በትግራይ ክልል የተፈጸመ ከፍተኛ የሕግ ጥሰት የኢፌዴሪ መንግሥት ወደ አስገዳጅ ሕግ ማስከበር ተግባር እንዲገባ አድርጎታል… የኖርዌይ ምሁራን ለኖቤል ኮሚቴ በጻፉት ደብዳቤ

126254707 2810582949184166 5759599654954266963 o በትግራይ ክልል የተፈጸመ ከፍተኛ የሕግ ጥሰት የኢፌዴሪ መንግሥት ወደ አስገዳጅ ሕግ ማስከበር ተግባር እንዲገባ አድርጎታል... የኖርዌይ ምሁራን ለኖቤል ኮሚቴ በጻፉት ደብዳቤበኖርዌይ የሚኖሩ 28 ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮ-ኖርዌጂያን ምሁራን እና ባለሙያዎች ለኖቤል ኮሚቴ በጻፉት ደብዳቤ፣ የኢፌዴሪ መንግሥት በትግራይ ክልል የተፈጸመው ከፍተኛ የሕግ ጥሰት ወደ አስገዳጅ መጠነ ሰፊ ሕግ የማስከበር ተግባር እንዲገባ ማድረጉን አስታወቁ።
ምሁራኑ እና ባለሙያዎቹ ቀደም ሲል ሐምሌ ወር 2012 ዓ.ም ላይ በጠባብ ብሔርተኛ ቡድኖች እና ግለሰቦች አነሳሣሽነት ኢትዮጵያ ውስጥ እየታዩ ያሉ ፖለቲካዊ እና ሰብአዊ ቀውሶች አሳስቧቸው ለኮሚቴው ደብዳቤ መጻፋቸውን አስታውቀዋል።
የኢፌዴሪ መንግሥት በቅርቡ በትግራይ ክልል የተፈጸመ ከፍተኛ የሕግ ጥሰት ወደ አስገዳጅ ሕግ የማስከበር ተግባር እንዲገባ ማስገደዱንም ጠቅሰዋል።
ይሁን እንጂ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ እና የኖቤል ኮሚቴ በትግራይ ክልል እየተከናወነ ስላለው የሕግ ማስከበር ተግባር ሆነ ተብሎ የተሳሳተ ግንዛቤ እና የተዛባ መረጃ እንዲደርሳቸው እየተደረገ እንደሆነ እንደሚያምኑ ገልጸዋል።
የዓለም የሰላም ኖቤል ያሸነፉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በዚህ መሰል የሕግ ማስከበር እርምጃ ላይ መሰለፍ እንደሌለባቸው የሚገልጹ የተዛቡ ዘገባዎች ማየታቸውንም ጠቅሰዋል።
ይህ በራሱ ፍጹም ስሕተት ነው ያሉት ምሁራኑ እና ባለሙያዎቹ፣ በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ ውስጥ ስላለው የፍትሕ ሁኔታ አያሳይም ሲሉ አመልክተዋል።
በመሆኑም በኢትዮጵያ መንግሥት እና በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ላይ እየተሰራጩ ያሉት የተሳሳቱ መረጃዎች እና የስም ማጥፋቶች አሳስቧቸው ደብዳቤ ለመጻፍ እንዳነሣሣቸው ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ እንደሚከታተል ትውልደ ኢትዮጵያዊ ምሁርነታችን፣ ለኖቤል ኮሚቴ ትክክለኛውን ገጽታ እና በአገሪቱ ያለውን እውነታ ማሳወቅ እንፈልጋለን ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ መጋቢት 2010 ዓ.ም ላይ ወደ ሥልጣን ከመጡ ጀምሮ ያደረጓቸውን ለውጦች ለ30 ዓመታት ገደማ የትግራይ ክልልን እየመሩ ያሉት የሕወሓት አመራሮች ለመቀበል ፈቃደኛ አለመሆናቸውን አመልክተዋል።
ይህም ከለውጡ በፊት የነበረው ሕወሓት መሩ ግንባር ኢትዮጵያ ውስጥ የተገነባው ግለሰብን በማግነን እና በራስ ፍላጎቶች ላይ እንደነበር ግልጽ ነው ብለዋል።
አብዛኞቹ አክራሪ ሕወሓቶች ዓለም “እኛ ሥልጣን ላይ ከሌለን ኢትዮጵያ አትኖርም” የሚለውን እንዲያምንላቸው የሚፈልጉ ናቸው ሲሉ ጠቅሰዋል።
የአገሪቱን ሥልጣን ለቅቀው ወደ ክልላቸው ተጠቃልለው ከገቡ በኋላ በድብቅ ሲያከናውኗቸው የነበሩ ተግባራት በተከታታይ የፌዴራል መንግሥቱን በመገዳደር ይህንን ትርክታቸውን እውን እንዲመስል ማድረግ ነበር ብለዋል።
በርካታ ምሁራን፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና ግለሰብ ዜጎች በሥልጣን ላይ ያለው መንግሥት በተልይም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የመንግሥት ተቀዳሚ ተግባር የሆነውን ሕግ እና ሥርዓት የማስከበር እርምጃ እንዲወስዱ ሲወተውቱ መቆታቸውን ጠቅሰዋል።
በዚህም ሕወሓት እና በርሱ የሚደገፉ ወንበዴ ቡድኖች ሲፈጥሩት በነበረ ዘር ተኮር ብጥብጥ እና ግጭቶች የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ መንግሥት የትችት ናዳ ሲወርድበት መቆየቱን ገልጸዋል።
በእነዚህም ዘር ተኮር ግጭቶች እና ብጥብጦች በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ለሞት፣ ሚሊየኖችን ለመፈናቀል፣ ለሀብት ንብረት ውድመት እንዲሁም አገሪቱን መጠነ ሰፊ አለመረጋጋት ውስጥ ከትቷል እንደነበር አስታውሰዋል።
የአሁኑ ግጭት መንስኤም የሕወሓት ኃይሎች በሰሜን የአገሪቱ ክፍል በሚገኘው የኢፌዴሪ መከላከያ ኃይል ላይ ጭካኔ የተሞላበት ጥቃት በመፈጸሙ የተከሰተ መሆኑን አብራርተዋል።
ይህንንም ተግባር በይፋ መፈጸማቸውን የሕወሓት ከፍተኛ ባለሥልጣን የሆነው ሶኩቴሬ ጌታቸው በክልሉ ቴሌቪዥን ባደረጉት ውይይት ማረጋገጣቸውን ጠቅሰዋል።
ይህም ሕወሓት የኢፌዴሪ መንግሥት ወደ ሕግ ማስከበር ተግባር ተገድዶ እንዲገባ እንደገፋው ጠቅሰዋል ።
/ኢብኮ/

1 Comment

  1. Adanech Abebe’s net worth increased by two folds since she became Mayor of Addis Ababa this year , making her the richest government official in Ethiopia next to Abiy Ahmed , Takele Uma and Lemma Megerssa.What makes Adanech Abebe’s case so astonishing is the quickness of the time she took to become filthy rich.

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.