ኢትዮጵያን ከጁንታው አዲስ የሳይበር ጥቃት ሴራ የመታደግ ሀገራዊ ጥሪ! – ጌች ዘለቀ

126808007 1185116611885975 1964292491273303825 nበቅርቡ ከእስር የተፈታውና ኢንሳ/INSA ውስጥ የዶ/ር አብይ ምክትል የነበረ የሳይበር ቴክኖሎጂ ኤክስፐርት አቶ ቢንያም ተወልደ ከትህነግ ጋር በመሆን በኢትዮጵያ ላይ ከባድ ሴራ እያሴሩ ነው። ከቢንያም ተወልደ እና ወያኔ ቀድማ በብዛት ቻይና ልካ ያሰለጠነቻቸው ወጣት የትግሬ ኢንጂነሮች በጋራ በመስራት ትግራይን ከፌደራል የቴሌኮሚኒኬሽን ቁጥጥር ነጻ በማውጣት አሁን ግንኙነታቸውን ከኔትዎርክ አቅራቢ የቻይና ድርጅት ሁዋዌ ጋር እንዲሆን አድርገዋል። ይህ በጁንታው የተደራጀው የቴክኖሎጂ ክንፍ የኢትዮጵያን የባንክ፣ የቴሌኮም፣ የኢንሳ እና የሚዲያ ተቋማላት ላይ የሳይቨር ጥቃት ለማድረግ ከውጭ ሀገራት የቴክኒክ ድጋፍ ለማግኘት እየሰሩ ነው። ለዚህም በውጭ ሀገራት የሚኖሩ የጁንታው አባላት ልጆችና የጥፋት ቡድኑ አባላት በያሉበት አካባቢ ከአለምአቀፍ የቴክኖሎጂ ተቋማት ድጋፍና የቴክኒክ መፍትህ እንዲያፈላልጉ መመሪያ ተሰጥቷቸዋል።
ይህ የጁንታ ክንፍ እነዚህን ስራዎች በአብዛኛው በኢንሳና በመከላከያ የቴክኖሎጂ ክፍሎች ውስጥ ሲሰሩ በነበሩ የጥፋት አካላት ስራው እንዲሰራ ተልዕኮ ተሰጥቷል። በመንግስት በጀት በአመት ውስጥ በተደጋጋሚ ከፍተኛ የደህንነትና ሚሊተሪ ስልጠናዎችን በዝምድናና በጁንታዊ ማንነት ጥቅማጥቅሞችን ሲያግበሰብሱ የነበሩ አካላት ሀገር ለማውደም በከፍተኛ ደረጃ ተሰብስበዋል።
126860408 1185116668552636 2611884546911865041 n
በእነዚ እናት ጡት ነካሾችና ያበላ እጅ ሰባሪዎች ከፍተኛ የሀገር ክህደት ወንጀል እየተፈፀመ ስለሆነ በተያያዥ ሙያዎች ያለ ማንኛውም ዜጋ ከፍተኛ የሆነ ሙያዊ ግዴታውን እንዲጣ ግድ ይላል። በጁንታው የተዋቀሩት ኢላማዎችም የሚዲያ ኔትወርክ፣ ወሳኝ የሆኑ የፌስቡክ አካውንቶችን መቆጣጠር፣ የሀገሪቱን የቴሌቭዥንና የሪዲዎ ጣቢያዎችን መጥለፍና መረበሽ፣ ለረዥም ግዜ የመቆይ የቴሌኮሚኒኬሽን አገልግሉት ክልከላ እና ጠለፋ ከዚህም በተጨማሪ የገንዘብ ተቋማትን ሲስተም ሰብሮ በመግባት ምዝበራ፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩን የፋይናንስ ዝርዝር ዳታን መመንተፋ፣ የገንዘብ እንቅስቃሴውን የመቆጣጠርና የመጥለፍ ሴራን የሚሰራ የጥፍት ቡድንም ለብቻው ተቋቁማል። ከጦርነቱ ጋር በተያያዘ የሳተላይ ምስል መረጃዎችን ምንጭ መፈተሽነ አስፈላጊውን መረጃ የሚወስድ የጥፋት ቡድንም መስርተዋል። የድሮኖችን የሳተላይ ግኑኝነት መጥለፍና አቅጣጫ ማስቀየር ወይም ግኑኝነቱን ለማበላሸት የሚሰራ ቡድንም አዘጋጅተዋል።
በመሆኑም ጁንታው ይሄን የጥፋት ቡድን አዘጋጅቶ ስራ ውስጥ ስለገባ መላው ኢትዮጵያዊ በተሰማራበት ሙያ የበኩሉን እንዲወጣና የተለየ ነገር ሲያጋጥመው ለመንግስት ሪፓርት በማድረግ ሀገራዊ ግዴታችንን እንድንወጣ ጥሪ ተላልፏል።
የኢትዬጵያ መንግስት ከቻይና መንግስት ጋር በፍጥነት በመነጋገር ሁዋዌ የተባለው የሳተላይት ኔትዎርክ አቅራቢ ድርጅት ከአሸባሪ ሀይል ጋር እየሰራ መሆኑ ተነግሮት ውሉን እንዲያፈርስና አገልግሎቱን እንዲያቋርጥ መደረግ አለበት። በነገራችን ላይ ይህንን ሴራ የሚሰራው አርከበ እቁባይ ቻይና በሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ ከተሰገሰጉ ጥቅመኞች ጋር በቅንጅት መሆኑ ግን በዚህ አጋጣሚ ይሰመርበት።
ጌች ዘለቀ

