የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም ከድርጅቱ መርህ ውጭ ለትህነግ ጁንታ ቡድን ወታደራዊ ድጋፍ በማፈላለግ እየተላላኩ መሆኑን የቱርክ አናዶሉ የዜና ወኪል ዘግቧል

126121434 407575097363941 8611207752581862672 o የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም ከድርጅቱ መርህ ውጭ ለትህነግ ጁንታ ቡድን ወታደራዊ ድጋፍ በማፈላለግ እየተላላኩ መሆኑን የቱርክ አናዶሉ የዜና ወኪል ዘግቧልዋና ዳይሬክተሩ በብዙ የዓለም ክፍሎች ደጅ በመጥናት ለትህነግ የዲፕሎማሲ እና ወታደራዊ ድጋፍ በመጠየቅ ላይ ሙሉ ተሳትፎ እያደረጉ መሆናቸውንም ዘገባው ጠቅሷል፡፡
አንድ የሀገሪቱን ከፍተኛ ባለስልጣን ጠቅሶ አናዶሉ እንደዘገበው በትህነግ/ህውኃት ቡድን ላይ የሕግ ማስከበር ዘመቻ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት የዶክተር ቴዎድሮስ እንቅስቃሴ በተመለከተ በሚገባ መረጃ አለው፡፡
ዶክተር ቴዎድሮስ የተባበሩት መንግስታት ድርጅቶችን፣ የፌዴራል መንግስት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በትህነግ/ህውኃት ቡድን ላይ እየወሰደ ያለውን ወታደራዊ እርምጃ እንዲያስቆሙ በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ ጫና ለማሳደር ሲጠይቁ ነበር ተብሏል፡፡
ዶክተር ቴዎድሮስ መንግስት እየወሰደ ያለውን ህግ የማስከበር ዘመቻ እያጣጣሉ እንደሆነና ግብፅ ለትህነግ/ህውኃት ቡድን ወታደራዊ ድጋፍ እንድታደርግ ጭምር መጠየቃቸውንም ባለስልጣኑ ለአናዶሉ ጠቅሰዋል፡፡
ባለስልጣኑ ቴዎድሮስ አድሃኖም ለ10 ዓመታት ኢትዮጵያን በማተራመስ እና የታላቁን ህዳሴ ግድብ ግንባታን ለማስተጓጎል ከቆመችው ግብፅ ጋር መመሳጠራቸው የሀገር ክህደት ነው ሲሉ መግለጻቸውንም ዘገባው ጠቅሷል፡፡
የአናዶሉ መረጃ ምንጭ የሆኑት ከፍተኛ ባለሥልጣን ዶክተር ቴዎድሮስ የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ሥራን በማይመለከት ጉዳይ እና የድርጅቱን መርህ በጣሰ መልኩ እየሰሩ መሆናቸውን አጋልጠዋል፡፡
ጋዜጠኛ፡ የማብርሃን ጌታቸው
አብመድ

5 Comments

 1. አብይ ይሾመዋል ምናለ በለኝ በነሱ አይጨክንም አሳድገዉታልና። አሳምነዉን ለማጥፋት ሌሊቱ እሰኪነጋ አልጠበቀም እርምጃ ለመዉሰድ። እነሱ ላይ ሲደርስ ልቡ ይሸበራል። ቴድሮስ አዳኖም ትግሬን ወክሎ ሳይሆን ኢትዮጵያን ወክሎ እዛ ከመቀመጡም ባሻገር ከድርጅቱ አላማ በተጻራሪ ቁሞ እንዲህ ያለ አስነዋሪ ስራ ሲሰራ ጥሩ መሪ ቢኖር ሌላ ያደርግ ነበር። ምን ያድርግ ደብረፅዮንስ አካሄዱን አይቶ ቢንቀዉ አይደል 60% የመከላከያ ሀይሉንና ጦር ሰራዊቱን ይዞ እንዲህ ጉድ የሰራዉ። ቴዎድሮስ በርታ አንተ ትሻላለህ ከሱ። መሪ አልወጣልን አለ ከተማሪ ብጥብጥ በሗላ።

 2. የኢትዮጵያ መንግሰት የጁንታው ግሩፕ አፈቀላጤ የአለም ጤና ድርጅት ተወካይ መነሳ እንዳለበት አቋማን ማሳወቅ አለባት፡፡ በፊትም ቢሆን Sabotage ነው የተመረጠው፡፡

  It is a shame that one big institution Director General works in tyrant junta group. He also did many sabotage in favoring Tigray region whereas by ignoring other areas, … etc. Hence he is doing against the objectives of WHO in which at this world catastrophic (COVID 19 others Pandemic time) where people are looking for vaccination to save their life. So WHO committee shall fire him as he don’t represent Ethiopian nation.

 3. የኢትዮጵያ መንግሰት የጁንታው ግሩፕ አፈቀላጤ የአለም ጤና ድርጅት ተወካይ መነሳ እንዳለበት አቋማን ማሳወቅ አለባት፡፡ በፊትም ቢሆን Sabotage ነው የተመረጠው፡፡ It is a shame that one big institution Director General works in tyrant junta group. He also did many sabotage in favoring Tigray region whereas by ignoring other areas, … etc. Hence he is doing against the objectives of WHO in which at this world catastrophic (COVID 19 others Pandemic time) where people are looking for vaccination to save their life. So WHO committee shall fire him as he don’t represent Ethiopian nation.

 4. በትግራይ “የህግ ማስከበር ዘመቻ” ተብዬው ጦርነት የሚካሄደው ሁለት ህግ በጣሱ እና ህግ እየጣሱ ባሉ አካላት መካከል ነው።
  “እውርን እውር ቢመራው ……” ነው የሁለቱ የጦርነት ሩጫ የመጨረሻ ውጤት።

  እንደው እውነት እንነጋገር ከተባለ ፕርስፐሪቲ ምንም ያህል የተሻለ አይደለም ከህወሀት/ትህነግ በህግ ማክበር ሥራ ሆነ ወይም ህግ በማስክብር ሥራ ። ሁለቱም ህግ አያከብሩም። ህግ የማስከበር ሥራ ሙከራ ሲሰሩም እራሳቸው የባሰ ብዙ ህግ ይጥሳሉ። “አትፍረድ ይቅር በል ……..” ብለው እፍዘው ህዝቡን እና ህግ አስከባሪውን አካላት ድንገት እማራ ልዩ ኃይል እና ትግራይ ልዩ ኃይልን አስረፈረፉዋቸው ሁለቱ ዝሆኖች (ፕሮስፐሪቲ እና ትህነግ/ህወሀት) ሲጣሉ ሣሩ (ምስኪን ልዩ ኃይል) ነው የተጎዳው ። አዛዦቹማ ምናቸው ተነክቶባቸው። እስር ቢገቡ ኢህአዴጎች አሳሪዎቻቸው ከአማራ ገበሬ በላይ ተንፈላስው ነው እቀማጥለው ነው የሚንከባከቡዋቸው ። ክንፍ ዳኘው እንደሚቀማጠለው።

 5. nebeyu

  መቶ በመቶ ትክክል ብለሀል። እንደ አንተ አይነት እውነትን የሚያፍረጥርጥ መሪ ነው የሚያስፈልገን የኢህአዴግ መሪ ተብዬዎቹ እየከተቱን ካሉት ማጥ ለማምለጥ። አስብበት የቤትሰብ ወይም ሌላ እንቅፋት የሚሆኑ ምክንያቶች ከሌሉብህ አንተ ብትመራን?

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.