪድ-19) የተሰኘው ተላላፊ በሽታ በጋረጠው ችግር ሳቢያ፣ ላለፉት 28 ዓመታት፣ ያልተመረጡትን ተመረጡ እያለ «ሲያስመርጥ» የነበረው «የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ» 6ኛውን ዙር ብሔራዊና ክልላዊ ምርጫ ወቅቱን ጠብቆ ማካሄድ እንዳይቻል እንዳደረገው አሳውቋል። እንደዚህ ያሉ ያልተጠበቁ ሁኔታዎች ሲከሰቱ በምን መንገድ ችግሮቹን መወጣት እንደሚቻል፣ ሕገ-መንግሥቱ የደነገገው ባለመኖሩ፣ የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶች የተለያዩ የመፍትሔ ሀሳቦችን ሲሰነዝሩ እያስተዋልን ነው። በርካታዎቹ ከመጀመሪያውም ሕዝቡ የታገለው እና እየታገለም ያለው የአገሪቱና የሕዝቡ የችግር ቋጠሮው ሕገ-መንግሥቱ ስለሆነ፤ እርሱ መለወጥና በአዲስ ሕዝቡ የኔ በሚለውና የሕዝቡን ፍላጎት ያካተተ ሕገ-መንግሥት ይተካ። ለዚህም የሽግግር ሥርዓት ይኑረን የሚለው የብዙዎቹ ድርጅቶች ጥያቄ መሆኑ ይታወሳል። የዚህ ሀሳብ አራማጆች አክለውም በሥልጣን ላይ ያለው መንግሥት ለሽግግር መንግሥት ምሥረታ ፈቃደኛ ካልሆነ ደግሞ፣ የምርጫ ጊዜው መራዘም አለበት፣ የሚል አቋም ይዘው በኅብረትም በተናጠልም ሲያሰሙ መቆየታቸው አይዘነጋም።—————–

———–[ሙሉውን መግለጫ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]——–——

2 Comments

  1. በሊንኩ መሰረት ፅሑፉን ሁሉም ቢያነበው ጥሩ ነው፡፡ የሽግግር መንግስት ተብየው ምን ያህል አማራን የማግለል ስራ እንደተሰራበት ያሳያል፡፡ የለስሙ፡፡ በመሰረቱ አሁን ያለው መንግስት የጀመረውን ህግ-ማስከበር ስራ ካጠናቀቀ፣ ትግራይን ነፃ ካወጣ፣ በጋምቤላ፣ ኦሮሚያ እና በሌሎች አካባቢም ሰላም ካሰፈነ በኃላ ቀጠይ ስራ የሚሆነው ከምርጫ በፊት ይህ መሰረታዊ ችግር ያለው ህገ-መንግስት ይቀይረዋል ተብሎ ይታሰባል፡፡ ፓርቲዎች በብሔር፣ በጎሳ የሚደራጁ ከሆነ ትግራይን እና ሌላ አካባቢም ህግ ለማስከበር የተደረገው ስራ ሜዳ ላይ ስለሚቀር የብሔር ፖለቲካ መኖር የለበትም፡፡ አንቀፅ 39 እና ሌሎቹም ችግር ስላለባቸው ሙሉ ለሙሉ መቀየር ነው ያለበት፡፡

