አማራ መንግስትን ጠብቆት እንጅ መንግስት አማራን መቼ ጠብቆት ያውቃል?

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com)

አገርን እንደ ጣቃ የቦጫጨቀው የይህ አድግ የዘራፊዎች ቡድን መንግስት፣ ቤተክርስቲያንን የሰነጠቀውና በሰላይ መነኩሴዎች የሞላው ገረመድን ፓትርያሪክ፣ ተበዳይን ተበደለው እግር እንዲወድቅ ያደረገው ኤፍሬም ይሳቅ የአገር ሽማግሌ፣ አገር አፍራሽና ዘረ አጥፊዎችን በሎሌነት ያገለገለው እንድርያስ እሼቴ ምሁር መባል ተጀመሩ ወዲህ የኢትዮጵያ ነገር ቅጥ አንባሩ ጠፍቶታል፡፡

የነፃነት መሰረት የሆኑት ቀረርቶና ፉከራ እንደ ኋላቀርነት ተቆጥረው የባርነት መሰረት የሆኑት የምዕራባውያን ዳንስና ሙዚቃ እንደ ስልጣኔ ተተቆጠሩ ወዲህ ኢትዮጵያ በክብር ተተኮፈሰችበት መድረክ ተሽቀንጥራ እንድትወድቅ አድርጓታል፡፡

ወንዱ ቀበቶውን አጥብቆ ዋሽንቱን እያንቆረቆረ መሸለሉንና መፎከሩን ትቶ ሱሪውን ተጪኑ ታጥቆ ጠጉሩን እየቆጣጠረና እንደ መለኮ ቅባት እየተለቀለቀ በማይክል ጃክሰን ዳንስ ሲወላገድና ሲውለደለድ መዋል ተጀመረ ወዲህ ወንድነት ፈተና ገጥሟታል፡፡ ሴቷም በአልደፈር ባይነት ነፍጡን ይዞ እንደ አንበሳ የሚገማሸረውን ጀግና መምረጡን ትታ የወጥ እንጨት ይዞ  ምድጃ ለምድጃ ተሚልፈሰፈስ ወለወልዳ መለኮ ስትላላስ መዋል ተጀመረች ወዲህ የጀግና ሺል ለመፀነስ አንቀጥ ሆኖባታል፡፡

ባለፉት ሰላሳ ዓመታት አማራን ለማጥፋት የተነሱት ጠላቶች በጀግና አምራች ባህሉ ዘምተው ሽለላውን፣ ፉከራውን፣ የሰምና ወርቅ ዘፈኑንና የአልደፈር ባይነት ወኔውን ሊያጠፉ ድንጋዩን ብቻ ሳይሆን አፈሩን ፈነቃቅለውታል፡፡ በዚህም ምክንያት አማራ ራሱን ለመጠበቅ እንዳነሰ ሁሉ አማራ ተዱራቸው ሄዶ ያለመዳቸው አውሬዎች እንደገና አውሬ ሆነው በየጥሻው በነከሱት ቁጥር “የመንግስት ሥራው የሕዝቡን ደህነንት መጠበቅ ነው!” ሲባል ይደመጣል፡፡ መንግስት የሌሎች አገሮችን ሕዝብ ደህነንት ጠብቆ ሊያውቅ ይችላል፡፡ አማራ ግን እርሱ መንግስትን ሲጠብቅ እንጅ መንግስት አማራን ሲጠብቀው መቼ ታይቶ ያውቃል?

ተጨማሪ ያንብቡ:  የጥላቻ መንስዔው ፣ መዘዙና መፍትሄው ምን ነው? - የቅራኔ አፈታት ባለሙያ የሆኑት ፕሮፌሰር ብርሃኑ መንግስቱ ይናገራሉ

