የኢትዮ360 ጁንታ! ሚድያ – የፖለቲካ ፓርቲ ወይስ የነፃ ሚድያ? – ደጀኔ አያኖ

በአሁኑ ጊዜ፣ የኢትዮጵያ ሐገራችን ህልውና ወሳኝ መዕራፍ የደረሰበት ወቅት ነው። ከሃያ ሰባት ዓመታት ከፍተኛ የህዝብ አፈና፣ ስቃይ፣ ምዝበራ፣ ጭቆናና አምባገነናዊነት ነፃ ለመውጣት የሚደረግበት ወሳኝ ጊዜ ነው። በዚህ ወሳኝ የሕዝባዊ ትግል ጊዜ፣ በክህደት የተጨፈጨፈው የመከላከያ ሰራዊታችን የሚያደርገውን ሐገራዊ ተጋድሎ፣ መላው ነፃነቱን የሚወደው የኢትዮጵያ ሕዝብ እየደገፈው አብሮት ቆሟል።

Ethio 360 Media

ነገር ግን፣ በዚህች አንገብጋቢ ሰዓት፣ በዚህች የኢትዮጵያን ህልውና ወሳኝ በሆነች ጊዜ፤ የኢትዮ360 ጁንታ በሚዲያው የሚነዛው ቅጥ ያጣና ወቅታዊ ያልሆነ፣ ለጠላት የሚመች፡ ለወዳጅ ደግሞ የሚሳፍር ሀተታው ነው።

እኔን ያልገባኝ ነገር የኢትዮ360 ጁንታ የአሁኑ ይዘት ነው። ጁንታ ያልኩትም፣ ልክ መከላከያችን አሁን እንደሚዋጋው ጁንታ እነሱም “ከኔ በላይ አላዋቂ” እንዲሉ የማንኛወንም ሃሳብ አዋቂና አሸናፊ መሆናቸውን በየደቂቃው በመስማቴ ነው። ኢትዮ360 የተቃዋሚ ፓርቲ ድርጅት ወይንስ የነፃ ሚዲያ የሚለውንም ጥያቄ አስነሳብኝ?

የአቢይ አህመድ መንግሥት ያወራውንም የፃፈውም ሁሉ፣ የኢትዮ360 ጁንታ እንደ ዶሮ ብልት ሁል ጊዜም እንዳብጠለጠለ ነው። ትክክልም ይሁን ሀሰትም። እነዚህ ሁሉን እናውቃለን የሚሉት የኢትዮ360 ጁንታ ተንታኞች “ይህንን ብለን ነበር”፣ “ያንንም ብለን ነበር” “ይህንን አስጠንቅቀን ነበር” እያሉ እራሳቸውን በጣም ትንቢቱ እንደተገለጠለት ሳይኪክ በየቀኑ ይናዘዛሉ። የታዋቂዎች ሥም በመጥራትና ታዋቂ መፃህፍትንም በመጥቀስ “ከኔ በላይ ንፋስ” ለማለት ይሞክራሉ። ከጥቂት ሰዓታት በፊት አንብበው የመጡትን መፅሐፍ ልክ የዛሬ ሃያ አመት እንዳነበቡት ለማሳየት ይብለጠለጣሉ።

ኢትዮጵያ ውስጥ ለሚከሰተው የፖለቲካዊ ሂደት ኪሳራና ስኬት ሁሉ የኢትዮ360 ትንበያ ነበረበት ይሉናል። ከነሱ ቲወሪና ትንበያ ውጭ የሚሆን ነገር በፍፁም የለም። ካለም ደግሞ በጣም የተሳሳተ ነው። ስለ አሁኑ የኢትዮጵያ መሪዎች የወያኔ ሥልጠና ሲተነትኑ ደግሞ፣ እነሱም ቢሆኑ የዚያው ትምህርት ቤት ምሩቅ መሆናቸውን፣ እንዲያውም በማሰልጠኑ ላይም መሳተፋቸውን ይረሳሉ። የነሱን የኋላ ታሪክ ከረሱት ደግሞ፣ የሊሎቹን የወያኔ ምሩቆች የኋላ ታሪክ ትተው በዛሬው ላይ ትኩረት መስጠትን ግድ ይላል። እንሱም ተለወጥን ካሉ፣ የሌላውን የመለወጥ ችሎታ ማሳነስ የለባቸውም። “ለራስ ሲቆርሱ አያሳንሱ” ካልሆነ በቀር።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የብርሃኑ ዳምጤ (አባመላ) ቅልቅል (ከክንፉ አሰፋ) ጋዜጠኛ

