የመከላከያ ሠራዊት፣ የአማራ ልዩ ኃይል ፖሊስ እና የፀጥታ አካላት በትግራይ በምሥራቅና በምዕራብ ግንባሮች ወሳኝ ድሎችን ተቀናጁ

safe image 6
የመከላከያ ሠራዊት፣የአማራ ልዩ ኃይል ፖሊስ እና የፀጥታ አካላት በዛሬው ዕለት በትግራይ በምሥራቅና በምዕራብ ግንባሮች ወሳኝ ድሎችን ተቀዳጅቷል።
በምሥራቁ ግንባር ራያ ሙሉ በሙሉ ነጻ ወጥቷል። ጨርጨር፣ ጉጉፍቶ መሖኒን ሠራዊቱ ነጻ አውጥቷል። በየቦታው የነበሩ ወሳኝ የኮንክሪት ምሽጐችንም አፍርሷል። ሠራዊቱ በአሁኑ ጊዜ ወደ መቀሌ በመገሥገሥ ላይ ነው።
በምዕራብ ግንባር ደግሞ በአዲ ነብሪድና በአዲ ዳእሮ የሚገኙ ከባድ ምሽጎችን በማፍረስ ሽሬን ተቆጣጥሮ ወደ አኩስም በመገሥገሥ ላይ ይገኛል።
በውጊያው እጅግ ብዙ መሣሪያዎች ከመማረካቸውም በላይ ህወሓት ለክፉ ዓላማው ያሰለፋቸው የትግራይ ልዩ ኃይል አባላት በቁጥጥር ሥር ውለዋል።
126021563 4690340281038141 8861955301808175354 n
የመከላከያ ሠራዊቱ የህወሓት ጁንታን በሕግ ቁጥጥር ሥር ለማዋል እየገሠገሠ ሲሆን የጁንታው ኃይል የመከላከያ ሠራዊቱን ክንድ መቋቋም አቅቶት ወደኋላ እየሸሸ ነው።
ምንጭ፦ አማራ ፓሊስ

1 Comment

  1. Heartbreaking!
    Woyane has to go, and it will forever. But what is “victory” at the end? Perhaps, as they say “Ash in the mouth” ፟፟፤ የወያኔዎች ይቅር: ዝምታን የመረጣችሁ የትግራይ ልሂቃን እነዚህን ልጆች እያያችሁ እንዴት እንቅልፍ ይወስዳችኋል? ጭራሽ “ድል የኛ ነው” እያላችሁ ልጆቹን ወደ እሳት ትማግዳላችሁ፤፤ በየጥሻው የቀረውን አስቡት፤፤ መንግስትስ በሚችለው መንገድ ሁሉ እጅ እንዲሰጡ/እንዳይዋጉ በቂ ቅስቀሳ አድርጓል ወይ? “ሟችም እኛ፤ ገዳይም እኛ”፤ መከራችንን ያሳጥርልርን!

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.