    ትህነግ በፊት ለራሱ እንደፈለገ እንዲያመቸው ያዘጋጀው ስለሆነ መቀየር ግድ ይላል፡፡ ማንም ተነስቶ ነገ ችግር ከሚፈጥር የነአብይ አስተዳደር ታሪክ መስራት ከፈለጉ ይህንን ማድረግ ሲቻል ነው፡፡ የህዝብ vote ቢሰበሰብ ያለምንም ተፅዕኖ ሁሉም ህገ-መንግሰተ ይቀየር እንደሚል ነው፡፡ አሜሪካን የሚያህል ግዙፍ አገር 52 ስቴቶችን USA ብለው በአንድ ህግ ሲያስተዳድሩ ለኛ ጥሩ ምሳሌ ናቸው፡፡ ቋንቋ መለያ መሆን የለበትም ከዛ ይልቅ የጋራ በሃሉ፣በደም መዛመዱ አማራ፣ ትግሬ፣ ኦሮሞ፣ ሱማሌ ወዘተ የበለጠ ይጠቅማል፡፡ ስለዚህ እንደውም ክልል፣ ብሔር የመሳሰሉ ቀርቶ ኢትዮጵያን እንደ አገር ለቀጠይ ትውልድ ማስተላለፍ ከፈለግን እና ልጆች በሰላም እንዲኖሩ ከተፈለገ እነዚህን ነገሮች አስቀርቶ አገሪቷ በራስ-ገዝ እንደመልካአምድሩ አቀማመጥ/Geographic Location/ ቢከፋፈል ጥሩ ነው፡፡ ዛሬ በስሜት የሚደረግ በሙሉ ነገ አደጋ ስለሚያስከትል ጥንቃቄ ያስፈልጋል፡፡ ከህዋአት ጥፋት ሁሉም ትምህርት ሊወስድ ይገባል፡፡

    ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!

  2. በሊንኩ መሰረት ፅሑፉን ሁሉም ቢያነበው ጥሩ ነው፡፡ የሽግግር መንግስት ተብየው ምን ያህል አማራን የማግለል ስራ እንደተሰራበት ያሳያል፡፡ ያለስሙ፡፡ በመሰረቱ አሁን ያለው መንግስት የጀመረውን ህግ-ማስከበር ስራ ካጠናቀቀ፣ ትግራይን ነፃ ካወጣ፣ በጋምቤላ፣ ኦሮሚያ እና በሌሎች አካባቢም ሰላም ካሰፈነ በኃላ ቀጠይ ስራ የሚሆነው ከምርጫ በፊት ይህ መሰረታዊ ችግር ያለው ህገ-መንግስት ይቀይረዋል ተብሎ ይታሰባል፡፡ ፓርቲዎች በብሔር፣ በጎሳ የሚደራጁ ከሆነ ትግራይን እና ሌላ አካባቢም ህግ ለማስከበር የተደረገው ስራ ሜዳ ላይ ስለሚቀር የብሔር ፖለቲካ መኖር የለበትም፡፡ አንቀፅ 39 እና ሌሎቹም ችግር ስላለባቸው ሙሉ ለሙሉ መቀየር ነው ያለበት፡፡

    ትህነግ በፊት ለራሱ እንደፈለገ እንዲያመቸው ያዘጋጀው ስለሆነ መቀየር ግድ ይላል፡፡ ማንም ተነስቶ ነገ ችግር ከሚፈጥር የነአብይ አስተዳደር ታሪክ መስራት ከፈለጉ ይህንን ማድረግ ሲቻል ነው፡፡ የህዝብ vote ቢሰበሰብ ያለምንም ተፅዕኖ ሁሉም ህገ-መንግሰተ ይቀየር እንደሚል ነው፡፡ አሜሪካን የሚያህል ግዙፍ አገር 52 ስቴቶችን USA ብለው በአንድ ህግ ሲያስተዳድሩ ለኛ ጥሩ ምሳሌ ናቸው፡፡ ቋንቋ መለያ መሆን የለበትም ከዛ ይልቅ የጋራ በሃሉ፣በደም መዛመዱ አማራ፣ ትግሬ፣ ኦሮሞ፣ ሱማሌ ወዘተ የበለጠ ይጠቅማል፡፡ ስለዚህ እንደውም ክልል፣ ብሔር የመሳሰሉ ቀርቶ ኢትዮጵያን እንደ አገር ለቀጠይ ትውልድ ማስተላለፍ ከፈለግን እና ልጆች በሰላም እንዲኖሩ ከተፈለገ እነዚህን ነገሮች አስቀርቶ አገሪቷ በራስ-ገዝ እንደመልካአምድሩ አቀማመጥ/Geographic Location/ ቢከፋፈል ጥሩ ነው፡፡ ዛሬ በስሜት የሚደረግ በሙሉ ነገ አደጋ ስለሚያስከትል ጥንቃቄ ያስፈልጋል፡፡ ከህዋአት ጥፋት ሁሉም ትምህርት ሊወስድ ይገባል፡፡

    ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.