የአሜሪካ መንግሥት “እየተባባሰ ለመጣው የኢትዮጵያ ግጭት አፋጣኝ ዲፕሎማሲያዊ እርምጃ እንዲወስድ” ቦብ ሜኔንዴዝ የተባሉ ሴናተር ጠየቁ

1 K2YGxP9E pmjAgw7RK6uuwየአሜሪካ መንግሥት “እየተባባሰ ለመጣው የኢትዮጵያ ግጭት አፋጣኝ ዲፕሎማሲያዊ እርምጃ እንዲወስድ” ቦብ ሜኔንዴዝ የተባሉ ሴናተር ጠየቁ። ቦብ ሜኔንዴዝ ትናንት ረቡዕ ሕዳር 9 ቀን በአሜሪካ ሴኔት ለውጭ ጉዳይ ኮሚቴ ባቀረቡት ደብዳቤ ኢትዮጵያ “በታሪካዊ የዴሞክራሲ ሽግግር ላይ ነች” ተብሎ በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ተስፋ ቢጣልባትም ይልቁን “ወደ የርስ በርስ ጦርነት እየተንሸራተተች ነው” ሲሉ ሥጋታቸውን ገልጸዋል።
“ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ተጨማሪ ኹከትን ለመከላከል በፍጥነት እርምጃ ካልወሰደ ደም አፋሳሽ እና ረዘም ላለ ጊዜ የሚዘልቅ ግጭት የማይቀር ነው የሚል ፍርሐት አለኝ” ሲሉ ሴናተሩ አስጠንቅቀዋል።
“በተለይም ማይ-ካድራ ውስጥ በተፈፀመ የሰላማዊ ሰዎች ጭፍጨፋ በጣም አዝኛለሁ። ይኸንን ድርጊት እና በሰላማዊ ዜጎች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን ሁሉ በብርቱ አወግዛለሁ” ያሉት ቦብ ሜኔንዴዝ “በገለልተኛ ወገን ጥልቅ እና ግልጽ ምርመራ እንዲደረግ” ጠይቀዋል።
“በፌድራል መንግሥት የአየር ድብደባ ሰላማዊ ሰዎች ሞተዋል፣ በጅምላ ተፈናቅለዋል፣ በብሔራቸው እየተለዩ ታስረዋል መባሉ እጅግ አሳስቦኛል። የትግራይ ባለሥልጣናት ወደ ጎረቤታቸው ኤርትራ ዋና ከተማ ሮኬት መተኮሳቸውን አረጋግጠዋል። የሮኬት ጥቃቶቹ ግጭቱን የሚያባብሱ እና ውጤት አልባ በመሆናቸው መቆም አለባቸው። ግጭቱ ከኢትዮጵያ ድንበሮች ባሻገር ይሰፋል የሚለውን ሥጋት የበለጠ ያረጋግጣሉ” ያሉት ሜኔንዴዝ ሥጋታቸው ከዚያም እንደሚበረታ ለአሜሪካ ሴኔት የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ በደብዳቤ አብራርተዋል።
“በትግራይ የተጀመረው ግጭት ዝም ብሎ ከተተወ ወደ ከፋ እልቂት እና ሰብዓዊ ቀውስ ማምራት ብቻ ሳይሆን ተጨማሪ ጠላትነት ፈጥሮ የኢትዮጵያን ዴሞክራሲያዊ ዕድገት በማደናቀፍ መላ ቀጠናውን ያተራምሳል” በማለት ያስጠነቀቁት ሴናተር የኢትዮጵያ ፌድራል መንግሥት እና የትግራይ ባለሥልጣናት “የሰላምን መንገድ” እንዲመርጡ ጠይቀዋል።
“ለአሁኑ ቀውስ መፍትሔ በማበጀት ረገድ የኢትዮጵያ ቁርጠኝነት እና እርምጃ ቢጠይቅም አሜሪካ እና ሌሎች የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ አባላት ቁልፍ ሚና ሊጫወቱ ይችላሉ” ያሉት ሴናተር ሜኔንዴዝ የጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ መንግሥት እና የትግራይ መስተዳድር መሪዎች ወደ ድርድር እንዲመለሱ ጫና ሊደረግ እንደሚገባ ጠቁመዋል።
DW
ተጨማሪ ያንብቡ:  ወደ ገሰንገሳ ተራራ ለግዳጅ የተላኩ የሕወሓት ወታደሮች ላይ እርምጃ ተወሰደ | አምስቱ በሳንጃ ተወግተው ተገድለዋል