ዛሬ (ዓርብ ህዳር ፩፩) የኢትዮ360 ጁንታ የሚያስተላልፈውን የ“ዛሬ ምን አለ፣ የቀጠለው ጥርነት” የሚለውን ፕሮግራም ስከታተል ነበር። ጀግናውን የሐገር መከላከያ ሰራዊት እንደማበረታትትና፣ የኢትዮጵያን ሕዝብ ከኋላው እንዲቆም እንደማበረታታት፣ እንደለመዱት የጄኔራል ብርሃኑን መግለጫ ማብጠልጠል ጀመሩ።

ለመሆኑ፣ በአሁኑ ወሳኝ ጊዜ የሐገር መከላከያ መሪን ሳይሆን የወያኔን ጨፍጫፊ፣ ዘራፊና የወንበዴና የአሸባሪ ቡድን ለምን አታብጠለጥሉም? አላማችሁ ምንድነው? ማንን ለመርዳት ነው? አሉላና ወያኔን? ወያኔ በዘረፈው የኢትዮጵያ ሃብት የዓለም አቀፍ ሜዳያዎችን ገዝቶ የዓለም ህዝቦችን እይንታ በዩትዩብ፣ ብፌስቡክ፣ በኢንስቶግራምና በትዊተር በሚያሰራጨው ውሸት እያሳሳተ ይገኛል። እናንተስ የተከፈላችሁ ነገር አለ?

ብርሃኑ ጁላ ለጄኔራልነት ማዕረግ የደረሰው ብዙ የወታደር ትምህርትና ሥልጠናዎችን አካቶ እንጂ እንደ አንዳንዱ ለሆዱ አዳሪ ካድሬ የወገኖቹን ደም መጦ አይደለም። ወይንም በዘሩ ብቻ በማደግ አይደለም። በወያኔ አመራር ጊዜ በስራውና በጀግንነቱ አስመስክሮ ያገኘው እንጂ።

ቆራጥና ብቁ ወታደር መሆኑን ለማሳየት ሱሪው ቀጥ ብሎ መተኮስ የለበትም። ወይንም በተጠንቀቅ ቆሞ ተኮሳትሮ መናገር አይጠበቅበትም። ትላለቅ ድሎችን ያስመዘገቡ የዓለም ታላቅ ጄኔራሎችን አለባበስ ዞር ብሎ መቃኘት ይህንንው በገሃድ ያሳያል። ቀጥ ብሎ የተተኮሰ የወታደር ልብስ ለሰልፍ እንጂ በሥራ ላይ አያምርም። “አላዋቂ ሳሚ ንፍጥ ይለቀልቃል” እንዲሉ ስለጂኔራሉ ጫማም ከዚህ ቀደም ብሎ የተሰጠም አስተያየት ነበር። ግን “ጥላሁን ያረፈ ቀን” በተባለው መፅሀፍ አብሮ የሚሰራን ባልደረባ በአንባብያን ፊት “ለሃጫም” ብሎ መስደብ ግበረገብነትን አጉልቶ ስላሳየን በዚሁ ይቁም።

