ትናንት ራያ ላይ ጦርነት ሲደረግ ውሏል

125477673 405910950863689 2227663275815759702 n ትናንት ራያ ላይ ጦርነት ሲደረግ ውሏል
ዋጃና ጥሙጋ ትናንት ከሌሊት ጀምሮ መከላከያ ሠራዊቱ ገብቶ ነበር። ዛሬ ደግሞ መከላከያ ሠራዊቱ አላማጣ ከተማን ተቆጣጥሯል። ዋጃ፣ ጥሙጋ እና አላማጣ ከተሞችን ያለ ምንም ውጊያ ነው መከላከያ ሠራዊቱና የአማራ ልዩ ኃይል የተቆጣጠረው።
ሌላኛው ውጊያ በከፍተኛ ደረጃ የተካሄደበት ከአፋር በኩል ወደ ራያ አቅጣጫ የጨርጨር አካባቢ ላይ ነው። ዋጃ፣ ጥሙጋ እና አላማጣ የነበረው የህወሓት ኃይል ወደ ኋላ ፈርጥጦ በጨርጨር በኩል ካለው የህወሓት ሠራዊት ጋር በአንድ ላይ ተደርቦ ውጊያ ሳይገጥም አይቀርም። አሸባሪው ህወሓት ከፍተኛ ትኩረትና ትግል አድርጎ የጨርጨርን በር ለማስከፈት ብዙ መስዋእትነት ከፍሏል።
125501392 405911027530348 3676682531330601162 n ትናንት ራያ ላይ ጦርነት ሲደረግ ውሏል
የመረጃ ምንጮቸ እንዳሉኝ በጨርጨር እየተካሄደ ያለው ውጊያ የአፋርን ድንበር በመስበር ወደ ጂቡቲና ሶማሊያ ሊያመልጥ የሚፈልግ የህወሓት ኃይል እንዳለ የሚጠቁም ነው ብለዋል። ምናልባትም ሹማምንቶቹ ሊያመልጡ የመረጡት አቅጣጫ ሊሆን ይችላል። በአፋር ክልል ከምትገኘው ከለዋ ሆስፒታል በርካታ የትግራይ ልዩ ኃይል እና የመከላከያ ሠራዊት አባላት ቆስለው ህክምና እያገኙ እንደሆነ መረጃወች አግንቻለሁ። የትግራይ ልዩ ኃይል አባላትም በብዛት እንደተማረኩና ወታደሮች እንደሞቱ ለማወቅ ችያለሁ።
የመከላከያ ሠራዊታችን ከአፋር ልዩ ኃይል ጋር በመሆን ጀምበር ልትጠልቅ ገዳማ ከመሆኒ ከተማ 5 ኪሎሜትር ርቀት ላይ ከተማውን ዙሪያዋን ከቦ እንደነበርና የጨርጨሯ ከተማ ኮርሚም በዚሁ ሠአት በመከላከያ ሠራዊቱ ተከባ እንደነበር ሰምቻለሁ። አስተማማኝ ምንጭ ባይሆንም አሁን ከመሸ የመጣልኝ መረጃ ደግሞ ጨርጨርና መሆኒ ሙሉ ለሙሉ በመከላከያ ሠራዊቱ ቁጥጥር ውስጥ ገብተዋል።
ይህ ማለት ቆላማወቹ የራያ አካባቢወች ከህወሓት አገዛዝ ነጻ ወጥተው በመከላከያ ሠራዊቱና በአማራ ልዩ ኃይል ቁጥጥር ስር እንደገቡ ነው። የህወሓት ሠራዊት ደግሞ ከተማረከው፣ ከሞተውና ከቆሰለው ውጭ ፈርጥጦ ወደ ደጋማዎቹ የራያ አካባቢወች እንደሄደ ለመረዳት አይከብድም።
መከላከያ ሠራዊቱ አሁን በሚሄድበት ፍጥነት እርምጃውን ከቀጠለ የራያ ደጋማ አካባቢወች ነገ ሙሉ ለሙሉ ነጻ ወጥተው ወደ እንደርታ በኩል የሚጠጋ ይመስለኛል። ከዚህ እንደምንረዳው መቐለ ላይ ማዕከሉን ያደረገው የህወሓት ቡድን ከደቡብ አቅጣጫ በራያ በኩልና በምስራቁ ደግሞ በአፋር አብአላ በኩል እንደተከበበ ነው። መቐለ ከተማ ከደቡብና ከምስራቅ አቅጣጫ በጥቂት ኪሎ ሜትሮች ርቀት በመከላከያ ሠራዊቱ ተከባለች። ከሰሜን አቅጣጫ በአዲግራት በኩል ስላለው ነገር ማወቅ አልቻልኩም።
ብሩክ አበጋዝ

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.