Amharaተራሱ አልፎ መንግስትንና አገሩን ሲጠብቅ የኖረው አማራ ቅባት እየቀባባ እንደ ፍቅረኛ ምጥጥ አድርጎ የሚስማትንና የሚያቀማጥላትን መውዚሩን “መጠበቂያዬ” እያለ ያቆላምጣታል፡፡ ባለ መውዚሩ አማራ እንኳን ራሱን ሜዳውን፣ ወንዙን፣ ሸንተረሩን፣ ተራራውን፣ ጫካውን፣ ባህሩን፣ ሀይቁን፣ የአገሩን ሰማይና መንግስትን ሲጠብቅ ቢያንስ አራት ሺህ ዘመናት አሳልፏል፡፡

አማራ ጣና ሀይቅን ጠብቆ ቪክቶሪያ ሀይቅ ተመባል አድኖታል፡፡ አማራ ዓባይን ጠብቆ ናይል ሪቨር ተመባል አድኖታል፡፡ አማራ ራስ ደጀንን ጠብቆ ኪሊማንጃሮ ተመባል አትርፎታል፡፡ አማራ እጅጉን ጠብቆ ኢድዋርድ ተመባል አድኖታል፡፡ አማራ ሀጎስን ጠብቆ ሄንሪ ተመባል አድኖታል፡፡ አማራ ገቢሳን ጠብቆ ጆቫኒ ተመባል አድኖታል፡፡ አማራ ደሌቦን ጠብቆ ዳኮታ ተመባል አድኖታል፡፡

ተራሱ አልፎ ሌሎችን፣ አገርና መንግስትን ሲጠብቅ የኖረው አማራ እጁ አመድ አፋሽ መሆን ተጀመረ ግማሽ ክፍለ-ዘመን ሆኖታል፡፡ እጅ አመድ አፋሽ ያደረጉት በምዕራባውያንና በአረቦች ሸርና ትከሻ ወንበር የጨበጡ ባንዳዎች ህልውናውንም ተፈታትነውታል፡፡ ስለዚህ አማራ የባህል ጃኖውን አንስቶ እንደገና ግጥም አርጎ ይለብሳል፡፡ ቀበቶውን ጥብቅ አርጎ ያስራል፡፡ ዝናሩን እስተ ብብቱ ይታጠቃል፡፡ የወኔ ዜማውን በዋሽንቱ ያንቆረቁራል፡፡ እረ ጎራው እያለ ይሸልላል፡፡ እንደ አንበሳ አግስቶ እየተንጎራደደ ይፎክራል፡፡ አማራ ሊያጠፋው የተነሳውን አውሬ ተናንቆ ራሱን፣ አገሩንና ሕዝቡን እንደ ልማዱ ይጠብቃል፡፡

በሰላም ጊዜ በማረሻ በርቃሽ በጦርነት ወቅት በመውዚር በጣሽ የሆነው አማራ ራሱን እንዳይጠብቅ ሊያጠፋው የመጣው የይህ አድግ አገዛዝ ኢትዮጵያና የዓባይ ግድብ በሚል የስብከት ገመድ አስሮታል፡፡ አማራ ይኸንን የማታለያ እስር በጥሶ ራሱን ተመጥፋት ያድናል፡፡

አማራ የተሰራበት ግፍ ደመናውን አልፎ ሰማይ ነክቷል፡፡ አማራ እንኳን ተአገሩ ምድር ተውጪ የመጣን እንግዳ እግሩን አጥቦና አልጋውን ሰጥቶ ያሳድራል፡፡ እርሱ ግን በገዛ አገሩ መጤ እየተባለ አንገቱን ይታረዳል፡፡ ጽንሱ ሳይቀር የእናት ሆድ ተቀዶ ይገደላል፡፡ አማራ ተገፍቶ ተገፍቶ ተጫፍ ደርሷል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  የተሳሳተው ማነው? የአሜሪካ መንግሥት ወይንስ የዐብይ መንግሥት?- ክፍል ሶስት

አማራ እንደተለመደው የውጪ ታሪካዊ ጠላቶቹ ተውስጥ ባንዳዎች ጋር አሲረውበታል፡፡ ነገር ግን አማራ እንደ ቅደም አያቶቹ ራሱንም ሆነ እርስቱን ተውጭ ወራሪዎችና ተውስጥ ባንዳዎች ይከላከላል፡፡ አማራ የቴዎድርስን፣ የሚኒልክን፣ የተክለሃይማኖትን፣ የሚካኤልን፣ የበላይ ዘለቀን፣ የአበበ አረጋይንና ተመረብ እስክ ጊቤና ባሮ ወንዞች በባንዳዎች ተጀርባ እየተወጋ የተዋደቀውን የጥቁር አንበሳ ጦር አደራ ይጠብቃል፡፡