የጄኒራሉ አንዲት ቦታ ሥም መርሳትም እንደ ትልቅ ሃጥያት ተቆጥሯል። ይህ ጄኔራል በየደቂቃው የሚመጡ ብዙ ከበድ ያሉ መረጃዎች ይደርሰዋል። ለነዚህም ተገቢውን ውሳኔም መስጠት ይጠበቅበታል። ጊዜው ጄኔራሉ የሚመራው የሐገር መከላከያ ሕግ የሚያስከብርበት ውቅት ነው። በየግንባሩ እየተዋደቀ ነው። የሚሰራ ብቻ ነው የሚሳሳተው። ቁጭ ብሎ የጀግናውን ሰራዊታችንን መሪ በዚህ ወሳኝ ወቅት የሚያንጓጥጥና የሚተች ግን ሥራን የማያውቅ ሰነፍ ብቻ ሳይሆን የሐገር ክህደትንም ይጠቁማል። ይህ መላውን ያጣ የኢትዮ360 ጁንታ ነቀፌታ ሳይንሳዊ ምክንያት የሌለው ነው። የሕዝቡን ድጋፍ አሰባስቦ ወያኔን ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመደምሰስ እንደመታገል፤ በአንፃሩ ይህን አላማ ከግቡ እንዲደርስ የሚጥሩትን የሀገር የመከላከያ መሪዎች ማዋረድና ማጥላላት፣ ለወያኔው ጁንታና አጃቢዎቹ የፍንጥር ማለት ነው። ለታንቡራቸው መምቻ በትር ማቀበል ነው። ሌላ መልስ የለውም።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የትግሬ-ወያኔ አመራር በቅርቡ ባደረገው ስብሰባ ዐማራን ፈጽሞ ሳያጠፋ እንቅልፍ እንደማይወስደው ዳግም አረጋገጠ!

ምነው አንደኛውን የኢትዮጵያ መንግሥት እነዚህን የኢትዮ360 ጁንታ የጦር ጄኔራሎች፣ የኤኮኖሚ ባለሞያዎች፣ የፖለቲካ ልሂቃኖች፣ ሁሉን አዋቂ ፈላስፋዎች አዲስ አበባ አስመጥቶ “በሉ እንግዲህ ይኸውና ችግራችንን ሁሉ ፍቱልን” ብሎ እነዚህን ዩኒፎርማቸውን እንኳን በደንብ የማይተኩሱ ጄኔራሎችንና ፍሬ ፈርስኪ የሆኑትን ሚንስተሮቹን ቢያሰናብት? ውይ!! ሐገሪቷ የት ብትደርስ!!

እኔ እንደሚመስለኝ፣ የኢትዮ360 ጁንታ በ “ላይክ” ሳይሰክር አልቀረም። የሐገርን ወሳኝ ወቅታዊ አካሄድ አለመገንዘብና አካሄድን ከሕዝቡ ፍላጎት ጋር አለማስማማት ከራስ ወዳድነት ጋር ይጣመራል። በሺህ የሚቆጠሩ ተከታዮች ፕሮግራሙን ስለሚሰሙት፣ ሁሉንም ሰሚዎች/ተከታታዮች እንደ ደጋፊ መቁጠር ተላላነት ነው።

ይህ በሺህ የሚቆጠር የፕሮግራሙ ተከታታይ እንደሮቦት ተጎልቶ የሚሰማ አይደለም። እንደ የኢትዮ360 ጁንታ ተንታኞች “የመለስ ዜናዊ” አይነት “ተረበኛ” ወይንም “እኔ ነኝ የማውቅልህ” የሚል ስነ ልቦና ባይኖረውም፣ የሰፊውን ሕዝብ “ትዕግሥት” ያላበሰው ጭምተኛ ተከታታይ በመሆኑ በትዝብት ያልፈዋል። ምናልባት፣ ነገሩ ገባቸውም አልገባቸውም፣ በመቶ የሚቆጠሩት አድናቂ ተከታዮቻችሁ በየሰኮንዱ የሚወረውሩት የ “ላይክ” ድጋፍ ሊይሳውራችሁ ችሎ ይሆናል። አንዳንድ ጊዜ በቅርብ ያሉ ጓደኞች በሚሰጡት አድናቆት ብቻ ተመርተው እሳት ውስጥ የሚገቡም አሉ። ግን በዚህ ፊት ለፊት ገጥማችሁ የማታዋዩትን፣ አቅሙንና ችሎታውን የማታውቁትን፣ ጠላት ይሁን ወዳጅ የማትለዩትን የፕሮግራም ተከታይ መናቅ ድክመት ነው።