4 Comments

 1. ምን አይነት ወገናዊነት ስራ ነው እየተሰራ ያለው በአሜሪካ ሴናተር እና ዲፕሎማት፡፡ አንድ አንባገነነ፣ በዘር ፍጅት የሚጠየቅ ፓርቲ ነው መጠየቅ ያለበት ወይስ ህግ ለማስከበርና ህዝብን ነፃ ለማውጣት የሚጥር የአብይ መንግስት ነው መጠየቅ ያለበት??? ይህ ጉዳይ እኮ የነአብይ ብቻ አይደለም፡፡ የመላ ህዝብ ጥያቄ ነው፡፡ እነሱ ለግል ጥቅማቸው ሲሉ መላ ዓለምን እየለመኑ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ዲፕሎማት፣ ሙሁራን፣ የውጪ ጉዳይ በዚህ ላይ በስፋት የአገሪቷን አቁዋም ማሳወቅ ያስፈልጋል፡፡ በ BBC, CNN, AL-Jezera ላይ በስፋት ማሰወቅ ያስፈልጋል፡፡ ለዚህ ሁሉ ሜስ የአሜሪካ ዕጅ ነበረበት ወንጀለኛ የህዋአት ቡድን በነሱ ድጋፍ ለዚህ በማብቃት፡፡ አሁንም ኢትዮጵያ በተፋጠነ ሁኔታ ውጊያውን ለመቋጨት መገስገስ አለባት፡፡ ይህ ትግል እኮ አሁን የመላ ህዝቡ ትግል ነው፡፡ አብይ ብቻውንም ሊደራደርበት አይችልም፡፡ የማይታሰብ ነው፡፡ የተነቃነቀ የህዋአት ጥርስ ቶሎ እንዲነቀል ነው እን እንጂ ጥያቄው፡፡

 2. ምን አይነት ወገናዊነት ስራ ነው እየተሰራ ያለው በአሜሪካ ሴናተር እና ዲፕሎማት፡፡ አንድ አንባገነነ፣ በዘር ፍጅት የሚጠየቅ ፓርቲ ነው መጠየቅ ያለበት ወይስ ህግ ለማስከበርና ህዝብን ነፃ ለማውጣት የሚጥር የአብይ መንግስት ነው መጠየቅ ያለበት??? ይህ ጉዳይ እኮ የነአብይ ብቻ አይደለም፡፡ የመላ ህዝብ ጥያቄ ነው፡፡ እነሱ ለግል ጥቅማቸው ሲሉ መላ ዓለምን እየለመኑ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ዲፕሎማት፣ ሙሁራን፣ የውጪ ጉዳይ በዚህ ላይ በስፋት የአገሪቷን አቁዋም ማሳወቅ ያስፈልጋል፡፡ በ BBC, CNN, AL-Jezera የቻይና CCTV ወዘተ ላይ በስፋት እና በፍጥነት ማሰወቅ ያስፈልጋል ፡፡ ለዚህ ሁሉ ሜስ የአሜሪካ ዕጅ ነበረበት ወንጀለኛ የህዋአት ቡድን በነሱ ድጋፍ ለዚህ በማብቃት፡፡ አሁንም ኢትዮጵያ በተፋጠነ ሁኔታ ውጊያውን ለመቋጨት መገስገስ አለባት፡፡ ይህ ትግል እኮ አሁን የመላ ህዝቡ ትግል ነው፡፡ አብይ ብቻውንም ሊደራደርበት አይችልም፡፡ የማይታሰብ ነው፡፡ የተነቃነቀ የህዋአት ጥርስ ቶሎ እንዲነቀል ነው እን እንጂ ጥያቄው፡፡

  What they are doing American Senator’s & Diplomats here??? You are reporting to your president Trump, so what??? He is already against of Ethiopia, so what? Because, you are big country in which ruled only in-favor your policy? This is a fake stand as TPLF leaders nag you & make petition to you. No way, Ethiopia will not negotiate with small junta group as it has a capacity to place order.

  This is not solely Abiy position right away instead it is now a question of all Ethiopians to bring that tyrant group to justice once for all. No compromise by Ethiopian people. So those diplomats & senator’s just keep quiet and be on side of Ethiopian people. You will soon see the result.

  Long live to Ethiopia, down-down to junta group.