2 Comments

  1. ዶ/ር አብይ አህመድ የሳይበር ጥቃት መመከትን ሆነ ከፈለገም የሳይበር ጥቃት መሰንዘርን ከእነርሱ በላይ ያውቅበታል አቅሙም አለው። ጠ/ሚ አብይ አህመድ ጋር ያለው ችግር እነርሱን ሆኖ አብሮዋቸው እያገዛቸው እያገዙት አብዛኛውን እድሜውን ማሳለፉ ነው። ይህም አጥቂዎችን ወደ መደገፍ እና ተጠቂዎችን ወደ አለመስማት ባህል አድርሶታል።

    ከእነርሱ ከትግራይ ጁንታዎች ብዙ በሽታዎች ወደ ዶ/ር አብይ አህመድ ትጋብተውበታል።የትግራይ ጁንታ ተብዬዎች ከመቀሌ ተነቅለው ቢሆንም እንኳን ኢትዮጵያ ሰላም የላትም ምክንያቱም ጠ/ሚ አብይ አህመድ እራሱ ሥራው በሙሉ እንደ የትግራይ ጁንታዎቹ ነው። አንድ ጁንታ ከትግራይ ተነቅሎ ሌላ የአብይ ጁንታ በትግራይ እየተተካ ነው ልክ በሌላው ኢትዮጵያ ላለፉት ሶስት አመት እንደተተኩት።ወደፊት ይቅር ተባብለው የአብይ ጁንታዎች ከወያኔ ጁንታ ርዝራዦች ጋር በጥቅም ተሳስረው አብረው እንደሚሠሩ ሳይታለም የተፈታ ነው። የሚገርሙኝ አብይ ሰንኮፍ ሊነቅል ነው ብለው የዘመቱት ኃይሎች እና አብይ ሀገር ያበለጽጋል የሚ የባንክ ደንበኞች የኢትዮጵያ ባንክ ውስጥ ገንዘብ አለኝ ብለው የሚገምቱት የአብይ ደጋፊዎች ናቸው።