ልብ አድርጉ፣ ኢትዮጵያ ከመቶ ሃያ ሚሊዮን ያላነሰ ጭንቅላት አላት። ሁሉም ጭንቅላቶች ከሌላው ጭንቅላት ያላነሰ የዕውቀት ማህደር አላቸው። እባካችሁ ይህን ልክ የሌለውን እብደታችሁን አቁማችሁ ስከኑ። እየታዘብናችሁ ነው።

 

የማያወላውል ድጋፍ ለሐገር መከላከያና ለጭቁኑ የኢትዮጵያ ህዝብ።

የተጨቆነው የኢትዮጵያ ሕዝብ ያሸንፋል።

ድል ለጀግናው መከላከያ ሰራዊት። ሞት ለወያኔ ዘረኛና አሸባሪ ወንበዴ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ታጣቂ ሕዝብ ሲገል ካህን ተዝካር ይዝቃል - በላይነህ አባተ

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር።

ደጀኔ አያኖ

4 Comments

 1. Ethio360:

  Although I do not completely agree with what the write said, I do not like your tendency of “I know it all” approach to everything. Nobody is an expert in everything. You better ask war experts about war, economists about economy, medical experts about medicine, political scientists about politics etc.
  However, unlike the writer, I do not doubt the patriotism of ETHIO360 staff.
  The problem is that given ethnic politics is not political science, everybody talks about ethnic politics.

