በማይካድራ ከ600 በላይ ሰዎች መገደላቸውን የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ገለጸ

esemeguበትግራይ ክልል ማይካድራ ከተማ ጥቅምት 30 ቀን 2013 ዓ.ም በወቅቱ በስልጣን ላይ በነበረው የአካባቢው መስተዳድር የጸጥታ መዋቅርና ሳምሪ በተባለ ኢ-መደበኛ የወጣቶች ቡድን የተፈጸመው ጥቃት፤ ግድያ፣ ጉዳትና ውድመት፤ ጠቅላላ ድርጊቱና ውጤቱ ግፍና ጭካኔ የተሞላበት በሲቪል ሰዎች ላይ የተፈጸመ የጭፍጨፋ ወንጀል መሆኑን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አስታወቀ፡፡
ኮሚሽኑ ይህን ያለዉ ከሕዳር 5 እስከ ሕዳር 9 ቀን 2013 ዓ.ም. ድረስ በማይካድራ ከተማ እንዲሁም በአብርሀጅራ፣ በሳንጃ፣ በዳንሻ፣ በሁመራ እና በጐንደር ከተማ ተዘዋውሮ ባደረገው ምርመራ የደረሰበትን ግኝቶች ይፋ ባደረገበት የመጀመሪያ ደረጃ ቀዳሚ ሪፖርት ነው። የማይካድራዉ ድርጊት ከፍተኛ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት በሰብአዊነት ላይ የተፈጸመ ወንጀል እና የጦር ወንጀል ሊሆን እንደሚችል የሚያመለክት በመሆኑ ኮሚሽኑ ዝርዝር ማስረጃዎቹን እና ወንጀሉን የሚያቋቁሙትን የሕግና የፍሬ ነገር ትንተና በሙሉ ሪፖርቱ ላይ በዝርዝር አጣርቶ ያቀርባል ተብሎአል።
በኮሚሽኑ ቀዳሚ ሪፖርቱ እንደተመለከተው በአካባቢው የነበረው የሚሊሽያና የፖሊስ ጸጥታ መዋቅር በፌዴራሉ አገር መከላከያ ሰራዊት እርምጃ ሸሽቶ አካባቢውን ለቅቆ ከመውጣቱ በፊት ሳምሪ ከተባለ መደበኛ ያልሆነ የትግራይ ወጣቶች ቡድን ጋር በማበርና በመተባበር በተለይ ‹‹አማሮችና ወልቃይቴዎች›› ያሏቸውን የአካባቢው ነዋሪ ሲቪል ሰዎች ከቤት ቤት እየዞሩና በየጐዳናው ላይ በገመድ በማነቅ፣ በስለት በመጥረቢያ በዱላ በመደብደብ ገድለዋል፣ የአካል ጉዳት አድርሰዋል፣ እንዲሁም ንብረት አውድመዋል፡፡ ኢሰመኮ ከአካባቢው ምንጮች እስከ አሁን በአገኘው መረጃ በአነስተኛ ግምት እስከ 600 ሰዎች የተገደሉ ሲሆን ትክክለኛው ቁጥር ከዚህ ሊበልጥም እንደሚችል በሪፖርቱ ተመልክቷል፡፡
ሳምሪ የሚባለው የትግራይ ወጣቶች ቡድን በዚህ ከባድ ወንጀል ላይ ቢሰማራም፤ በአንጻሩ የትግራይ ብሔረሰብ ተወላጅች የሆኑ ሌሎች የአካባቢው ነዋሪዎች አጥቂው ቡድን ሲያሳድዳቸው የነበሩ ሲቪል ሰዎችን በቤታቸው፣ በቤተክርስቲያን እና በእርሻ ቦታ ደብቀው በመሸሸግ ሕይወታቸውን እንዳተረፉላቸው ኢሰመኮ ያነጋገራቸው ምስክሮች ማረጋገጣቸዉ በመግለቻዉ ተጠቅሶአል፡፡
ኢሰመኮ የተጎዱን ማቋቋም እና የአጥፊዎችን ተጠያቂነት ማረጋገጥ ይገባልም ሲል ዛሬ ዘለግ ያለ መግለጫ ይፋ አድርጓል።

2 Comments

  1. ዋናዎቹ አቀነባባሪዎች እና ወንጀሉን የጠነሰሱት ብቻ ሳይሆን በወንጀሉ የተሳተፉ ወጣቶች በሙሉ እየተጣራ በሰብዓዊ መብት ጥሰትና የጦር ወንጀለኛነት በአስቸኳይ እንዲጠየቁ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ እነዚህ ወጣቶች ለመጪው ትውልድም መጥፎ አርዓያ ናቸው፡፡

  2. Well, you did what you are supposed to do as far as the very purpose of your existence as human rights body is concerned!
    But why you terribly failed to investigate and come up with reports on similar if not the same type of politically motivated crimes against humanity and of course genocidal crimes not only once or twice but multiple times in regional administrations such as Oromia and Benehangul ? Was it or is it because the government did not allow you to do so or you do your job selectively?
    I hate to say but I have to say that although what you did now is truly the right thing, what you did not do about what happened for the last more than two years and what is still happening in the regional administration I mentioned above seriously challenges and undermines your independent duty and mission to accomplish. You did not do what you were supposed to because the ruling elites were not happy about doing independent investigation and coming up with reports in those regional administrations. Now, you did what you are supposed to because the ruling elites are happy with your report as it blames and holds TPLF’s brutal inner circle. And this is deeply troubling as far as the very essence of human rights is to do the right thing anywhere and anytime it happens. If you do it in a selective manner by presenting any clumsy and deceptive excuses, your mission is badly influenced by the palace politics. Do not get me wrong that what I am trying to say is this report is not the right thing to do .It is absolutely the right thing to do! What I am trying to say is that both innocent citizens who are victims of TPLF atrocities and those innocent citizens who are victims of atrocities in the Oromia and Benishangul and the South had and have the same priceless lives nobody can take them away. Yes, what I am trying to say is that ones you miss this critical issue, you yourself become victim of a very deadly political game of the ruling circle.

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.