    ስንሞት ለልጅ እንኳን ማውረስ ያልተቻለ በባንክ ያለ ገንዘብ “ላም አለኝ በሰማይ ኩበትዋንም አላይ” አስብልዋል።

  2. የሰላይ ተሰላይ ድሮ ቀረ ዛሬ ስላዪ ሶፋው ላይ ቁጭ ብሎ በኢንተርኔት እልፍ ኪሎሜትሮችን ዘልቆ መግደል፤ መሸጥ፤ መለወጥ፤ ማታትና መስረቅ ይችልበታል። ወያኔ ከጣሊያንና ከሌሎችም በገዛው የሚስጢር ፍልፈላ ሶፍትዌር የሃገራችን የባንክ የኮሚኒኬሽን ከላይ እስከታች ከመቆጣጠሩም ሌላ በውጭ ሃገር ባሉ ጀሌዎቹ አማካኝነት ብዙዎችን የሴራው ሰለባ አድርጓል። አሁን ባለንበት አለም ሁሉም ነገር ከንግድ ጋር የተያያዘ ነው። ፈረንጆች Surveillance Capitalism ይህኑ ኢንፎርሜሽን ቀምሮ ለጥብስ የሚያቀርብ ስልት ነው። በዪቱብ፤ በሌሎች ሶሻል ሚዲያዎች በተለይም ፌስ ቡክ ተብሎ በሚጠራው የሞኝ መገናኛ ቦታ ስንቶች ሰላባ እንደሆኑ ቤቱ ይቁጠረው። ሌላው ደግሞ Dark Web ተብሎ በሚጠራው መንገድ ይህ ነው የማይባል የድብቅ ተግባር ይፈጸማል። የወያኔን ከእኔ በላይ ማን በሰው ስለላም ሆነ በኢንተርኔት ጥቃት የሚያደርሱትን መልሶ ለመቋቋም እነርሱ የሚጠቀሙባቸውን ዘዴዎች ጠንቅቆ ማወቅ ተገቢ ነው። ይህ እውቀት ለሁለት ነገር ይጠቅማል። የዘረጉትን የሰውና የሰውር መረብ ለመበጣጠስ፤ የራስን የስለላ መረብ ለመዘርጋትና በሃገርና በህዝብ ወዳድ ወገኖች ለመተካት ይጠቅማል። ለዚህ ነው አባቶች “እሾህን በእሾህ” የሚሉት። ዝም ብሎ ዶ/ር አብይ የእነርሱን ሴራ ያውቃል ገለ መሌ ማለቱ ለእኔ አይታየኝም። የስለላ ዘይቤና አሰራራ በየቀኑ ተለዋዋጭ ነው። ወያኔ በአንድ ሲያዝ በሌላ መንገድ ይዘረጋል። የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በየመን መታፈን፤ የብዙ ምርጥ የኢትዮጵያ ልጆች እየተለቀሙ መገደል፤ የሃገሪቱ ሃብት በአሜሪካ፤ በእስያ፤ በአውሮፓ ለእነርሱና ለልጆቻቸው መሆን ከዚህ የሴራ ተንኮል ጋር ይያያዛል። አሁን ሚስቴንና ልጄን አውጡልኝ የሚለው ዶ/ር ደብረጽዪን ውጊያ ላይ የሚሞቱትን የደሃ ልጆች ደም ለእርሱና ለመሰሎቹ የሰው ደም አይደለም። አቶ ስዬ አብርሃ ዛሬ በቦስተን ከነቤተሰቡ በሰላም መኖሩ ይገርማል። አይ አሜሪካ አያግበሰብሰው የለ። አሁን ማን ይሙት ይህ ስንቶችን የገደለና ያስገደለ ግለሰብ በሰላም መኖር ይገባዋል? ሌሎችም በአውስትራሊያ እና በሌሎችም የአውሮፓ ሃገሮች ሶፋቸው ላይ ተቀምጠው አይዞአቹ እያሉ ሰው የሚያጫርሱ ጉዶች በእውነት ለትግራይ ህዝብ ያስቡ ይሆን? መቼ ነው የትግራይ ህዝብ በመረጠው፤ ሲፈልግ በሚያወርደው በራሱ ለራሱ አስቦ የሚኖረው? መቼ ነው ከዚያች ምድር የጥይት ድምጽ የሚጠፋው? አቶ አሉላ የሚባል የወያኔ አቀንቃኝ ውጭ ሃገር ላይ ተቀምጦ በአልጄዚራና በሌሎች ሚዲያዎች ላይ የሚነዛውን ለተመለከተ እነዚህ ሰዎች ታመዋል ያሰኛል። በቅርቡ ለምን አማራ ብቻ አይገጥመንም ማለቱ የቱን ያህል የላሸቀና ጊዜ ያለፈበት የሻገተ ሃሳብ ይዞ እንደሚጓዝ ያሳያል።