 2. የዘመድ ቄስ እየፈታ ያለቅስ ይባላል።
  የነቢያት እጣም ተመሳሳይ ነው። ሕዝቡን ቀድመው ጥፋት እንዳይመጣበት ሲያስጠነቅቁት፣ ሲጮኹለትና ሲያለቅሱለት ይቆያሉ፣ በእንቢታው ወይም በግዴለሽነቱ ጸንቶ ጥፋት ሲያገኘው ደግሞ እኔስ ነግሬ ነበር እያሉ አብረውት ያለቅሳሉ። ጋዜጠኞች የሆኑ የሥርዓቱን ባሕርይ ጠንቅቀው የሚያውቁ፣ መረጃን እግር በእግር እያወጡ እኛ ሁላችን ኮንፊውዝድና ኮንቪንስንድ ሆነን ለውጥ አለ በሚለው ስካር ተጠልፈን ባለንበት አደጋ እንደተደቀነብን ቢነግሩን፣ ቢያስጠነቅቁን አልሰማ ብለን በታሪካችን ደርሶብን የማያውቅ ውርደት ደረሰብን።
  የሰሜን እዝ የሀገሪቱን መከላከያ 70 % የሰው ኃይልና የመካናይዝድ አቅም እንደያዘ በ1 ሌሊት ተደመሰሰ። ይህንን ሊያስቆም የሚችል መረጃ፣ ከ9 ወራት በፊት ኢትዮ 360ዎች አቅርበው ነበር። መንግሥት በመረጃው ምንም ባለመጠቀሙ ጉዳቱን በከፊል እንኳን መታደግ ሳይቻል ቀርቷል። እንዲህ ያለው ተቋም ለወደፊትም ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት፣ እንዲህ ያሉት ውስጥ አወቅ ጋዜጠኛና ተንታኞችም ሊመሰገኑ እና ሊበረታቱ የሚገባቸው ናቸው። እርግጥ ከሰው ኃይል እና ከባጀት እጥረት እለት እለት ፕሮግራም ከማዘጋጀትም ጫና፣ በሚጠበቀው ደረጃ ሊሠሯቸው ያልቻሏቸው ሥራዎች እንዳሉ ግልጽ ነው። ጸሐፊው እንደጠቆሙትም ከነሱ በችሎታ የላቁ ኤክስፐርቶችን በየጊዜው ቢያቀርቡ የተሻለ ሥራ ሊሠሩ ይችላሉ። ከወጣትነታቸውም አኳያ ጠለቅ ያለ የኢትዮጵያ ታሪክና መልክዐ ምድራዊ እውቀት የላቸውም። በሕወሃት ዘመን በጥቅላላ የኢትዮጵያ ተቋማት ላይ በተደረገው ጥቃት ውስጥ የጎረመሱና የጎለመሱ እንደመሆናቸው በአንጻራዊነት በሚያስደንቅ ደረጃ ከትውልዱ ግንባር ቀደም ናቸው ለማለት ግን ይቻላል። ብዙ ሰው ከሚያደርገው ሥህተትም የሚድኑበትን መንገድ ከሕወሃት ጋር መሥራታቸው እድል ሰጥቷቸዋል።
  ራሴን ጨምሮ አብዛኞቻችን የሕወሃት ተቃዋሚዎች ለድርጅቱ ካለን ወደር የለሽ ጥላቻ እንኳን የድርጅቱን የተለያዩ ሰነዶች ልንመረምር፣ ውስጣዊ አሰራሩን ልናጠና ይቅርና የአመራሩን ስሞች ለማወቅ እንኳን የማንፈልግ፣ ባጠቃላይ ሕወሃት ሲባል የሚያጥወለውለን እና የሚያቅለሸልሸን ስለ ሕወሃት ጠላት መሆኗን ከማወቅ በስተቀር ሌላ ነገር ለማወቅ የማንፈልግ ነን። ይሄ ደግሞ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል በሀገራችን ላይ። ሕወሃትም በሥልጣን እንድትቆይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርጓል። ባጭሩ እነ ኤርምያስ ውስጥ አወቅ መሆናቸው ለጸረ ሕወሃት ትግሉ በረከት እንጂ እርግማን አይደለም። ሕወሃት ማለት ግን መቀሌ ፕላኔት ሆቴል ወይም አንድ ቤተክርስትያን ውስጥ ቆሞ የሚያጣጥረው የነስብሃት ነጋ ቡድን ብቻ አይደለም። ሕወሃት እንደ ራዕየ ዮሐንሱ አውሬ ብዙ ጭንቅላቶች ያሉት ብዙ ድራጎኖች ፈልፍሎ ያሳደገ ሲዖላዊ ድራጎን ነውና የሕወሃትን መሠረታዊ የሀገር ከፋፋይ አስተሳሰብ እና መዋቅራዊ ጥፋት ሳይዘናጉ ጎን ለጎን መፋለም የግዴታ ነው።