አማራ እንደ አድዋውና እንደ አምስቱ ዘመን በአንድነት ተዋድቆ ራሱንም ሆነ ሌሎቹን ተተናካሽ አውሬዎች ይከላከላል፡፡ ድሮስ ተራሱ በቀር ለአማራ ማን ደርሶለት ያውቃል? እርሱ ሌላውን እንጅ ሌላው አማራን በየትኛው ዘመን ጠብቆት ያውቃል? አማራ መንግስትን ሲጠብቅ እንጅ  መንግስት አማራን ሲጠብቅስ መቼ ታይቷል?

 ህዳር ሁለት ሺ አስራ ሶስት ዓ.

2 Comments

  1. “አማራ/ፋኖ ኃይለማርያም ደሣለኝ ላይ እንደ ኦሮሞ/ቄሮ በብዛት አላመጸም” የሚል የተረኞች አባባል አማራን እንደገና ለእነርሱ ታዛዥ እንዲሆን በዕቅድ የተሰራበት ነው። አማራ/ፋኖ ጃስ በተባለበት ሊነክስ እንዲወስን ሆንዋል። መፈንቅለ መንግስት ብለው እነ አሳምነውን አስጨርሰው እነ ጥሩነህን እንደለማዳ ችሎ አዲስ አበባ አስቀምጠው ፣ የባህር ዳር ከንቲባን በአለም ሲያበኑት ከርመው ድንገት አሉ ፋኖን “ጃስ ጃስ” እያሉ ላኩት አማራን እንስሳ እንዲያድን ።

    አማራ/ፋኖ እራሱንም እንደ ኦሮሞ/ቄሮ በብዛት አልተሰዋም ኃይለማርያምን እና ወያኔን ከስልጣን ለማስወገድ የሚለው ትርክት የእነ አብይ ስልጣን ማጠናከሪያ ሆኖላቸዋል። ከእነ ጃዋር “እኛ ብቻ አማራ ፋኖ ሳይታገል ቄሮ ብቻውን እኮ ስድስት ሺህ ቄሮ/ ኦሮሞ ገብረን ነው ወያኔን ትግራይ ድረስ የገፋናቸው” ከሚለው የሐሰት አባባል ጋር ተደምሮ አማራን ከመንግስት ውጭ አድርጎት ቢቆይም መንግስት አማራን ባይደርስለትም ይኸው መንግስትን አተረፈውአማራ/ፋኖ እራሱ እየሞተ በህይወቱ ብቻ ሳይሆን እውነት ባህሉ እና ኩራቱ አንድነቱ ሞቶ ከርሞ።

    “አማራ ዱቄት” የሚሉን እኮ በነፈሰበት ስንበን ስለሚያዩን ነው። አማራ / ፋኖ አንድ ላይማ ቢጋገር እንዲህ እንደነፈሰበት በአየር ላይ ወዲህም ወዲያም ብን ብሎ ዘሩ ሊያጠፉት ወጥነው አይደፈሩትም ነበር። እውን “አማራ ዱቄት” ነውን??? ጊዜ ይፈርዳል ! አማራ ያብራል! ጀግኖችን እንስሳት ውድ ማንነቱ ይመለሳል ዘሩን በሙሉ ጨርሰው ከማጥፋታቸው በፊት።

  2. Bomb hand grenades were thrown at the first lady and PM Abiy Ahmed at a rally but the Addis Ababa residents saved them from the attack , even after that Abiy Ahmed failed to save the Addis Ababa residents from eviction , job hiring discrimination at the City of Addis Ababa , Condo theft , Querro hullligans various crimes………..

    Abiy Ahmed need to be voted out ASAP
    Let’s punish him in the election ,if there is going to be election.

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.