    የታወቀ ነው ወያኔዎች ለራሳቸው መኖር ሲሉ እናታቸውን ገቢያ አውጥተው ይሸጣሉ። እነዚህ ጥርቅሞች ሙት ስለሆኑ ብዙዎችን ይዘው ይሞታሉ። አሁንም በለው በለው ከህዋላ የትግራይን ልጆች ማግደው እነርሱ ቀድመው ባዘጋጅት መንገድ ግብጽ፤ ሱዳን፤ ሌላም ሃገር ሆነው ከሩቅ ድንጋይ መወርወራቸውን አያቋርጡም። ወያኔ በሁለት ነገር ተክኗል። ግድያና ዝርፊያ። ሌላው ሁሉ ለፓለቲካ ፍጆታ ተብሎ የሚበተን ገለባ ነው። ከጫካ እስከ ከተማ ታሪካቸው ይህ ብቻ ነው። ሰው በተኛበት መግደልም በሰሜን እዝ ላይ የተደረገው የመጀመሪያ አይደለም። የራሳቸውን ወገኖች በተኙበት ነው የረሸኗቸው።
    አንድ ነገር ልበልና ላብቃ። ወያኔ የስለላ መረቡ ከሃገር ቤት እሰከ ውጭ ሃገር የስደተኛ መጠለያ ጣቢያዎች ጭምር ነው። በመሆኑም ከኤርትራ ወጥተው በድንበር ላይ የሰፈሩ ኤርትራዊያን ቀድመዋቸው ሃገር ለቀው በየአለማቱ የተበተኑ ወገኖቻቸው አልፎ አልፎ ገንዘብ እንደሚልኩላቸው ወያኔ ጠንቅቆ ያውቃል። ዘረፋውን ለማቀላጠፍ በሃዋላ በሌላም መንገድ በውጭ በተለይም በአዲስ አበባና በመቀሌና ዙሪያዋ ባሰማራቸው ሰዎች የሚላከው ገንዘብ ወጋገን ባንክ እንዲላክላቸው ለኤርትራዊያኑ ይነገራቸዋል። እነርሱም ለወገኖቻቸው በዚሁ እንዲልኩ ያደርጋሉ። ያው በጥቁር ሂሳብ በመካከል ያለው ሰው ለውጦ ወጋገን ያስገባል። የውጭው ጥሬ ገንዘብ ለወያኔ ባለስልጣኖች ገቢ ይሆናል። አሁን ወጋገን ሲዘጋ እልፍ ኤርትራዊያን ገንዘባቸውን ማውጣት አልቻሉም። ይህ የወያኔ ሴራ ሌላም ሌላም ጉድ አለው። ወደፊት ሰዎች ይጽፉታል። ለዛሬው የሰላይ ተሰላይን የተሰላይ ሰላይን ዘይቤ ለማምከን ቅድሚያ ዘዴአቸውን ለይቶ ማወቅ ያስፈልጋል። ውጊያው በጦር ሜዳ ላይ ብቻ አይደለም። በእያንዳንድ የሰው ጭንቅላት ጭምር እንጂ። የውሸትና የፈጠራ ዜናው ሰበር ተብሎ የሚተረክበት ጊዜ ላይ ነው ያለነው። ግን የተሰበረ ዜና ለመስማት ሲሮጡ ወድቆ ከመሰበር ፈጣሪ ይሰውረን። ወሬው ሁሉ 95% ፈጠራና የተጋነነ ነው። እውነት ብልጭ ድርግም እያለች ነው በአለማችን ላይ። ልብ ያለው ልብ ይበል። በቃኝ!

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.