  በዳቦ ስማቸው ራሳቸውን ዓለማቀፍ ሕብረተሰብ ለሚሉት ምእራባውያን ስለ ሕወሃት ለማስረዳት ትንፋሽ መጨረስ ለቀባሪው አረዱት የሆነ ተግባር ነው። አሰልጥነው፣ አስታጥቀው በብቸኝነት ኢትዮጵያ ላይ የአፓርታይድ ሥርዓት ዘርግቶ የሩዋንዳን ድንኳን እንዲዘረጋ ዘርፎ እንዲያዛርፋቸው የጎለቱብንን ሕወሃትን መጨረሻም የተፈጠረበትን ሥራ ከግብ ሲያደርስ በተረኛ አሻንጉሊት የተኩትን ሕወሃትን ነው ለነሱው የምናሳጣው? አሁን ባእዳን በጋራ ከሕወሃት ጋር ሆነው ከዘረፉት ሃብት ውስጥ ለሕወሃት የደረሰውን ድርሻ ከሕወሃት የሚያስተፉበት ደረጃ ላይ እንገኛለን። በሁሉም የአፍሪካ አሻንጉሊት አስተዳደሮች የሚደረገው ይኸው ነው። ኃያላን በመፈንቅለ መንግሥት ወይም በሌላ ዘዴ አሻንጉሊታቸውን ይጎልቱብሃል። በአሻንጉሊታቸው አማካኝነት ከእርሱው ጋር ተካፍለው ሀገርህን ይዘርፋሉ። ይህን በሚያደርግበት ጊዜ አሻንጉሊታቸው የሚሰራውን ወንጀል ይሸፋፍኑለታል። ከዚያ ሕዝቡ የአሻንጉሊታቸው ግፍ ሲመረው የገዛ ወንጀሉን አጋልጠው፣ የርሱን ድርሻ ምርኮና ዝርፊያም ቀምተው ሌላ አሻንጉሊት ይተኩበታል። ስለዚህ አሻንጉሊቱን መጀመሪያውኑ ለጎለቱት ጌቶቹ ስለክፋቱ በማስረዳት ትንፋሽ ከመጨረስ ጭቁኑ ሕዝብ ሌላ የራሱ መሪ እንጂ ሌላ አሻንጉሊት እንዳይጎለትበት ያለችውን ጉልበት ቆጥቦ መጠቀም ይገባዋል። ለኛ ሀገር — በግልጽ ለመገጋገር — የኪሲንጀርን መመሪያ ተጠቅመው የትግሬ ተረኛ፣ የኦሮሞ ተረኛ፣ የአማራ ተረኛ እየለዋወጡ የምንገነባውን መሠረተ ልማት፣እና የሰው ኃይል በፈረቃ እያወደሙ በቁርቆዛ አዙሪት ሊያኖሩን ካሰቡበት ወጥመድ የምንወጣበትን ማሰብ ነው የሚበጀን።
  1953 ግርግር // ለልማት በግንባር ቀደም የተሰለፉት እነ ጄኔራል ሙሉጌታ ቡሊ፣ እነ ራስ አበበ አረጋይ ተረሸኑ
  1967 አብዮት // የሀገሪቷ ግንባር ቀደም ምሁራንና ባለሥልጣናት 60 ዎቹ ተረሸኑ
  1969 አብዮት // አንድ ትውልድ ፊደል የቆጠረ ፣ ግንባር ቀደም የነበረ ተጨፈጨፈ
  1981 መፈንቅለ መንግሥት // እንዲከሽፍ በተወጠነ መፈንቅለ መንግሥት 200 የሃገሪቱ የበላይ የጦር አዛዦች ተገደሉ፣ ታሠሩ
  1983 የደርግ ውድቀት // የኢትዮጵያ ሠራዊት ፈረሰ፣ ተበተነ
  1984 የወያኔ ንግሥና // 42 የዮኒቨርሲቲ ምሁራን ተባረሩ። ከኢትዮጵያ መሥሪያ ቤቶች ነባር ባለሙያዎች ተፈናቀሉ
