ከሃዲው የህወሃት ቡድን የዓለም አቀፉን ማህበረሰብ በማሳሳት በሀገሪቱ ዳግም ስልጣን መጋራት ይፈልጋል … አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ

127535793 2814736478768813 4475177052890048729 o
የከሀዲው የህወሃት ቡድን አመራሮች ዓለምአቀፉን ማህበረሰብ በማሳሳት ላለፉት ወንጀሎቻቸው ከቅጣት ለማምለጥና በድርድር ስም ዳግም ወደ ስልጣን መምጣት እንደሚፈልጉ የቀድሞው የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ በፎሬይን ፖሊሲ ድረገጽ ላይ በወጣው ጽሁፍ ገልጸዋል።
ላለፉት 27 አመታት ሃገሪቱን በተንኮል ያስተዳደረው የህወሃት የጥፋት ቡድን በታላቅ ህዝባዊ ተቃውሞ ተገፍቶ ሲወድቅ አለም አቀፉን ማህበረሰብ አሳስቶ ዳግም ወደ ስልጣን ለመምጣት እቅድ ስለመንደፉም በጽሑፋቸው አብራርተዋል።
በሰላም ስምምነቶች ወቅት የግጭቶች ትክክለኛ ባህሪና አባባሽ ምክንያቶች እንዲሁም ተሳታፊ አካላት ተዘርዝረው ስለማይታዩ በርካታ ስምምነቶች ዋጋ ቢስ ስለመሆናቸውም ነው የገለጹት።
ከሀዲው የህወሃት ቡድን ያለፈው ጥፋቱንና የሰራው ወንጀል እንዳይጋለጥ የሚፈልገው፤ ዓለም አቀፉን ማህበረሰብ ለማሳሳት እንዲያስችለው ከፌዴራል መንግስት ጋር ግጭት ውስጥ በመግባትና በድርድር ስም ስልጣን በመጋራት በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ዳግም የጥፋት ተግባሩን ለመፈጸም እንደሆነ ነው የጠቀሱት።
ቡድኑ ይሄን እቅዱን ለማሳካት ሶስት መንገዶችን እየተከተለ እንደሆነ ያብራሩ ሲሆን፤ የመጀመሪያው በድርድርና በስልጣን መጋራት መፍትሄነት አለም አቀፉን ማህበረሰብ በማሳሳት ያለፉ ወንጀሎች ሁሉ እንዲሰረዙረሱ ማድረግ ነው።
እሳቸው እንደገለጹት ሁለተኛው አንዳንድ የውጭ ሃገራት ተንታኞችን ከፊት በማሰለፍ ራሱን ሰላማዊ አስመስሎ በማቅረብ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የሚያደርገውን የህግ ማስከበር ዘመቻ ጥላሸት መቀባትና የህግ ማስከበሩን ሥራ ማሳነስ ነው።
ሦስተኛው ምክንያት ደግሞ በኢትዮጵያ ህዝብና በመከላከያ ሰራዊት ላይ ለበርካታ አስርተ ዓመታት ሲዘራ በነበረው ልዩነትና መከፋፈል ምክንያት ህዝቡና የፌዴራል መንግስቱ ከህወሃት ልዩ ሃይል በሚሰነዘርበት ጥቃት በቀላሉ ይሸነፋል የሚለው እቅድ እንደነበረም ገልጸዋል፡፡
የቡድኑ ዓላማም ግጭቶቹን ወደ ሁሉም የኢትዮጵያ ክፍሎች ብሎም ወደ ክፍለ አህጉሩ በማዛመት የፌዴራል መንግስቱንም ሆነ የአካባቢውን ሃገራት ባልተቋረጠ የእርስበእርስ ጦርነት እረፍት መንሳት እንደሆነ የገለጹት አቶ ሃይለማርያም፤ ህወሃት በሁሉም አቅጣጫዎች በሮች ስለተዘጉበት ይሄን የማድረግ አቅሙ እጅግ ደካማ ነው ሲሉ በጽሑፋቸው አስፍረዋል።