 3. ምን አይነት ወገናዊነት ስራ ነው እየተሰራ ያለው በአሜሪካ ሴናተር እና ዲፕሎማት፡፡ አንድ አንባገነነ፣ በዘር ፍጅት የሚጠየቅ ፓርቲ ነው መጠየቅ ያለበት ወይስ ህግ ለማስከበርና ህዝብን ነፃ ለማውጣት የሚጥር የአብይ መንግስት ነው መጠየቅ ያለበት??? ይህ ጉዳይ እኮ የነአብይ ብቻ አይደለም፡፡ የመላ ህዝብ ጥያቄ ነው፡፡ እነሱ ለግል ጥቅማቸው ሲሉ መላ ዓለምን እየለመኑ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ዲፕሎማት፣ ሙሁራን፣ የውጪ ጉዳይ በዚህ ላይ በስፋት የአገሪቷን አቁዋም ማሳወቅ ያስፈልጋል፡፡ በ BBC, CNN, AL-Jezera የቻይና CCTV ወዘተ ላይ በስፋት እና በፍጥነት ማሰወቅ ያስፈልጋል ፡፡ ለዚህ ሁሉ ሜስ የአሜሪካ ዕጅ ነበረበት ወንጀለኛ የህዋአት ቡድን በነሱ ድጋፍ ለዚህ በማብቃት፡፡ አሁንም ኢትዮጵያ በተፋጠነ ሁኔታ ውጊያውን ለመቋጨት መገስገስ አለባት፡፡ ይህ ትግል እኮ አሁን የመላ ህዝቡ ትግል ነው፡፡ አብይ ብቻውንም ሊደራደርበት አይችልም፡፡ የማይታሰብ ነው፡፡ የተነቃነቀ የህዋአት ጥርስ ቶሎ እንዲነቀል ነው እን እንጂ ጥያቄው፡፡

  What they are doing American Senator’s & Diplomats here??? You are reporting to your president Trump, so what??? He is already against of Ethiopia, so what? Because, you are big country in which ruled only in-favor your policy? This is a fake stand as TPLF leaders nag you & make petition to you. No way, Ethiopia will not negotiate with small junta group as it has a capacity to place order. This is not solely Abiy position right away instead it is now a question of all Ethiopians to bring that tyrant group to justice once for all. No compromise by Ethiopian people. So those diplomats & senator’s just keep quiet and be on side of Ethiopian people. You will soon see the result. Long live to Ethiopia, down-down to junta group.
  ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

 4. ምን አይነት ወገናዊነት ስራ ነው እየተሰራ ያለው በአሜሪካ ሴናተር እና ዲፕሎማት፡፡ አንድ አንባገነነ፣ በዘር ፍጅት የሚጠየቅ ፓርቲ ነው መጠየቅ ያለበት ወይስ ህግ ለማስከበርና ህዝብን ነፃ ለማውጣት የሚጥር የአብይ መንግስት ነው መጠየቅ ያለበት??? ይህ ጉዳይ እኮ የነአብይ ብቻ አይደለም፡፡ የመላ ህዝብ ጥያቄ ነው፡፡ እነሱ ለግል ጥቅማቸው ሲሉ መላ ዓለምን እየለመኑ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ዲፕሎማት፣ ሙሁራን፣ የውጪ ጉዳይ በዚህ ላይ በስፋት የአገሪቷን አቁዋም ማሳወቅ ያስፈልጋል፡፡ በ BBC, CNN, AL-Jezera የቻይና CCTV ወዘተ ላይ በስፋት እና በፍጥነት ማሰወቅ ያስፈልጋል ፡፡ ለዚህ ሁሉ ሜስ የአሜሪካ ዕጅ ነበረበት ወንጀለኛ የህዋአት ቡድን በነሱ ድጋፍ ለዚህ በማብቃት፡፡ አሁንም ኢትዮጵያ በተፋጠነ ሁኔታ ውጊያውን ለመቋጨት መገስገስ አለባት፡፡ ይህ ትግል እኮ አሁን የመላ ህዝቡ ትግል ነው፡፡ አብይ ብቻውንም ሊደራደርበት አይችልም፡፡ የማይታሰብ ነው፡፡ የተነቃነቀ የህዋአት ጥርስ ቶሎ እንዲነቀል ነው እን እንጂ ጥያቄው፡፡

  What they are doing American Senator’s & Diplomats here??? You are reporting to your president Trump, so what??? He is already against of Ethiopia, so what? Because, you are big country in which ruled only in-favor your policy? This is a fake stand as TPLF leaders nag you & made petition to you. No way, Ethiopia will not negotiate with small junta group as it has a capacity to place order. This is not solely Abiy position right away instead it is now a question of all Ethiopians to bring that tyrant group to justice once for all. No compromise by Ethiopian people. So those diplomats & senator’s just keep quiet and be on side of Ethiopian people. You will soon see the result. Long live to Ethiopia, down-down to junta group.

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.