  2013 የወያኔ ግብአተ መሬት // በመከላከያ ውስጥ በተለያየ እርከን የሚገኙ የሰሜን እዝ ወታደሮች ተረሸኑ። በዚህ ድርጅት አቀፍ ክህደት መንስኤ ብዙ የወያኔ ጄኔራሎችና ሌሎች መኮንኖች ይታሰራሉ፣ ከሥራ ይባረራሉ። በመቶዎች የሚቆጠሩ። የሀገሪቱ የመካናይዝድ አቅም በራሷ አየር ኃይል ተደመሰሰ።
  ነገስ? ነገ ደግሞ ዛሬ በኮንሶ፣ በጉሊሶ፣ በሻምቡ፣ በሻሸመኔ፣ በመተከል፣ በከማሺ፣ በከሚሴ፣ በጉራ ፈርዳ፣ በሐረርጌ የዘር ጭፍጨፋ የሚያካሂዱ ባለሥልጣናት ከሥራ ይወገዳሉ፣ ለፍርድ ይቀርባሉ።
  ከዚህ ትውልድን በሀገሪቷ አንጡራ ሃብት ለሥልጣን እያበቁ፣ መልሶ ደግሞ እያወረዱ ድባቅ ከመምታት አዙሪት የምንወጣበትን ማሰብ ይገባናል። ወያኔ ኤክስፓየሪ ዴቷ ካለፈ የከረመች ስለሆነች በወደቀች ወያኔ ላይ ብቻ እናተኩር ብለን ሌላ ከወያኔ የረቀቀ፣ የገዘፈ፣ የከፋ፣ ጥፋት ቀንድ እንዲያወጣብን መዘናጋት ፈጽሞ አይመከርም።
  ፈረንጆቹ እኛ ስለወደድነውና ስለጠላነው አይደለም አሻንጉሊት የሚመርጡልን። ከራሳቸው ጥቅም አኳያ እንጂ። ለማስረጃው እንደሆነ አስረጂ አያስፈልጋቸውም። በመቶ ምናምን ኤምባሲ፣ እና የእርዳታ ድርጅት ስም ዝርዝር ዕለታዊ ዘገባ የሚደርሳቸው በመሆኑ። ትንፋሻችንን የምር ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ለመገንባት ለመረባረብ እናውለው። ለዚህ ደግሞ ገንቢ ተቃውሞ የሚያደርጉ እንደ ኢትዮ 360 ሚድያ ያሉትን ልናጠናክር ይገባናል። ከአርባ አምስት አመት በላይ በመንግሥት ሚዲያ ብቻ እንድንደነቁር ተደርገን በገዛ ሀገራችን ጉዳይ እጅግ የጫጨ አስተሳሰብ ያለው ትውልድ እንድንሆን የተፈረደብን አይበቃም? ግዴለም ዲሞክራሲን ባይፈቅዱልንም እንለማመደው።
  በነገሬ ላይ እነ ሃብታሙና እነ ኤርምያስ እኮ እጅግ ድንጉጥና እንደልባቸው እንኳን ለመናገር የማይደፍሩ ናቸው። ዘመድኩን በቀለን በሚድያቸው ያቀረቡት ቀን ፊታቸው ላይ ይነበብ የነበረው ምነው የርሱን ነጻነት ላንድ ቀን እንኳን ብታደለው የሚል የመጓጓትና የመቅናት ስሜትና ወዲያውም የመተንፈስ ስሜት ነበር። እንግዲህ እንዲህ ያሉትን ትሁቶችና ድንጉጦች ልንፈራ አይገባም። ማሸማቀቅም የለብንም። ግዴለም ሕወሃት በተጠራችበት ስም አንጥራቸው። ምንም ዶ/ር ዐቢይ ሕወሃትን አሸባሪ እንዳትባልበት ተጨንቆና ተሳቅቆላት ጁንታ የሚል በሕግ የማይጎዳት ስም ቢያወጣላትም። ሆኖም ይህ ቅጽል ወያኔን ባይጎዳትም እርሷን የመሰለች ወንጀለኛና ሀገር አፍራሽ ሰይጣናዊ ድርጅት የተጠራችበት እንደመሆኑ ቅጽሉን ሌሎች ላይ መጠቀሙ ለማይገባ ውግዘትና ጥቃት የሚያጋልጥ ይሆናል።
  ሥራቸውን እየተቹና እያረሙ፣ እያመሰገኑና እየኮተኮቱ፣ እየነቀፉና እየደገፉ፣ ለሀገር መድኅን የሚድያ ተቋም እንዲሆኑ ማበረታት ይቀጥል።