5 Comments

 1. Good! Yes, TPLF is the mastermind of the horrible general crisis we have gone through and continued to go through at this very moment and it must be dealt with any appropriate means and must be dismantled!
  But are you ready once again to be willing to take responsibility and accountability for your own deadly or bloody part or role you have played as the very YES or LOYAL satellite or subordinate of TPLF (your godfather) for so long? Who enabled TPLF to stay in power using the very deadly politics of ethnocentrism which has brought us where we are now? Do you agree with the majority of the Ethiopian people that the very root cause of all evils we have been forced to go through and still forced to face are the constitution, federal structure, and governmental structures? Do you agree that these root causes must be the subjects of very timely and fundamental democratic change? By the way, do you have a moral and political ground that makes you innocent as long as what you have done for a long time is concerned? How many of you members of the former EPRDF, now Prosperity are immune from the untold suffering and blood of countless innocent citizens for about three decades?
  I hate to say but I have to say that although it is the right thing to make TPLF the thing of the past and be sued as a very painful lesson how the politics of ethnocentrism is very dirty and cruel. Do you agree or you die for it?
  I strongly believe and argue that call it EPRDF of Prosperity is a very dangerous liability in Ethiopian politics and it should be replaced by a true democratic force that embraces Ethiopians as good citizens! EPRDF/Prosperity is not and cannot be an asset as it is badly stained with the very blood of innocent citizens for three decades! It goes without saying that the country will never be in any relative stability or peace and development as long as the deadly ethnocentric political system remains the power base of you guys!
  So, it is the right thing to defeat and make TPLF irrelevant to this 21st century political desires of the people! But, you guys can’t be better than your godfather (TPLF) as long as you continue with the same bloody political game of ethnocentrism which emanates from the very deadly constitution! Do you agree and are you courageous enough to make necessary or fundamental change and free not only the people but also yourself soon, not latter? If you say yes, you will make history and the people may give you a chance to renew your extremely damaged political background or history! If you say no, forget about trying to show yourself to the Ethiopian people in particular and to the world in general that you are better than your godfather (TPLF)! It is time to choose what is good or better to the general public and make history that has gone terribly wrong right! Do not tell us, show us please how you are courageous enough to cleanse your hands which are either directly or indirectly badly stained with millions of innocent citizens for a long period of time!
  Help God by telling the truth and doing the right thing so that He can help you !!!!

 2. ምነውሳ እየዘገያችሁ መንቃት ደግሞ ጀመራችሁ እንዴ?
  ቢያንስ ተንኮልን ሸርቦ በማደርና በመዋል The very dynamic person of the end of the 20th century and beginning of 21 century’ን Aka መለስ ዜናዊን በጨረር አቃጥለው ካስወገዱ በኋላ፣ ይሄው ባንዳው የተንኮልና የክፋት ዳይናሚኩ፣ በሬነታቸውን ሳይኮሎጂካሊ እያጣራ እርሱን ያገለግሉ ዘንዳ ወደ ስልጣኑ አካባቢ ያሰለፋቸውን መላ ሆዳሞችን (ለምሳሌ: አንተና፣ ቴዎድሮስ ሓጎስን የመሳሰሉን) እየተጠቀሙ አይደለም እንዴ አሁን ደርሰንበት ወደምንገኘው Semi-Hutusim ህብረተሰብ ለመሆን በቅተን ያለነው ኣያኒኒ የትላንትናው የማሌሊት አቤት ወዴት ባዩና የዛሬው “critical” ቃል ሰንዛሪ መሳዩ…………………!??
  ይልቁንስ ጦርነት የሚባል ነገር በጅምላ ለሁሉም ጉዳትን እንጂ ምንም ጥቅም እንዳሌለው ብትሰብክሳ ምን ይመስልሃል…!!

 3. For me, it is a surprise to see such a bombastic article from the former PM on TPLF junta group as he is always reserved. It is known that he is dynamic and fluent but I think it is his first time to openly and strongly criticize his former bosses. I really appreciate the approach,content, language proficiency and timing of his article.

 4. ይህንን አስመሳይ ወንበዴ አትስሙት። በእርሱ ስልጣን ዘመን የተጨፈጨፉት ንፁሀን ዜጎች ቁጥር ስፍር የላቸውም። አሁን የእራሱ የፖለቲካ ፓርቲን ለማዳን በከንቱ እየተፍጨረጨረ ነው።

  ህወሀት እና ፕሮስፐሪቲ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታ መሆናቸው አላበቃም!

 5. “ሃይለማርያም ደሳለኝ፡ መራሕቲ ትግራይ ‘ዓለም ክትደናገጸሎም ይፍትኑ አለው’ ክብል ነቒፉዎም”

  ‘ዝኣኽለንያ ጢሒነንስ በኣለ ማርያም ይብላ’ ከምዝብሃሎ እዩ ነገራቱ..!
  ትማሊ’ዶ ምስኦም ኮይኑ ይግህፅ ኣይነበረን፣ ንምኳኑ ነቲኣ ምስ መንግስቱ ሃይለማርያም ኮይኑ ዝተስኣላ ስእሉ’ኸ ኣላ’ዶ ትኸውን..!? ኣብ ኩሉ ቦታታትስ ሱቕ ኢልካ ምሕምዟቕ፣ መሃረነ ሕሊና ኣበይስ ኣተኺ………..! ወቐሳን ነቐፈታን ብዓርስኻ እዩ ዝጅመር…..!!

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.