የጦር ሀይሎች ጠ/ኢታማዦር ሹም ጀነራል ብርሀኑ ጁላ ፣ ሠራዊታችን በሁሉም ግንባሮች ድልን እየተጎናፀፈ እንደሚገኝ አረጋገጡ

Jula
ጁንታው እያንዳንዳቸው 2 ሺ 500 የሰው ሀይል የያዙ 11 ብርጌድ ልዩ ሀይል ፣ 14 ብርጌድ የዞን ታጣቂ እና ሚሊሻ ቢገነባም ፣ አሁን ነፍስ አውጭኝ ላይ ይገኛል ብለዋል ።
ጀግናው ሠራዊታችን በምዕራብ ትግራይ ከዳንሻ – ባዕከር ፣ ማይካድራ ፣ አዲጎሹ ፣ እንድሪስ ፣ ሸራሮ ፣ አዲ ሀገራይ ፣ አዲጉዞምን ሰብሮ ትናንት ሽሬን መቆጣጠሩን አረጋግጠዋል ።
በደቡቡ ግንባርም ፣ ከዋጃ ጀምሮ አላማጣን ይዞ ወደፊት ቀጥሏል ።
በምስራቁ ግንባር ፣ ጨርጨር ፣ መሆኔ ፣ ራያ ዘቦ እና ሌሎች ቦታዎችን በቁጥጥር ስር አውሏል ። ጁንታውን ለህግ ለማቅረብም ግስጋሴውን ቀጥሏል ።
ነጻ በወጣው አካባቢ የሚገኘው ህብረተሰብ ለሠራዊታችን ከፍተኛ ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ ጀነራል ብርሀኑ አስታውሰው ፣ ህዝቡ ሠራዊታችንን ከሁዋላው እንዲመታ ቢያስታጥቁትም ፣ ምንም ሳይተኩሱ 200 መትረየስና ክላሽ አዲኮኮብ ፣ እንዳባጉና እና ሽሬ ላይ ለሠራዊታችን እስረክቧል ብለዋል ።
ጁንታው ኮማንድ ፖስቱን እና ተተኳሾቹን ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ቢያደርግም ሠራዊታችን ነጥሎ ለመምታት ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ይገኛል ብለዋል ።
ጀነራል ብርሀኑ እንዳሉት ፣ ከሀዲው ቡድን ፣ የሠራዊታችንን ማጥቃት ለመግታት አስፓልቶችን በዶዘር ቆፍሯል ። በርካታ ድልድዮችን አፈራርሷል ። ሠራዊታችን ግን በፅናት ተሻግሯቸዋል ።
በአሁኑ ሰዓት ፣ ጁንታው ፣ ኢትዮጵያን ወደ ጦርነት ለማስገባትና ለመበታተን ያቀደው እንደከሸፈበትና በመከበቡ ነፍስ አውጭኝ ላይ እንደሚገኝ አረጋግጠዋል ።
FDRE Defense Force – የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.