 3. Dear Ahoon, God bless you in abundance! And I will try my best to disseminate this timely important message through all the means I have.

 4. Liji Dejene Ayano,
  I wish you could teach us by pointing out and explaining what is wrong with Ethio-360 in an objective and rational way of critique instead of just blowing up your out of control emotion and outrage .I strongly believe and argue that Ethio-360 guys can make mistakes just as any human being who can be mistaken in carrying out his or her work or mission. But it is absolutely nonsensical to try to make what they are doing totally valueless. It is ridiculous for you to give your uncritical appreciation to your guys of EPRDF/PROSPERITY who have been causing a very painful and bloody political mess and are not still willing to get out of it whereas you to try to totally invalidate those guys who are trying their best to challenge what went wrong and is going wrong with the political discourse of our country . Believe or not, this kind of very infantile and undigested way of political thinking is the greatest enemy of the people of Ethiopia whose painful problem is the absence of democratic system of politics and government , not the politics of ethnocentrism at all!

  Can you rationally and genuinely tell me what is wrong with the following critical point of view addressed to the Prime Minister as far as making people’s dream for freedom, justice, peace, etc. a reality is concerned?

  Well, as a matter of deeply painful and crystal clear facts of what TPLF’s inner circle has done and continued to do, there is no doubt that it must be engaged and defeated with very minimum collateral damages. To this very desirable end of the very unfortunate if not painfully stupid war between or among those politicians of EPRDF who had been one and the same forces of the very unjust and bloody politics of ethnocentrism for a quarter of a century , one and one extremely critical question must be addressed sincerely and unequivocally and timely of course. And this question is: Is this the war of power struggle between the factions of EPRDF ( one in Arat Killo palace and the other one pushed out and forced to retreat to Mekele ) or aimed at ending the bloody politics of ethnocentrism altogether with its deadly constitution and federalism of division, exclusion, hatred, animosity and mutual destruction or elimination ? Is it aimed at getting rid of those elements of very dangerous political trends and ambitions of Oromization who are directly or indirectly parts and parcels of ODP-led palace politics or allow them to replace TPLF in a much more miserable way? Is the prime minister courageous or patriotic enough to get out of his very immature (infantile), narcissist, hypocritical, cynical, and extremely misleading and confusing political personality and behavior and pave the way for the realization of a fundamental democratic transition and establishment or to strengthen his ethnic-based power grab? Will he be heroic enough to assure the people of Ethiopia who have been and continued to be victims of the deadly political game (ethnocentrism) in which he himself was one of the notorious cadres and still keep playing a leading role as a prime minister that this war of nonsense will be the turning point of making history of democratic system in which individual as well as group rights can prevail without going antagonistic to each other or he will use this as an opportunity to “win” the so called election and continue the very vicious cycle of ethnocentric politics? Will he be courageous enough to get out of his fake and highly deceiving apology he made when he took over the palace politics from his very politically stupid and morally bankrupt predecessor, Hailemariam Desalegn and recommit a true sense of apology and promise? Will he be patriotic enough to set up a national peace and reconciliation platform at which any member of EPRDF (including TPLF) will be confessing and willing to present himself or herself to the due process of justice and pardon in such a way that it will serve as a very bitter lesson for this very confused generation and the generations to come or he will continue playing not only the same but much more worse ODP-led ethnocentric political game?
  Believe or not or agree or disagree that this nonsensical war will end by hook or crook. But one and one absolutely critical issue remain pending. And that issue is the question of taking all necessary and decisive measures that should pave the way for the realization of a political system of freedom, justice, peace , equal opportunity, unquestionable or uncompromised rights of citizens to live and work anywhere in their own country without being victims of any sort of their identity. And this shall become real or practical if only and only the continued deadly political system of EPRDF, now Prosperity (ethnocentrism) comes to its end irreversibly! This very noble political discourse and action cannot be done or accomplished by the same political groupings which are badly infected by a very toxic if not canorous political game of ethnocentrism dominated by a certain political elites of ethnicity such as previously TPLF and now ODP ( elites of Oromization) . That is why the very idea of national dialogue, peace and reconciliation through which fundamental democratic change can be achieved is absolutely essential if we have to get out of the vicious cycle of wars of power struggle once and for all! If this is not the right case to deal with and get it done, it must be clear that politicians of Oromization will definitely do what TPLF’S inner circle is doing now whenever they would face people’s resistance or struggle against their politics of “it is our turn to rule by hook or crook”.
  Are you willing and ready Mr. Prime minister? Although the way you behaved and are behaving does not seem, you are still given the very benefit of the doubt. Do the right thing and be a man of making history and who cleansed his very terribly damaged political background of being a very loyal cadre of a bloody political system of ethnocentrism!!!

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.